• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ፡ ሽምግልና ለምኔ?

September 22, 2016 01:44 am by Editor 2 Comments

ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ችግሮች ለመውጣት ሽምግልናን እንደ መፍትሄ አድርጋ መውሰድ ትችላለች ወይ? እስቲ ይህንን ሀሳብ በተመለከተ ጉዳዩን ከሁሉም አቅጣጫ ረጋ ብለን እንመልከት።

ከኢህአዴግ አንዳንዶች አንድ ምርጫ ብቻ እንዳለ ሊያስቀምጡ የፈለጉ ይመስላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን ፀጥ ለጥ አሰኝቶ መግዛት አሊያም በሃይልም ቢሆን መግዛት እንችላለን ብለው የሚያምኑ እስኪመስል ድረስ ሃይልንም ሲጠቀሙ ይታያል። በተቃዋሚ ጎራ ያሉ አንዳንዶች ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ምርጫ ብቻ እንዳለ አድርገው ያስቀምጣሉ። ያም የሚያስከትለውን ዋጋ ከፍሎና  በአመፅ አብዮት አካሄዶ መንግስትን መገልበጥ ነው እንጂ መነጋገር የትም አያደርስም ብለው ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ።

እና ምን ይሻላል? ተያይዞ ገደል መግባት ወይስ አውጥቶ አውርዶ፥ ከሁለቱም ተቃራኒ አስተሳስብ ይልቅ ሌላኛ ሶስተኛ አስተሳሰብ አለ ብለን መንግስትንና የተቃዋሚ አካላትን መሞገት?

የኢትዮጵያ ሕዝብ በመቻቻልና በመተሳስብ አብሮ የኖረ ሕዝብ ነው። ያልታደለው እኩልነትን አንግሶ በፍቅር የሚያያይዘውና አንድ የሚያደርገው አስተዳደር እስካሁን አለመገኘቱ ነው። ፈሪሃ ፈጣሪን የተላበሰው ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእውነት ላይ የተመሰረተ ጥል ሆነ ጥላቻ አንዱ በሌላው ላይ የለውም። መሪዎች እንደ ሕዝቡ ቅን ሆነው እኩልነትና ፍቅርን ቢዘሩ የሚታጨደው የፍቅር አዝመራ የሚያስጎመጅ በሆነ ነበር።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ህብረ ብሔር በሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በመሪዎች የስህተት አካሄድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግስት በተቀዳሚነት ለዚህ ስጋት ሃላፊነትን ራሱ መውሰድ ይገባዋል። ራሱንም ተጠያቂ ካደረገ በኋላ፥ ወደዚያ ጥፋት ከሚመራው የሃይል እርምጃ ታቅቦ ኢትዮጵያን ለማዳን ውይይትና መግባባትን እንደ ብቸኛ አማራጭ በመውሰድ አማራጭ ሃይሎችን ለሰላሙ ጉዞ መጋበዝ ይኖርበታል።

አብዮት ላለፉት አራት አስርተ አመታት ያተረፈልንን እያየነው ነው። ችግርን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ለዛሬና ለወደፊቱ ፍቱን መድሃኒት ነው። አብዮት የዛሬን ችግር ፈቶ ሲያበቃ የነገውን ችግር ይወልዳል። መንግስት ጊዜ ሊገዛ ፈልጎ የውሸት ሽምግልና ቢመርጥ ያንን ውድቅ ማድረግ ያባት ነው። አለበለዚያ ግን በጭፍን ሽምግልና ዋጋ የለውም ማለት ከማስተዋል ሃላፊነት መጉደል ይሆንብናል።

ሽምግልና ይሰራል አይሰራም ሳይሆን ጥያቄው፥ የትኛው ሽምግልና ይሰራል ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ሁለት አይነት የሽምግልና አካሄድ ሊኖር ይችላል። አንድም አድሏዊ የሆነ ከሃይለኛው ጋር የወገነ የይስሙላ ሽምግልና ሲሆን ሌላኛው ደግሞ፥ አድሏዊ ያልሆነ ከማንም ያልወገነና እውነተኛ ሽምግልና ነው። በርግጥ የይስሙላ ሽምግልና ምንም ፋይዳ ላይሰጥ ይችላል። ነገር ግን ለእውነተኛው ሽምግልና እድል ተሰጥቶት ኢትዮጵያ ካለችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ ድልድይ ቢሰራ ሀገራችን ዘላቂ ሰላም ይሰፍንባታል።

የዚህ እውነተኛ ሽምግልና ግብና ዓላማ የሚያዛልቀው ሶስተኛው (ሌላኛው) መንገድ፥ በውይይትና በመግባባት አገሪቱን በሰላማዊ መንገድ ወደ ዘላቂ ዲሞክራሲ ፍትህ እኩልነትና ዕድገት የሚያመራውን ሂደት ለመፍጠር ሁኔታዎችን የሚያመቻች ነው። ዞሮ ዞሮ ይህን ዓላማና ግብ ሁላችንም የምንፈልገው ነው።

እግዚብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Takele says

    September 26, 2016 04:13 pm at 4:13 pm

    Well done brother , that is why peace and justice for Africa is trying to do its best . Let us unite , talk , discuss the problem and come to the table with a clean heart and bright mind . All sides have to restrain from where they were and say byegones be byegones . In order to make this happen the government, opposition parties , elderlies , religious leaders , and concerned fellow Ethiopians like you have to pay serious attention and cooperate with PJA ( Peace and Justice for Africa ) to make it real . The current Ethiopian situation is going from bad to worst and our beloved country is on the sharp edge of the cliff . We all wish if our naturally beautiful country go in the right direction and become one of the best democratic and prosperous country in the world . please , please citizens and friends of Ethiopia let us change this worst atmospher and make our country comfortable for everyone of us to live .

    Reply
  2. Alewa Geremew says

    October 5, 2016 03:42 am at 3:42 am

    Selam Dr. Zelalem,

    It is not time to split hair. The premise that TPLF will participate in a genuine reconciliation is wrong. I know you very well and you are a very intelligent person even when we were in college.
    Over the years, I noticed when your posting shows up. I am not sure it is intentional but most of the time you choose the wrong time.

    Dr. Zelalem, I recall how you were devastated when you lost loved ones. So please do not make a trivial argument when people of Ethiopia is mourning.

    Thousands of Amhara, Oromo, Konso, Benshangul, and many other ethnic groups have been massacred by the regime. The Ethiopian people have to get rid off this terrorist government.
    What you are preaching is exactly what these fascists are looking for to buy time.

    My heart is broken when the woman in Wollega was forced to sit on her son’s dead body and beg for mercy to save her daughter. I am heart broken when millions show up for thanksgiving and massacred! I don’t have to be an Oromo to feel the pain. The genocide in Amhara region is beyond belief.

    Victory to Ethiopian People!

    Take care Brother!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule