
እንደመግቢያ
ፌደራሊዝም የመንግስት ኣወቃቀር ሰፊ የቆዳ ስፋትና ብዙ ህዝብ ላላቸው ኣገሮች፣ በዛ ያሉ የተለያየ ቋንቋና ባህል ያላቸው ቡድኖች ላላቸው ሃገሮች፣ ተመራጭ ኣስተዳደራዊ መዋቅር እንደሆነ እጅግ ብዙ ሰው በዓለም ላይ ይስማማል። ፌደራሊዝም የተመረጠበት ዋናው ምክንያት ስልጣን እና ፍትህ ከህዝቡ እንዳይርቅ ነው። እንዳይርቅ ስንል ከመልክዓ ምድርም ከወረፋም ኣንጻር ነው።
ትላልቅ የሆኑ ኣገሮች ስልጣንን ቢያማክሉ ዜጎች ለኣንዳንድ ጉዳዮች ስልጣን ወደተጠራቀመበት ለመሄድ ስለሚርቃቸው ብዙ ከሆኑ ደግሞ ሰልፉ ስለሚበዛ ወረፋው መጉላላትን ስለሚፈጥር ነው። ዜጎች ስልጣን ወርዶ ከፍተኛ የሆኑ ጉዳዮቻቸውን ሳይቀር በክልሎቻቸው እንዲታይላቸው መደረጉ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ፍትህንና ኣገልግሎትን ለማደል በጣም ይረዳል። ስልጣን ተማክሎ የመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ባለስልጣናት እንደ ቧንቧ ማስተላለፍ ብቻ ከሆነ ስራቸው መንግስትና ህዝብ ልብ ለልብ ከመራራቃቸውም በላይ በውሳኔና በእቅድ ላይ ተሳትፎኣቸው ዝቅተኛ ይሆናል ኣገልግሎት ኣሰጣጡም ብዙ ችግር ይገጥመዋል።
ሌላው ደግሞ የተለያየ ባህልና ቋንቋ ያላቸው ቡድኖች በተለያየ መልክዓ ምድር ለብቻ ለብቻ ሰፍረው ነገር ግን ደግሞኣንድ ኣገር መስርተው እየኖሩ ከሆነ እንዲሁ ባንድ በኩል ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ጠብቀው በኣንድ ሃገር ጥላ ስር እንዲኖሩ የሚረዳ መሆኑንም ሁሉም ይረዳል። ኢትዮጵያ ካላት የቆዳ ስፋትና ካላት የህዝብ ብዛት እንዲሁም ካላት የቡድኖች ብዛት ኣንጻር ፌደራሊዝም ተመራጭ ኣስተዳደር መሆኑን እጅግ ብዙ ሰው ያምናልና በዚህ ላይ ውይይት ኣስፈላጊ ኣይደለም። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply