• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያና አሜሪካ

May 20, 2015 08:06 am by Editor 1 Comment

ዱሮ ዱሮ ምዕራባውያን የሶቭየት ኅብረትን ኮሚዩኒዝም መስፋፋት ለመቋቋም ከእሥራኤል ሌላ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ አገሮችን ሲያስሱ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱርክና ፋርስ እየታጩ ነበር፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተወዳጀበትና በአስመራ ቃኘው ጣቢያን የተከለበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፤ የፋርስ ጉዳይ ከንጉሠ ነገሥቱ መፈንቅለ መንግሥትና ሞት ጋር አበቃ፤ ቱርክ እያንገራገረም ቢሆን የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ማኅበር ውስጥ አለበት፤ እሥራኤል በአረቦች አካል ላይ እሾህ እንደሆነች ጥጋበኛ የአሜሪካ ቅምጥል ሆናለች።

የፋርሱ ጉዳይ ከፋርሱ ንጉሠ ነገሥት ጋር እንደተያያዘው ሁሉ የኢትዮጵያም ጉዳይ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ጋር የተያያዘ ነበር፤ የእውቀት ጥበብ (ቴክኖሎጂ) እያደገ ሲሄድ የቃኘው ጣቢያ ለአሜሪካ አማራጭ የሌለው መሆኑ ቀረ፤ አሜሪካ ኮተቱን ይዞ ወደህንድ ውቅያኖስ ሲሄድ ኢትዮጵያን ችላ ማለት ተጀመረ፤ መቃቃሩ እየበረታ ሲሄድ የአሜሪካ እብሪትና የኢትዮጵያ ኩራት ተጋጩ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ የአሜሪካኑን አምባሳደር አስከማስወጣት ደረሱ፤ ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ያኔ ተጀመረ፤ የፋርሱ ንጉሠ ነገሥት ሲገለበጥ ቀጣዩ አገዛዝ ከአሜሪካ ጋር ጠላት እንደሆነው የአጼ ኃይለ ሥላሴም አገዛዝ ሲገለበጥ ቀጣዩ አገዛዝ ከአሜሪካ ጋር ጠላት ሆነ።

አሜሪካ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ጣልቃ እየገባ የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው ግፍ የጀመረው ከዚያ ወዲህ ነው፤ የደርግ አገዛዝ ኮሚዩኒስት መሆኑን አወጀ፤ የደርግ አገዛዝ ከሶቭየት ኅብረት ጋር ማኅበርተኛ መሆኑን አወጀ፤ የደርግ አገዛዝ የአሜሪካ መንግሥት ዓለም-አቀፍ ቄሣራዊነትን የሚያራምድ መሆኑን እየደሰኮረ የአሜሪካ ባላጋራ መሆኑን አስታወቀ፤ ይህ ሁሉ እውነት ነው፤ ነገር ግን አንዱም የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈቃድ ያዘለ አይደለም፤ አንዱም ኢትዮጵያን እንደአገር የሚያስጠይቅ አይደለም።

ከላይ ለተጠቀሱት የደርግ ‹አዋጆች› የአሜሪካ መንግሥት መልስ የሰጠው ለደርግ መንግሥት ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ነበር፤ መልሱ ይህ ነበር፤

አንደኛ ኢትዮጵያን የወረረችውን ሶማልያን ረዳ፤

ሁለተኛ ሻቢያንና ወያኔን የሚረዳውን የኑሜሪን ሱዳንን ረዳ፤

ሦስተኛ ሻቢያንና ወያኔን ረዳ፤

አራተኛ የኤርትራን መገንጠል ደገፈ፤

አምስተኛ የወያኔን አምባ-ገነን አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ተክሎ አቅፎታል፤

እነዚህ የአሜሪካ መልሶች ደርግ ወንበሩን አስረክቦ ቃሊቲ ከገባ በኋለም መቀጠላቸው የአሜሪካ ጠብ ከደርግ ጋር ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያም ጋር የሆነ ያስመስላል።

በኢትዮጵያውያን ድካምና በአሜሪካ ጫና ኢትዮጵያ ዛሬ ሁለት ሆናለች፤ በአንዱ ክፍያ ላይ አሜሪካ እግሩን ዘርግቶ አድራጊ ፈጣሪ ቢሆንም በሌላው ክፍያ ላይ እግሩን ማስገቢያ አላገኘም፤ ብዙ ሰው ያልተረዳውና የሚያስደንቀው የአሜሪካ ዶላርና የአሜሪካ ጫና ኤርትራን ማንበርከክ አለመቻሉን ነው፤ ሎሌ ሆኖ ጌታ ከመምሰል ደሀ ሆኖ መከበር ይሻላል፤ ይህ የቀድሞው የኢትዮጵያዊነት አልበገርም-ባይነት፣ የክብርና የኩራት ምልክት ነው፤ አልጠፋም!

በአለፉት ዓመታት ውስጥ አሜሪካ በኢራቅ ምን አደረገ? ማንን ጠቀመ? ማንን ጎዳ? በአፍጋኒስታንስ? በፓኪስታንስ? በሶርያና በየመን የሚካሄደውስ ብጥብጥ የት ድረስ ይሄዳል? የትስ ይቆማል? ቀደም ሲል በኮሪያ (ኢትዮጵያን አስከትሎ) ምን ፋይዳ ሠራ? ሁለት ኮሪያዎችን ፈጠረ፤ በቭየትናም ሕዝብ ጀግንነት ቭየትናም አንድነቱን ይዞ በድል ወጣ፤ መከፈል ለሱዳንም ደረሰው፤ መከፋፈል ሲጀምርም የማይቆም መሆኑን በሱዳን እያየን ነው።

ነገ በኬንያ ምን ይሆናል? ዛሬ ኬንያውያን ሳይገባቸው አገራቸው ውስጥ እሳት እየተቀጣጠለ ነው፤ እሳቱ ወዴት እንደሚዘምትና ማንን እንደሚያጠፋ ወደፊት እናያለን፤ በየመን በኩል የሚቀጣጠለው እሳትም በጂቡቲና በሶማልያ በኩል ባሕር የሚገባ አይመስለኝም።

ኢትዮጵያን የማላነሣው ረስቼ አይደለም፤ አንዴት ብዬ! አንዱ የወያኔ ጮሌ ‹ምሁር› በፌስቡክ ላይ መቀሌ አይባልም፤ መቐሌ ተብሎ መጻፍ አለበት ብሎ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር ነበር፤ እንደሚመስለኝ አሸነፈ መሰለኝ! አዋቂነት መሆኑ ነው! ነገ ደግሞ አንዱ ተነሥቶ ባቄላ አይደለም፤ ባኤላ ነው፤ ቢል ማን እንደሚያሸንፍ አላውቅም፤ እንደፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴ (ነፍሱን ይማረውና)፣ እንደፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽና እንደፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ያሉ የታሪክ አዋቂዎች ስድስት ሺህ ዓመታት ሲቆጥሩ ገና ፊደል የቆጠሩት የዘመኑ ደርሶ አዋቂዎች ደግሞ ዳዴ ሊያስኬዱን ይፈልጋሉ፤ ስለዚህም ገና የእውቀትን መስፈሪያና የታሪክን ማበጠሪያ አላረጋገጥንም፤ ከግራም ሆነ ከቀኝ ለሚመጣብን አደጋ በአሜሪካ ላይ የምንተማማን ከመሰለን የደቡብ አሜሪካን፣ የምሥራቅ እስያንና የመሀከለኛው ምሥራቅ አገሮች ከአሜሪካ ጋር የነበራቸውን ታሪክ እናጥና።

አሁን ደግሞ የጦርነት ዓይነት በጣም እየተለወጠ ነው፤ በሰልፍ የጦር ሜዳውን የሚሞለው ወታደር የለም፤ የመሣሪያው ዓይነትና ብዛት እምብዛም ዋጋ የለውም፤ ጥቂት ሰዎች በጥቂት ፈንጂዎች ከባድ ጥፋትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ አሸባሪ ቡድኖቹ ለሰው ሕይወት ዋጋ የላቸውም፤ ለሀብትም ሆነ ለባህላዊ ቅርስ ግድ የላቸውም፤ የራሳቸውን ሕይወት ወደመሣሪያነት ለውጠውታል፤ አንድ ቦታ አይቆዩም፤ ይዘዋወራሉ፤ ጥላቻ እንጂ ፍቅር አያውቁም፤ ሞት እንጂ ሕይወት አያውቁም፤ ጥፋት እንጂ ልማት ዓላማቸው አይደለም፤ አቃጥሎ መቃጠልን እንደመጨረሻ ዓላማ የሚከተሉ ናቸው፤ የሚያከብሩት ሕግ፣ የሚፈሩት ኃይል የለም፤ ከነዚህ ጋር ጦርነት መግጠም የማይበርድ እሳት ውስጥ መግባት ነው፤ ታላቁ አሜሪካ ከማያልቀው ሀብቱና ወደር ከሌለው የጦር ኃይሉ ጋር ላለፉት ስድሳ ዓመታት ከደቡብ አሜሪካ ጀምሮ እስከእስያ፣ ከቤይሩት እስከቭየትናም ጥረቱ ሁሉ ከሽፏል፤ ውድና ክቡር የአሜሪካ ሕይወት በአረመኔዎች እንዳይቀጠፍ ከደሀ አገሮች የእሳት እራት የሚሆኑ ወታደሮችን ይከራያል፡፡

ግንቦት 2007

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Selamu says

    May 22, 2015 02:34 pm at 2:34 pm

    ፕሮፌሰር መስፍን የጻፉት የሚያሳስብ ጉዳይ ነው። አሜሪካ እንደ አብዛኛዎቹ ሐገሮች የምትከተለውና የምትታተኩረው በግል ጥቅሟ ላይ ብቻ ነው። ከዚህ በላይ የሚያሳዝነው፤ ጥቅሟን የምትመለከተው ከአፍንጫዋ በማይርቅ ለአጭር ጊዜ ብቻ በሚበጃት ስልት ነው። ለዘለቄታው የሚጎዳትም ድርጊት መሆኑን በመመልከት ጥንቃቄ አታደርግም።
    ቢሆንም፤ የፕሮፌሰር አሉታዊ አቀራረብ ኢትዮጵያን የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም አይደለም። ምክንያቱም በአሜሪካ ቅር የተሰኙ ሁሉ አሜሪካን አርግፍ አድርጎ በመተው ወደ ቅያሜ አቅጣጫ ቢመሩ ዋናው ተጠቃሚ ወያኔ ብቻ ነው የሚሆነው።
    ይልቅስ ለሐገራችን የሚበጀው በዲፕሎማቲክ ዘዴ በመጠቀም የአሜሪካን ፖሊሲ ወደ ኢትዮጵያ ጥቅም ለመመለስ መሞከር ነው የሚሻለው። በዚህም ዘዴ ብዙ ሐገሮች ይጠቀማሉ። ለዚህ ተምሳሌት የሆነችው እሥራኤል ናት። የአሜሪካ መንግሥት፤ ፕሬዚዳንት ኦባማ ጭምር፤ በኢትዮጵያ የሚያላግጡበት አንደኛው አሳፋሪ ምክንያት አሜሪካ የሚኖሩትና የሐገሩ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን በምርጫ መብታቸው በመጠቀም ተገቢውን እርምጃ ስለማይወስዱ ነው። እንደ ሌሎች ዜጎች በምርጫ መብታቸው እየተጠቀሙ የኮንግሬስ ሰዎችንና የስቲት ዲፓርትሜንት መሥሪያ ቤትን እንዲሁም ኦባማን በአጽንኦት ቢከታተሉ ሐገራችን እስከዚህ አትደፈርም ነበር። ይህም ሥልት ለመለማመጥ ሳይሆን ለአሜሪካና ለኢትዮጵያ በሚበጅ የዘለቄታ ጥቅም በተመሠረተ ዓላማ መከናወን አለበት። ስለዚህ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመብታቸው ሳይጠቀሙ ቀርተው የአሜሪካንን መንግሥት ማማት ጉዳት እንጂ የሚያስገኘው ጥቅም የለም። የሚያዋጣው በሰከነና በነጠረ የዲፕሎማሲ ዘዴ መጠቀም ነው እንጂ አጉል መኩራራትና በብስጭት ማጥላላት ለማንም አይበጅም

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule