ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ነች። ከዚህ በፊትም ሁለቴ አርግዛ አዋላጆቿ የሚያደርጉትን ስላላወቁ እናት ብዙ ደም ፈሷት ከሞት አፋፍ ድናለች። የሦስተኛው ምጥ አዋላጅ ኢሕአዴግ ይሳካለት ይሆን?
እንዴት እዚህ ደረስን?
በዘመናዊ ትምህርትና በምዕራባዊያንና ምስራቃዊያን ፍልስፍናና ርዕዮተ አለም የተቀረፀው የ1960ቹ ትውልድ ኢትዮጵያን እንደሌሎቹ አገሮች የዳበረችና የበለፀገች አገር ለማድረግ ምኞቱና እምነቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ፤ የንጉሱም እድሜ 80ዎቹ ውስጥ ስለነበረ፣ አለምአቀፋዊ ኢኮኖሚያዊ ሂደቶች/የነዳጅ ዋጋ ስለናረና፣ አለምአቀፋዊ ሁለት ግዙፍ የፓለቲካ ጎራዎች ገዝፈው ከመውጣታቸው ጋር ተደምሮ ኢትዮጵያን ከባህላዊ አስተዳደር ወደ ህዝባዊ አስተዳደር ተስፈንጥራ እንደትገባ የሚታገል አብዮታዊ ትግል ተጧጧፈ። አብዮትም ፈነዳ።
የተማሪው ንቅናቄ ያስተናገደውና ወደ ውስጡ ያሰረፀው የምስራቃውያን ርዕዮት ኢትዮጵያን ከኃላቀርነትና ድህነት ወደ ስልጣኔና ብልፅግና ለማሸጋገር አቻ የሌለው አማራጭ ተደርጎ በወታደሩ፣ በተማሪውና በፓለቲካ ድርጅቶች ሊሂቃን ውስጥ ቅቡልነት አገኘ። “ኢሕአዴግ ዛሬ ለምን ከአገልግሎት አሰጣጥ ተሃድሶ ይልቅ ወደ ፓለቲካዊ ስርዓት ተሃድሶ አይገባም?” ለሚለውም ጥያቄ ዋናው ምክንያቱ ርዕዮታለማዊ መሰረቱ ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply