• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የነፈሰበት ኢትዮጵያዊነት

April 9, 2014 02:32 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያ የ5 እና የ 6ሺ ዘመን ታሪክ ያለት ሀገር ነች። የመንግስት ስርዐትም ፈጥረው ከኖሩ ሀገሮች መካከል በቅድሚያ የምትጠራ ሀገር ናት። ሆኖም ግን አንዳንዶቹ የአሁኑ ድህነታችን፣ በቴክኒኦሎጂ ወደሁዋላ መቅረታችን፣ የቀደመ የኢትዮጵያንና የህዝቡዋን ትልቅነት ለማየት ይቸግራቸዋል። ”ቤት ሲያረጅ ትሁዋን ይፈጥራል” እንደሚባለው ካልሆነ በቀር ከታሪክ እንደምንረዳው፣ አንድ ሀገር ይወድቃል ይነሳል፡ ይደኸያል ይበለጽጋል፡ ይዋረዳል ይከበራል። ሆኖም በህዝቡ የመንፈስ ጽናትና ቆራጥነት፣ የገጠመውን ድህነት፣ ውድቀትና ፈተና ሁሉ ታግሎ አሸንፎ ወደ ነበረበት የክብር ቦታው ይመለሳል። ዛሬ እኛ ደህይተናል፣ ወድቀናል፣ ተዋርደን ህዝባችን በየሀገሩ ተበትኖ የስቃይ ህይወት መኖሩ አልበቃው ብሎ በሀገሩም በሰላም እንዳይኖር በኢትዮጵያ የቅርብና የሩቅ ጠላቶች በሚደጎሙና አለኝታን ባገኙ ከሀዲዎች ሀገራችን በብሄር ተሸንሽና ኢትዮጵያዊነት ላይ ጦር ተሰብቆበታል። በተለይ ኢትዮጵያዊነቱን ጥርጣሬ ውስጥ ያላስገባው የአማራው ህዝብ በጠላትነት ተፈርጆ ይፈናቀላል፣ ይታሰራል፣ ይገደላል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ድህነትና ወደ ሁዋላ መቅረት ጭንቅላታችንን ቀና አድርገን በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከማየት ሊጋርደን አይገባም። ወይም በአማራው ህዝብ ላይ በሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ እኔ የለሁበትም ለማለት ምክንያቶችን በመፈብረክ የሁለት ብሄሮች ችግር አድርጎ ማቅረብ፣ ወይም ድርጊቱን የሚፈጽሙትን በጀምላ የአንዱ ወይም የሌላው ብሄር የባህሉ መገለጫ አድርጎ ማቅረብ፣ በተለይ ለሀገርና ለህዝብ መፍትሄ ያፈልቃሉ ተብለው የሚጠበቁ የተማሩ ዜጎች በተቃራኒው የአማራውን ህዝብ ግዳይ በመጣል ስልጣን ከያዙና ጉልበት ካለቸው ጋር ለመተቃቀፍ በጽሁፍ፣ በድምጽና በምስል ቅጅዎች፣ በትብብርና ዝምታን መደበቂያ አድርጎ በመምረጥ የሚያሳዩት ግብራአበርነት ኢትዮጵያዊነትን አይገነባም።

ዛሬ በአንድ የአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው አንድን ሰውና ወገን፤ ከአማራ ወላጆች መወለዱን ብቻ ዋናና አይነተኛ ምክንያት አድርጎ አንድን ሰው ተወልዶ ካረጀበት ቀየው ማፈናቀል፣ ማሰር፣ ማጋዝና መግደል ነገ ሌላውን ተረኛ አያደርግም ብሎ ማሰብ፣ አርቆና አሻግሮ ማየት አለመቻልን ብቻ ሳይሆን፡ አንድነት፣ ሙሉነት፣ ጥራት፣ አይነተኛነት የጎደለው የነፈሰበት ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆኑን ግልጽ አድርጎ የሚያሳይ ይመስለናል።

ኢትዮጵያዊነት መከባበር፣ መተዛዘን፣ መነፋፈቅ፣ መፈቃቀር፣ መተሳሰብ እንጂ አንድ ህዝብ ተለይቶ ሲጋዝ፣ ሲሰደድ፣ ሲፈናቀል፣ በህይወት በገደል ሲጣል፣ ቤት ተዘግቶበት ሲቃጠል፣ ማስተባበያ ምክንያት እየፈጠሩ ከአጥቂው ጋር መወገን፣ ሙሉነቱንና አይነተኛነቱን፣ ሀቀኛነቱንና ጽናቱን የተገፈፈ የነፈሰበት ኢትዮጵያዊነት ከመሆን ያለፈ አይሆንም።

ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የመንግስት ስርአት መስርታ የኖረች ሀገር በመሆኑዋ የአማራው ህዝብ አሁንም ቢሆን ተወልዶ ከአረጀበት፣ ያያት የቅድመ አያቱ አጽም ካረፈበት፣ አባት አያት ቅድመአያቱ ከውጭ ወራሪ፣ ከውስጥ ከሀዲ የደም ዋጋ ከፍለው ካወረሱት ሀገሩ፣ ”ይህ ያንተ ሀገር  አይደለም” ተብሎ ሲፈናቀል አሁንም ቢሆን ለመንግስት አቤት ይላል። ይህ በረጅም ዘመን የተገነባው በህግና በመንግስት ላይ ያለን እምነት ከስር ከመሰረቱ ከህዝብ ስነልቦና ሰልቦ በምትኩ በህዝብ መካከል አለመተማመንን፣ መጠራጠርንና የጎሪጥ መተያየትን ለመተካት በህዘብና በሀገር  ከሀዲዎች ሳያዛንፍ ከ20  ዓመት በላይ አንድን ህዝብ ለይቶ የማጥፋት ዘመቻ የሚፈጥረው፣ የነፈሰበት፣ የተበላሸ፣ የተመረዘ ኢትዮጵያዊነት እንጂ፣ በእምነቱ የጸና፣ የተከበረና የኮራ ኢትዮጵያዊነትን አይሆንም።

በአንድ አካባቢ፣ ቀበሌና ቀዬ በእድሩ፣ በማህበሩ፣ በቤተ ክርስቲያኑ፣ በመስጊዱና በመሳሰሉት ህብረተሰቡን በሚያገናኙት ነገሮች አንድ ሆኖ በአንድነት የኖረን ህዝብ፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ታሪካዊ የቅርብና የሩቅ ጠላቶች በገንዘብ፣ በመሳሪያ፣ በሎጅስቲክና በመሳሰሎ ነገሮች እርዳታና ስልጠና አግኝተው ለስልጣን ከበቁ የሀገርና የህዝብ ከሀዲዎች ኢትዮጵያዊነትን መጠበቅ ከእባብ የእርግብ እንቁላል መጠበቅ ይሆናል።

የአማራው ህዝብ ”ነግ በኔ” የሚል ነገን አሻግሮ የሚያይ አኩሪ ባህል ያለው ህዝብ በመሆኑ፣ ክፉውን ከደጉ ለይቶ፣ በከንቱነት ፈርጇቸው ትግሉን በአንድ ኢትዮጵያዊነትና በአንድ የኢትዮጵያ ህዝብነት ሙሉ እምነት ትግሉን በትእግስትና በጽናት እስካሁን ተቋቁሟል፣ ነገም ይቋቋማል። እህቶቻችን በአምካኝ መድሀኒት ዘር እንዳይተኩ ሆነዋል፡ አባቶቻችን በህይወት በገደል ተጥለዋል፣ ቆዳቸው ተገፎ ተገለዋል፤ ወንድሞቻችን ያባቶቻቸው አጽም ካረፈበት ቀያቸው ሀገራችሁ አይደለም ተብለው ተፈናቅለዋል፡ ታሪካችንን ወደሁዋላ ሄደን እንድንመረምር ተገፍተናል፣ ሀገራችንና ህዝባችን በጣሊያን ወረራ ወቅት ያሳለፉትን ፈተና ከወረቀት አልፎ በአይን አይተናል። አንድን ህዝብ በቋንቋ መክፈል፣ የነፈሰበት፣ የተሳከረ ኢትዮጵያዊነት እንጂ፣ አንድነቱ የጸና እና በኢትዮጵያዊነቱ የኮራ ኢትዮጵያዊነት ይገነባል የሚል ቅዠት የለንም።

ኢትዮጵያ በልጆቿ የመንፈስ ጽናት ተመልሳ በእግሯ ትቆማለች።

ኢትዮጵያ በነጻነቷና በአንድነቷ ለዘላለም ኮርታ ትኑር

ሞረሽ ወገኔ ማህበር በስዊድን

moweswe@gmail.com

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule