• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመረጃ ነፃነት?

January 13, 2014 10:54 pm by Editor 1 Comment

‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡

መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት  መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡

በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም አቀፍ ስምምነት በመደረሱ የመናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የዲሞክራሲ ዋና የድም ስር ነው የተባለው፡፡ ስለዚህም ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራ ስለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

ለመደርደሪያነት የዚህን ያኸል ከተባለ ወደ ዋናው ጉዳይ አስፈቅደን ሳይሆን ፈቅደን እንገባለን፡፡ ያነሳነው አሳብ ‹‹ መረጃ ›› እንደመሆኑ መጠን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተፍጥሯዊ መብታችን በፈለግነውና በፈቀድነው መንገድ እንገልፃለን፡፡ እኛ ስል ለመረጃ ነፃነት የቆምነው ሁላችንም ማለቴ ነው፡፡

ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶ ናት፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡ ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? ያሉት ጋዜጦች እና መፅሔቶች እየደረሰባቸው ያለው ማስፈራሪያና ዛቻ ደረጃው ምን ያኸል ደርሶአል የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አክራሪነትና ፅፈኝነት የሚያበረታቱና የሚያሰራጩ በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡

በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ ንግግር ነው፤ በመናገር መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውል ሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡

በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከሰሞኑ የህዝብ ሳይሆን የገዥው መንግስት አንደበት በሆነው በኢቲቪ  በተላለፈው የዘጋቢ ፊልም ግለሰቦችም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ ለኢሳት መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠቡ ምክር መሰል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል፡፡

ለዚህም እንደምክንያት የቀረበው ኢሳት የተባለው የመገናኛ ብዙሃን በሽብርተኛ ድርጅት የሚደገፍ ነው የሚል ምክንያት ነው፡፡ ኢቲቪ በኢህአዴግ እንደሚደገፍ ሁሉ ኢሳት በማንም ሊደገፍ ይችላል፤ ቁም ነገር ሆኖ መታየት ያለበት ኢቲቪ ሆነም ኢሳት የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድነው ፡፡ በተጨማሪ መልዕክቱ ለህግም ሆነ ለሞራል ምን ያኸል ተቃራኒ ነው የሚለውን ነው፡፡ በተጨማሪ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ መደመጥ እንዲሁም መሰማት የተከለከሉ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው ወይ ተብሎ መጠየቅና መልስ ሊሰጥባቸው የሚገባ አሳቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ወደ መልሱ ስናመራ ኢቲቪ እንዲሁም ኢሳት በህግ የተከለኩ አይደሉም ዋንኛው እና አስፈላጊው ነገር ይሄ ነው ሌላው የህጉ ደጋፊ ሃሳብ ነው፡፡

በመሆኑም ከዚህ በኋላ የህግ ጉዳይ ሳይሆን የፍላጎት ምርጫ ነው የሚሆነው፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከኢቲቪ ኢሳት ከአዲስ ዘመን አዲስ አድማስ የዝወትር ፍላጎታቸው ለሆነ እንዲሁም በተመሳሳይ ከኢሳት ኢቲቪ ከአዲስ አድማስ አዲስ ዘመን ለመረጡ ምርጫቸውን ማክበረ ነው፡፡

ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰበ ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በኢሳት ሆነ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡

yidnekachew
ይድነቃቸው ከበደ

ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ሃሳብን በመግለፅ እና መረጃን በመስጠት ዙሪያ ግዴታ ሊያመጣ የሚችለው ምንድነው የሚለው ነው፡፡ ግለሰቡ ወይንም ተቋሙ በግልፅ በህግ የተከለከለ መረጃ ወይም ሃሳብ የገለፀ እንደሆነ ግዴታው ተጠያቂነትን ስለሚያመጣ በህጉ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ይህ የህግ ተጠያቂነት አዱላዊነት የሌለበት ለሁሉም በሁሉም ቦታ እኩል የሚሰራ ነው፡፡ ይህም ማለት በህግ የሚያስጠይቅ ንግግር በኢሳትም ሆነ በኢቲቪ እንዲሁም በቢቢሲ ያደረግ በህግ ከመጠየቅ ንግግር ያደረገበት የብዙሃን መገኛኛ ሊታደገው አይችልም እንደማለት ነው፡፡

በመሆኑም በኢሳት ሃሳብን መግለፅ  እንዲሁም መረጃ መስጠት አልፈልግም ማለት መብት ነው፡፡ ነገር ግን በኢሳት አሳባችሁን አትግለፁ መረጃም አትስጡ ማለት ከፍላጎት የመነጨ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን የለየለት የእብሪት ተግባር ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ አሰፋሪ ምኞት እና ተግባር የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ተምሮ ያለመለወጥ ልክፍትም ጭምር ነው! በተለይ በመንግስት ደረጃ ሲታሰብ  እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    January 18, 2014 06:03 am at 6:03 am

    በነፃ ለመረዳት!‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› ኢህአዴግ ይጠይቃል? ሕዝቡም ይመልሳል በአንተ ተፈጠርን፤ አንተ ባትኖር የተረሳን፣ ተጨቆንን፣ ተረገጥን፣ ማንነትችንን የማናውቅ፣ የብሄር ብሄረሰቦች ለአንተና በአንተ አምነን በአንድ አንተ አስተሳስብና ምሪት ጥላ ሥር የታቀፍን አንተ ከሌለህ የምንጠፋ ነን ሲሉ ይመልሳሉ።
    ኢህአዴግም ይላቸዋል “ህወአት እባላለሁ በሻቢያ የተፈጠርኩ የበኩር ልጁ ነኝ። ኦነግብ ኦብነግም የሚባሉ ወንድሞችና ታናናሽ አህቶችም ነበሩኝ እኔን ግን አብልጦ ስለሚወደኝ ከቀኙ አስቀመጠኝ እናንተን ሰው ላደርግ ወደ መሐል መጣሁ…”ሙሉ ትንታኔው በማኒፌስቶው (ህገመንግስቱ ላይ ተዘርዝሯል)ሻ ቢያ ስለሌሎችም ያውቃል ግን ማን እንደበኩር ልጅ!? የበኩር ልጅ ወንድምና እህቶቹን ብቻ ሳይሆን ገና እያስታቀፈ የሚፈለፍላቸውንም ያውቃል፡ ስለዚህ ሁሉም በቋንቋቸው ይናገሩና አንዱ አንዱን አይረዳም የሚገባቸው ግን ፈጣሪያቸው የተናገረው ብቻ ነው እነሱ የሚናገሩት ለራሳቸው እንጂ ለእርሱ አይገባውም ለምን በእርሱ ተፈጥረዋልና የሚለውን ከመድገም በቀር ማፍለቅም መሥራትም አይችሉም። በለው! “የሟቹን ራዕይ ሳይበረዝ፣ ሳይከለስ፣ ሳይሸራራፍ፣ እናስቀጥላላን!። ታጋይ አይሞትማ። ለዚህ ነው በዘጠኙም ክልል ተቀብሮ ሥልጣኑን፹፭ሚሊየን አወረሰ የሚባለው።

    አዎን! አባሻና ልመና! ለመኖር፣ለማናገር፣ ለማፃፍ፣ ለማንበብ፣ ለመሰለፍ፣ ለመዋወርና ለመቀበር እንኳ ቢሆን አሳውቆ ለምኖ አስፈቅዶ!” ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷና ቀዳማዊት ናት፡፡እንዲሁ መካከላኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ይገባልን!? እንግዲህ በሙሉ ፍቃደኝነት ላይ በተመሰረተ እራስን አሳልፎ ለሌላ በመስጠት ስምምነት “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ ለመሆኑ ማንኛውም ሰው ማለት የትኛው የምናወራው በሕገመንግስት ታቅፏል ለተባለው ብሀየር በህረሰብ ነው ወይንስ ለሕዝቦቹ ብቻ ወይንስ “ማንኛውም ሰው የሚለው ቃል ከኢትጵያ ውጭ ለሆኑ ሰዎች ለኤርትራ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ግብጽና ጅቡቲ ማለት ነው!? ኢህአዴግ ፲ቦታ ጥዶ ዘጠኙ አረረበት ያለው ማን ነበር!?
    አንቀፅ ፳፱ (፮)እነህ መብቶች ገደብ ሊጣልባቸው የሚችለው የሀሳብና መረጃ ማግኘት ነፃነት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ሊያስከትል በሚችለው ውጤት ሊገታ አይገባውም በሚል መርህ ላይ ተመስርተው በሚወጡ ሕጎች ብቻ ይሆናል።(የወጣቶችን ደህንነት የሰውን ክብርና መልካም ሥም ለመጠበቅ ሲባል ሕጋዊ ገደቦች በእነዚህ መብቶች ላይ ሊደነገጉ ይችላሉ።
    >>_______የብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች ለምን በወጣቱና በታዋቂ ፖለቲከኞች ላይ ብቻ የተለየ የሕግ ከለላ አስፈለገ?
    ሀ)የሀገሪቱ ከፍተኛው ቁጥር ዕድሜው ከ፴፪ዓመት በታች የሆነ ስለሆነ ና ! ሲሉት ይሄዳል ጩህ ሲሉት ይጮሃል ካኒቴራና ባርኔጣ እያላበሱ ያስጨፍሩታል። በምርጫም ጫጫታ ላይ ከፍተኛውን ኮሮጆ የሚሞላውም ይሁን የሚገለብጠው ወጣቱ ስለሆነ ወጣቱ የአብዮቱ ትኩስ ኅይል ነው የሚለው “ወጣቱ ኢህአዴግ የግል ንብረት ነው!” ለዚህም እንግዲህ በክንፍ በነጠላና በጅምላ ይደራጃል ይሰባሳባል ተቃቅፎ ይጨፍራሉ።”ድንገት አንድ ለየት አለ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አረንጓዴው ልማታዊ መንግስት ቃል(ራዕይ)ውጭ አዲስ ሐሳብ በሰሙ ወይንም በተመለከቱ ግዜ እንደ መንዝ በግ ይደነብራሉ “(የወጣቱን ጭንቅላት በማናወጥ)በሚል በአዲስ ሓሳብ አፍላቂው ማናቸውም ሰውም ሆነ ፓርቲ ወይም ቡድን ላይ ክስ ያስመሰርትበታል ማለት ነው።
    (ለ) “የሰውን ክብርና መልካም ሥም ለመጠበቅ” ይህ ሰው ማነው? (ህዝቦች) ማለት ነው። የሻቢአህወአት/የኢህአዴግ አባልና ባለሥልጣን የአጋር ፓርቲ ሹማምንትንም ጨምሮ በሙስና ሥም ተጠርጥረው እንደሸንኮራ ተመጠው እስኪተፉ እጃቸው ለካቴና እግራቸው ለቃሊቲ እስኪበቃ ድረስ ሙሉ ጥበቃና የኢህአዴግ ከለላ ይደረግላቸዋል። መጠየቅም መተቸትም ወይንም የተናገሩትንና የሰሩትን ሁሉ ከማሞገስ በቀር የሚደረገው ማናቸውም ትችት ለምን? እንዴት? ብሎ ጥያቄ ማጫር አጥብቆ የተከለከለ ነው። “መላጣ ነው ማለት ትችላላህ መላጣ መንካት አትችልም! ” አጋር ፓርቲ ሹማንትን የሚቃወም ሁሉ ኢህአዴግ አደለም ቆሻሻ ሌባ ነው። አቶ ልደቱ እደግመዋለሁ የቀድሞው ሥርዓት ናፋቂ ሌባ ነው። እያሉ ማኒፌስቶውን ያብራሩ ነበር እኛ የሞቱ ጠ/ሚኒስትር። ለመሆኑ አብዛኛው ገበሬ ብሄር ብሄረሰብ የሚደረግለት የተለየ ጥበቃ የለም ማንበብና መፃፍ ባለመቻሉ?…ሚሊነየር ሆኗልና ቃሉ ጎርንኗል ማለት ነው? የሚያመጣው ነገር የለም እንቢኝ ካለ ያቺን የቀመሳትን ስኳር ይከለከላል ብለው ይሆን።በእርግጥ ሁለተኛና ሦስተኛ ዜግነት ፀና!? ጉድ በል ሰላሌ ኢትዮጵያዊ አደለህም ተባልክ አለ አቤ ቶክቻው።

    **በዲሞክራሳዊ ሥርዓት ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡የመናገር መጠየቅ ማንበብና መፃፍ መንቀሳቀስ የግድ የመንግስት ህገመንግስታዊ ፍቃድ ሳይሆን የፈጣሪ ቸርነትም ለራሱ ለመግስትና ባላሥልጣናትም እነደሆነ ሳይዘነጉ…የሕግ የበላይነትም የሚያከብረውና የሚያስከብረው ለመንግስትም አባልና ካድሬ ጨምሮ ለሕዝብም አድልዎ ሳይኖረው እንጂ አገም ጠቀም፣ በመፈክር፣ በቡጠራ በጭብጫቦ፣ በመደናነቅ ብቻም አደለም። በመተቻቸትም በተሻለ ሀሳብ ሀገር ግንባታ አለ። ለመሆኑ ካላደነቃችሁን ታሰሩ ከሀገር ውጡ አሸባሪዎች የሚለው ፍልስፍና እንዴት ፳፩ኛው ክፍለዘመን ላይ እንደ ድንጋይ ዳቦ ዘመን አልጠፋም! ለነገሩ እንቁላል ዕንቁ የሆነበት ልማታዊ መንግስት የባሰ አታምጣ ይቺንም አትንሳን እያሉ በልመና ከመናገር ተቆጥቦ እያለቀሱ ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረተ ብቻ ታጋይ የሚሰጠውም የሚነሳህም ከስኳርና ጤፍ ቀጥሎ ወደ እድገት ውጤትነት ተሸጋግሯል፡፡
    *ይህ ሁሉ ነገር በእኛ ለእኛ የራዕይና የትራንስፎርሜሽኑ በጎ ገፅታ ከሆነ ትራንስፎርሜሽኑና ዕራዩ ካልተሳካ ምን ይሆናል። እንደ መብራት ሁሉነገር በፈረቃ፣በልመና፣ በማስፈቀድ የተገነባ ዲሞክራሲ የቀድሞው ሥርዓት እኛ እናውቅልሃለን በእኛ እመን እና ስለአንተ እንናገራለን አለ ሲባል… ኢህአዴግ ሁሉ ነፃ በነፃ ነው ብሎ ሁሉንም በችርቻሮና በጅምላ ቸበቸበው የገባቸው ሼም ነው እረ ሼም ነው ሲሉ ሌሎችም የእውቀት ማነስ፣፣እብሪት፣ የማን አለብኝነት፣ የትውልድ ንቀት ነው አሉ ግን እኮ “እነሱ ሲዞሩ ስንዞርላቸው እኛ መች አወቅን እንደዞረባቸው”ያለው ይህ አደለምን!?እንቢኝ በለው! እነቢኝ ባለ ነው ዮሐንስ፣ መይሳው፣ምንይልክ ተከብረን የኖርነው ሕግ ማክበር እንጂ በግለሰቦች የሥልጣን መከታ ማስፈራራት ድብደባና እስራት ፍራቻ ሰው መሆናችንን አሳልፈን አንሰጥም! እንናገራለን! የምንናገረውን እናውቀዋለን! ለጠየቅነው አጥጋቢ መልስ ይሰጠን! ፣ለተናገርነውም ማስረጃና እውነታ አለን እውነትን ካልፈራችሁ አታፍኑን!የሁላችንም የበላይ የሀገር ሕግ አለና ደግመን ለማስታወስ በህግ አምላክ እንላላን…እናንተም…አንቺም…አንተም በለው! በቸር ይግጠመን>>>>>>>>

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule