
ሉዓላዊነት እና አብሮነትን የሚፈታተኑ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም እንዳሉት አንዳንድ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት በትግራይ ክልል ላይ የሰሯቸው ዘገባዎች በአጠቃላይ የጋዜጠኝነት ሙያ አስተምህሮ እና ሙያዊ ስነ ምግባር ጥያቄዎችን የሚያስነሱ ናቸው።
ሥራዎቻቸው በጣም የሚያስተዛዝቡ እና የሚያበሳጩ ጭምር መሆናቸውን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ሚዲያውን እና ዘገባው የሰራውን ባለሙያ ለይቶ ማየት ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ወንድወሰን ተናግረዋል።
አንድ የሚዲያ ተቋም የላከው ጋዜጠኛ ስህተት ሰራ ማለት ሚዲያው ሙሉ በሙሉ ከእውነት፣ ከፍትህ እና ከሀቅ የተፋታ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እንደማያስችልም አንስተዋል።
የተዛቡ ዘገባዎችን በሚሰሩ ባለሙያዎች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች የመጨረሻ ግብ አይደሉም ያሉት አቶ ወንድወሰን፤ በቀጣይም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ እንዲሁም አብሮነትን የሚፈታተኑ ሥራዎችን የሚሰሩ ሚዲያዎችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ማስጠንቀቃቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል። (ኢቢሲ)
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply