ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች” በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡
የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ ማለትም ከውጭ መንግሥታትም ይሁን ከሀገር ውስጥ ነገሥታት መልዕክት ይጻጻፉ የነበረው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን ይሠሩ የነበሩት በአማርኛ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ትግሬ ሆነው ሳለ ይሄንን ማድረጋቸው ቅር ያሰኛቸው የትግሬ ሹማምንት በራስዎ በትግርኛ ቋንቋ የማይጠቀሙት ለምንድን ነው? ብለው ጠየቋቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛም አማርኛ የአክሱማዊያን ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ለእነሱ በማስታወስ ይህንን መለወጥ እንደማይኖርባቸውና እንደማይገባም በመግለጽ ለሹማምንቶቻቸው ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ አክሱማዊያን አማሮች ነበሩ ወይም አማርኛ የእክሱማዊያን ቋንቋ ነው የሚለውን ታሪክ አክሱም አካባቢ ሄዳችሁ ብትጠይቁ የአክሱም ሰዎች በትውፊት ይዘውት እንደመጡ ማለትም አባቶቻቸው አማርኛ የአክሱም ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ይነግሯቸው እንደነበር ይገልጹላቹሀል፡፡ በላይ ግደይ የተባሉ ጸሐፊም “አክሱም” በተባለው መጽሐፋቸው ይሄንን ገልጸውታል፡፡
ታዲያ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ አማራን ወይም አማርኛን ከአክሱምና አከባቢዋ ማንና እንዴትስ አጠፋው ለሚለው ተገቢ ጥያቄ ታሪክ አጥኝዎችና ተመራማሪዎች እስከአሁን አልደረሱበት ሆኖ ይሁን? ወይም አውቀውት ነገር ግን በአንድም በሌላም ምክንያት መግለጽ ስላልፈለጉ? ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡ ከዚህ አኳያ ይህ ጽሑፍ እስከ አሁን ያልተገለጸ ከታሪክ ኩነት መዞ ወይም ገልጦ መረጃ ይሰጣል፡፡
ጥንት ቋንቋቸው አማርኛ ኖሮ ዛሬ ላይ ቋንቋቸው ትግርኛ የሆነ አክሱሞች ብቻ አይደሉም፡፡ ከዚያው ከአጠገባቸው የወልቃይትና ከፊል ጠገዴን ሕዝብ ታገኛላቹህ፡፡ የእነኚህን አካባቢ ሰዎችን ማንነታቸውን ብትጠይቋቸው አማራ ጎንደሬ እንደሆኑ ይነግሯችኋል፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ግን ትግርኛ ነው፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሀገራቸውን ከጎንደር ቆርጦ ወደ ትግራይ ሲቀላቅልባቸውም ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደተቃወሙ ነው፡፡ በተለያዬ ጊዜ በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ወልቃይቶች የዚህ መንግሥት አመራርና ነባር ታጋይ የሆኑትም ሳይቀሩ ለመንግሥት ሥራ እውጭ ባሉበት “እኛ ትግርኛ ስለተናገርን ብቻ እንደ ትግሬ ልንቆጠር አይገባም ማንነታችን ይጠና እኛ ትግሬ አይደለንም” በማለት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ በተቃውሞ ሰልፉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡
የአክሱም ነገሥታት አማርኛ የቤተመንግሥት የሚስጥር ቋንቋ አድርገው ከመፍጠራቸው በፊት ቋንቋቸው ሙሉ ለሙሉ ግእዝ ነበር፡፡ አማርኛ ሊቀድም እንደሚችልም የሚያመላክቱ አንዳንድ ጠቋሚ ነገሮችም አሉ፡፡ የአክሱም ነገሥታት ስሞቻቸውን ያዬን እንደሆነም በተለያዩ ምክንያቶች በባዕዳን ማለትም በዕብራይስጥ፣ በጽርእ፣ በሮማይስጥ ስሞች ከተጠሩት ውጪ ስሞቹ ግእዝ ካልሆኑ አማርኛ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ የጠፉ ወይም የተረሱ የአማርኛ ቅላት ሆነው ለመረዳት የሚያስቸግሩ አማርኛዎች ቢበዙም አሁንም ድረስ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ባሉ ቃላት የሚጠሩ የአክሱም ነገሥታት ስሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን ብናነሣ ምኒልክ (ምንይልክ) ቅ.ል.ክ 982-957፣ ዙዋሬንብረት 1ኛ ቅ.ል.ክ. 599-558፣ ዙዋሬንብረት 2ኛ ቅ.ል.ክ. 276-260፣ ግርማአስፈር 77-86 ዓ.ም፣ አርፍድ (ገ/መስቀል) ከ357-361 ዓ.ም፣ ወሰንሰገድ 557-572 ዓ.ም፣ ጉም 693-717 ዓ.ም፣ አስጎምጉም ከ717-722 ዓ.ም፣ ለትም ከ722-738 ዓ.ም፣ ተላተም ከ738-759 ዓ.ም፣ አይዞር ለ6 ሰዓታት፣ ውድማአስፈር ከ787-817 ዓ.ም፣ አንበሳውድም (አንበሳአውድም) ከ882-902 ዓ.ም ድልነአድ 902-912 ዓ.ም፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት ሕዝቡ በዘር አማራ ሆኖ እንዴት ባለ ሁኔታ ይገዛ ቋንቋቸውን አጥፍተው ወይም ትተው ቋንቋቸው ያልነበረውን ትግርኛን ቋንቋቸው ሊያደርጉ እንደቻሉ እንይ፡፡ ይህ ድርጊት ከመጀመሪያውና ለ40 ዓመታት በተከታታይ ያለ ሟቀረጥ ከተፈጸመው እጅግ ከባዱና አሰቃቂው በአማራ ሕዝብ ላይ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ዘመኑ 842 ዓ.ም 882 ዓ.ም ድረስ በጨካኟና በክፏዋ “እሳቶ ወይም ጉዲት” በመባል በምትታወቀዋ ዮዲት የተፈጸመ ነው፡፡ የዓረብና የምዕራቡ ዓለም ታሪክ ጸሐፍት “ክርስትና የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ በ አራተኛው መቶ ክ/ዘመን በአብርሃና አጽብሐ ወይም በኢዛናና ሳይዛና ከመታወጁ ጋራ በተያያዘ በመጨረሻ በአማራ አሸናፊነት እስኪጠናቀቅና ተሸናፊዎቹ ፈላሾች በሀገሪቱ አርሶ የመጠቀም መብት ተነፍገው በእጅ ሞያና በጉልበት ሥራዎች የአማሮች አገልጋዮች እንዲሆኑ እስኪፈረድባቸው ጊዜ ድረስ በአማሮችና በፈላሾች (ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩ ቤተ እስራኤሎች) ማለትም አይሁዶች መሀከል እስከ ዮዲት ጊዜ ድረስ ለአምስት መቶ ዓመታት የዘለቀ ጦርነት ተደርጓል” ሲሉ ጽፈዋል፡፡ ልብ አድርጉ “በአማሮችና በፈላሾች” መካከል፡፡
የዮዲት ጉዲት ዘመን ግን ፈላሾች ጦርነቱን አሸንፈው ያሻቸውን ማድረግ የቻሉበት በኢትዮጵያ ታሪክ ሊገለጽ ከሚችለው በላይ ሀገሪቱ ከዚያ ዘመን በፊት የነበራትን ሥልጣኔ የሚያሳዩ ቅርሶችን ከጥቂት ምልክቶች በስተቀር ወድሞ የጠፋበት ዘመን ነበር፡፡ በዚያ ዘመን የክርስትና መታወጅ መጀመሪያ ግጭት ፈጠረ እያደር ግን በሀገሪቱ የአይሁድና የክርስቲያን ቀጠና ለይቶ ሀገሪቱን ለከባድ ኪሣራ ለዳረገና እጅግ ለተራዘመ ጦርነት ምክንያት ሆነ፡፡ ከ500 ዓመታት በኋላም አይሁዶች ወይም ፈላሾች በለስ ቀንቷቸው ጦርነቱን አሸንፈው በገነኑበት በ40 ዓመታት በዮዲት ጉዲት ዘመን ነበር አማሮችን በአክሱምና አካባቢዋ በተቻላትም መጠን በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል እንዲጠፉ ያደረገችው፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለነገሩ ወደ ታችም ወረድ ይላል አንድ ትውፊታዊ አባባል አለ እሱ ምንድን ነው? በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል “አማራ” ማለት የዘር ስም ብቻ አይደለም የሃይማኖትም ስም ጭምር እንጂ፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሰዎች በዘር ትግሬ ወይም ሌላ ቢሆኑም ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ ክርስቲያን ነኝ ለማለት “አማራ” ነኝ ይላሉ፡፡ ይህ አንድ ዐቢይ ነገርን ግልጽ አድርጎ ያሳያል፡፡ በዚያ ዘመን ይደረግ የነበረው ጦርነት በማንና በማን መሀከል ይደረግ እንደነበረ፡፡
በመሆኑም ዮዲት ጉዲት ጠላቶቿ አድርጋ የተነሣችባቸውን በዘርና በሃይማኖት “አማሮች” የሆኑትን አክሱማዊያንን ከመላ ሀገሪቱ ያለ ርህራሔ በጨከነና በማይታጠፉ ውሣኔ ጨርሶ የማጥፋት ዘመቻዋን በመላ ዘመኗ (ለ40 ዓመታት) ስትፈጽም በነበረበት ዘመን አማሮች ከዚያ መቅሰፍት ለመዳን ለመትረፍ ወይም ለማምለጥ ከመሰደድ በመለስ የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ አማራነታቸውን ማስተባበል ወይም አማራ እንዳልሆኑና ትግሬ እንደሆኑ ለአጥፊዎቻቸው ለዮዲት ጉዲት ሠራዊት መግለጽ ነበር፡፡ ይህ የመከራ ዘመን የአንድ ትውልድን ዘመን (33 ዓመታት) ጨርሶ የቀጣዩን ትውልድ ዘመንም አጋምሶ ስለነበርና ዮዲት ጉዲት ድል ከተመታችም በኋላ ያ መራራ መከራ ደግሞ ተመልሶ ላለመምጣቱ እርግጠኛ ያለመሆን ሥጋት ችግር እንዲህ ነበርን ከሚለው ትውፊታዊ ውርስ በቀር የአክሱምና የአካባቢዋን ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከማንነቱ ማለትም ከአማራነቱና ከቋንቋው አለያይቶት ሊቀር ቻለ፡፡
ከዚያም በኋላ የቤተክርስቲያንና የሀገራችን ታሪክ ጸሐፍት በሰዓቱ ግልጽ ሆኖ የሚታየውና የሚታወቀው ነገር ልክ በእነሱ ዘመን በግልጽ እንደሚታወቀው ሁሉ በኋላ ዘመንም እንደዚያው በግልጽ ታውቆ የሚቀጥልና ዛሬ ያለው ያ ችግር የፈጠራቸው የታሪክ ባለቤት ማንነት ያለመታወቅና ለተሳሳተ ግንዛቤ የሚዳርጉ ክፍተቶች በኋለኛው ዘመን ላይ የታሪክ መሳከር ወይም መጣረስ ሊያስከትል እንደሚችል ባለመገመታቸው ጦርነቱ ሃይማኖታዊ እንደነበረ ዮዲት ጉዲት በቤተክርስቲያን በሕዝቡና በሀገሪቱ ላይ ያወረደችውን መዓትና ጥፋት እንጂ በአማራና በፈላሻ መሀከልም እንደነበረ አጉልተው ወይም ግልጽ ባለ ቋንቋ ሳይገልጹት ቀርተዋል፡፡
እንግዲህ ይህ ታሪክ ማለትም የዮዲት 40 ዓመታት ዘመን፤ አይደለም በሀገራችን በውጭ ጸሐፍት ሳይቀር በሚገባ የሚታወቅ አሳዛኙ የታሪካችን ገጽታ ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከያኔያን (አርቲስቶች) ሳይቀሩ ንቁ ተሳታፊ ሆነው እየተንቀሳቀሱበት ያሉበት በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳልሞተና በእሳት ሰረገላ እንደተነጠቀ የተገለፀው ነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ሰው እንደመሆኑ በዳግም ምጽአት ዋዜማ ሞትን ለመቅመስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በትርጓሜ መጻሕፍት በግልጽ ተጽፎ እያለ ነብዩ ኤልያስ ኢትዮጵያን ሊታደግ በሁለት አፉ የተሳለ ሰይፍ ይዞ መጥቷል የሚሉ የሐሳዊያን ቡድን ያሰራጨው መረጃ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ የሚታወቁ እውነቶችን በተቃራኒው በመገልበጥ በፈጠራ ታሪክ መጥፎውን መልካም አጥፊውን ገንቢ ኃጥኡን ቅዱስ እንደነበሩ በማበል ፈጽሞ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ታሪክን የማጠፋፋት ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡
ለምሳሌ በዚህች ሀገር ላይ ያንን ሁሉ ጥፋት በማድረሷ ታሪክ የሚያውቃትን ዮዲት ጉዲትን ቅድስት እና ሠማዕት ናት እንጂ አጥፊ አይደለችም ይላሉ፡፡ እሷን ብቻም ሳይሆን በዐፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በኑፋቄአቸው ወይም በክህደታቸው ምክንያት ንጉሡ የቀጧቸውን ቤተክርስቲያን ያወገዘቻቸውን መናፍቃንን ማለትም ደቂቀ እስጢፋዎችን ከሀዲያን መናፍቃን ሳይሆኑ ቅዱሳን ሠማዕታት ናቸው በማለት በጠራራ ፀሐይ በሀገሪቱና በቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ አስገራሚና አስደንጋጭ እጅግ ኃላፊነት የጎደለው የጥፋትና የክህደት ደባውን በመተብተብ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንድ የዚህ ቡድን ሌላ ክንፍ ሊሆን እንደሚችል የሚገመት በመንግሥትም ድጋፍ የሚደረግለትና የብዙኃን መገናኛ ሽፋን እየተሰጠው ያለ ሌላ ቡድን የዐፄ ዘርዓያዕቆብንና የደቂቀ እስጢፋን የጥል ጉዳይ ምክንያት ዛሬም ባለው የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ማረጋገጥ የሚቻል ሆኖ እያለ ጎዳዩ ሃይማኖታዊ እንዳልነበረና ፖለቲካዊ እንደነበር ጸቡ የአማራና የትግሬ እንደነበር አድርጐ በሰፊው በመለፈፍ ላይ ይገኛል፡፡ የእነዚህ ሁለት የሐሳዊያን ቡድኖች በአንድ ወቅት አንድ ዓይነት መልዕክትና አቋም ይዘው ብቅ ማለት እንዲሁም በስውር ጥቅሙን ሊያስጠብቁለት የፈለጉት አካል ማንነትና ሌሎች ነገሮች ሲታይ ከእኒህ እንቅስቃሴዎች ጀርባ ይህ የአገዛዝ ሥርዓት መኖሩን ይጠቁማል፡፡
እዚህ ላይ አንድ ገጠመኝን ብናገር ነገሩን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ አንድ ድንግላዊ ነኝ የሚል ግን መነኩሴ ያልሆነ በቅቻለሁ በደመና ተጭኘ ኢየሩሳሌምን ጨምሮ የፈለኩበት ሀገር እመላለሳለሁ ከተሠወሩ ቅዱሳን ጋርም እገናኛለሁ ከሚል ሰው ጋር ጓደኞቼ አስተዋወቁኝ ለጊዜው በጓደኞቼ ወሬ ተሞልቼ ስለነበር እውነትም የበቃ ከቅዱሳን አንዱ መስሎኝ ነበር፡፡ ይህ ሰው እንደላይኞቹ ቡድኖች ሁሉ ዮዲት ጉዲትንና ደቂቀ እስጢፋን የሚያወድስ ከመሆኑም በላይ ትንቢት ነው እያለ የሚያወራው የዚህን ሥርዓት ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ ቀምሮና አበጃጅቶ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን እየተሠራ ያለውን ደባ ለመግለጽ ስለወደደ ይህ ሰው ማን እንደሆነ የማውቅበትን ጥሩ አጋጣሚ ፈጠሮ እንዳውቅ አደረገ፡፡ እናም ይህ ሰው ድንግላዊ ሳይሆን የቤተሰብ ኃላፊ መሆኑንና ሥራውም እራሱን እየለዋወጠ በየገዳሙና በየጸበሉ እየዞረ የሚሰልል “የመንግሥት” መረጃ ወይም ሰላይ መሆኑን ደረስኩበት፡፡ እንግዲህ እነኝህ ሰዎች ለምን ዓላማ የቱን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶኛል፡፡
ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ እናም የዮዲት መጨረሻ ሲቃረብ ማለትም ሸዋ መራቤቴ ላይ በተደረገው ጦርነት ዮዲት ጉዲት ከተገደለችና ሠራዊቷም ከተደመሰሰ በኋላ አማሮች ወይም አክሱማዊያን የነበረውን የአክሱም ሥርዎ መንግሥት ለማስቀጠል ሞክረው ነበር ነገር ግን ለ40 ዓመታት ያህል የነበረው መከራ የሥርዎ መንግሥቱን መሠረት እጅግ አናግቶት ስለነበር ለ30 ዓመታት ከቆዩት ሁለት ነገሥታት በኋላ ማስቀጠል ሳይችሉ በዛጉዌ ወይም በአገው ሥርዎ መንግሥት ተገልብጦ የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥትም ከ912-1245 ዓ.ም ድረስ ለ333 ዓመታት 11 ነገሥታትን አንግሦ ኢትዮጵያን ሲገዛ ቆይቶ አቡነ ተክለሃይማኖት ሥልጣኑ ለነበረው ለሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት መመለስ አለበት በማለታቸው አቡነ ተክለሃይማኖትና የመጨረሻው የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥት የመጨረሻው የነበረውን ንጉሥ ይትባረክ ባደረጉት ሰላማዊ ስምምነት ሥልጣኑ ወደ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ተመልሶ መቀመጫውን ግን አክሱም ሳይሆን ሸዋ አደረገ፡፡ በእርግጥ የአክሱም ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ሸዋ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው አልነበረም ከአብርሃ ወአጽብሐ ከ298 ዓም – አምሲ 461 ዓ.ም ድረስ 28 የአክሱም ነገሥታት ከአክሱም ባሻገር መቀመጫቸውን ሸዋ የረር ላይ ማለትም አዲስ አበባ ምሥራቃዊ ጫፍ ላይ ከሚታየው የረር በመባል በሚታወቀው ከፍታ ቦታ ላይ አድርጎ ቆይቷል፡፡ አሁንም ድረስ የዚያ ታሪክ አሻራዎች በቦታው ይገኛሉ፡፡
ከዚያም ይህ ሥርዎ መንግሥት እስከ ግራኝ መሐመድ በወረራውና በጦርነቱ ከነሕዝቡ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ገፍቶ እስከ ሰደዳቸውና ሁለተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ለ15 ዓመታት ያህል እስከተከሰተበት ጊዜ ዐፄ ልብነ ድንግል ድረስ ቆየ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል በጦርነቱ ከመናገሻቸው ሸዋ ከተረፈው ሕዝባቸው ጋር ተፈናቅለውና ተሰደው ሰሜን ኢትዮጵያ ጫፍ ድረስ ተሰደው አንዳሉ በሞት ተለዩ ግራኝ መሐመድ ለ15 ዓመታት ያህል ክርስቲያኑን (አማራውን) ሕዝብ እያሳደደ ፈጀው በሀገሪቱም ላይ ከዮዲት ጉዲት በከፋና ተወዳዳሪ በማይገኝለት ጨርሶ ኢትዮጵያዊ ወገናዊነት ባልተንጸባረቀበት በፍጹም ባዕዳዊ ስሜት ሀገሪቱን ከሥር ነቀላት አደቀቃት የቤተመንግሥትና የቤተክህነትን ሀብቶችና ቅርሶችን ሁሉ ጥርግ አድርጎ ለእርዳታ ላመጣቸው አረቦችና ለቱርኮች ጦር ሰጠ፡፡
ተንቀሳቀሽ ያልሆኑትንም አፈራረሰ ደመሰሰ ሌላው ቀርቶ በሀገሪቱ አንዲት ዛፍ እንኳን ቆሞ እንዳይቀር እስከ ማድረግ የደረሰ በገሪቱን ከሥር የመንቀል የጥፋት ዓላማ አንግቦ አወደመ፡፡ ሕዝቡንም አልሰልምም ያለውን እየሰየፈ ሞትን ፈርተው እሽ ያሉትን እያሰለመ ሲዋጋ የቀረው ሕዝብ ከንጉሡ ጋር ተሰዶ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተቅበዘበዘ እንዳለ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ቀየውን ጥሎ በመሰደዱ ባዶና ነጻ ሆኖ ያገኙትን መሬት በ15 ዓመታቱ ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው በቦረና በኩል በመግባት ሰፊ መሬት ለመቆጣጠር ዕድል አገኙ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል ከሞቱ በኋላ ልጃቸው ዐፄ ገላውዴዎስ በስደት እንዳሉ በ1530 ዓ.ም ነግሠው ከፖርቹጋሎች ባገኙት እርዳታ ታግዘው ግራኝን ጎንደር ፎገራ ላይ ገድለው ድል አደረጉት ግራኝን ከገደሉና ሠራዊቱንም የማረኩትን ማርከው የሸሸውም ከሸሸ በኋላ ወደ አባቶቻቸው መናገሻ ሲመለሱ ከሀገሩ የሚበዛው በእንግዶች ማለትም በኦሮሞ ተወላጆች ተይዞ አገኙት፡፡ ንጉሡም የሕዝባቸውን ማለቅ ተመልክተው በጣም የሳሳውን የሕዝባቸውን ቁጥር ለማካካስ እንደሚረዳቸው በማሰብና ፈቃደ እግዚአብሔር እንደሆነ በመገመት ለእንግዳው ሕዝብ የጎሳ አለቆች ሕዝቡ ሀገሬውን መስሎ ለመንግሥት እየገበረ የሚኖር ከሆነ ሕዝቡ ካለበት ስፍራ መኖሩን እንደሚፈቅዱ አስታወቁ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ አለቆችም ይህንን ችሮታ በደስታ በመቀበል ሀገሬውን መስለው እንደሀገሬው ሕዝብ እየገበሩ ለመኖር ቃል በመግባት የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን አገኙ፡፡ ሌላ አዲስ ፈላሲ እንዳይገባ ግን የቦረናን በር ዘጉ፡፡ እንግዲህ ይህ ከሆነ ረጅም ወይም በጣም ሩቅ የማይባል ማለትም አምስት መቶ ዓመታት መሆኑ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳል በፋሽስት ጣሊያን የ5 ዓመታት የወረራ ጊዜ የፋሽስትን የጥፋት ምክር በመስማት እንዲሁም የ1983ቱን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ የጥፋት መልዕክተኛ በሆኑት ምክርና ግፊት በሚያሳዝን ሁኔታ የኦሮሞ ተወላጆች ከዐፄ ገላውዴዎስ ጋር አድርገውት የነበረውን ስምምነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች እውነቱን እያወቁ ሳያውቁም ሊሆን ይችላል እራሳቸውን እንደባለቤት በመቁጠር ጭራሽ አማራውን ሀገራችንን ለቃቹህ ውጡልን በማለት ከዚያም አልፈው የብዙ ንጹሐን ዜጎችን ደም በጭካኔ አፈሰሱ መጠኑ ከፍተኛ ነው ባይባልም ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ የተደረገው አራተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል ነበር፡፡ ሦስተኛው የዘር ማጥፋት ሊባል የሚችለው ኦሮሞዎቹ ሸዋ ላይ የነበረውን ሰሎሞናዊ ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ጎንደር እንዲያደርግ እስከ መገደድ ድረስ የደረሰ አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን ማውደምን የጨመረ ጥቃት በተለያየ ጊዜ በፈጸሙ ጊዜ ያደረሱት ጥፋት ነው፡፡
ዛሬ ደግሞ ነገሩ ከዚያም አልፎ የኦሮሞን ሕዝብ ስም ያለ ፍላጎቱ መጠቀሚያ ያደረጉ እንገነጥላለን የሚሉ የጥፋት ኃይሎች ተፈጥረው ቁጭ አሉ፡፡ ኧረ ተዉ ሕሊና ይኑረን እንጂ ምነው? የማንን ሀገር ነው የምትገነጥሉት? ለነገሩ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ብሔረሰቦች አንዱ ከሌላው ጋር ተቀላቅሉ ተዋልደው ተዋሕደው ወቶላቸዋልና አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ. የሚባል ሕዝብ ባይኖርም ቅሉ አሁን ትላንትና በእንግድነት ተገብቶ ዝም ተብሎ የሰው ሀገር መገንጠል አለ እንዴ? ለዚያ ውለታ ልትከፍሉት የሚገባው ብድራትስ ይሄ መሆን ነበረበት እንዴ? ሁላችንም ዘራችንን ወደ ኋላ ብንቆጥር አንድና ከአንድ በላይ የሌላ ዘር ደም ተቀላቅሎበት እናገኛለን መረጃውን ለማግኘት ውስንነት ወይም የአቅም ችግር ካላጋጠመን በስተቀር፡፡ በመሆኑም የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ ጨርሶ ሊሠራ አይችልም ለመሥራት ከተሞከረም በእውነት ላይ ያልተመሠረተና ድንቁርና የተሞላ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስላለውና ስለምናየው ሳይሆን ስለሌለውና ስለማናየው እናወራለን እንደክማለንና ጅሎችም ነን፡፡ ይሄንን ማለት ግን የአማራ የትግሬ የጉራጌ የኦሮሞ የመሳሳሉት ባሕል ቋንቋና ሌሎችም መገለጫዎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ እነሱም ቢሆኑ ግን አንደኛው ከሌላኛው ጋር አልተወራረሰም አልተቀላቀለም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡
ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና አፄ ገላውዴዎስ ሸዋ ሆነው ከገዙ በኋላ ከሳቸው በኋላ ከነገሡት ከዐፄ ሚናስ በኋላ ያሉት የዚህ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት መቀመጫቸውን ወደ ጎንደር በማዞር በመጨረሻ በዳግማዊ ምኒልክ ወደ ሸዋ ከመመለሱ በፊት በላስቴው ዐፄ ተክለጊዮርጊስ 1860 ዓ.ም-1863 ለሦስት ዓመታት መቀመጫቸውን ጎንደርና ላስታ በማድረግ ቀጥለውም የትግሬው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከ1863 ዓ.ም-1881 ዓ.ም መቀመጫቸውን መቀሌና ጎንደር በማድረግ ጣልቃ ከመግባታቸው ውጭ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ መቀመጫውን ጎንደር አድርጎ ቆይቶ ነበር፡፡
እንግዲህ ይሄንን ታሪክ ማለትም በአክሱማዊያን (አማሮች) ዙሪያ ያለውን እውነት የሕወሀት ባለሥልጣናት በሚገባ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ በሁለት መንገዶች 1ኛ እንደማንኛውም የትግራይ ሕዝብ ተወላጅ በትውፊታዊ መረጃ 2ኛ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በአንድ 100 ዓመታትን በራቁ የትግራይ ተወላጅ ሽማግሌ አባት ይሰጣቸው በነበረ ምክርና ትምህርት፡፡ እኒህ አረጋዊ ሰው የኢሕአዴግን ምልክት ንብ እንዲሆን ያስቻሉም ሰው ናቸው፡፡ እኒህ ሰው ሕወሀቶችን እናንተ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ የካሳ ምርጫ ልጆች ናቹህ እያሉ ይነግሯቸው እንደነበር የሕወሐት አመራሮች ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳ ይህንን እውነት የሚያውቁ ቢሆንም በዮዲት ጊዜ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አሁን ባለው የሕዝብ አሰፋፈር አማሮች ወይም አማርኛ ተናጋሪ አክሱም አካባቢ አለመኖራቸውና አካባቢው በትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መያዙ ቢያንስ ምንም የታሪክ ዕውቀት በሌላቸው ዜጎች ዘንድ አክሱም የትግሬ ተወላጆች እንደነበረ ተደርጎ እንዲታሰብ በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በሰው ወርቅ ለመድመቅ ሲሞክሩና ሲቋምጡ ይታያሉ፡፡
ይሁንና ሥነ ልቡናቸውና ሰብእናቸው ማለትም ሕወሐቶች ለታሪክ ለድንበር ለቅርስ ለመሳሰሉት ሀብቶቻችንና እሴቶቻችን ያላቸው አመለካከት ሲታይ ግን ከአክሱም ሥርዎ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንዳልነበራቸው ሲያሳብቅባቸው ወይም ሲያሳጣቸው ይታያል ምክንያቱም ሕወሀቶች ለእነዚህ እሴቶቻችን ባጠቃላይ ለሀገሪቱ ታሪክና እሴቶች ያላቸው ግልጽ የሆነ ጥላቻና ዴንታቢስነት ወይም ለእነዚህ እሴቶቻችን ያላቸው ፍቅርና አቅርቦት ደካማ ወይም የምናውቀውን ያህል ነውና፡፡ ይህ ማለት ግን የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ለታሪካችን ለነጻነታችን ለሉዓላዊነታችን ለድንበራችን ለቅርሶቻችን ወዘተ. ዴንታ ቢስና ግድየለሽ ነው ማለት አይደለም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የአማራን የባለአደራነት ስሜት ማለትም ለታሪክ ለቅርስ ለድንበር በአጠቃላይ ለሀገር ያለውን ተቆርቋሪነት ያየን እንደሆነ የሚመሰገንና አርዓያነትም ያለው ነው፡፡ እንግዲህ ይሄ ከየትም የሚመጣ ሳይሆን እንደ ንብረት ሁሉ ከቀደሙት ትውልዶች የሚወረስ የባለ አደራነት የባለቤትነት ስሜት መንፈሳዊ ውርስ ሀብት ወይም እርሾ በመኖሩ ነው፡፡ ይሄንንም ስል የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ስሜት የለውም እያልኩ አለመሆኔ ይታወቅ፡፡ ትንታኔዬ ያተኮረው ከላይ በተገለጸው አካባቢና ርዕሰ ጉዳይ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
የ1983 ዓ.ም የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ በአማራ ሕዝብ ላይ በግልጽና በስውር በእቅድና በተጠና መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬም እንደ ዮዲት ዘመን ለመኖርና ለመብላት በሚል ማንነቱን ማለትም አማራነቱን የካደውና የደበቀው ለአማራነቱ ግድ የለሽ የሆነው ጭራሽም እንዴት እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ቅንጣት ቁጭትና ጸጸት ሳይታይባቸው ከግፈኞች ጋር ተባባሪ በመሆን በገዛ ማንነታቸው ላይ የዘመቱ ሰዎች ቁጥር የትየሌሌ ነው፡፡ የዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል መገለጫ ዘርፈ ብዙና የተወሳሰበም ነው፡፡ በገሀድ ከተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በቅርብ ትውስ የሚሉትን ስናነሣ በእነ ታምራት ላይኔ ዓይነቱ በሕወሃት መራሹ “መንግሥት” ባለሥልጣናት ገፋሪነት ሥልጣን በያዙ ማግሥት በአቦምሳ ወይም በአርባጉጉ በሌሎችም ሥፍራዎች በአማራነታቸው ብቻ ከሕፃን እስከ አረጋዊያን በጭካኔ የተገደሉና በተለያዬ ጊዜም ከበደኖ ከጉራፈርዳ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ንብረታቸውን ወርሰው ማባረራቸው የገዛ ሕገመንግሥታቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ስፍራ ሠርቶ የማደር ኑሮውን የመመሥረት ሕገመንግሥታዊ መብት አለው እያለ በአንድ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ማፈናቀል በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ተፈጸመ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ሲጠየቁ ምን ብለው መለሱ ይህ የክልሉ መንግሥት ጉዳይ ነው ሕገወጥ ሰፋሪዎች ናቸው ካለና አልፈልጋቸውም ካለ መብቱ ነው ይችላል በማለት የገዛ ሕገመንግሥታቸውን የሚፃረር ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ መልሳቸውም ይህ ጉዳይ የተፈፀመው በእሳቸው ትዕዛዝ መሆኑን ጠቆመ ለነገሩ በ21 ዓመታቱ የወያኔ መንግሥት አስተዳደር ተሞክሮ እንደምንረዳው እንዲህ ዓይነቱ ከባድና አሳሳቢ ውሣኔ በክልል አስተዳደሮች ደረጃ ሊወሰን እንደማይችል መረዳት አያዳግትም፡፡ አቶ መለስ እንዲህ ብለው ሲሉ እናንተም በጊዜአቹህ እኛ እንዳደረግነው ሁሉ ትግሬን ባዶ እጁን አራግፋቹህ አፈናቅላቹህ ማባረር ትችላላቹህ ማለታቸውና ይህንን አዲስ አዙሪት ባርከው መጀመራቸው እንደሆነ አቶ መለስ ጨርሶ አልገባቸውም፡፡
“አየ ጭንቅላት አየ የኛ አርቆ አሳቢ” የብልህነትንና የአርቆ አሳቢነትን ትርጉም ለማያውቁ ሰዎች አርቆ አሳቢ መሪ ማለት ውሎ አድሮ ምን ሊያስከትል እንደሚችል መገመት ተስኖት በሰላምና በፍቅር የሚኖርን ሕዝብ እንዲናቆር ማሴር እንዲፋጅ እንዲባላ መሸረብና መጣር ቀን እንዲጠባበቅ ማድረግ ሳይሆን እንኳን ያላጣውን ሰላም ፍቅር አንድነት ሕብረት ያጣ ሕዝብ እንኳን ቢሆን ኖሮ እንዲህ የሆነውን ሕዝብ ማስማማት ማግባባት ማፋቀር ማዋደድ መቻል ነው ብልህና ባለአእምሮ መሪ ማለት እንጅ የሚያናቁረውና ለማፋጀት የሚጥረው አይደለም ያ ደደብ ደንቆሮ እንጂ ብልህና አሳቢ ሊባል ከቶ እንዴት ይቻላል? የኢትዮጵያ ሕዝብ አላውቃቸው ብሎና ተስፋ አልቆርጥ ብሎ ነው እንጂ ከእነዚህ መንግሥታዊ ዳሲኘሊን (ሥነ ሥርዓት) ከማያውቁ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚባል ነገር ጨርሶ ከማይገባቸው፣ የጫካ አውሬዎች የመንደር ወጠጤዎች የስርቻ ወሮበሎች የቆሻሻ ሥነ ምግባር መፍለቂያዎች ከሆኑ ከእነዚህ ጉዶች ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቅ ኖሯል፡፡ እድሜ ዘመናቸውን ሳይለወጡና ሳይሰለጥኑ ጭራሽ እየባሰባቸውና እየደነቆሩ ሄደው ቁጭ አሉ፡፡ ይለወጣሉ ብላቹህም ከቶም ተስፋ አታድርጉ፡፡
ወደ ሌሎቹ አማራን የማጥፋት ወንጀሎች ዓይነቶች ስናልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የአማራ ተወላጅ በስውር ደባ ሠርቶ የመኖር ዕድል መነፈጉ፣ በአንድ ወቅት ላይ በተለይ ጎጃም የወባ ወረርሽኝ ገብቶ ሕዝቡን ሲጨርስ የአገዛዙ አካላት ተነግሯቸውና እያወቁ ፓርላማ ውስጥ መነጋገሪያ እስከመሆን ሲደርስ መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ደርጅቶች እስኪታዘቡ ድረስ አገዛዙ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ምንም ዓይነት የህክምና አቅርቦት እንዳይሰጥ በማድረግ ሕዝቡ እንዲያልቅ መደረጉ፣ ከዓመታት በፊት የጎንደር ፖሊስ በወገናዊነት ቁጭት በመነሣሣት ጫትን በቸልተኝነት ዝም ብለን በመመልከታችን ትውልዱ እንዳለ የጫት ሱሰኛ እስከመሆን ደረሰ አሁን ደግሞ ይሄ ሺሻ የሚባለውን ዝም ብንል ነገ እንደጫቱ ልንቀለብሰው ከማንችልበት ደረጃ መድረሳችንም አይደለ? በማለት ተነሣስተው ከየጫት ቤቱ ሲሰበስቡ ወዲያውኑ ከክልል ተደውሎ ማን አዛዛቹህ አሁኑኑ በአስቸኳይ መልሱ ተብለው እንዲመልሱና ትውልዱ ሱሰኛና እንኩቶ ብላሽ እንዲሆን ጥረት መደረጉ፣ በሀገሪቱ ሁለት ዓይነት የትምህርት ሥርዓት በመቅረጽ በትግራይና በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ያለውን በመለያየት በተለይ ደግሞ የአማራውን ክልል የትምህርት ጥራት ደረጃ አሳዛኝ በሆነ መልኩ እንዲወድቅ መደረጉ የመሳሰሉት ሲሆኑ በስውር ከሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ደግሞ ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ፡-
አንደኛው በአማራ ክፍላተ ሀገራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምክንያታቸው ያልታወቁና ያልተገለፁ በየጊዜው የሚከናወኑ የጅምላ ክትባቶች አሉ፡፡ እነኝህ ክትባቶች የተከተቡትን ሰዎች መውለድ እንዳይችሉ የሚያደርጉ ክትባቶች ናቸው፡፡ ይህ ክትባት በተደጋጋሚ ሲፈጸም የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ በክትባቱ ወቅት በመቅረት ሳይከተቡ የሚቀሩ ወገኖች እንዳሉ ታወቀ፡፡ የስውር ደባ ሰለባ እየሆኑ እንደሆነ የገባቸው ተማሪዎች የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ ላለመከተብ የሚያደርጉት ጥረት የአሳዛኙ ቲያትር አስቂኝ ገጽታ ሆኖ ታይቷል፡፡ ወደ ኋላም ሕዝቡ ይሄንን ጉዳይ ጭራሽ የወጉ ማጣፈጫና ማምረራያ አድረጎት አረፈ፡፡ ሽለ ሙቅ የሆነች ሴት ስትታይ “አሀ ይች ከክትባት ያመለጠች ናት” ያባላል ስሜተ ቀዝቃዛዋን ደግሞ፣ “ይች ተከታቢ ናት” እያለ እስኪቀልድበት ድረስ ይህ ጉዳይ የሕልውናውን ጉልህ ሥፍራ እንደያዘና ማወቁን ወይም መንቃቱን ጠቆመ፡፡ ከዚህ የተለየ ግን ምንም ያደረገው ነገር የለም፡፡ በሌሎች ሀገሮች ቢሆን ግን ከዚህ የበለጠ የሕዝብ አመጽ ሊቀሰቅስ የሚችል ምክንያት ባልነበረ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በተለይ 1996/97 ዓ.ም. ፀረ ትራኮማ ክትባት በሚል ሽፋን በበርካታ አካባቢዎች በተለያዬ ጊዜ የተደረጉ ክትባቶች ብዙ ሕፃናትንና ነፈሰጡር እናቶችን ለሞት አብቅተዋል፡፡ በነዚህ የአማራ አካባቢዎች የቀብር ስፍራዎች ብትዘዋወሩ ከቀድሞው በተለየና ባልተለመደ መልኩ በርካታ የሕፃናትና የነፍሰጡር እናቶች መቃብሮችን ታያላችሁ፡፡ እንግዲህ እነኝህና ሌሎች እነኝህን የመሳሰሉ ስውርና ድብቅ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ በግልጽ በአደባባይ በዓለም አቀፉ በሕብረተሰብ እይታ ስር በዘራቸው ምክንያት ብቻ የዜጐችን ንብረት ዘርፎ የሚያፈናቅል የሚያባርር የእርዳታ እህል የሚከለክልና በረሃብ የሚያሰቃይ ሌላም በግልጽ የሚታዩ ግፎችን የሚፈጽም ግፈኛ አገዛዝ በስውር ወይም በድብቅ እነኚህን የጠቀስኳቸውንና ሌሎችንም አያደርግም ብሎ የሚጠራጠር ሰው ወይም ዜጋ ካለ እጅግ የዋህና ያልበሰለ መሆኑን ዛሬ ይወቅ፡፡
ወያኔ ቢወድቅ ወይም ከሥልጣን ቢወገድ የሚከተለውን አጸፋ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በተቻለው መጠን በሥልጣን እያለ ይህንን የበቀል እርምጃ ይወስድብኛል ብሎ የሚፈራውን ሕዝብ (አማራን) በግልጽም ይሁን በስውር በሚያደርጋቸው የማጥፊያ ዘዴዎች ለቅሞ ማጥፋት ዋነኛውና ሌት ተቀን የሚሠራበት ዓላማው ነው የሚል ከባድ ሥጋት አለብኝ፡፡ እስከ 1999 ዓ.ም በተሠራው ደባ ያገኙት ድምር ውጤት ከ6 ዓመታት በፊት በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ በሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልታየና እንግዳ በሆነ መልኩ የሌላው ሕዝብ በቅድሚያ ትንበያው መሠረት እና ከዚያም በላይ ሆኖ ሲገኝ የአማራ ሕዝብ ግን ይደርሳል ተብሎ ከተጠበቀው የትንበያ ቁጥር ወይም መድረስ ከነበረበት ቁጥር አለመድረሱ ብቻ ሳይሆን ጭራሽም በሚሊዮኖች (አእላፋት) አሽቆልቁሎ እንደተገኘ ማስታወስ ይቻላል፡፡ ገና ከ4 ዓመታት በኋላ በሚደረገው ቆጠራም ከ1999 ዓ.ም በኋላ በሠሩት ደባ ከዚህም በከፋ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ይገመታል፡፡
በየሙያ መስኩ ሰዎች ስንት ጉድ ያውቃሉ መሰላችሁ ለመናገርና ለመመስከር ጊዜን የሚጠብቁ፡፡ የሚገርመኝና ግራ የሚገባኝ ነገር ቢኖር በዚህ ሕዝብ ላይ እንዲህ ጥርስ የተነከሰውና የተጨከነው ለምንድን ነው? ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በመሆን የዚህችን ሀገር ነጻነት አስጠብቆ ባቆዬ? ከቀደምት ሥልጡንና ኃያላን ሀገራት ጎራ ባሰለፈ? ለእነኝህና ለሌሎች ኩራቶቻችን ሲል ስንትና ስንት መከራ ባሳለፈ? ለምን? ይህ ያስመሰግነዋል እንጂ በምን ተአምር ነው ለጥፋት ድግስ ሊዳርገው የሚገባው? በኢትዮጵያዊነቱና በሀገሩ ኩራትና ክብር የሚሰማው ባለውለታና የሚያስብ ሕሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዝምታና በይሁንታ የሚመለከትበት አቅል ይኖራል ብሎ ማሰብ ይቻል ይሆን? አረማዊያን ሆይ በምሳሩ ላይ ቆማቹሀል ለራሳችሁም ይብስባቹሀል፡፡ አየ የኛ ልማታዊ መንግሥት ለማያውቅሽ ታጠኝ አያ፡፡ አንባቢያን ሆይ ደኅና ሁኑ ከዚህ በኋላ እንኳን የምንገናኝ አይመስለኝም፡፡ (በመግቢያው ላይ ያለው ፎቶ ለማሳያነት የቀረበ)
ኢትዮጵያ ከውድ ልጆቿ ጋር በክብር በነጻነትና በልዕልና ለዘላለም ትኑር!!!
amsalugkidan@gmail.com
Qaalluu says
ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል። ኣቶ አምሳሉም ይህንኑ ተረታቸውን ደጋግመው ይነግሩናል።
“ነገደ ዮቅጣን የሴም የልጅ ልጆች ናቸው። — ዮቅጣን 13 ልጆች ወለደ። ስፍራውም በእስያ ምድር ከሜሻ እስከ ሥፋር እስከ ምስራቅ ተራራ ድረስ ነው ዘፍ፡ ፲፡ ፴
ከነዚህ ካ፲፫ቱ የዮቅጣን ልጆች ፭ቱ ሳባ፡ አውፌር፡ ሀዊላ፡ አባል፡ አቢማኤል ቦታ ባነሳቸው ስፍራ በጠበባቸው ጊዜ ከእስያ ተነስተው ብዙ ሰራዊት ሁነው ሲፈልሱ፡ ሲሄዱ ሲጓዙ የመን ደረሱ። እኒሁ የሴም ዘር ነገደ ዮቅጣን ወደ የመን በገቡ ጊዜ ምንም በፖለቲካ ምክር ባይስማሙ ለኩሳ የመን ይገብሩ ነበር። በኋላ ግን የኩሳ የመንን ደካምነት አይተው በተንኮልና በሊላም ጥበብ እርስ በርሱ አሽፍተው ከወግናቸው ያሮባ የተባለውን ብልሀተኛ ጀግና አንግሠው ለየመን ሁሉ ባለቤቶች ሆኑ። —እነዚህ ነግድ በኋላ አግዓዝያን ተበሉ። ከነገደ ሴም ዮቅጣን ከየመን ተነሥተው ብዙ ሠራዊት ሆነው በባብእል መንደብ ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ።” (ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮ ገጽ ፻፲-፻፲፪)
በወቅቱ በአካባቢ የነበሩ የኩሽ ንጉስና ልጆቹ ነበር። ከነዚህም ውስጥ ዳጪ (የኦሮሞ ግንድ) ወንድሞቹ በለው፡ ከሎ፡ ዳሞት፡ ሳሆ፥ መረባ (የኦሮሞ ጎሳ) ኣገው፡ ቤጃ፡ ኖባ(የኦሮሞ ጎሳ) ነበሩ። እነዚህ አግዓዝያን እየበረቱ ሲሄዱ። ዳጪ ወደ ደቡብ ተገፋ። በለው ወደ ምዕራብ ተገፋ፥ ኖባ ወደ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ አስከ ነጭ ኣባይ ርቆ ሰፈራ። መረዋ ወደ ሰሜን ምዕራብ ወደ ኑቢያ (ሜሮዌ) ተገፈ፥ በኋላ ወደ ደቡብ ተስፋፈ።
“ከዚህ ሁሉ ጋር አማሮችና ትግሮች “የኢትዮጵያ” ዋና ባላባቶችና ባላገሮች መሆናቸውንና ከሴም ዘር ከነገደ ዮቅጣን ልጆች የእስራኤል ዘሮች እንደሆኑ የሚያስረዳ ብዙ ምስክር አላቸው። በነገደ ኩሳ መንግሥት ጊዜ በዚያ ዘመን የህንድ ነገሥታት በርትተው ወደ የመን እየመጡ በጦር በዘረፋም ባወኩዋቸው ጊዜ በየመን ከነበሩት 5ቱ ነገደ ሲቀሩ— ነገደ ሳባ ነገደ ኦባል ነገደ ኦፊር በነገደ ካም በኩሳ ዘር መንግሥት መጨረሻ ንጉስ በጲኦሪ ዘመን ከየመን ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ መጡና ጥቂት ጊዜ በአንድነት ተቀመጡ። — ነገደ ሳባ ነጋዶች ሆነው ለነገደ ኩሳ መንግሥት ቀረጥና ግብር በመስጠት ትቂት ዘመን ስለተቀመጡበት የዚያ አገር ስም ትግሬ አሉት። ትግሬ ፡ አማራ ማለት የግብር ስም ነው።”(ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮)
“የአማራና የትግሬ አባት የሴም የልጅ ልጅ የኤቦር ልጅ ዮቅጣን ነው። በመልክም በጠባይ፡ በቋንቋ ጥቂት በጥቂት ይለያያሉ እንጂ ብዙ ነገር ይዋረሳሉ።
ያማራ ህዝብ የነገደ ሴም ወገኖች የዮቅጣን ልጆች የእስራኤል ዘሮች እንደሆኑ ፈጽሞ የሚያስረደ ጠባያቸው ልማዳቸው መልካቸው ስማቸው ስመ ሀገራቸው ቋንቋቸው ነው።”(ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮)
“— በ፲፩፻፴-፶ ዓም በላሊባላ ንጉሥ ዘመን፦— ሳይንት ባላገሩ አረመኔ ነበረ። መታመኛ ሲሉ ዘንዶውንና እባቡን ተመን አሉት። ይህንኑ ህዝብ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያስተምሩት ነበሩ። ፲፪ ዓመት በዚያ ወንጌል ሲሰብኩ ካማሮች ጋር ተዋወቁ። ከዛጉዌ ቤት ወደ ቀዳማዊ ምኒልክ ዘር ቤት መንግሥት ለመመልስ የመከሩ ብዚያ ነው። (ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮ ገጽ ፻፲፭)
“አምሓራ ወይም አማራ ማለት አራሽ ማለት ነ። ሳይንት ማለትም ባረብኛ የእህል መከማቻ ጎተራ ማለት ነው። አማሮችም ይኩኖ አምላክን አንግሠው ከዛጉዌ ነገድ የሚሆን ንጉሥ ይትባረክን ዋድላ ላይ ገደሉት። — አማሮች ግን ይኩኖ አምላክን ካነገሡ በኋላ ሰው ሁሉ አማሪኛ ይነገር ጀመር። —- ባጼ ይኩኑ አምላክ ጊዜ ያማሪኛ ቋንቋ ፈጽሞ ሠለጠነ። — ለንግግር የተስማማ ሆኖ ስለ ተገኘ የቤተ መንግሥት ቋንቋ ሆነ እንጂ ንግግሩስ አስቀድሞ የነበረ ነው። (ዮ ወ ማ ገጽ ፻፲፮)
“ኣሁን የአማራ ህዝብ የመጣበትን የመሥመር አቅጣጫ እንፈልግ። ከደቡብ ዓረብ ከክርስትና በፊት ኤርትራን ተሻግረው በሰሜን ኢትዮጵያ ተበታትነው የተቀመጡትን የኛን የግዕዙ ታሪካ ነገሥት ነገደ ዮቅጣን ይላቸዋል። ዛሬ የተጣራው ታሪክ በደቡብ ዓረብ ሳባዊያን፡ ሀበሳን፡ ሂሚሪት፡ ሖሜሪት እንደነበሩና ክነዚህ የሴም ወይም የዮቅጣን ነገዶች ውስጥ የኤርትራን ባህር ተሻግረው በኢትዮጵያ ሰሜን በያውራጃው ተሰማርተው ተቀመጡ። — የጨረቃ አምልካቸውን ከነምልክቱ የነገሥታት አስተዳደር ልማድ በደቡብ ዓረብ ከሚገኛው ጋር ፍጹም አንድ ወይም ተመሳሳይ በመሆኑ ነው። የአምልክቱ ስም ማህረም፡ አስታር፡ አልመቅህ፡ ሀውባስ—- እያለ በደቡብ ዓረብ የተገኘው በኢትዮጵያ ሰሚንም ተገኝቷል።
የሆነ ሆኖ የመሬቱ አቀማመጥ ሲታይ በደቡብ ዓረብ ፊት ለፊት የሚታየው የኢትዮጵያ ሰሜን ነው። ስለዚህ የሳባ ወገኖች ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው በሐማሴን፡ አካለ ጉዛይ፡ በኣጋሜ፡ የሀበሳን ወግኖች በአሳሆርታ በሓውዜን ሲሳማሩ፡ በዓረብ አገር ሳሉ ከሳባ በተደቡብ የሚኖሩት ሂሚያሪትና ሆሚሪት የኤርትራን ባህር ከተሻገሩ በኋላ ሳባና ሀበሳን ከሠፈሩበት በስተደቡብ በኩል ያለውን ሰፋፊ አውራጀ ይዘው ስለሰፈሩ ሂሚሪያት ወይም ሆሜሪት የሚባለው ስያሜ በጊዜ ብዛት ትንሽ ፊደሉንና አባባሉን እየለወጣ መጥቶ በሂሚያሪት አምሓራ ተብሎ ይሆናል። እውነትም የአማሮች የመዠመሪያ መሠረታዊ አገር አምሓራ ሳይንት ነው። — በአሁኑ ጊዜ የዛጉዌን መንግሥት በአማሮቹ የቤተ ክህነት አባቶች በነአቡኑ ተክለ ሃይማኖት በነአባ እየሱስ ሞአ እየተረዳ ውስዷል ማለት ነው። ባንድ በጠቅላላ በአማራ ስም የሚጠረው ህዝብ በቀን ብዛት እርሱም ደግሞ ቅርንጫፍ እያበጀ የመሬት ስፈት ወርዱንም ቁመቱንም እያስፋፋ ኖረ።
“ነገሥታቱ በሸዋ( የንጉሥ ሸለቆ) መንዝ ተጉለት ቢቀመጡም በዘመናቸው ሁል ጊዜ የአማሮቹ የመዠመሪያ መደበኛ ሥፍራ ወደ ነበረው ወደ ቤተ አምሓረ (ሳይንት ወይም ዳውንት) እየሄዱ በዚያ በየስማቸው ቤተ ክርስትያን መሥራት ያዘወትሩ ነበር። — አውረጃውን ማክበርና ማድማቅ እየሄዱ በየጊዜው መጎብኘት የአባቶቻቸውን አጽም በዚያ ማሳረፍ ይወዱ ነበር።
(የግራኝ ወረራ በተክለ ጸድቅ መኩሪያ ገጽ 7-9)
“— የአክሱም ነገሥታት ከደቡብ ዓረብ የመጡ በሳባና በግዕዝ የሚጽፉ የጨረቃ አምላክ የሚያመልኩ ስለአደረጋቸው— በራሳቸው የቋንቋ ጽሁፍ በሳባና በግዕዝ ለይ በዘመኑ የገነነውን ግሪኩን ጨምረው ሲጽፉ አንድ ጊዜም የዕብራይስጥ ቋንቋ አልጨመሩም። ማህረም ሲነሳም የእሥራኤል አምላክ የሕቤ ዢሆባ ወይም አዶናይ ተብሎ አልተጠቀሰም። እያንደንዱ ነጋሢ የቅርብ አባቶቹን በየሐውልቱ ላይ ሲያወሳ የዳዊትን የሰለሞንን እንኳን ሰለሞንን የመዠመሪያ ንጉሥ የሆነውን ምኒልክን የሚያነሣ አስካሁን አልተገኛም።” (ግራኝ ወረራ ገጽ 12)
እንግዲህ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መልኩ የተደራረተ ታሪክ እያላቸው ከርስትና በሁለት የግሪክ ዝርያ ያለቸው የሶሪያ ነገዴዎች ፍሬምናጦስና ኤክሶዶስ በሚባሉ ሰዎች መጣላቸው። እነሱም የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ወደ ግብጽ ሄደው ጉዳዩን ለኮፕትክ ቤተክርስቲያን አሳወቁ። በኋላ ፍሬምናጦስ ተመልሶ ጳጰስ ሆናለቸው። በዚህ ሁኔታ እያሉ የአክሱምን ሥረዋመንግስት በአገው ሥረዋመንግሥት ተተከ። ትንሽ ቆይቶ የሃይማኖት ጭቅጭቅ በኣገዎችና ግብጦች መሃል ተነሳ።
ከዚያ በኋላ ለሐበሾች እስከ 1954 (በሀይለ ስላሴ) ጊዜ ድረስ ጰጰሶች ከግብጥ ይመጡ ነበር። ይህ በዚህ እያሌ የእክሱሞች ሥርዋመንግስት ወድቆ የዛጉዌዎች (አገው) ሥርዋመንግስት አካባቢን ተቆጠጠረ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ማለት 901-1270 ድረስ የኣገው ነገሥታትና ግብጦች መሃል የሃይማኖት ጭቅጭቅ ተነሳ። የጭቅጭቁ ሰበብ ዛጉዌዎች የራሳቸው ሴኖዶስ እንዲኖራቸውና ካስኖዶሶች ውስጥ ጳጳስ እንዲሾሚላቸው ይፈልጋሉና። ነገር ግን ግብጦች የሓበሻ ቤተክህናት ከእነሱ ነጻ እንዲትሆን አይፈልጉም ነበርና። እንዲሁም ብዙ ምልጃና ስጦታዎች፣ ግብር ስልምቀርበት ነው። በዚህ ሰበብ ግብጦቹ ተንኮል ሰሩ። ይህም “በኒቅያ ጉባኤ 320 (18) የሃይማኖት ሊቃውንት በተገኙበት ሐበሾች/ኢትዮጵያኖች የራሳቸው ጰጰስ እንዳይኖራቸው ተወሰነ” ብለው አወጁ። ጭቅጭቁ ለ200 ዓመታት ቀጠለ።
ሌለው ስለ ንግሥት ሳባ የቀድሞ ተረቶችን ትተን ሴትዮዋ ሙሉ በሙሉ የአረቦች ንግስት ናት። በመጽሀፍ ቅዱስ ሁሉ ቦታ የተጠቀሰው ስለ ኢትዮጵያ መሆንዋ የምገልጽ የለም። አንደንድ ቦታ እስራኤሎችም አረቦችም “የአዜብ ንግስት” ይላሉ። አዜብ በህብሩና በአረብኛ “ደቡብ” ማለት ነው። ሼባም ትሁን ሳባ ንግስት የአረቦች ነች።
ኢትዮጵያ መሆንዋን የሰበኩ ግብጣዊያን ናቻው። ይህም ከግብጥ ኮፕትክ ቤተክርስቲያን ለሓበሻ ኦርቶዶክስ ተቀርጾ የተሰጣ “ክብራ ነገስትና ፍትሃ ነግስት” የሚባሉ በአረብኛ ተጽፎ ወደ ግዕዝ ተተርጉሞ የተሰጣ ሰነድ ነው። ይህም የሆነው ከሶሪያ ነጋዴዎች ውስጥ ፍሬምናጦስ እና ኤክሶዶስ የሚባሉ ወደ አክሱም 360 ዓም አካባቢ መጥተው ስለ ክርስትና ከሰበኩ በኋላ ወደ ግብጽ ሄደው ጉዳዩን ለኮፕቲኩ አሳወቁ። እስከዚያ ዲረስ ሃበሾቹ በጨረቀና በድንጋይ ያመልኩ ነበር። ስለ ኦሪት ሃይማኖት የሚያዉቁት አልነበራም። ኦሪት የኩሾች እምነት እንጂ የሴሜትኮች (ኣቢሲኒያና አረቦች) አልነበረም።
ከዚህ በመቀጠል ‘ክብረነገስቱና(የነገስታት ክብር) እና ፍትሐነግስት(የነገስታት ህግ) የሚለውን መጽሀፍና የነገስታቱ ክብር የተባሉትን የግብጽና ይሁዲ ዝሪያ ያላቸውን 110 ሰዎችን ይዘው ከግብጽ ወደ ሀበሻ መጡ። እንግዲህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ “ሳባ ንግስት ለሰለሞን ወለደች። የኢትዮጵያ ንግስት ነበረች። ይህ ይህን አገር የሰላሞን ዘር መግዛት አለበት” ብለው ለነገሥታቱ ነገሩ።በወቅቱ ማንም ሰው ሳያምናቸው ቀረ። ጭቅጭቁ ለሁለት ዓመታት ዘለቀ። ይህ በዚህ እንዳለ የግብጹ ሊዑካን ተንኮላቸውን ማጠንጠን ጀመሩ። ስለዚህ ለቄሶች እና በወቅቱ ክርስትና ተከታይ የሆኑ ሰዎችና ወቶአደሩን/ሰራዊቱን አሳመኑ። በዚህ ጊዜ የሰራዊቱ አለቃ የአማረው ነገድ (ጎሳ)ይኩኑ አምላክ ነበር። ቀሶቹ በቄሴ ተክለ ሃይማኖት መሪነት። ሰራዊቱ በአማራው ዘር ይኩኑ መሪነት የዛጔን መንግሥት በኃይል ገልብጠው በመቅቱ የሥርዋመንግስቱ መሪ የነበረ ይትባረክ የተበለውን ከስልጣን አበረው ወርሂመኑ በተባለው ቦታ ደርሶበት አርደው ገደሉት። እንግዲህ ይህን ሸሪ የስሩ የግብጾች የሃይማኖት ሊኡካንና የሓበሻ ቄሶችና የአማራው ሰራዊት/ወቶኣደር ናቸው።
ስለዚህ ሼባ ወይም ሳባ የሚትባል ነግሥት በዚህ በኢትዮጵያ ምድር አልነበራችም። ነገር ግን ሃበሾች የአረብና እስራኤል ነገድ ዘሮች ስለ ነበሩ፡ እስዋም በአገሯ ወንድ በማጠቷ ከነገርዷ ድንግልዋን ወስዳ ለእስራኤል ንጉስ አስረከበች። በጣም የሚያሳፍር ተረት። ወንድ በአገሯ አጥታ ያን ሁሉ አገር አቁዋርጣ ክብርናዋን ማዋረድ። በሌላ በኩል በምስራቅ አፍሪካ ያሉት የአረብ ዝሪያዎች (ሓበሾች) በአገራቸው (የመን) እያሉ ንግስታቸው ነበረች። በመሆኑም እዚህ ከመጡ በኋላ፣ ጉልባት እስኪያገኙ ድራስ ለኩሳ ንጉሥ ይገብሩላት ነበር። ልክ መንዝና መረቤቴ ለጎንደር ይገብሩ እንደነበር ሁሉ ሀበሾችም በአረቢየ የኣሁኑ የመኒያ መንግሥት ግብር ይሊኩ ነበር። መሰረታቸው እዚያ ስለሆነ።
በሌላ በኩል የኩሾች ንግሥት ከንዳኬ/እንዳኬ የሚትባል በኑቢያ ቴበስ ከተማ እንደነበራችና፣ መቃብርዋ እዚያው መኖሩ እሙን ነው ብዙ የታሪክ ሰነዶችም አሉ።
ከዚያ በኋላ አማራዎቹ አገዎችን እንደገና እንዳይነሱ ብዙዎቹን ፈጁዋቸው። ጥቂቶች ሰቆጣ ኣካባቢ፣ ጥቂቶች በጎጃም ውስጥ ጥቂቶች ደግሞ ወደ ቦጎስ ሀልሀል (ኤርትራ) ተሰደዱ። በዚህ ሁነታ ነው እንግዲ አማሮች ሌሎችን ብሔሮች ሲፈጁና፣ መሬቱን ሲቀሙ የነበረ። እስክ ሃይላ ሥላሴ የመጨረሻ ሥልጣን ድረስ በዚህ ሁኔታ ቆዩ፡” (ዶክተር ላጵሶ ጌ ዴሌቦ ኢትቭ እና መጽሐፈቸው ስለ ኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥቱ ይ ማልከቱ)
ስለዚህ አማራው በወረራ እንጂ አንድም ይዞታ ከደቡብ ኢትዮጵያ አልነበረውም። በ13ኛው ክፍለዘመን ከኦሮሞ የነጠቁት የመንዝ የመራቤቴ ገደላገደል አገር ነው። ይህ ቦታም የመጽሀፍ ቅዱስ ስም “ሸዋ” የሚል ትርጉሙ “የንጉሥ ሸለቆ” የሚለውን አወጡለት። የቀድሞ የዚህ ቦታ ስም በአፋን ኦሮሞ( Afaan Oromootin Firkuta jedhama) ፊርኩታ ይባል ነበር። የአካባቢ ገዥዎችም ማማ፡ ጌራ፡ ደራ ፡ፋጂና(Maamaa, Geeraa, Dharraa, Faajjii) ወዘተ ይባሉ ነበር።
Amsalu G/Kidan Argaw says
አቶ ቃሉ ምን ይሻልሀል ስለ ሴማዊያን ኩሻዊያንና ስለ አንተ እኮ ከአንዴም ሦስት ጊዜ ደጋግሜ ነገርኩህ እኮ እንዴት አይገባህም? እኔ እኮ ትረዳለህ ብየ ነው ይሄንን ያህል የምደክምልህ አንተ ግን ምንም ጠብ ሊልልህ አልቻለም፡፡
በጣም ይገርማል ኦሪን ወይም አራምን አንሥተህ ኩሽ ነውና ኦሮሞ ነው አልክ፡፡ ኦሪ ወይም አራም እኮ የአዳም ልጅ ነው ይሄ እኮ የሆነው የሰው ልጆች በጥፋት ውኃ ጠፍተው የኖህ ልጆች በነገደ ካም(ኩሽ) ሴምና ያፌት ከመከፈላቸው ሁለት ሽህ ዓመታት በፊት እኮ ነው ኦሪ ወይም አራም የነበረው፡፡ እባክህን ንባብህ ጥልቀት ይኑረው ግልብ አትሁን፡፡
ስለ ነገደ ዮቅጣንም አወራህ ታዲያ ይሄንን እያመንክበት አክሱምን እንዴት የኩሻውያን ነው ልትል ትችላለህ? እስኪ እነሱ ገቡ የሚባልበትን ዘመን ወይም ሥልጣን የያዙበትን ዘመንና የአክሱምን ሥልጣኔ ዘመን ያለውን ርቀት አጢነው? አስተውል….?
ባጠቃላይ ግል ልልህ የምፈልገው የታሪክና የቤተክርስቲያን መረጃዎች ልትገምተው ከምትችለው በላይ በሚያሳዝን ሁኔታ ከውጭ በመጡትም ሆነ ከውስጥ በተነሡትም ተበርዟል ተከልሷል ተወናብዷል ተምታትቷል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ መረጃዎች አሉኝ፡፡ የተሻለውንና ተአማኒ ነው ያልኩትን ስለ ሀገራችንና ስለ ሕዝቧ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ለማብራራት ሞክሬያለሁ፡፡ ድገምልኝ ካልከኝ፡-
ቅ.ል.ክ. ሰባት መቶ ዓመታት በፊት ልዑል እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል የተናገረውን ቃል እንመልከት፣ የዚህችን ሀገር ሥረመሠረትና ማንነት ለመረዳት ይበጃል፡፡ ኢሳ.፲፰ን ስናነብ በዚሁ አጭር ምዕራፍ ሁለት ጊዜ ተደጋግሞ የተጻፈን ቃል እናገኛለን፡፡ ቃሉም “እናንት ፈጣኖች መልእክተኞች ሆይ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደሆነ ወገን ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሒዱ” ይላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሱት ኢትዮጵያና ግብጽ በመሆናቸው ይህ ቃል በትክክል ለኢትዮጵያ ይሁን ለግብጽ ማንን ለመግለጽ እንደሆነ ግልጽ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ቃሉን ልብ ብለው ቢመለከቱት ግን ቃሉ በትክክልም ኢትዮጵያን የሚገልጽ እንደሆነ ይረዳሉ፡፡ “ወንዞች ምድራቸውን ወደ ሚከፍሉት ሕዝብ” በማለት ከ ዘጠኝ እስከ ዐሥራሁለት በሚደርሱ ታላላቅ ወንዞቿ ምድሯ የሚከፈለው ኢትዮጵያ እንጂ በወንዞች ሳይሆን በአንድ በዓባይ ለዚያውም በእኛ ወንዝ ብቻ ምድሯ የሚከፈለውን ግብጽ አለመሆኗን ይረዳል፡፡ ይህ ጥቅስ የሀገራችንን ታሪክ፣ ልዕልና ክብር ኃያልነት ወይም አጠቃላይ ማንነት ተጠቅልሎ የተያዘበትና የተገለጸበት ቃል ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሀገራችን ውጪ በእንደዚህ ዓይነት ቃል የተገለጸ ሀገር የለም፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጥንታዊ የአውሮፓ ታሪክ ጸሐፍትም ጭምር ገናና ታሪኳ በስፋት የተገለጸበት አጋጣሚ አለ፡፡ የጥንቱ የአውሮፓዊያኑ የዓለም ካርታ አትላንቲክ ውቂያኖስን ከሁለት ቆርጦ ደቡቡን ክፍል “የኢትዮጵያ ውቂያኖስ” ብሎ ይጠራው ነበር፡፡ በምሥራቁም ዓለም ከታሪክ እንደምንረዳው ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕንድን አልፋ እስከ ቻይና የባሕር ጠረፍ ድረስ ትገዛ እንደነበረ መዛግብት ቢያስረዱም አሁን ያለንበት እና የወደቅንበት ማጥ ይህንን ገናናና የከበረ ታሪክ የሚሰማውንና የሚያነበውን ሁሉ እውነት የነበረ እና የተደረገ መሆኑን እንዳያምን ወይም እጅጉን እንዲጠራጠር ሲያደርገው ይታያል ወይም ይስተዋላል፡፡ አንዳንዴም እንዲያውም “አይ ሌላ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች እንጅ ይህችማ ልትሆን አትችልም” በማለት በድፍረት ያለሐፍረት እስከመናገርና እስከ መጻፍ ሲደረስ ይታያል ለዚያውም ከኢትዮጵያዊያንም ጭምር፡፡ ነገር ግን ያቺ ገናናና ልዕለ ኃያላን የነበረችው ሀገር በእርግጥም ይህች ዛሬ ወድቃ የምናያት አገራችን ኢትዮጵያ መሆኗን መጽሐፍ ቅዱስ የምትገኝበትን መልክዐምድራዊ ቦታ ጭምር እንዲህ ባለ ቃል ይገልጻል፡፡ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፡፡ እሱም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል” ዘፍ. 2፡13 በማለት፡፡ በመሆኑን ግዮን ወይም ዓባይ ከኢትዮጵያ ውጭ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ውስጥ ፈልቆ ምድሯን የሚከባት ወይም የሚዞራት ሀገር ያች ማለት ኢትዮጵያ ናት ስለሆነም ምንም የሚያደናግር ወይም የሚያምታታ ነገር የለም፡፡
እርግጥ ነው ትላንት የነበረችው የኢትዮጵያ አካለመጠን ወይም የቆዳ ስፋት ዛሬ ያለችው ኢትዮጵያ ብቻ እንዳልሆነች በዚህ ዘመን ያለን ኢትዮጵያዊያን የዓይን ምስክር በመሆንም ጭምር የምንረዳው እና የምናውቀው ሀቅ ነው፡፡ ነገር ግን ያቺ ትላንትና የነበረችው ግዙፏና ኃያሏ ኢትዮጵያ የግዛት አካሏ እየተቀነሰ እየተቀነሰ የሚቀነሰው የራሱን ስም እያወጣ ሲሔድ ኢትዮጵያ የሚለው ስም አሁን ያለችው ኢትዮጵያ መጠሪያ ሆኖ ቀረ፡፡ ይሄ መሆኑ ደግሞ ጥንት የምትታወቀዋ ያቺ ገናና ባለሰፊ ግዛት ኢትዮጵያ ትባል የነበረችው ሀገር ምንም እንኳ የግዛት አካሏ ሰፊና ግዙፍ ቢሆንም በወቅቱ ዋና ማዕከሉ ግን ይች አሁን የምናውቃት ኢትዮጵያ እንደነበረ አሁን ድረስ ስሙን ይዛ መቆየቷም አንዱ ማረጋገጫ ነው፡፡ በመሆኑም የጥንቷ ኢትዮጵያ ገናና ታሪክና እሴቶች ሁሉ የማዕከሉ ወይም አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ሀብት መሆኑ እርግጥ ነው ማለት ነው፡፡ ወይም የሚያሻማ ጉዳይ አይሆንም ማለት ነው፡፡
አሁን ቀደም ሲል ወደአነሣነው የነቢዩ ኢሳይያስ ቃል ልመለስ እና “ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ” ረጅም አለ እንጂ እረጃጅም አለማለቱን ልብ ይሏል፡፡ እንዲህ ማለቱም ሊናገር የፈለገው የሕዝቡን ታሪክ እርዝማኔ እንጂ የሰዎቹን የቁመት እርዝማኔ አይደለምና፡፡ “ለስላሳ” አለ ጠባእዬ ሕዝቡን ሲገልጽ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላምና በፍቅር ለመጣው ሁሉ ያለውን ፍቅርና አቀባበል ሲገልጽ፡፡ “ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደሆነ ወገን” እንግዲህ ትልቁ ነገር ይህ ነው፡፡ ከላይ ያልነው ወይም የጠቀስነውን በዓለም ታሪክ ጸሐፍት እንደነ ሄሮዱቶስ እንደነ ሆሜር ባሉት ዘንድ የተነገረውን የጥንቷን ገናና ኢትዮጵያን ታሪክ ከዚህ ጋር ያያይዟል፡፡ ነቢዬ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ከክርስቶስ ልደት ሰባት መቶ ዓመታት በፊት ምን አለ “ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደ ሆነው ወገን” የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀግንነት ታሪክ ከማንም የቀደመ መሆኑን ሲያጠይቅ “ከመጀመሪያው” አለ “ወገን” ማለቱ በአምልኮተ እግዚአብሔር እንደምንዛመድ ለማጠየቅ፡፡ ከዚያም ቀጠለና “ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሒዱ” አለ፡፡ “ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ” ማለቱ ለጊዜው በዘመኑና ከዚያም በፊት የነበረውን ታሪኩን ሲናገር ነው ፍጻሜው ደግሞ በጌታ ምጽአት መቃረቢያ የምትኖረውን በብዙ የትንቢት መጻሕፍት የተነገረላትን ኃያሏን ኢትዮጵያን መግለጡ ነው፡፡ “ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ” አለ ወንዞች ብሎ የበርካታ ወንዞች ባለቤት መሆኗን ሲናገር፡፡ “ምድራቸውን” አለ ያ ታላቅና ገናና ያንን ሁሉ ታሪክ የሠራ ሕዝብ ከደቡብ ዓረቢያ ፈልሶ ምንትስ እንደሚሉት ቀባጣሪያን ዲስኩር ሳይሆን ከመጀመሪያውም መሠረቱ እዚያው መሆኑን ከየትም ስደተኛ መጻተኛ ሆኖ የገባ አለመሆኑን ሲያጠይቅ ሲያረጋግጥ “ምድራቸውን” አለ፡፡
እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔርን አምላኪው ሕዝብ ለዚህም እስከአሁን ድረስ አሻራው ምልክቱ ማስረጃው ያለው ሕዝብ ማን ነው የሚለውን አንተ አጢነውና ማንን ማለቱ እንደሆነ ተረዳ፡፡ እስኪ ልብህን ያብራልህ፡፡
mulat says
የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!
(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)
displaced
July 14, 2014 01:48 am By Editor 5 Comments
ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች” በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡
የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ ማለትም ከውጭ መንግሥታትም ይሁን ከሀገር ውስጥ ነገሥታት መልዕክት ይጻጻፉ የነበረው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን ይሠሩ የነበሩት በአማርኛ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ትግሬ ሆነው ሳለ ይሄንን ማድረጋቸው ቅር ያሰኛቸው የትግሬ ሹማምንት በራስዎ በትግርኛ ቋንቋ የማይጠቀሙት ለምንድን ነው? ብለው ጠየቋቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛም አማርኛ የአክሱማዊያን ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ለእነሱ በማስታወስ ይህንን መለወጥ እንደማይኖርባቸውና እንደማይገባም በመግለጽ ለሹማምንቶቻቸው ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ አክሱማዊያን አማሮች ነበሩ ወይም አማርኛ የእክሱማዊያን ቋንቋ ነው የሚለውን ታሪክ አክሱም አካባቢ ሄዳችሁ ብትጠይቁ የአክሱም ሰዎች በትውፊት ይዘውት እንደመጡ ማለትም አባቶቻቸው አማርኛ የአክሱም ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ይነግሯቸው እንደነበር ይገልጹላቹሀል፡፡ በላይ ግደይ የተባሉ ጸሐፊም “አክሱም” በተባለው መጽሐፋቸው ይሄንን ገልጸውታል፡፡
ታዲያ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ አማራን ወይም አማርኛን ከአክሱምና አከባቢዋ ማንና እንዴትስ አጠፋው ለሚለው ተገቢ ጥያቄ ታሪክ አጥኝዎችና ተመራማሪዎች እስከአሁን አልደረሱበት ሆኖ ይሁን? ወይም አውቀውት ነገር ግን በአንድም በሌላም ምክንያት መግለጽ ስላልፈለጉ? ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡ ከዚህ አኳያ ይህ ጽሑፍ እስከ አሁን ያልተገለጸ ከታሪክ ኩነት መዞ ወይም ገልጦ መረጃ ይሰጣል፡፡
ጥንት ቋንቋቸው አማርኛ ኖሮ ዛሬ ላይ ቋንቋቸው ትግርኛ የሆነ አክሱሞች ብቻ አይደሉም፡፡ ከዚያው ከአጠገባቸው የወልቃይትና ከፊል ጠገዴን ሕዝብ ታገኛላቹህ፡፡ የእነኚህን አካባቢ ሰዎችን ማንነታቸውን ብትጠይቋቸው አማራ ጎንደሬ እንደሆኑ ይነግሯችኋል፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ግን ትግርኛ ነው፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሀገራቸውን ከጎንደር ቆርጦ ወደ ትግራይ ሲቀላቅልባቸውም ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደተቃወሙ ነው፡፡ በተለያዬ ጊዜ በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ወልቃይቶች የዚህ መንግሥት አመራርና ነባር ታጋይ የሆኑትም ሳይቀሩ ለመንግሥት ሥራ እውጭ ባሉበት “እኛ ትግርኛ ስለተናገርን ብቻ እንደ ትግሬ ልንቆጠር አይገባም ማንነታችን ይጠና እኛ ትግሬ አይደለንም” በማለት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ በተቃውሞ ሰልፉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡
የአክሱም ነገሥታት አማርኛ የቤተመንግሥት የሚስጥር ቋንቋ አድርገው ከመፍጠራቸው በፊት ቋንቋቸው ሙሉ ለሙሉ ግእዝ ነበር፡፡ አማርኛ ሊቀድም እንደሚችልም የሚያመላክቱ አንዳንድ ጠቋሚ ነገሮችም አሉ፡፡ የአክሱም ነገሥታት ስሞቻቸውን ያዬን እንደሆነም በተለያዩ ምክንያቶች በባዕዳን ማለትም በዕብራይስጥ፣ በጽርእ፣ በሮማይስጥ ስሞች ከተጠሩት ውጪ ስሞቹ ግእዝ ካልሆኑ አማርኛ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ የጠፉ ወይም የተረሱ የአማርኛ ቅላት ሆነው ለመረዳት የሚያስቸግሩ አማርኛዎች ቢበዙም አሁንም ድረስ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ባሉ ቃላት የሚጠሩ የአክሱም ነገሥታት ስሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን ብናነሣ ምኒልክ (ምንይልክ) ቅ.ል.ክ 982-957፣ ዙዋሬንብረት 1ኛ ቅ.ል.ክ. 599-558፣ ዙዋሬንብረት 2ኛ ቅ.ል.ክ. 276-260፣ ግርማአስፈር 77-86 ዓ.ም፣ አርፍድ (ገ/መስቀል) ከ357-361 ዓ.ም፣ ወሰንሰገድ 557-572 ዓ.ም፣ ጉም 693-717 ዓ.ም፣ አስጎምጉም ከ717-722 ዓ.ም፣ ለትም ከ722-738 ዓ.ም፣ ተላተም ከ738-759 ዓ.ም፣ አይዞር ለ6 ሰዓታት፣ ውድማአስፈር ከ787-817 ዓ.ም፣ አንበሳውድም (አንበሳአውድም) ከ882-902 ዓ.ም ድልነአድ 902-912 ዓ.ም፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት ሕዝቡ በዘር አማራ ሆኖ እንዴት ባለ ሁኔታ ይገዛ ቋንቋቸውን አጥፍተው ወይም ትተው ቋንቋቸው ያልነበረውን ትግርኛን ቋንቋቸው ሊያደርጉ እንደቻሉ እንይ፡፡ ይህ ድርጊት ከመጀመሪያውና ለ40 ዓመታት በተከታታይ ያለ ሟቀረጥ ከተፈጸመው እጅግ ከባዱና አሰቃቂው በአማራ ሕዝብ ላይ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ዘመኑ 842 ዓ.ም 882 ዓ.ም ድረስ በጨካኟና በክፏዋ “እሳቶ ወይም ጉዲት” በመባል በምትታወቀዋ ዮዲት የተፈጸመ ነው፡፡ የዓረብና የምዕራቡ ዓለም ታሪክ ጸሐፍት “ክርስትና የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ በ አራተኛው መቶ ክ/ዘመን በአብርሃና አጽብሐ ወይም በኢዛናና ሳይዛና ከመታወጁ ጋራ በተያያዘ በመጨረሻ በአማራ አሸናፊነት እስኪጠናቀቅና ተሸናፊዎቹ ፈላሾች በሀገሪቱ አርሶ የመጠቀም መብት ተነፍገው በእጅ ሞያና በጉልበት ሥራዎች የአማሮች አገልጋዮች እንዲሆኑ እስኪፈረድባቸው ጊዜ ድረስ በአማሮችና በፈላሾች (ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩ ቤተ እስራኤሎች) ማለትም አይሁዶች መሀከል እስከ ዮዲት ጊዜ ድረስ ለአምስት መቶ ዓመታት የዘለቀ ጦርነት ተደርጓል” ሲሉ ጽፈዋል፡፡ ልብ አድርጉ “በአማሮችና በፈላሾች” መካከል፡፡
የዮዲት ጉዲት ዘመን ግን ፈላሾች ጦርነቱን አሸንፈው ያሻቸውን ማድረግ የቻሉበት በኢትዮጵያ ታሪክ ሊገለጽ ከሚችለው በላይ ሀገሪቱ ከዚያ ዘመን በፊት የነበራትን ሥልጣኔ የሚያሳዩ ቅርሶችን ከጥቂት ምልክቶች በስተቀር ወድሞ የጠፋበት ዘመን ነበር፡፡ በዚያ ዘመን የክርስትና መታወጅ መጀመሪያ ግጭት ፈጠረ እያደር ግን በሀገሪቱ የአይሁድና የክርስቲያን ቀጠና ለይቶ ሀገሪቱን ለከባድ ኪሣራ ለዳረገና እጅግ ለተራዘመ ጦርነት ምክንያት ሆነ፡፡ ከ500 ዓመታት በኋላም አይሁዶች ወይም ፈላሾች በለስ ቀንቷቸው ጦርነቱን አሸንፈው በገነኑበት በ40 ዓመታት በዮዲት ጉዲት ዘመን ነበር አማሮችን በአክሱምና አካባቢዋ በተቻላትም መጠን በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል እንዲጠፉ ያደረገችው፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለነገሩ ወደ ታችም ወረድ ይላል አንድ ትውፊታዊ አባባል አለ እሱ ምንድን ነው? በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል “አማራ” ማለት የዘር ስም ብቻ አይደለም የሃይማኖትም ስም ጭምር እንጂ፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሰዎች በዘር ትግሬ ወይም ሌላ ቢሆኑም ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ ክርስቲያን ነኝ ለማለት “አማራ” ነኝ ይላሉ፡፡ ይህ አንድ ዐቢይ ነገርን ግልጽ አድርጎ ያሳያል፡፡ በዚያ ዘመን ይደረግ የነበረው ጦርነት በማንና በማን መሀከል ይደረግ እንደነበረ፡፡
በመሆኑም ዮዲት ጉዲት ጠላቶቿ አድርጋ የተነሣችባቸውን በዘርና በሃይማኖት “አማሮች” የሆኑትን አክሱማዊያንን ከመላ ሀገሪቱ ያለ ርህራሔ በጨከነና በማይታጠፉ ውሣኔ ጨርሶ የማጥፋት ዘመቻዋን በመላ ዘመኗ (ለ40 ዓመታት) ስትፈጽም በነበረበት ዘመን አማሮች ከዚያ መቅሰፍት ለመዳን ለመትረፍ ወይም ለማምለጥ ከመሰደድ በመለስ የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ አማራነታቸውን ማስተባበል ወይም አማራ እንዳልሆኑና ትግሬ እንደሆኑ ለአጥፊዎቻቸው ለዮዲት ጉዲት ሠራዊት መግለጽ ነበር፡፡ ይህ የመከራ ዘመን የአንድ ትውልድን ዘመን (33 ዓመታት) ጨርሶ የቀጣዩን ትውልድ ዘመንም አጋምሶ ስለነበርና ዮዲት ጉዲት ድል ከተመታችም በኋላ ያ መራራ መከራ ደግሞ ተመልሶ ላለመምጣቱ እርግጠኛ ያለመሆን ሥጋት ችግር እንዲህ ነበርን ከሚለው ትውፊታዊ ውርስ በቀር የአክሱምና የአካባቢዋን ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከማንነቱ ማለትም ከአማራነቱና ከቋንቋው አለያይቶት ሊቀር ቻለ፡፡
ከዚያም በኋላ የቤተክርስቲያንና የሀገራችን ታሪክ ጸሐፍት በሰዓቱ ግልጽ ሆኖ የሚታየውና የሚታወቀው ነገር ልክ በእነሱ ዘመን በግልጽ እንደሚታወቀው ሁሉ በኋላ ዘመንም እንደዚያው በግልጽ ታውቆ የሚቀጥልና ዛሬ ያለው ያ ችግር የፈጠራቸው የታሪክ ባለቤት ማንነት ያለመታወቅና ለተሳሳተ ግንዛቤ የሚዳርጉ ክፍተቶች በኋለኛው ዘመን ላይ የታሪክ መሳከር ወይም መጣረስ ሊያስከትል እንደሚችል ባለመገመታቸው ጦርነቱ ሃይማኖታዊ እንደነበረ ዮዲት ጉዲት በቤተክርስቲያን በሕዝቡና በሀገሪቱ ላይ ያወረደችውን መዓትና ጥፋት እንጂ በአማራና በፈላሻ መሀከልም እንደነበረ አጉልተው ወይም ግልጽ ባለ ቋንቋ ሳይገልጹት ቀርተዋል፡፡
እንግዲህ ይህ ታሪክ ማለትም የዮዲት 40 ዓመታት ዘመን፤ አይደለም በሀገራችን በውጭ ጸሐፍት ሳይቀር በሚገባ የሚታወቅ አሳዛኙ የታሪካችን ገጽታ ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከያኔያን (አርቲስቶች) ሳይቀሩ ንቁ ተሳታፊ ሆነው እየተንቀሳቀሱበት ያሉበት በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳልሞተና በእሳት ሰረገላ እንደተነጠቀ የተገለፀው ነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ሰው እንደመሆኑ በዳግም ምጽአት ዋዜማ ሞትን ለመቅመስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በትርጓሜ መጻሕፍት በግልጽ ተጽፎ እያለ ነብዩ ኤልያስ ኢትዮጵያን ሊታደግ በሁለት አፉ የተሳለ ሰይፍ ይዞ መጥቷል የሚሉ የሐሳዊያን ቡድን ያሰራጨው መረጃ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ የሚታወቁ እውነቶችን በተቃራኒው በመገልበጥ በፈጠራ ታሪክ መጥፎውን መልካም አጥፊውን ገንቢ ኃጥኡን ቅዱስ እንደነበሩ በማበል ፈጽሞ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ታሪክን የማጠፋፋት ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡
ለምሳሌ በዚህች ሀገር ላይ ያንን ሁሉ ጥፋት በማድረሷ ታሪክ የሚያውቃትን ዮዲት ጉዲትን ቅድስት እና ሠማዕት ናት እንጂ አጥፊ አይደለችም ይላሉ፡፡ እሷን ብቻም ሳይሆን በዐፄ ዘርዓያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በኑፋቄአቸው ወይም በክህደታቸው ምክንያት ንጉሡ የቀጧቸውን ቤተክርስቲያን ያወገዘቻቸውን መናፍቃንን ማለትም ደቂቀ እስጢፋዎችን ከሀዲያን መናፍቃን ሳይሆኑ ቅዱሳን ሠማዕታት ናቸው በማለት በጠራራ ፀሐይ በሀገሪቱና በቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ አስገራሚና አስደንጋጭ እጅግ ኃላፊነት የጎደለው የጥፋትና የክህደት ደባውን በመተብተብ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንድ የዚህ ቡድን ሌላ ክንፍ ሊሆን እንደሚችል የሚገመት በመንግሥትም ድጋፍ የሚደረግለትና የብዙኃን መገናኛ ሽፋን እየተሰጠው ያለ ሌላ ቡድን የዐፄ ዘርዓያዕቆብንና የደቂቀ እስጢፋን የጥል ጉዳይ ምክንያት ዛሬም ባለው የቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ማረጋገጥ የሚቻል ሆኖ እያለ ጎዳዩ ሃይማኖታዊ እንዳልነበረና ፖለቲካዊ እንደነበር ጸቡ የአማራና የትግሬ እንደነበር አድርጐ በሰፊው በመለፈፍ ላይ ይገኛል፡፡ የእነዚህ ሁለት የሐሳዊያን ቡድኖች በአንድ ወቅት አንድ ዓይነት መልዕክትና አቋም ይዘው ብቅ ማለት እንዲሁም በስውር ጥቅሙን ሊያስጠብቁለት የፈለጉት አካል ማንነትና ሌሎች ነገሮች ሲታይ ከእኒህ እንቅስቃሴዎች ጀርባ ይህ የአገዛዝ ሥርዓት መኖሩን ይጠቁማል፡፡
እዚህ ላይ አንድ ገጠመኝን ብናገር ነገሩን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ አንድ ድንግላዊ ነኝ የሚል ግን መነኩሴ ያልሆነ በቅቻለሁ በደመና ተጭኘ ኢየሩሳሌምን ጨምሮ የፈለኩበት ሀገር እመላለሳለሁ ከተሠወሩ ቅዱሳን ጋርም እገናኛለሁ ከሚል ሰው ጋር ጓደኞቼ አስተዋወቁኝ ለጊዜው በጓደኞቼ ወሬ ተሞልቼ ስለነበር እውነትም የበቃ ከቅዱሳን አንዱ መስሎኝ ነበር፡፡ ይህ ሰው እንደላይኞቹ ቡድኖች ሁሉ ዮዲት ጉዲትንና ደቂቀ እስጢፋን የሚያወድስ ከመሆኑም በላይ ትንቢት ነው እያለ የሚያወራው የዚህን ሥርዓት ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ ቀምሮና አበጃጅቶ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን እየተሠራ ያለውን ደባ ለመግለጽ ስለወደደ ይህ ሰው ማን እንደሆነ የማውቅበትን ጥሩ አጋጣሚ ፈጠሮ እንዳውቅ አደረገ፡፡ እናም ይህ ሰው ድንግላዊ ሳይሆን የቤተሰብ ኃላፊ መሆኑንና ሥራውም እራሱን እየለዋወጠ በየገዳሙና በየጸበሉ እየዞረ የሚሰልል “የመንግሥት” መረጃ ወይም ሰላይ መሆኑን ደረስኩበት፡፡ እንግዲህ እነኝህ ሰዎች ለምን ዓላማ የቱን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶኛል፡፡
yoditወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ እናም የዮዲት መጨረሻ ሲቃረብ ማለትም ሸዋ መራቤቴ ላይ በተደረገው ጦርነት ዮዲት ጉዲት ከተገደለችና ሠራዊቷም ከተደመሰሰ በኋላ አማሮች ወይም አክሱማዊያን የነበረውን የአክሱም ሥርዎ መንግሥት ለማስቀጠል ሞክረው ነበር ነገር ግን ለ40 ዓመታት ያህል የነበረው መከራ የሥርዎ መንግሥቱን መሠረት እጅግ አናግቶት ስለነበር ለ30 ዓመታት ከቆዩት ሁለት ነገሥታት በኋላ ማስቀጠል ሳይችሉ በዛጉዌ ወይም በአገው ሥርዎ መንግሥት ተገልብጦ የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥትም ከ912-1245 ዓ.ም ድረስ ለ333 ዓመታት 11 ነገሥታትን አንግሦ ኢትዮጵያን ሲገዛ ቆይቶ አቡነ ተክለሃይማኖት ሥልጣኑ ለነበረው ለሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት መመለስ አለበት በማለታቸው አቡነ ተክለሃይማኖትና የመጨረሻው የዛጉዌ ሥርዎ መንግሥት የመጨረሻው የነበረውን ንጉሥ ይትባረክ ባደረጉት ሰላማዊ ስምምነት ሥልጣኑ ወደ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ተመልሶ መቀመጫውን ግን አክሱም ሳይሆን ሸዋ አደረገ፡፡ በእርግጥ የአክሱም ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ሸዋ ሲያደርግ ይህ የመጀመሪያው አልነበረም ከአብርሃ ወአጽብሐ ከ298 ዓም – አምሲ 461 ዓ.ም ድረስ 28 የአክሱም ነገሥታት ከአክሱም ባሻገር መቀመጫቸውን ሸዋ የረር ላይ ማለትም አዲስ አበባ ምሥራቃዊ ጫፍ ላይ ከሚታየው የረር በመባል በሚታወቀው ከፍታ ቦታ ላይ አድርጎ ቆይቷል፡፡ አሁንም ድረስ የዚያ ታሪክ አሻራዎች በቦታው ይገኛሉ፡፡
ከዚያም ይህ ሥርዎ መንግሥት እስከ ግራኝ መሐመድ በወረራውና በጦርነቱ ከነሕዝቡ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ገፍቶ እስከ ሰደዳቸውና ሁለተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ለ15 ዓመታት ያህል እስከተከሰተበት ጊዜ ዐፄ ልብነ ድንግል ድረስ ቆየ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል በጦርነቱ ከመናገሻቸው ሸዋ ከተረፈው ሕዝባቸው ጋር ተፈናቅለውና ተሰደው ሰሜን ኢትዮጵያ ጫፍ ድረስ ተሰደው አንዳሉ በሞት ተለዩ ግራኝ መሐመድ ለ15 ዓመታት ያህል ክርስቲያኑን (አማራውን) ሕዝብ እያሳደደ ፈጀው በሀገሪቱም ላይ ከዮዲት ጉዲት በከፋና ተወዳዳሪ በማይገኝለት ጨርሶ ኢትዮጵያዊ ወገናዊነት ባልተንጸባረቀበት በፍጹም ባዕዳዊ ስሜት ሀገሪቱን ከሥር ነቀላት አደቀቃት የቤተመንግሥትና የቤተክህነትን ሀብቶችና ቅርሶችን ሁሉ ጥርግ አድርጎ ለእርዳታ ላመጣቸው አረቦችና ለቱርኮች ጦር ሰጠ፡፡
ተንቀሳቀሽ ያልሆኑትንም አፈራረሰ ደመሰሰ ሌላው ቀርቶ በሀገሪቱ አንዲት ዛፍ እንኳን ቆሞ እንዳይቀር እስከ ማድረግ የደረሰ በገሪቱን ከሥር የመንቀል የጥፋት ዓላማ አንግቦ አወደመ፡፡ ሕዝቡንም አልሰልምም ያለውን እየሰየፈ ሞትን ፈርተው እሽ ያሉትን እያሰለመ ሲዋጋ የቀረው ሕዝብ ከንጉሡ ጋር ተሰዶ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተቅበዘበዘ እንዳለ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ቀየውን ጥሎ በመሰደዱ ባዶና ነጻ ሆኖ ያገኙትን መሬት በ15 ዓመታቱ ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው በቦረና በኩል በመግባት ሰፊ መሬት ለመቆጣጠር ዕድል አገኙ፡፡ ዐፄ ልብነ ድንግል ከሞቱ በኋላ ልጃቸው ዐፄ ገላውዴዎስ በስደት እንዳሉ በ1530 ዓ.ም ነግሠው ከፖርቹጋሎች ባገኙት እርዳታ ታግዘው ግራኝን ጎንደር ፎገራ ላይ ገድለው ድል አደረጉት ግራኝን ከገደሉና ሠራዊቱንም የማረኩትን ማርከው የሸሸውም ከሸሸ በኋላ ወደ አባቶቻቸው መናገሻ ሲመለሱ ከሀገሩ የሚበዛው በእንግዶች ማለትም በኦሮሞ ተወላጆች ተይዞ አገኙት፡፡ ንጉሡም የሕዝባቸውን ማለቅ ተመልክተው በጣም የሳሳውን የሕዝባቸውን ቁጥር ለማካካስ እንደሚረዳቸው በማሰብና ፈቃደ እግዚአብሔር እንደሆነ በመገመት ለእንግዳው ሕዝብ የጎሳ አለቆች ሕዝቡ ሀገሬውን መስሎ ለመንግሥት እየገበረ የሚኖር ከሆነ ሕዝቡ ካለበት ስፍራ መኖሩን እንደሚፈቅዱ አስታወቁ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ አለቆችም ይህንን ችሮታ በደስታ በመቀበል ሀገሬውን መስለው እንደሀገሬው ሕዝብ እየገበሩ ለመኖር ቃል በመግባት የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን አገኙ፡፡ ሌላ አዲስ ፈላሲ እንዳይገባ ግን የቦረናን በር ዘጉ፡፡ እንግዲህ ይህ ከሆነ ረጅም ወይም በጣም ሩቅ የማይባል ማለትም አምስት መቶ ዓመታት መሆኑ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳል በፋሽስት ጣሊያን የ5 ዓመታት የወረራ ጊዜ የፋሽስትን የጥፋት ምክር በመስማት እንዲሁም የ1983ቱን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ የጥፋት መልዕክተኛ በሆኑት ምክርና ግፊት በሚያሳዝን ሁኔታ የኦሮሞ ተወላጆች ከዐፄ ገላውዴዎስ ጋር አድርገውት የነበረውን ስምምነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች እውነቱን እያወቁ ሳያውቁም ሊሆን ይችላል እራሳቸውን እንደባለቤት በመቁጠር ጭራሽ አማራውን ሀገራችንን ለቃቹህ ውጡልን በማለት ከዚያም አልፈው የብዙ ንጹሐን ዜጎችን ደም በጭካኔ አፈሰሱ መጠኑ ከፍተኛ ነው ባይባልም ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ የተደረገው አራተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀል ነበር፡፡ ሦስተኛው የዘር ማጥፋት ሊባል የሚችለው ኦሮሞዎቹ ሸዋ ላይ የነበረውን ሰሎሞናዊ ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ጎንደር እንዲያደርግ እስከ መገደድ ድረስ የደረሰ አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን ማውደምን የጨመረ ጥቃት በተለያየ ጊዜ በፈጸሙ ጊዜ ያደረሱት ጥፋት ነው፡፡
ዛሬ ደግሞ ነገሩ ከዚያም አልፎ የኦሮሞን ሕዝብ ስም ያለ ፍላጎቱ መጠቀሚያ ያደረጉ እንገነጥላለን የሚሉ የጥፋት ኃይሎች ተፈጥረው ቁጭ አሉ፡፡ ኧረ ተዉ ሕሊና ይኑረን እንጂ ምነው? የማንን ሀገር ነው የምትገነጥሉት? ለነገሩ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ብሔረሰቦች አንዱ ከሌላው ጋር ተቀላቅሉ ተዋልደው ተዋሕደው ወቶላቸዋልና አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ወዘተ. የሚባል ሕዝብ ባይኖርም ቅሉ አሁን ትላንትና በእንግድነት ተገብቶ ዝም ተብሎ የሰው ሀገር መገንጠል አለ እንዴ? ለዚያ ውለታ ልትከፍሉት የሚገባው ብድራትስ ይሄ መሆን ነበረበት እንዴ? ሁላችንም ዘራችንን ወደ ኋላ ብንቆጥር አንድና ከአንድ በላይ የሌላ ዘር ደም ተቀላቅሎበት እናገኛለን መረጃውን ለማግኘት ውስንነት ወይም የአቅም ችግር ካላጋጠመን በስተቀር፡፡ በመሆኑም የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ ጨርሶ ሊሠራ አይችልም ለመሥራት ከተሞከረም በእውነት ላይ ያልተመሠረተና ድንቁርና የተሞላ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስላለውና ስለምናየው ሳይሆን ስለሌለውና ስለማናየው እናወራለን እንደክማለንና ጅሎችም ነን፡፡ ይሄንን ማለት ግን የአማራ የትግሬ የጉራጌ የኦሮሞ የመሳሳሉት ባሕል ቋንቋና ሌሎችም መገለጫዎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ እነሱም ቢሆኑ ግን አንደኛው ከሌላኛው ጋር አልተወራረሰም አልተቀላቀለም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡
ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና አፄ ገላውዴዎስ ሸዋ ሆነው ከገዙ በኋላ ከሳቸው በኋላ ከነገሡት ከዐፄ ሚናስ በኋላ ያሉት የዚህ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት መቀመጫቸውን ወደ ጎንደር በማዞር በመጨረሻ በዳግማዊ ምኒልክ ወደ ሸዋ ከመመለሱ በፊት በላስቴው ዐፄ ተክለጊዮርጊስ 1860 ዓ.ም-1863 ለሦስት ዓመታት መቀመጫቸውን ጎንደርና ላስታ በማድረግ ቀጥለውም የትግሬው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከ1863 ዓ.ም-1881 ዓ.ም መቀመጫቸውን መቀሌና ጎንደር በማድረግ ጣልቃ ከመግባታቸው ውጭ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ መቀመጫውን ጎንደር አድርጎ ቆይቶ ነበር፡፡
እንግዲህ ይሄንን ታሪክ ማለትም በአክሱማዊያን (አማሮች) ዙሪያ ያለውን እውነት የሕወሀት ባለሥልጣናት በሚገባ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ በሁለት መንገዶች 1ኛ እንደማንኛውም የትግራይ ሕዝብ ተወላጅ በትውፊታዊ መረጃ 2ኛ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በአንድ 100 ዓመታትን በራቁ የትግራይ ተወላጅ ሽማግሌ አባት ይሰጣቸው በነበረ ምክርና ትምህርት፡፡ እኒህ አረጋዊ ሰው የኢሕአዴግን ምልክት ንብ እንዲሆን ያስቻሉም ሰው ናቸው፡፡ እኒህ ሰው ሕወሀቶችን እናንተ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ የካሳ ምርጫ ልጆች ናቹህ እያሉ ይነግሯቸው እንደነበር የሕወሐት አመራሮች ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳ ይህንን እውነት የሚያውቁ ቢሆንም በዮዲት ጊዜ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አሁን ባለው የሕዝብ አሰፋፈር አማሮች ወይም አማርኛ ተናጋሪ አክሱም አካባቢ አለመኖራቸውና አካባቢው በትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መያዙ ቢያንስ ምንም የታሪክ ዕውቀት በሌላቸው ዜጎች ዘንድ አክሱም የትግሬ ተወላጆች እንደነበረ ተደርጎ እንዲታሰብ በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በሰው ወርቅ ለመድመቅ ሲሞክሩና ሲቋምጡ ይታያሉ፡፡
ይሁንና ሥነ ልቡናቸውና ሰብእናቸው ማለትም ሕወሐቶች ለታሪክ ለድንበር ለቅርስ ለመሳሰሉት ሀብቶቻችንና እሴቶቻችን ያላቸው አመለካከት ሲታይ ግን ከአክሱም ሥርዎ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንዳልነበራቸው ሲያሳብቅባቸው ወይም ሲያሳጣቸው ይታያል ምክንያቱም ሕወሀቶች ለእነዚህ እሴቶቻችን ባጠቃላይ ለሀገሪቱ ታሪክና እሴቶች ያላቸው ግልጽ የሆነ ጥላቻና ዴንታቢስነት ወይም ለእነዚህ እሴቶቻችን ያላቸው ፍቅርና አቅርቦት ደካማ ወይም የምናውቀውን ያህል ነውና፡፡ ይህ ማለት ግን የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ለታሪካችን ለነጻነታችን ለሉዓላዊነታችን ለድንበራችን ለቅርሶቻችን ወዘተ. ዴንታ ቢስና ግድየለሽ ነው ማለት አይደለም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የአማራን የባለአደራነት ስሜት ማለትም ለታሪክ ለቅርስ ለድንበር በአጠቃላይ ለሀገር ያለውን ተቆርቋሪነት ያየን እንደሆነ የሚመሰገንና አርዓያነትም ያለው ነው፡፡ እንግዲህ ይሄ ከየትም የሚመጣ ሳይሆን እንደ ንብረት ሁሉ ከቀደሙት ትውልዶች የሚወረስ የባለ አደራነት የባለቤትነት ስሜት መንፈሳዊ ውርስ ሀብት ወይም እርሾ በመኖሩ ነው፡፡ ይሄንንም ስል የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ስሜት የለውም እያልኩ አለመሆኔ ይታወቅ፡፡ ትንታኔዬ ያተኮረው ከላይ በተገለጸው አካባቢና ርዕሰ ጉዳይ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
የ1983 ዓ.ም የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ በአማራ ሕዝብ ላይ በግልጽና በስውር በእቅድና በተጠና መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬም እንደ ዮዲት ዘመን ለመኖርና ለመብላት በሚል ማንነቱን ማለትም አማራነቱን የካደውና የደበቀው ለአማራነቱ ግድ የለሽ የሆነው ጭራሽም እንዴት እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ቅንጣት ቁጭትና ጸጸት ሳይታይባቸው ከግፈኞች ጋር ተባባሪ በመሆን በገዛ ማንነታቸው ላይ የዘመቱ ሰዎች ቁጥር የትየሌሌ ነው፡፡ የዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል መገለጫ ዘርፈ ብዙና የተወሳሰበም ነው፡፡ በገሀድ ከተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በቅርብ ትውስ የሚሉትን ስናነሣ በእነ ታምራት ላይኔ ዓይነቱ በሕወሃት መራሹ “መንግሥት” ባለሥልጣናት ገፋሪነት ሥልጣን በያዙ ማግሥት በአቦምሳ ወይም በአርባጉጉ በሌሎችም ሥፍራዎች በአማራነታቸው ብቻ ከሕፃን እስከ አረጋዊያን በጭካኔ የተገደሉና በተለያዬ ጊዜም ከበደኖ ከጉራፈርዳ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ንብረታቸውን ወርሰው ማባረራቸው የገዛ ሕገመንግሥታቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ስፍራ ሠርቶ የማደር ኑሮውን የመመሥረት ሕገመንግሥታዊ መብት አለው እያለ በአንድ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ማፈናቀል በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ተፈጸመ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ሲጠየቁ ምን ብለው መለሱ ይህ የክልሉ መንግሥት ጉዳይ ነው ሕገወጥ ሰፋሪዎች ናቸው ካለና አልፈልጋቸውም ካለ መብቱ ነው ይችላል በማለት የገዛ ሕገመንግሥታቸውን የሚፃረር ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ መልሳቸውም ይህ ጉዳይ የተፈፀመው በእሳቸው ትዕዛዝ መሆኑን ጠቆመ ለነገሩ በ21 ዓመታቱ የወያኔ መንግሥት አስተዳደር ተሞክሮ እንደምንረዳው እንዲህ ዓይነቱ ከባድና አሳሳቢ ውሣኔ በክልል አስተዳደሮች ደረጃ ሊወሰን እንደማይችል መረዳት አያዳግትም፡፡ አቶ መለስ እንዲህ ብለው ሲሉ እናንተም በጊዜአቹህ እኛ እንዳደረግነው ሁሉ ትግሬን ባዶ እጁን አራግፋቹህ አፈናቅላቹህ ማባረር ትችላላቹህ ማለታቸውና ይህንን አዲስ አዙሪት ባርከው መጀመራቸው እንደሆነ አቶ መለስ ጨርሶ አልገባቸውም፡፡
“አየ ጭንቅላት አየ የኛ አርቆ አሳቢ” የብልህነትንና የአርቆ አሳቢነትን ትርጉም ለማያውቁ ሰዎች አርቆ አሳቢ መሪ ማለት ውሎ አድሮ ምን ሊያስከትል እንደሚችል መገመት ተስኖት በሰላምና በፍቅር የሚኖርን ሕዝብ እንዲናቆር ማሴር እንዲፋጅ እንዲባላ መሸረብና መጣር ቀን እንዲጠባበቅ ማድረግ ሳይሆን እንኳን ያላጣውን ሰላም ፍቅር አንድነት ሕብረት ያጣ ሕዝብ እንኳን ቢሆን ኖሮ እንዲህ የሆነውን ሕዝብ ማስማማት ማግባባት ማፋቀር ማዋደድ መቻል ነው ብልህና ባለአእምሮ መሪ ማለት እንጅ የሚያናቁረውና ለማፋጀት የሚጥረው አይደለም ያ ደደብ ደንቆሮ እንጂ ብልህና አሳቢ ሊባል ከቶ እንዴት ይቻላል? የኢትዮጵያ ሕዝብ አላውቃቸው ብሎና ተስፋ አልቆርጥ ብሎ ነው እንጂ ከእነዚህ መንግሥታዊ ዳሲኘሊን (ሥነ ሥርዓት) ከማያውቁ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የሚባል ነገር ጨርሶ ከማይገባቸው፣ የጫካ አውሬዎች የመንደር ወጠጤዎች የስርቻ ወሮበሎች የቆሻሻ ሥነ ምግባር መፍለቂያዎች ከሆኑ ከእነዚህ ጉዶች ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቅ ኖሯል፡፡ እድሜ ዘመናቸውን ሳይለወጡና ሳይሰለጥኑ ጭራሽ እየባሰባቸውና እየደነቆሩ ሄደው ቁጭ አሉ፡፡ ይለወጣሉ ብላቹህም ከቶም ተስፋ አታድርጉ፡፡
ወደ ሌሎቹ አማራን የማጥፋት ወንጀሎች ዓይነቶች ስናልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የአማራ ተወላጅ በስውር ደባ ሠርቶ የመኖር ዕድል መነፈጉ፣ በአንድ ወቅት ላይ በተለይ ጎጃም የወባ ወረርሽኝ ገብቶ ሕዝቡን ሲጨርስ የአገዛዙ አካላት ተነግሯቸውና እያወቁ ፓርላማ ውስጥ መነጋገሪያ እስከመሆን ሲደርስ መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ደርጅቶች እስኪታዘቡ ድረስ አገዛዙ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ምንም ዓይነት የህክምና አቅርቦት እንዳይሰጥ በማድረግ ሕዝቡ እንዲያልቅ መደረጉ፣ ከዓመታት በፊት የጎንደር ፖሊስ በወገናዊነት ቁጭት በመነሣሣት ጫትን በቸልተኝነት ዝም ብለን በመመልከታችን ትውልዱ እንዳለ የጫት ሱሰኛ እስከመሆን ደረሰ አሁን ደግሞ ይሄ ሺሻ የሚባለውን ዝም ብንል ነገ እንደጫቱ ልንቀለብሰው ከማንችልበት ደረጃ መድረሳችንም አይደለ? በማለት ተነሣስተው ከየጫት ቤቱ ሲሰበስቡ ወዲያውኑ ከክልል ተደውሎ ማን አዛዛቹህ አሁኑኑ በአስቸኳይ መልሱ ተብለው እንዲመልሱና ትውልዱ ሱሰኛና እንኩቶ ብላሽ እንዲሆን ጥረት መደረጉ፣ በሀገሪቱ ሁለት ዓይነት የትምህርት ሥርዓት በመቅረጽ በትግራይና በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ያለውን በመለያየት በተለይ ደግሞ የአማራውን ክልል የትምህርት ጥራት ደረጃ አሳዛኝ በሆነ መልኩ እንዲወድቅ መደረጉ የመሳሰሉት ሲሆኑ በስውር ከሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ደግሞ ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ፡-
አንደኛው በአማራ ክፍላተ ሀገራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምክንያታቸው ያልታወቁና ያልተገለፁ በየጊዜው የሚከናወኑ የጅምላ ክትባቶች አሉ፡፡ እነኝህ ክትባቶች የተከተቡትን ሰዎች መውለድ እንዳይችሉ የሚያደርጉ ክትባቶች ናቸው፡፡ ይህ ክትባት በተደጋጋሚ ሲፈጸም የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ በክትባቱ ወቅት በመቅረት ሳይከተቡ የሚቀሩ ወገኖች እንዳሉ ታወቀ፡፡ የስውር ደባ ሰለባ እየሆኑ እንደሆነ የገባቸው ተማሪዎች የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ ላለመከተብ የሚያደርጉት ጥረት የአሳዛኙ ቲያትር አስቂኝ ገጽታ ሆኖ ታይቷል፡፡ ወደ ኋላም ሕዝቡ ይሄንን ጉዳይ ጭራሽ የወጉ ማጣፈጫና ማምረራያ አድረጎት አረፈ፡፡ ሽለ ሙቅ የሆነች ሴት ስትታይ “አሀ ይች ከክትባት ያመለጠች ናት” ያባላል ስሜተ ቀዝቃዛዋን ደግሞ፣ “ይች ተከታቢ ናት” እያለ እስኪቀልድበት ድረስ ይህ ጉዳይ የሕልውናውን ጉልህ ሥፍራ እንደያዘና ማወቁን ወይም መንቃቱን ጠቆመ፡፡ ከዚህ የተለየ ግን ምንም ያደረገው ነገር የለም፡፡ በሌሎች ሀገሮች ቢሆን ግን ከዚህ የበለጠ የሕዝብ አመጽ ሊቀሰቅስ የሚችል ምክንያት ባልነበረ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በተለይ 1996/97 ዓ.ም. ፀረ ትራኮማ ክትባት በሚል ሽፋን በበርካታ አካባቢዎች በተለያዬ ጊዜ የተደረጉ ክትባቶች ብዙ ሕፃናትንና ነፈሰጡር እናቶችን ለሞት አብቅተዋል፡፡ በነዚህ የአማራ አካባቢዎች የቀብር ስፍራዎች ብትዘዋወሩ ከቀድሞው በተለየና ባልተለመደ መልኩ በርካታ የሕፃናትና የነፍሰጡር እናቶች መቃብሮችን ታያላችሁ፡፡ እንግዲህ እነኝህና ሌሎች እነኝህን የመሳሰሉ ስውርና ድብቅ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ በግልጽ በአደባባይ በዓለም አቀፉ በሕብረተሰብ እይታ ስር በዘራቸው ምክንያት ብቻ የዜጐችን ንብረት ዘርፎ የሚያፈናቅል የሚያባርር የእርዳታ እህል የሚከለክልና በረሃብ የሚያሰቃይ ሌላም በግልጽ የሚታዩ ግፎችን የሚፈጽም ግፈኛ አገዛዝ በስውር ወይም በድብቅ እነኚህን የጠቀስኳቸውንና ሌሎችንም አያደርግም ብሎ የሚጠራጠር ሰው ወይም ዜጋ ካለ እጅግ የዋህና ያልበሰለ መሆኑን ዛሬ ይወቅ፡፡
ወያኔ ቢወድቅ ወይም ከሥልጣን ቢወገድ የሚከተለውን አጸፋ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በተቻለው መጠን በሥልጣን እያለ ይህንን የበቀል እርምጃ ይወስድብኛል ብሎ የሚፈራውን ሕዝብ (አማራን) በግልጽም ይሁን በስውር በሚያደርጋቸው የማጥፊያ ዘዴዎች ለቅሞ ማጥፋት ዋነኛውና ሌት ተቀን የሚሠራበት ዓላማው ነው የሚል ከባድ ሥጋት አለብኝ፡፡ እስከ 1999 ዓ.ም በተሠራው ደባ ያገኙት ድምር ውጤት ከ6 ዓመታት በፊት በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ በሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልታየና እንግዳ በሆነ መልኩ የሌላው ሕዝብ በቅድሚያ ትንበያው መሠረት እና ከዚያም በላይ ሆኖ ሲገኝ የአማራ ሕዝብ ግን ይደርሳል ተብሎ ከተጠበቀው የትንበያ ቁጥር ወይም መድረስ ከነበረበት ቁጥር አለመድረሱ ብቻ ሳይሆን ጭራሽም በሚሊዮኖች (አእላፋት) አሽቆልቁሎ እንደተገኘ ማስታወስ ይቻላል፡፡ ገና ከ4 ዓመታት በኋላ በሚደረገው ቆጠራም ከ1999 ዓ.ም በኋላ በሠሩት ደባ ከዚህም በከፋ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ይገመታል፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
በየሙያ መስኩ ሰዎች ስንት ጉድ ያውቃሉ መሰላችሁ ለመናገርና ለመመስከር ጊዜን የሚጠብቁ፡፡ የሚገርመኝና ግራ የሚገባኝ ነገር ቢኖር በዚህ ሕዝብ ላይ እንዲህ ጥርስ የተነከሰውና የተጨከነው ለምንድን ነው? ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በመሆን የዚህችን ሀገር ነጻነት አስጠብቆ ባቆዬ? ከቀደምት ሥልጡንና ኃያላን ሀገራት ጎራ ባሰለፈ? ለእነኝህና ለሌሎች ኩራቶቻችን ሲል ስንትና ስንት መከራ ባሳለፈ? ለምን? ይህ ያስመሰግነዋል እንጂ በምን ተአምር ነው ለጥፋት ድግስ ሊዳርገው የሚገባው? በኢትዮጵያዊነቱና በሀገሩ ኩራትና ክብር የሚሰማው ባለውለታና የሚያስብ ሕሊና ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዝምታና በይሁንታ የሚመለከትበት አቅል ይኖራል ብሎ ማሰብ ይቻል ይሆን? አረማዊያን ሆይ በምሳሩ ላይ ቆማቹሀል ለራሳችሁም ይብስባቹሀል፡፡ አየ የኛ ልማታዊ መንግሥት ለማያውቅሽ ታጠኝ አያ፡፡ አንባቢያን ሆይ ደኅና ሁኑ ከዚህ በኋላ እንኳን የምንገናኝ አይመስለኝም፡፡ (በመግቢያው ላይ ያለው ፎቶ ለማሳያነት የቀረበ)
ኢትዮጵያ ከውድ ልጆቿ ጋር በክብር በነጻነትና በልዕልና ለዘላለም ትኑር!!!
tes says
ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል። ኣቶ አምሳሉም ይህንኑ ተረታቸውን ደጋግመው ይነግሩናል።
“ነገደ ዮቅጣን የሴም የልጅ ልጆች ናቸው። — ዮቅጣን 13 ልጆች ወለደ። ስፍራውም በእስያ ምድር ከሜሻ እስከ ሥፋር እስከ ምስራቅ ተራራ ድረስ ነው ዘፍ፡ ፲፡ ፴
ከነዚህ ካ፲፫ቱ የዮቅጣን ልጆች ፭ቱ ሳባ፡ አውፌር፡ ሀዊላ፡ አባል፡ አቢማኤል ቦታ ባነሳቸው ስፍራ በጠበባቸው ጊዜ ከእስያ ተነስተው ብዙ ሰራዊት ሁነው ሲፈልሱ፡ ሲሄዱ ሲጓዙ የመን ደረሱ። እኒሁ የሴም ዘር ነገደ ዮቅጣን ወደ የመን በገቡ ጊዜ ምንም በፖለቲካ ምክር ባይስማሙ ለኩሳ የመን ይገብሩ ነበር። በኋላ ግን የኩሳ የመንን ደካምነት አይተው በተንኮልና በሊላም ጥበብ እርስ በርሱ አሽፍተው ከወግናቸው ያሮባ የተባለውን ብልሀተኛ ጀግና አንግሠው ለየመን ሁሉ ባለቤቶች ሆኑ። —እነዚህ ነግድ በኋላ አግዓዝያን ተበሉ። ከነገደ ሴም ዮቅጣን ከየመን ተነሥተው ብዙ ሠራዊት ሆነው በባብእል መንደብ ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ።” (ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮ ገጽ ፻፲-፻፲፪)
በወቅቱ በአካባቢ የነበሩ የኩሽ ንጉስና ልጆቹ ነበር። ከነዚህም ውስጥ ዳጪ (የኦሮሞ ግንድ) ወንድሞቹ በለው፡ ከሎ፡ ዳሞት፡ ሳሆ፥ መረባ (የኦሮሞ ጎሳ) ኣገው፡ ቤጃ፡ ኖባ(የኦሮሞ ጎሳ) ነበሩ። እነዚህ አግዓዝያን እየበረቱ ሲሄዱ። ዳጪ ወደ ደቡብ ተገፋ። በለው ወደ ምዕራብ ተገፋ፥ ኖባ ወደ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ አስከ ነጭ ኣባይ ርቆ ሰፈራ። መረዋ ወደ ሰሜን ምዕራብ ወደ ኑቢያ (ሜሮዌ) ተገፈ፥ በኋላ ወደ ደቡብ ተስፋፈ።
“ከዚህ ሁሉ ጋር አማሮችና ትግሮች “የኢትዮጵያ” ዋና ባላባቶችና ባላገሮች መሆናቸውንና ከሴም ዘር ከነገደ ዮቅጣን ልጆች የእስራኤል ዘሮች እንደሆኑ የሚያስረዳ ብዙ ምስክር አላቸው። በነገደ ኩሳ መንግሥት ጊዜ በዚያ ዘመን የህንድ ነገሥታት በርትተው ወደ የመን እየመጡ በጦር በዘረፋም ባወኩዋቸው ጊዜ በየመን ከነበሩት 5ቱ ነገደ ሲቀሩ— ነገደ ሳባ ነገደ ኦባል ነገደ ኦፊር በነገደ ካም በኩሳ ዘር መንግሥት መጨረሻ ንጉስ በጲኦሪ ዘመን ከየመን ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ መጡና ጥቂት ጊዜ በአንድነት ተቀመጡ። — ነገደ ሳባ ነጋዶች ሆነው ለነገደ ኩሳ መንግሥት ቀረጥና ግብር በመስጠት ትቂት ዘመን ስለተቀመጡበት የዚያ አገር ስም ትግሬ አሉት። ትግሬ ፡ አማራ ማለት የግብር ስም ነው።”(ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮)
“የአማራና የትግሬ አባት የሴም የልጅ ልጅ የኤቦር ልጅ ዮቅጣን ነው። በመልክም በጠባይ፡ በቋንቋ ጥቂት በጥቂት ይለያያሉ እንጂ ብዙ ነገር ይዋረሳሉ።
ያማራ ህዝብ የነገደ ሴም ወገኖች የዮቅጣን ልጆች የእስራኤል ዘሮች እንደሆኑ ፈጽሞ የሚያስረደ ጠባያቸው ልማዳቸው መልካቸው ስማቸው ስመ ሀገራቸው ቋንቋቸው ነው።”(ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮)
“— በ፲፩፻፴-፶ ዓም በላሊባላ ንጉሥ ዘመን፦— ሳይንት ባላገሩ አረመኔ ነበረ። መታመኛ ሲሉ ዘንዶውንና እባቡን ተመን አሉት። ይህንኑ ህዝብ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያስተምሩት ነበሩ። ፲፪ ዓመት በዚያ ወንጌል ሲሰብኩ ካማሮች ጋር ተዋወቁ። ከዛጉዌ ቤት ወደ ቀዳማዊ ምኒልክ ዘር ቤት መንግሥት ለመመልስ የመከሩ ብዚያ ነው። (ዮሃንስ ወልደ ማርያም ዘብሄረ ተጉልት ፲፱፻፴፮ ገጽ ፻፲፭)
“አምሓራ ወይም አማራ ማለት አራሽ ማለት ነ። ሳይንት ማለትም ባረብኛ የእህል መከማቻ ጎተራ ማለት ነው። አማሮችም ይኩኖ አምላክን አንግሠው ከዛጉዌ ነገድ የሚሆን ንጉሥ ይትባረክን ዋድላ ላይ ገደሉት። — አማሮች ግን ይኩኖ አምላክን ካነገሡ በኋላ ሰው ሁሉ አማሪኛ ይነገር ጀመር። —- ባጼ ይኩኑ አምላክ ጊዜ ያማሪኛ ቋንቋ ፈጽሞ ሠለጠነ። — ለንግግር የተስማማ ሆኖ ስለ ተገኘ የቤተ መንግሥት ቋንቋ ሆነ እንጂ ንግግሩስ አስቀድሞ የነበረ ነው። (ዮ ወ ማ ገጽ ፻፲፮)
“ኣሁን የአማራ ህዝብ የመጣበትን የመሥመር አቅጣጫ እንፈልግ። ከደቡብ ዓረብ ከክርስትና በፊት ኤርትራን ተሻግረው በሰሜን ኢትዮጵያ ተበታትነው የተቀመጡትን የኛን የግዕዙ ታሪካ ነገሥት ነገደ ዮቅጣን ይላቸዋል። ዛሬ የተጣራው ታሪክ በደቡብ ዓረብ ሳባዊያን፡ ሀበሳን፡ ሂሚሪት፡ ሖሜሪት እንደነበሩና ክነዚህ የሴም ወይም የዮቅጣን ነገዶች ውስጥ የኤርትራን ባህር ተሻግረው በኢትዮጵያ ሰሜን በያውራጃው ተሰማርተው ተቀመጡ። — የጨረቃ አምልካቸውን ከነምልክቱ የነገሥታት አስተዳደር ልማድ በደቡብ ዓረብ ከሚገኛው ጋር ፍጹም አንድ ወይም ተመሳሳይ በመሆኑ ነው። የአምልክቱ ስም ማህረም፡ አስታር፡ አልመቅህ፡ ሀውባስ—- እያለ በደቡብ ዓረብ የተገኘው በኢትዮጵያ ሰሚንም ተገኝቷል።
የሆነ ሆኖ የመሬቱ አቀማመጥ ሲታይ በደቡብ ዓረብ ፊት ለፊት የሚታየው የኢትዮጵያ ሰሜን ነው። ስለዚህ የሳባ ወገኖች ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው በሐማሴን፡ አካለ ጉዛይ፡ በኣጋሜ፡ የሀበሳን ወግኖች በአሳሆርታ በሓውዜን ሲሳማሩ፡ በዓረብ አገር ሳሉ ከሳባ በተደቡብ የሚኖሩት ሂሚያሪትና ሆሚሪት የኤርትራን ባህር ከተሻገሩ በኋላ ሳባና ሀበሳን ከሠፈሩበት በስተደቡብ በኩል ያለውን ሰፋፊ አውራጀ ይዘው ስለሰፈሩ ሂሚሪያት ወይም ሆሜሪት የሚባለው ስያሜ በጊዜ ብዛት ትንሽ ፊደሉንና አባባሉን እየለወጣ መጥቶ በሂሚያሪት አምሓራ ተብሎ ይሆናል። እውነትም የአማሮች የመዠመሪያ መሠረታዊ አገር አምሓራ ሳይንት ነው። — በአሁኑ ጊዜ የዛጉዌን መንግሥት በአማሮቹ የቤተ ክህነት አባቶች በነአቡኑ ተክለ ሃይማኖት በነአባ እየሱስ ሞአ እየተረዳ ውስዷል ማለት ነው። ባንድ በጠቅላላ በአማራ ስም የሚጠረው ህዝብ በቀን ብዛት እርሱም ደግሞ ቅርንጫፍ እያበጀ የመሬት ስፈት ወርዱንም ቁመቱንም እያስፋፋ ኖረ።
“ነገሥታቱ በሸዋ( የንጉሥ ሸለቆ) መንዝ ተጉለት ቢቀመጡም በዘመናቸው ሁል ጊዜ የአማሮቹ የመዠመሪያ መደበኛ ሥፍራ ወደ ነበረው ወደ ቤተ አምሓረ (ሳይንት ወይም ዳውንት) እየሄዱ በዚያ በየስማቸው ቤተ ክርስትያን መሥራት ያዘወትሩ ነበር። — አውረጃውን ማክበርና ማድማቅ እየሄዱ በየጊዜው መጎብኘት የአባቶቻቸውን አጽም በዚያ ማሳረፍ ይወዱ ነበር።
(የግራኝ ወረራ በተክለ ጸድቅ መኩሪያ ገጽ 7-9)
“— የአክሱም ነገሥታት ከደቡብ ዓረብ የመጡ በሳባና በግዕዝ የሚጽፉ የጨረቃ አምላክ የሚያመልኩ ስለአደረጋቸው— በራሳቸው የቋንቋ ጽሁፍ በሳባና በግዕዝ ለይ በዘመኑ የገነነውን ግሪኩን ጨምረው ሲጽፉ አንድ ጊዜም የዕብራይስጥ ቋንቋ አልጨመሩም። ማህረም ሲነሳም የእሥራኤል አምላክ የሕቤ ዢሆባ ወይም አዶናይ ተብሎ አልተጠቀሰም። እያንደንዱ ነጋሢ የቅርብ አባቶቹን በየሐውልቱ ላይ ሲያወሳ የዳዊትን የሰለሞንን እንኳን ሰለሞንን የመዠመሪያ ንጉሥ የሆነውን ምኒልክን የሚያነሣ አስካሁን አልተገኛም።” (ግራኝ ወረራ ገጽ 12)
እንግዲህ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መልኩ የተደራረተ ታሪክ እያላቸው ከርስትና በሁለት የግሪክ ዝርያ ያለቸው የሶሪያ ነገዴዎች ፍሬምናጦስና ኤክሶዶስ በሚባሉ ሰዎች መጣላቸው። እነሱም የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ወደ ግብጽ ሄደው ጉዳዩን ለኮፕትክ ቤተክርስቲያን አሳወቁ። በኋላ ፍሬምናጦስ ተመልሶ ጳጰስ ሆናለቸው። በዚህ ሁኔታ እያሉ የአክሱምን ሥረዋመንግስት በአገው ሥረዋመንግሥት ተተከ። ትንሽ ቆይቶ የሃይማኖት ጭቅጭቅ በኣገዎችና ግብጦች መሃል ተነሳ።
ከዚያ በኋላ ለሐበሾች እስከ 1954 (በሀይለ ስላሴ) ጊዜ ድረስ ጰጰሶች ከግብጥ ይመጡ ነበር። ይህ በዚህ እያሌ የእክሱሞች ሥርዋመንግስት ወድቆ የዛጉዌዎች (አገው) ሥርዋመንግስት አካባቢን ተቆጠጠረ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ማለት 901-1270 ድረስ የኣገው ነገሥታትና ግብጦች መሃል የሃይማኖት ጭቅጭቅ ተነሳ። የጭቅጭቁ ሰበብ ዛጉዌዎች የራሳቸው ሴኖዶስ እንዲኖራቸውና ካስኖዶሶች ውስጥ ጳጳስ እንዲሾሚላቸው ይፈልጋሉና። ነገር ግን ግብጦች የሓበሻ ቤተክህናት ከእነሱ ነጻ እንዲትሆን አይፈልጉም ነበርና። እንዲሁም ብዙ ምልጃና ስጦታዎች፣ ግብር ስልምቀርበት ነው። በዚህ ሰበብ ግብጦቹ ተንኮል ሰሩ። ይህም “በኒቅያ ጉባኤ 320 (18) የሃይማኖት ሊቃውንት በተገኙበት ሐበሾች/ኢትዮጵያኖች የራሳቸው ጰጰስ እንዳይኖራቸው ተወሰነ” ብለው አወጁ። ጭቅጭቁ ለ200 ዓመታት ቀጠለ።
ሌለው ስለ ንግሥት ሳባ የቀድሞ ተረቶችን ትተን ሴትዮዋ ሙሉ በሙሉ የአረቦች ንግስት ናት። በመጽሀፍ ቅዱስ ሁሉ ቦታ የተጠቀሰው ስለ ኢትዮጵያ መሆንዋ የምገልጽ የለም። አንደንድ ቦታ እስራኤሎችም አረቦችም “የአዜብ ንግስት” ይላሉ። አዜብ በህብሩና በአረብኛ “ደቡብ” ማለት ነው። ሼባም ትሁን ሳባ ንግስት የአረቦች ነች።
ኢትዮጵያ መሆንዋን የሰበኩ ግብጣዊያን ናቻው። ይህም ከግብጥ ኮፕትክ ቤተክርስቲያን ለሓበሻ ኦርቶዶክስ ተቀርጾ የተሰጣ “ክብራ ነገስትና ፍትሃ ነግስት” የሚባሉ በአረብኛ ተጽፎ ወደ ግዕዝ ተተርጉሞ የተሰጣ ሰነድ ነው። ይህም የሆነው ከሶሪያ ነጋዴዎች ውስጥ ፍሬምናጦስ እና ኤክሶዶስ የሚባሉ ወደ አክሱም 360 ዓም አካባቢ መጥተው ስለ ክርስትና ከሰበኩ በኋላ ወደ ግብጽ ሄደው ጉዳዩን ለኮፕቲኩ አሳወቁ። እስከዚያ ዲረስ ሃበሾቹ በጨረቀና በድንጋይ ያመልኩ ነበር። ስለ ኦሪት ሃይማኖት የሚያዉቁት አልነበራም። ኦሪት የኩሾች እምነት እንጂ የሴሜትኮች (ኣቢሲኒያና አረቦች) አልነበረም።
ከዚህ በመቀጠል ‘ክብረነገስቱና(የነገስታት ክብር) እና ፍትሐነግስት(የነገስታት ህግ) የሚለውን መጽሀፍና የነገስታቱ ክብር የተባሉትን የግብጽና ይሁዲ ዝሪያ ያላቸውን 110 ሰዎችን ይዘው ከግብጽ ወደ ሀበሻ መጡ። እንግዲህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ “ሳባ ንግስት ለሰለሞን ወለደች። የኢትዮጵያ ንግስት ነበረች። ይህ ይህን አገር የሰላሞን ዘር መግዛት አለበት” ብለው ለነገሥታቱ ነገሩ።በወቅቱ ማንም ሰው ሳያምናቸው ቀረ። ጭቅጭቁ ለሁለት ዓመታት ዘለቀ። ይህ በዚህ እንዳለ የግብጹ ሊዑካን ተንኮላቸውን ማጠንጠን ጀመሩ። ስለዚህ ለቄሶች እና በወቅቱ ክርስትና ተከታይ የሆኑ ሰዎችና ወቶአደሩን/ሰራዊቱን አሳመኑ። በዚህ ጊዜ የሰራዊቱ አለቃ የአማረው ነገድ (ጎሳ)ይኩኑ አምላክ ነበር። ቀሶቹ በቄሴ ተክለ ሃይማኖት መሪነት። ሰራዊቱ በአማራው ዘር ይኩኑ መሪነት የዛጔን መንግሥት በኃይል ገልብጠው በመቅቱ የሥርዋመንግስቱ መሪ የነበረ ይትባረክ የተበለውን ከስልጣን አበረው ወርሂመኑ በተባለው ቦታ ደርሶበት አርደው ገደሉት። እንግዲህ ይህን ሸሪ የስሩ የግብጾች የሃይማኖት ሊኡካንና የሓበሻ ቄሶችና የአማራው ሰራዊት/ወቶኣደር ናቸው።
ስለዚህ ሼባ ወይም ሳባ የሚትባል ነግሥት በዚህ በኢትዮጵያ ምድር አልነበራችም። ነገር ግን ሃበሾች የአረብና እስራኤል ነገድ ዘሮች ስለ ነበሩ፡ እስዋም በአገሯ ወንድ በማጠቷ ከነገርዷ ድንግልዋን ወስዳ ለእስራኤል ንጉስ አስረከበች። በጣም የሚያሳፍር ተረት። ወንድ በአገሯ አጥታ ያን ሁሉ አገር አቁዋርጣ ክብርናዋን ማዋረድ። በሌላ በኩል በምስራቅ አፍሪካ ያሉት የአረብ ዝሪያዎች (ሓበሾች) በአገራቸው (የመን) እያሉ ንግስታቸው ነበረች። በመሆኑም እዚህ ከመጡ በኋላ፣ ጉልባት እስኪያገኙ ድራስ ለኩሳ ንጉሥ ይገብሩላት ነበር። ልክ መንዝና መረቤቴ ለጎንደር ይገብሩ እንደነበር ሁሉ ሀበሾችም በአረቢየ የኣሁኑ የመኒያ መንግሥት ግብር ይሊኩ ነበር። መሰረታቸው እዚያ ስለሆነ።
በሌላ በኩል የኩሾች ንግሥት ከንዳኬ/እንዳኬ የሚትባል በኑቢያ ቴበስ ከተማ እንደነበራችና፣ መቃብርዋ እዚያው መኖሩ እሙን ነው ብዙ የታሪክ ሰነዶችም አሉ።
ከዚያ በኋላ አማራዎቹ አገዎችን እንደገና እንዳይነሱ ብዙዎቹን ፈጁዋቸው። ጥቂቶች ሰቆጣ ኣካባቢ፣ ጥቂቶች በጎጃም ውስጥ ጥቂቶች ደግሞ ወደ ቦጎስ ሀልሀል (ኤርትራ) ተሰደዱ። በዚህ ሁነታ ነው እንግዲ አማሮች ሌሎችን ብሔሮች ሲፈጁና፣ መሬቱን ሲቀሙ የነበረ። እስክ ሃይላ ሥላሴ የመጨረሻ ሥልጣን ድረስ በዚህ ሁኔታ ቆዩ፡” (ዶክተር ላጵሶ ጌ ዴሌቦ ኢትቭ እና መጽሐፈቸው ስለ ኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥቱ ይ ማልከቱ)
ስለዚህ አማራው በወረራ እንጂ አንድም ይዞታ ከደቡብ ኢትዮጵያ አልነበረውም። በ13ኛው ክፍለዘመን ከኦሮሞ የነጠቁት የመንዝ የመራቤቴ ገደላገደል አገር ነው። ይህ ቦታም የመጽሀፍ ቅዱስ ስም “ሸዋ” የሚል ትርጉሙ “የንጉሥ ሸለቆ” የሚለውን አወጡለት። የቀድሞ የዚህ ቦታ ስም በአፋን ኦሮሞ( Afaan Oromootin Firkuta jedhama) ፊርኩታ ይባል ነበር። የአካባቢ ገዥዎችም ማማ፡ ጌራ፡ ደራ ፡ፋጂና(Maamaa, Geeraa, Dharraa, Faajjii) ወዘተ ይባሉ ነበር።
Amsalu G/Kidan Argaw says
አቶ ቴስ የአቶ ቃሉን ሐሳብ እጋራለሁ ማለትህ ነው እሱኑ ገልብጠህ ያስቀመጥክልን? ነው ወይስ አቶ ቃሉ በሌላ ስም መጥቶ ነው? ለማንኛውም መልሳቹህ ያው፡፡ ተረት ተረታቹህን ግን ተውት ስለ ኩሽ ነገድ የተነገረው ሁሉ እኛን ይመለከታል አትበሉ፡፡ እንደማይመለከት ልባቹህ ያውቀዋል በቀላሉ ልትረዱ የምትችሉበትን ዘዴ ልንገርህ ለምሳሌ ስለ ግርዛት ስናነሣ ግርዛትን በመጠቀም ከዕብራዊያኑ እኛ እንቀድማለን አናንተ የኩሾች ነው የሚሉ ስላሉ የኛ ነው ትላላቹህ በእርግጥ እነ አገውና ቅማንትን የወሰድን እንደሆነ አዎ ባሕላቸው ነው ኦሮሞን በተመለከተ ግን ከዐፄ ምንሊክ በፊት ሌሎቹ ነገሥታት ሊያስለምዱ ሲሞክሩ አልሆን ብሎ ዐፄ ምንሊክ በአዋጅ እንድትገረዙ ማድረጋቸውንና ከዚያ በኋላ መገረዝ መልመዳቹህን አታውቅም? የአክሱም ሐውልትን ስጠቅስ አናንተ ደግሞ በኦሮሞ ባሕል ግንባራቸው ላይ የሚያደርጉትን የወንድ ብልት በመጥቀስ ባህላችን ነው ለማለት ዳዳቹህ፡፡ ባሕላቹህን አለማወቃቹህ ገረመኝ ከኦሮሞዎቹ ግንባራቸው ላይ ይሔንን ቅርጽ የሚያደርጉት እነማንና ለምን እንደነበረ አታውቁም? ያን ማድረግ የሚችል ኦሮሞ የወንድ ብልት የሰለበ ብቻ ነው፡፡ ወንድ አግኝቶ መስለብ ያልቻለ ያንን ነገር ግንባሩ ላይ ማድረግ አይችልም ነበር እሽ? ባሕላቹህን ንገረን ካላቹህኝ ይሄው ነው፡፡ ቅርጹ የተገረዘ ብልት ቅርጽ መሆኑ የተሰለበው የማን እንደሆነ ሊጠቁም ይችላል፡፡
Qaalluu says
ወሽካታ ደብተራ አምሳሉ፣ እኔም ደጋግሜ ነግረአለሁ። በቀደምት ደብተራዎች አዙሪት ውስጥ ነህ ያለሃው። ከዚያ አዙሪት ውጣና እውነታኛ ዕለም ተመልከት። ምጽሀፍ ቅዱስ ስለ ሓበሾች ኢቲዮጵያ አይደልም የሚያዋራ። ኹሽ ብሎ ነው የመጀመሪያው የተጸፈው። ያውም ከግብጽ በውጡ ሕብራዊያን (ሙሴ ተከታዮች)
ሌላው ስል አክሱም ደጋግመ አንስታሃል። በፍጹም የ ሃባሾች አይደለም። እናንት የመጣችሁ 500ዓመተ ዓአ- 100 ዓመተ ምህረት ውስጥ ነው። ከዚያ እስክ እዛና ድራስ ተገስታችሁ ትኖሩ ነበር። ያ ይዘረዘርከ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ በሙሉ። ልኩሾች በግሪክ ኢቲዮጵ ነው። አይመለካተችሁም። ግን ዜግነቱን የሚከለክላቹ የለም። ኢትዮጵያዊ ኩሽ ስለ አልሆናችሁ። ለመሆን ትፍጫራጫራላቹ። ዲቀሎች ስለሆናቹ በማንናተችሁ ስለምታፍሩ።”እማራናትህን ደብቀህ” በኢትዮጵያ ካባ ሥር መሆን ማረጥክ። ለላው ስለ ግዝራት አስታሃል። እራስ አተፍሪም።የኦሮሞን የግዝርት መጃማሪያ ወደ 100 ይሚተውርደው። እስክ የአባበሕርን ዲርሳቶች አንብብ። ስለ ሉባ ግርዛት ምንድነው የሚላው። አንተ ውሽካት ደብተረ የውጪ ጸሃፍትን ትኮንናለ። የአገር ውስጥም አታነብም ማለት ነው። እፍሪካኖች የጸፉትን፣ ስለ ኹሽ አምብብ።ኣርዕስቱ በትልቁ “ኹሽ” ይላልና። በተጨማሪ። ሙሴቬን የሰፈቸውን ተሴሶች አምብብ።
ግሪኮች ወደ አፍርካ ስጋቡ ስንቱን አዋደሙ። ሮማዊያን ዳጋሙ። በክርስቲና ስም የ”ፓጋን” በመለት ስንቱኡን አዋደሙ። ሙስልም ሲመጣ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙ።
ስለዚ አወዳምችሁ እንዚ የመጣችሁት ስልጣኔ የላም።
በነጋራችን ላይ። ሙስልሞች ካሳውዲ ዓራቢያ ሲመጡ የተቀበለው አማራ ሳይሆን በውቅቱ ባህራ ናጋሽ ግዥ የነባራ ነጋሺ የሚባል ኦሮሞ ነበር። “ነጋሺ” ማላት እንደእናንተ “ሹማኛ” ማለት ሳይሆን። በኦሮሞ “ሰላማዊው” ማላት ነው። ሰዎቹን ሲ ቀባላቸው “ሐሸማ” ብሎ ነው ያነገራቸው።
ታሪክ ገና ጉዳችሁን ያፍራጣርጣል። ይልቅ፣ ብሔር የለኝም ብለህ የጸፍከ፣ ጉድህን እያሳያን ነው። እሱን እዚያው ላይ እመልስልሃለሁ። ማለትም “ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከጥፋት የሚያድነው ብቸኛው መንገድ!!!” ለከው። አንተ ብሔር ስለሌላው፣ ሁሉም የለም ማለት አይደለምና።
Amsalu G/Kidan Argaw says
እኔ እኮ ግራ ገባኝ ስለ ነገደ ዮቅጣን እኮ ያወራኸው አንተው እራስህ ነህ እነሱ የገቡበትን ዘመን ስነግርህና እንድትነግረኝ ማለትም እንድታስተውለው ፈልጌ ሥልጣን የያዙበትን ማለትም የመጨረሻውን የኩሽ ንጉሥ ገድሎ መንግሥቱን የወረሰበትን ወራሪውን የህንድ ንጉሥና ሠራዊቱን ደምስሰው ሥልጣን የያዙበትን (ሦስት ሽህ ዓመት ከከክርስቶስ ልደት በፊት) ስጠይቅህ ደግሞ ላንተ አይመችህምና ወጣህና ከ500ዓ.ዓ. እስከ 100 ዓ.ም. ነው የገባቹህት አልከ በየትኛው መረጃ? የጠቀስከው መረጃ ሦስት ሽህ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው የሚለው፡፡ ሲጀመር በምትጠቅሰው መረጃ ካልተማመንክ ለምን ትጠቅሳለህ ታዲያ? ከዚህ አንጻር የአባ ባሕሪን መጽሐፍ መጥቀስህም ገርሞኛል፡፡
ይሄውልህ አስቀድሜም ነግሬሀለሁ አንተም አዎ አማርኛ 40 % ቃላቶቹ ኩሻዊ ናቸው በማለት አረጋግጠሀል ከዚህም ሊልቅ ይችላል ትክክለኛውን አኃዝ አልያዝኩትም፡፡ እናም አማርኛንና ተናጋሪዎቹን ሴማዊ ናቸው ማለት አይቻልም ኩሻዊም ማለት እንደዛው ፡፡ ሁለቱም ቢሆን የገቡት ከአፍሪካ ውጭ ነውና (እንደ መጽሐፍ ቅዱስ መረጃ) ማንኛው ቀደመ የሚለውን መመለስ አይቻልም፡፡ አንተ ባነሣኸው የነገደ ዮቅጣንን ትንታኔ በሚያምኑ መጻሕፍት መሠረት ከሆነ ኩሾች እስያ ከቆዩ በኋላ ነው ወደ እጣ ክፍላቸው አፍሪካ የገቡት ሴማዊያኑ ግን እጣ ክፍላቸው ባይሆንም ቀድመው ይኖሩባት እንደነበር ይናገራሉና በዚህ ጉዳይ ላይ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ ቢቸግረኝ ደጋግሜ ብነግርህም አልገባህ አለ እንጅ የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ የሚለው ይህ የእግዚአብሔር ሕዝብ መሠረቱ እዚሁ መሆኑን ነው፡፡ ያ ሕዝብ ይሄ ለመሆኑ እንዴት እናረጋግጣለን ካልክ ይሄ በጣም ቀላል ነው እስኪ ዝም ብለህ እየው እግዚአብሔርን በማምለክ ረጅም ታሪክ ያለው እስከ አሁንም ይዞት ያለው ማንኛው ነው? ይሄንን የሚያረጋግጡ የታሪክ አሻራዎችስ በማን እጅ ናቸው? ከዚህ ቀደም እግዚአብሔርም በማምለክ ከዕብራዊያኑ (ከእስራኤላዊያኑ) እንደምንቀድም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎችን ጠቅሸ መናገሬን አትርሳ፡፡
Qaalluu says
ደብተራው አምሳሉ! ከቀደምት ደብተራዎች ስንክሳር በስተቀር የእውነተኛው ኣለም ሃቅ መቸም አይገባህም። ስለ ግርዛት ስናነሳ ስለ ባህላችሁ ጃንዳረባ ውስጥ ዘለህ ትገባለህ። ከደብተራዎቹ አዙሪት መች እንደምትወጣ እግዛብሔር ብቻ ያውቃል። ለአሁን ግነ ያ የኔዎቹ ግንባር ላይ የሚያራጉት ስለ ሌለኝ። የአንተኑ ሰልቤ። ጥሩ ጀንዳራባ እንዲትሆነኝ አደርጋለሁኝ። ከዚያ የቀደምት ደብተራዎች በተመዘክር ጠበቂ እንዲትሆን የባጅሮንድ ሹመት ይሰጠሃል።
ለአሁኑ ግን ስለ ኩሽ ህዝቦችና ኦሮሞ ለመወቅ ከፈለክ ይህን ልኬልሃለሁ።
KUSH: Reconnecting The Root System of African Civilization.
Exmp.I A particular mode of Circumcision…(452)
Frankfort, “…because of a common origin the people of ancient Egypt and those of others parts of Africa , “extending up to Somaliland”, have similar cultural conventional. Comparing the cultures of ancient Egypt, of the Puntites, and of the Masai, “ he notes the following Similarities,
A particular mode of Circumcision…(452)
A particular method of time reckoning—(542)
DIop postulated that circumcision, social organization, and language are also useful concept to determine a Negro origin to Kemet.
There is some evidence of circumcision, but more research should be undertaken on this topic.
“… It was now that certain dietary laws were first insisted upon, and circumcision.
‘to distinguish Jews irrevocably from pagans’, (other people in antiquity, such as the Egyptians, practiced circumcision”
“Jense is however, unable to determine the point on the Gada grade system of the Boran when Circumcision is performed and if, in fact, it is connected with the beginning or the end of child bearing.” … However, remain unclear for our question insofar as here circumcision is connected neither with the entry into the Gada’s beginning (enirichtug) nor with the end of the same, but it is carried out so to speak in the middle of this period of life Lebensperiode) of the man …” (Prof. Asmarom Legese)
“… Jenen believes that there is a general symbolic and mythological link between death and birth, between circumcision and the end of child raising, such that men would begin to have children only after they have killed an enemy or animal, i.e., big game, and they would stop raising children after they were Circumcised.” (Adolf E Jensen, ‘Das Gada-system der Konso and die Alterklassen-system der Niloten”)
The class is circumcised on the 48th years of the cycle. This coincide with the transition rites of all the grades other than RABA and GADA, and occurs in the middle, or more accurately, on the 5th year of the Gada period, the term of office of the Gada leaders.
It is circumcision that has relevance to the right of childbearing and child rearing. They begin to raise daughters after the 48th years of the cycle (circumcision) and, at the same time, they take back their sons from the home of the surrogate parents. From this time on, there are no normative Gada constraint on child-raising.
3500 B. C. Egypt believed that God became incarnate in man. Circumcision was a rite universally practiced as a part of the religion of the old Egyptians, as long as the native institutions flourished. It was a rite of the ruling Ethiopian element. Under Greek and Roma rule it fell into disuse but was always retained by the priesthood and those who desired to cultivate ancient wisdom.
Herodotus said that all Ethiopian circumcisioned. Lenormant calls it original with them. The Coptic Church practices to this day. They did not adopt it from the Jews for they circumcise both sexes. Oldendorpe, finds the rite in western Africa. It must be a relied of ancient African customs. It is older than Mohammed, who did no regard it as a religious rite.
(Wonderful Ethiopians of Ancient Cushitic Empire), (Kush The jewel of Nubia by Mariam Ma’at- Ka-Re-Monges)
Exmp; II A particular method of time reckoning—(542)
The Basic Astronomical factor in the understanding of time in antiquity was the division of the earth into the east, or Orient (from the Latin for to be born, rise, grow’), and the west, The Occident (from to fall down, die). Ideas, a history of thought and invention p. 171)
“… Though the basic division of the day into twenty- four hours seems to have arisen in Egypt. There it was noticed that at regular intervals throughout the night stars arose, and this is how, at first, the hours of darkness were divided into twelve. Later the day was divided in the same way, through until medieval times, and the invention of the seasons: the longer the night, the longer the evening hours and the shorter the daylight hours. This Egyptian practice spread.”
“In other words, there was in ancient times a tendency to divide time in to subdivisions that are multiples of twelve or thirty and almost certainly this has to do with the division of the year into (roughly) twelve Lunation’s and each Lunation into (approximately) thirty days.”
“The main problem in recording time was to reconcile the lunar cycle with the solar cycle. The sun governed the seasons- vital in agricultural societies- where the moon governed the tides and was an important deity, which appeared to change from in a regular rhythm.
“The ancient Egyptians divided the year into twelve lunar months, of thirty days each, with five additional days at the end, which were considered very unlucky. This calculation was achieved on purely practical grounds, being the average amount of time between successive arrivals of the Nile flood at Heliopolis (the most impotent event in Egyptian life). The Egyptians soon noticed that, in fact, the actual year is slightly longer, 365 ¼ days, and made the adjustment. They also noticed that the rising of the Nile Occurred just as the last star appeared on the horizon, the Dog Star Sothic (Sirius as we would say). This ‘heliacal rising’ became the fixed point of the so called ‘Sothic calendar, and was more regular, and more accurate, than the flooding of the Nile.
Astronomical calculations have shown that the first day of the two calendars- the pre-Sothic and the Sothic agreed in 2773 BC, and scholars have concluded that this must have been when the Sothic calendar was introduced. So for the Egyptian, whether they knew it or not, the year 0 was in fact 2773.”
“The Oromo calendar has been misrepresented in the ethnographic literature. Almost every writer represents it as a simple solar calendar and ignores its lunar-stellar foundation.”
Borana time reckoning system is unique in eastern Africa and is a type that has only been recorded in three cultures in the history of humankind.” (Asmarom Leggese)
The best known example of the type of time reckoning are the Chinese, Mayan, and Hindu calendars.
However, it is very doubtful that these nations, who are Oceans away, had any influence on the geneses of the Borana astronomic colander or the Gada Institution as a whole. Oromo are not a seafaring people. The force of their nation is entirely terrestrial. They did not cross the Indian Ocean to gain access to the Hindu astronomic calendar, nor is there any recorded evidence that the Hindus hand substantial contact with the Oromo between the 16th and 19th centuries.
Asmarom Said, “I had to be educated for some months by Boran experts before gaining some understanding of their calendar, it is a permutation calendar based on observations of the moon and several constellations.
The lunar month is about 29.5 days long. The “year” consists of twelve such months or 354 days, eleven (11) days shorter than the solar years.”
“a Borona time reckoning expert (Ayyantuu) can tell the day, the month, the year, and the Gada period from memory. Should his memory fail him, he examines the relative position of the stars and moon to determine the day, the month astronomically.”
“In six out of the twelve lunar months the seven constellations appear successively. “in conjunction” with the moon, During the remaining six months none of these six stars and constellation is visible in conjunction with moon, In this period the first (Beta triangulum) is visible, only in the second half of the lunar month and is used in conjunction with successive phases of the waning moon in successive month.
“… stated differently, at the beginning of each month, the star Bata-Triangulum, appears “in conjunction” with the moon, at later and later stages of the waning moon.”
Exmp. III
“Petrie focuses on African cultural similarities that are due to direct descent from a common source. The evidence that he uses is from various scholars who had observed and interviewed various African ethnic groups, such as the Nyakang, Dinka, Babend, Yaos, Oromo, Akikuyu, Ankole, Unyoro, Nagadeh, Ibo, New Calbar, Aro, and the Inoku.
Petrie divides the similarities between Kemet and the rest of Africa into two categories.
I, Treatment of the body
1, Mummifying
2, Contracted burial,
3, Beheading the dead
4, Passage for the spirit
5,Vehicle for the spirit
6, Restoration of ability to the corpse
7, Recess grave
8, Pole over grave
9, Round-domed graves
10, Domed pit tomb
11, Sloping tomb
II Offerings for the Dead
12, Beer and flour offerings
13, Cloth offerings
14,Offerings at the grave
15, Killing the offerings
16,Offerings chamber above grave
17, Drain to the east
18, Men sacrificed at royal funeral
19, Eldest son the priest
20, The funeral image
21, Tall hate of officiates
22, Offering chamber for the image
23, The soul house
Hunting ford reports the following “institutions” as cultural similarities in Africa. More evidence of connections in East Africa particularly Kenya and Uganda.
1, The chief as priest
2, Mundane spirit world
3, Every object has its spirit
4,Sacred fig-trees
5, Contracted burial
EXMP; IV
“The Sanga, with its distinctive horn and hump, has become “the base stock of many of the indigenous African breeds.” According to UN Food and Agriculture Organization (FAO), the Sanga breeds of the Oromo spread to southern and western Africa from East Africa (the Horn of Africa) – the time is believed to be around 1600 B.C. This UN-FAO publication actually makes the Horn of Africa as the hub, where many of the cattle breeds in Africa originated from.”
“የኦሮሞ የቀንድ ከብቶች በግብጽ የሚገኙት ሻኛ ያላቸው ከብቶች ዝርያ ናቸው። ላሞች ብዙ ወተት ኣይሰጡም። ለእርድ የሚሆኑ ዝርያዎች ሳይሆኑ አይቀሩም።” (አሌክሳንደር ቡላቶቭች ሩሲያው መኮንን 1898 ሞስኮ በሩሲኛ ቋንቋ)
Amsalu G/Kidan Argaw says
አይ አቶ ቃሉ አንተማ ብትችል እኮ ለመግደልም ታስባለህ አይደል እንዴ እሱን ሐሳብ ቀየርክ? እንስሳ ነህና ካንተ ከዚህ የተሻለ ነገር ታስባለህ ብየ አልጠብቅም፡፡
በጣም አሳፋሪ ነው እነዚህን ሁሉ የአረማዊያንን (Atheists) መገለጫዎች ከሌሎች ከተጠቀሱት አፍሪካዊ ጎሳዎች ጋር እንጋራለን ስትል አያሳፍርህም?
ስለ ዘመን አቆጣተር ያነሣኸውም ኦሮሞዎችና ሌሎች ጎሳዎች ባሕላዊ የዘመን አቆጣተር እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡ ነጥቡ ግን ፕሮፌሰር አስመሮም ያልከው ሰው እናንተ የራሳቸሁን ባሕላዊ የዘመን አቆጣጠር ፈጠራቹህ ከሚልበት ዘመን እጅግ በራቀ ዘመን ኢትዮጵያ ፈጥራ ለግብጽም ተርፋለች፡፡ ይሄንንም የራሳቸው የግብጽ ዘመናዊ የዘመን አቆጣጠር ሊቅ “አቡሻኽር” መስክሯልና አትድከም፡፡
እኔም እኮ ብየሀለሁ አታስታውስም እንዴ? አንዳንዶች ኦሮሞዎች ምንጫችን ምሥራቅ አፍሪካ የዛሬዋ ሶማሊ ላንድ ነው እንደሚሉ፡፡
Qaalluu says
አይ!! አቶ አምሳሉ ስድብና ሊመና ባህላችሁ ነው። ደደብ እንስሳና ሰውን መለየት የማትችል። ልክ ከኮማሪት እንደተወለዳ ሰው በአፍ የመጠውን ትተፋለ።
ስል አይማኖቶች ልዩነቶች ኣንኳን ለይተህ የማተውቅ ደብተራ። እራማዊያን ማለት ክርስቲያን ወይም እስላም የልሆነ ማለት መሆኑን ኣንኳን ለይተህ የማተውቅ ነህ። ነጮች ለሁላችን የሚሉትን ነው የነገርክኝ። አዲስ አይደለም። አምሐራ እስከ 9ኛው ምዕት መገባዳጃ በዘንዶ ያምን ነበር። የተክለ ሃማኖት ገድል አምብብ። የግብጹ አቡሻከርም የእናንት ሳይሆን በኦርቶዶክሳችሁ አማካይነት ነው የመጣላቹ። እስከዚያ ዘመን የሚትቆጥሩ በንጉሶቸችሁ የሥራ ዛማን ነው።
ግን ማወቅ ያለብህ ሰውን ከእንስሳ የለየው ሥራው ነው። ብ21ኛው ክፍለ ዘመን አጎዛ/ቁርበት ለብሰው መለመን እንስሳነት ነው።
ስድብህን ትተህ ህዝቦችን የሚያቀራርብ ብትጽፍ ይበጃሃል። የብሔሮች እልውና ክደህ የፈለከውን ብትሞጫጨር ቅሌቱ ለራስህና፣ አምኖህ ለሚከተሉህ ነው።
Editor says
Qaalluu እና አምሳሉ – በተደጋጋሚ በምትሰጡዋቸው አስተያየቶች (በዚህ ጽሁፍም ይሁን በሌላ) ላይ የስድብንም ሆነ የዘለፋን ትርፍ ቃላትን ከመቆጠብ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን::
አስተያየቶቻችሁን ሁሉ ከግለሰቡ (ከጸሃፊው) ላይ በማንሳት በጉዳዩ ላይ ብቻ በማተኮር ብትመላለሱ ይበጃል:: ለምሳሌ “አንተ እንደዚህ ነህ … እንዲያ ነህ” ከማለት ይልቅ “በዚህ ነጥብ ላይ እንዲህ ብለህ የተናገርከውን አልቀበልም (አልስማማም) ምክንያቱም …” ይህ አይነቱ ልምድ እንዲዳብር የጋዜጣችን ዋና መመሪያ በመሆኑ ለናንተ ብለን እዚህ ላይ ብንጽፈውም ሌሎችም አንባቢያን ከዚህ ልምድ እንዲወስዱ ለማሳሰብ እንፈልጋለን::
ከዚህ ሌላ ግን Qaalluu እና አምሳሉ ጊዜያችሁን በመሰዋት ስለምታካሂዱት ክርክር ከልብ እናመሰግናቸሁዋለን::
አርታኢ/Editor
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
http://www.goolgule.com
editor@goolgule.com
ጥቁር ሰው says
ኢትዮጵያ ሙሉ አፍሪካን ትወክላለች።እንደናንተ በጭፍን ጥላቻ እና ጠባብ ዘረኝነት አትወከልም።ሁለታችሁም አሳፋሪ ናችሁ።ወደ ኃላ እየተመለሳችሁ እንደ ዝንብ ቁስል ላይ ማረፋ ችሁን አቁሙና በፍቅርና በሰላም ያለንን እየተጋራን ወደ ፊት እንጓዝ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር