አለመግባባት ለአገራችን ህልውና የሚፈጥራቸው አደጋዎች በየጊዜው እየጨመሩና እየተስፋፉ መምጣቱ በእጅጉ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። መንግስት ዋና ዋና ችግሮች ላይ አገራዊ መፍትሄን ለማግኘት ከህዝብ፣ ከህጋዊ ተቃዋሚዎችና ከዲያስፓራው ማህበረሰብ ጋር መግባባት ላይ ካልደረሰ አለመግባባት ወደ ቀውስና ግጭት ማደጉ አሳሳቢ ነው። መንግስት ለድርቅ አደጋ የተዳረጉ አስራ አመስት ሚሊዮን ዜጎችን አስፈላጊውን እርዳታና ድጋፍ እንዲያገኙ ሁሉንም ያሳተፈ፡ ግልጽና አፋጣኝ መፍትሄ ካልፈጠረ፤ እንዲሁም የኦሮሚያ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ላይ የሚያሰሙትን ተቃውሞ በማግባባት መፍትሄ ከመፍጠር ይልቅ ተማሪዎችን በመግደልና በማሰር ብቻ አላማውን የማስፈጸም አሰራሩ ከቀጠለ ለአገራችን ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አደጋ ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply