• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በአውሮፓ፣ ሮም ላይ ተዘርፏል?

October 17, 2017 01:50 pm by Editor 2 Comments

  • በአምስተርዳም ከተማ የተካሄደው አመታዊው የቦርድ አባላት ስብሰባ ጥያቄውን ይመልሳል

ካለፈው ኦገስት ወር ጀምሮ እጅግ ተጋንኖ ሲወራ የነበረ ጉዳይ ነው። ፌዴሬሽኑ ሮም ላይ ተዘርፏል። ይህንን “ዝርፍያ” ልዩ ያደረገው በቅንብር እና በጥናት የተሰራ ነው የሚሉት ጥቂት አልነበሩም። ከውጭ የሚወራው እና የሚጻፈው ነገር ብዙ ነው። ፌዴሬሽኑ እንዴት እና ለምን ተዘረፈ? የሚለው ጥያቄ ግን ምላሹ ከመላ ምት ያላለፈ አልነበረም። ቅዳሜ፣ 14 ኦክቶበር 2017 በአምስተርዳም ከተማ የተካሄደው አመታዊው የቦርድ አባላት ስብሰባ ይህንን እንቆቅልሽ የፈታው ይመስላል። በእለቱ ከሳሽ እና ተከሳሽ  በተገኙበት፤ ጉዳዩን በግልጽ ለመወያየት ተችሎ ነበር። ካሜራችን ሂደቱን በድምጽና ምስል ይዞታል። (ቪድዮውን ይመልከቱ Part 1)

የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን በአውሮፓ (ኢ.ስ.ካ.ፌ) ባለፈው ቅዳሜ፣ 14 ኦክቶበር 2017 አመታዊውን የቦርድ ስብሰባ  በአምስተርዳም ከተማ  አድርጎ ነበር። ከ 21 ክለቦች የተውጣጡ 45 አባላት የተሳተፉበት ይህ ስብሰባ አራት አጀንዳዎች ላይ የተወያየ ሲሆን፣ አንድ ቀን ከፈጀው ከዚህ ውይይት በኋላ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መርጧል። በ2018 እና 2019 አዘጋጅ ሃገሮችም ታውቀዋል። በዚህም መሰረት በ2018 ስቱትጋርት – በ 2019 ደግሞ ዙሪክ በክለብ ደረጃ ፌስቲቫሉን ከዘጋጁ በኋላ – የማዘጋጀቱን ሃላፊነት ፌዴሬሽኑ መልሶ ይወስዳል። ላለፉት ሁለት አመታት በሆላንድ እና በሮም በፌዴሬሽኑ ሃላፊነት የተካሄዱት ዝግጅቶች እንደተጠበቀው ውጤታማ ባለመሆናቸው ለመጭው ሁለት አመት የአዘጋጅነቱን ሃላፊነት አዘጋጅ ሃገር ክለቦች እንዲወስዱ ጉባኤው ወስኗል። የ2017ቱ የሮማ ዝግጅት ብዙ አወዛጋቢ ነገሮች ነበሩበት።

ከዝግጅቱ በኋላ የተወሰኑ ግለሰቦች የተሰራበትን ገንዘብ ይዘው መጥፋታቸው በስፋት ሲወራ መሰንበቱ ይታወሳል።  የፌዴሬሽኑ አመራር አባላት፣ ዮሃንስ መሰለ፣ ግርማ ሳህሌ፣ ከበደ ሃይሌ እና ኢብራሂም ገንዘቡ እንዴት እንደተወሰደ እና እነሱም ሊደርስ ከነበረው ችግር እንዴት እንዳመለጡ ተናግረዋል። በወቅቱ በዚያ ስፍራ የነበረው ጥሩ ያልሆነ ድባብ እና ወሬ የነበረው አማራጭ ስፍራውን ለቅቆ ማምለጥ እንደነበር ቢገልጹም፣ ያረፉበት ሆቴል ጭምር ያልታሰቡ ክስተቶችን ተጋፍጠዋል። ሆቴል የክፍላቸው በማስተር ቁልፍ  እንደበረበሩባቸውም ተናግረዋል።

የዝግጅቱ አስተባባሪ ከነበሩት ውስጥ አንድነት (ቀዮ) እና ፍራንሲስኮ በአምስተርዳም ተገኝተው በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል። የተባለውን ገንዘብ መውሰዱን ቀዮ ያመነ ሲሆን፣ ለዚህ ድርጊትም ምክንያት እንዳለው ይገልጻል።

ጉባኤው በአጀንዳው ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ በፌዴሬሽኑ እና በእነ ፍራንሲስኮ የቀረቡትን የፋይናንስ ዘገባ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ወስኗል። ከጣልያን ሮቤርቶ፣ ከሆላንድ ክንፉ አሰፋ እና ከኮለን ተስፋዬ ጉዳዩን መርምረው ለአጠቃላይ ጉባኤ እንዲያቀርቡ ተመርጠዋል።

ውድ ግዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ክህሎታቸውን እና ገንዘባቸውን በነጻ ሲያፈስሱ የቆዩ የአመራር አባላት ሃላፊነታቸውን በጨዋነት አስረክበዋል። እጅግ አስቸጋሪ ጉዞ እንደተጓዙ ግልጽ ቢሆንም ትእግስታቸው ግን የሚደነቅ ነበር። ጉባኤውም የቀድሞውን አመራር አባላት በከፍተኛ ምስጋና ካሰናበታቸው በኋላ 9 አባላት ያሉበት አዲስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መርጧል። አዲሶቹ የአመራር አባላት የሚከተሉት ናቸው።

  • አሳዬ ከኖርዌይ (ሊቀ መንበር)
  • ነቢዩ ሰቆጣው ከፍራንክፈርት
  • ተስፋዬ ከኮለን (ዋና ጸሃፊ)
  • ዳናኤል ከስዊዝ
  • አፈወርቅ አዘበርሊን
  • መስፍን  ከስቱትጋርት
  • ፋሲል ከካታንጋ – ለንደን
  • ሮቤርቶ ከሮማ
  • ቴዲ ከቤልጅየም
  • ብርሃኑ ክስዊድን (ገንዘብ ያዥ)

ቪድዮውን እዚህ ላይ ይመልከቱ

ክንፉ አሰፋ (ፎቶዎች በጸሃፊው የተላኩ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. ጎፋ says

    October 28, 2017 06:56 pm at 6:56 pm

    መቼ ይሆን እኛ ኢትዮጵያውያኖች በሃሳብ ተስማምተን ዓላማችንን የምናሳካው? አገር ቤት በወያኔ እናሳብባለን ውጭሳ በማን ሊሆን ይሆን? ብንተባበር። ወያኔ ክጥፌም አታልፍም ነበር።

    Reply
  2. cute-ehapa says

    November 8, 2017 01:51 am at 1:51 am

    These group of money grabbing ‘worrobelas’ don’t deserve to have their ‘meeting’ reported. Believe you me these are scums that are an embarrassment to diaspora. I know because I live in London!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule