ዕርቅ ምንድን ነው? በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዕርቀ ሰላም ላይ የሚመክርና የመፍትሔ ሃሳብ የሚያመነጭ ውይይት አድርጓል። ፎረም 65 በጉባኤው ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተወያይቷል። ያድምጡት!
* ለመጪው ትውልድ መግባባትን እናውርስ።
* Dhaloota Dhufuuf Wal-ta’insa, Haa Dhaalchifnuu.
* ንመፃኢ ወለዶ ምርድዳእ ነውርስ።
ፎረም 65 (info@65percent.org)
Ezira says
የጨነቀው እርጉዝ ያገባል….እንደተባለው ወያኔ በታምኑምባታምኑ በአገዛዝ ዘመኑ ብዙ ተግዳሮቶች የገጠሙት ቢሆኑም ማለትም(በህዝብ ሥልጣን ላይ በጉልበቱ ከወጣበት ጊዘ ጀምሮ) እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ በጣም የተፈታተነዉና የመውድቂያ ጊዜው አሁን መሆኑን ወያኔ ራሱ እንዲገባው ያዴረገው ታሪካዊ እንቅስቃሴ ፤ የዘንድሮ ህዝባዊ አመጽ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ወያኔ በአደባባይ ደረጃ ሳይቀረ በየጊዜው ከቁጥጥሩ ውጭ በሆነ ሁኔታ መረበትበቱ ራሱ ገላጭ ነው። ይሄ ህዝባዊ አመፅ በኦሮሞያ ክልል ተቀጣጥሎ እሳቱ እየነደድ ጎንደር ሲደርስ የጎንደሩ አመፅ ዓይነቱንና ይዘቱን ቀይሮ “የወንድሜ የኦሮሞ ህዝብ ደም የእኔም ደም ነው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ የበላይነት ማክተም አለበት” ወዘተ በሚል ጥሪውን አስተጋባ። ይሄ የብሶት ጥሪ የኦሮሞ ህዝብ ጋሻ መከታው መሆኑን ማሳየቱ ፣ የደደቢት ወንበዴዎችን አልጋ ነቀነቀ። እንቅልፍም ነሳቸው። ይሄ መቼም ለኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ድል ነው። የህወሓት/ ወያኔ አነደኛ ሰው፤ የገማና የገለማ ጭንቅላት የነበረው መለስ ዜናዊ ከተናገረው ውስጥ አንዱና ዋናው፤ “የወያኔ ማብቂያና የግፍ አገዛዛቸው ማከተሚያ የሚሆነው አማራ እና ኦሮሞ አንድ የሆኑ ዕለት ነው” ያለው የወያኔዎች ሁሉ “ፍካሬ ደደቢት” ነው ። ይሄ ደግሞ አሁን በኢትዮጵያ ምድር እየታዬ ነው። የህውኃት/ወያኔ ሥስ ብልት አሁን ተገኝቷልና ከአሁን በኃላ ወደ ኋላ የህዝቡን ተጋድሎ የሚመልሰው ምንም ኃይል የለም ። ወያኔ እና ህዝብ አሁን ደም ተቃብቷል። አሁን ብሶት ያንገሸገሸውው ህዝብ ዱሩን ቤቴ ብሏል። ጫካውን መከታ አድርጎ ወያኔን መግቢያ መዉጫ አሳጥቶታል። ዛሬ ትናንት ወያኔ ገና ሥልጣኑን ሳያጣጥም፤ የሥነ ልቡና ዝቅተኝነት ስሜቱ እንዳዘሬው በጮማ ሳይዴፈን እንደደነፋው “ጦርነት ሁሉ እንሠራለን” እንዳለው የእብሪት ንግግሩ አይደለም ዛሬ ሁሉ ነገር ለወያኔ። ስለዚህ ዛሬ ለደዴቢት ወንበዴዎች ነገሮቹ ሁሉ “እንዳይገፋው እሣት፤ እንዳይተወው ምፃት” ሆኖበታል። Thanks God ወያኔ ራሱ እንዲህ ሲቀዝን ማየት የድላችን ሁሉ ድል ነው። ድል ለህዝባችን