ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ??
尔,看起来是一句话,不过 尔,看起来是一句话,不过 木目心人尔,看起来是一句话,不过又是一句看不大懂得话,其实,ማንኛውም መርህ አልባ ቡድናዊ ትስስር – አደገኛ ጉዳይ ነው—ሊወገዱ እንደሚገባ ወስኗል?
个把两个字拆开成的一句话,木目心,就是想,人尔,就是你,合起来就是想你!!最初出现在一个网友的个性签名上,他的签名原来是:木目心人尔好好的!就是写给他心爱的人的哦! 想,其实就是一个人在木木的时候,双目看着一处一动不动的,这时候要是从ta的眼睛看进去,会看到有一个人在ta 的心里,而那个人就是ta 心爱的人!这就是恋爱中人对想的最好解释,也是木目心人尔真正的含义!心人尔,看起来是一句话,不过又是一句看不大懂得话,其实,它是把 字拆开成的一句话,木目心,就是想,人尔,就是尔,看起来是一句话,不过,合起来就是想你!!最初出现在一个网友的个性签名上,他的签名原来是:木目心人尔እንዲፈጠር በማድረጉም የተሰማውን ከልብ የመነጨ ፀፀት ይገልፃል??
好的!就是写给他心爱尔,看起来是一句话,不过人的哦! 想,其实就是一个人在木木的时候,双目看着一处一动不动的,这时候መንገድ የመዝጋት፣ የዜጎችን በነፃ የመንቀሳቀስ መብት የማወክ — እንዲቆሙ ይደረጋል??
是从ta的眼睛看个性签名上,他的签名原来是:木目心人尔好好的!就是写给他心爱的人的哦! 想,其实就是一个人在木木的时候,双目看着一处一动不动的,这时候要是从ta的眼睛看进去,会看到有一个人在ta 的心里,而那个人就是ta 心爱的人!这就是恋爱中人对想的最好解释,也是木目心人尔真正的含义去,会看到有一个人在የመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ አካላት በአስቸጋሪ ሁኔታ ሰላማችንን ለማስከበር ለከፈሉት መስዋእትነት ?✈️?✈️a 的木目心人尔,看起来是一句话,不过又是一句看不大懂得话,其实,它是把两个字拆开成的一句话,木目心,就是想,人尔,就是你,合起来就是想你!!最初出现在一个网友的个性签名上,他的签名原来是:木目心人尔好好的!就是写给他心爱的人的哦! 想,其实就是一个人在木木的时候,双目看着一处一动不动的,这时候要是从ta的眼睛看进去,会看到有一个人在ta 的心里,而那个人就是ta 心爱的人!这就是恋爱中人对想的最好解释,也是木目心人尔真正的含义!,而那个人 ሃገራዊ አንድነትን ለማጠናከር — አቅጣጫ አስቀምጧል????????
是ta 心爱的人!这就是恋爱中人对想的最好解释,也是木目心人尔真正的含义! 木目心人尔,看起来是一句话,不过又是一句看不大懂得话,其实,它是把两个字拆开成的一句话,木目心,就是想,人尔,就是你,合起来就是想你!!最初出现在一个网友的个性ከሁሉም ተቃዋሚ ድርጅቶችና ከህዝቡ ጋር በመሆን ለመቅረፍ — ወስኗል
上,他的签名原来是:木目心人尔好好的!就是写给他心爱的人的哦! 想,其实就是一个人在木木的时候,双目看着一处一动不动的,这时候要是从ta的眼睛看የግልና የመንግሥት የሚዲያ ተቋማት አካሄዳቸውን የሚያስተካክሉበት ሁኔታ ለመፍጠር —ወስኗል
看到有一个人在ta 的心里,而那个人就是ta 心爱的人!
这就是恋爱中人对想的最好解释!
也是木目心人尔真正的含义!
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ! (ምንጭ: Azhar Kïa Abadir facebook)
Mulugeta Andargie says
ጎልጉሎች!!! ምናለ ቢቀር ቢቀር በእንግሊዝኛ ብታደርጉት??? እኛም እኮ ዴሞክራሲን ልናጣጥማት እንፈልጋለን።።
በለው! says
የኢሀአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች:
“ድርጅታችን ኢህአዴግ ላለፉት ፳፮ አመታት በእናንተ በመተማመንና ከእናንተ ጋር እጅ ለእጅ በመተሳሰር ለመብታችሁና ጥቅማችሁ መከበር የምትበቁባት አገር መገንባት ጀምረናል፡፡”ለሩብ ምእተ አመት በእድገትና የለውጥ ጎዳና እንድትገሰግስ ያደረገውን ጥረትና የተመዘገቡትን ህዝባዊ ድሎች ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ እንዲፈጠር በማድረጉም የተሰማውን ከልብ የመነጨ ፀፀት ይገልፃል፡፡አገራችን በአንድ በኩል በተከተልነው መሰረታዊና ትክክለኛ አቅጣጫ በተገኙ መልካም ውጤቶች እጅግ የሚያስጎመዥ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡
**********************************
ከታች የተገለፁት ችግሮችና በተራዘመ ትግል የተገነባችውን አገር ለአደጋ ማጋለጥ የጀመሩት ጉድለቶች በዋነኛነት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር በተለይም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ድክመቶች ናቸው፡፡በመሆኑም ለተፈፀመው ስህተትና ለደረሰው ጉዳት ከፍተኛ አመራሩ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
__________________________________________________________!
__ ህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያችን የግልና የቡድን መብቶችን በማስከበር የሰላምና የእድገት መሰረት እንደሆነ በእነዚሁ አመታት ተረጋግጧል፡፡ ብዝሃነት የኢትዮጵያችን መሰረትና መገለጫ እንደሆነ በመቀበል ይህንኑ በአግባቡ ለማስተዳደር ያደረግነው ጥረት አገራችን ዜጎች ለረጅም አመታት በፍቅርና መከባበር የሚኖሩባት የሰላም አገር እንደሆነች አስመስክሯል፡፡
__ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፉት አስራ ሰባት ቀናት ባደረገው ግምገማ በየደረጃው ባሉ የአመራር እርከኖች በተለይ ደግሞ በከፍተኛው አመራር ደረጃ የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ እጦት ስር እየሰደደ እንደመጣ አረጋግጧል፡፡
___በጠባብ ቡድናዊ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ መርህ አልባ ግንኙነት ኢህአዴግና አባል ድርጀቶቹን የማዳከም ውጤት አስከትሏል፡
___ በአንድ ወይም በሌላ ብሔር ህዝብና ድርጅት ስም እየማሉና እየተገዘቱ ጥገኛ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሚንቀሳቀሱ ወገኖችን እንቅስቃሴ…
___ ሥራ አስፈፃሚው በድርጅታችን የዴሞክራሲ መጥበብ እዛው በዛው የውሳኔዎችን በታማኝነትና በቁርጠኝነት የመፈፀም ዲሲፒሊንን እያላላ እንደመጣ አረጋግጧል፡፡
____ አመራራችን ዴሞክራሲውን የማስፋት ግዴታውን ባለመወጣቱ ችግሮችና ልዩነቶች በግጭት መንገድ የሚፈቱበት ሁኔታ እንዲፈጠር አስተዋፆ አድርጓል፡፡ ይህም ለሰላማችን መታወክ የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
___በክልሎችም ሆነ በክልሎች መካከል በልዩ ልዩ ሰበቦች የሚከሰተው የሰላም መደፍረስ ለዜጎቻችን አሳዛኝ ሞት መበራከትና መቁሰል እንዲሁም ከባድ መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ የንብረት ውድመትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መገታት አስከትሏል፡፡ ይህ ለረጅም አመታት በሰላም በኖረችው አገር ውስጥ የስጋት መንፈስና ጭንቀት ፈጥሯል፡፡
___ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በድርጅታችንና በመንግስት መሪነት ለ፳፮ አመታት የቀጠለ ቢሆንም ከቅርብ አመታት ወዲህ የአስተሳሰብ ብዝሃነት በአግባቡ እንዲገለፅ የሚያደርግ ተጨባጭ ሁኔታ እየተዳከመ መጥቷል፡፡
____ የሃገራችን ሚዲያና ፕሬስ በሚገባው ደረጃ ነፃነታቸው ተጠብቆ የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆነው ያገለግሉ ዘንድ የተደረገው እንቅስቃሴ የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በግምገማው ተመልክቷል፡፡
___በክልልም ይሁን በፌዴራል ያሉ የህዝብ የሚዲያ አውታሮች ሕግና ሥርዓትን ጠብቀው የማይሠሩበት ሁኔታ እያመዘነ የህዝቡን ሰላምና አብሮ የመኖር ገንቢ ባህል የሚሸረሽሩ ሰበካዎች የሚሰጥባቸው፣ ብሎም ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩ አጥፊ ቅስቀሳዎች የሚካሄድባቸው እየሆኑ ለመምጣታቸው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚም ሆነ የሚመራው መንግሥት ድክመት አስተዋፅኦ እንዳደረገ ይቀበላል፡፡
____አመራሩ ዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ በመገንባትና በህገ መንግስታዊ ስርዓታችን ዙሪያ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር እየተገባው የህዝብ የተደራጀ ሲቪል እንቅስቃሴ እንዳልተጠናከረ አረጋግጧል፡፡
____ ልክ እንደ ዴሞክራሲው ሁሉ በአገራችን የህልውና ጥያቄ የሆነውን መልካም አስተዳደርን የማስፈን እንቅስቃሴያችን በአመራር ድክመት ምክንያት ለበርካታ ችግሮች እንደተጋለጠ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡
__ በሙስናም ሆነ በሌሎች ጥፋቶች ውስጥ የተዘፈቁ ግለሰቦችን በወቅቱና ህጋዊና አስተማሪ በሆነ መንገድ መጠየቅ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ ዜጎች በህገ መንግስቱ ዋስትና ያገኙ መብቶቻቸውን የሚጥሱ ሰዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ መሆን በሚገባው ደረጃ ሳይፈፀም ቆይቷል፡፡ በዚህ የተነሳ ከፍተኛ የህዝብ ምሬት ተፈጥሯል፡፡
____ በህብረተሰባችን ዘንድ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን፣ ልማታዊ አስተሳሰብና፣ በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ ኢትዮጵያዊ አንድነት በማጠናከር ረገድ የተሰራው ስራ መሆን የሚችለውን ያህል ውጤት ሳያመጣ እንደቀረ ሥራ አስፈፃሚው ባደረገው ግምገማ ማረጋገጥ ችሏል፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
” የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች፣ ምሁራን፤ የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች፣ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የፀጥታና የህግ አስከባሪ አካላት፤ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ ድሎቻችንን ለማስፋት የተለመደ ድጋፋችሁና ወሳኝ እንቅስቃሴያችሁ እንዳይለየን፤ ባጠፋንበት እያረማችሁ፣ ባጎደልንበት እየሞላችሁ አገራችንን ተባብረን እንድንገነባ የኢህዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
(፩) ሕዝባችን ወደተረጋጋ ኑሮው እንዲመለስ ማድረግ ፡ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ፡የሚታዩ የህግ ጥሰቶችን በመቆጣጠር ህግና ሰላምን በአስተማማኝ ደረጃ ማስፈን፡የሕዝቡን የእለት ተለት እንቅስቃሴ የሚያስተጓጉሉ የቡድንም የተናጠልም እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ፡ ሞትና መፈናቀል ሙሉ በሙሉ ለማስቆም፡ወስኗል፡፡
(፪) እያንዳንዱ ብሔራዊ ድርጅት በከፍተኛ አመራር ደረጃ የሚታይበትን ድክመት በጥልቀት ገምግሞ በግልጽነትና በተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ የማስተካከያና የእርምት ርምጃ እንዲወስድ ወስኗል፡፡
(፫) አሁንም ቢሆን ወደ ሩብ የሚጠጋው ሕዝባችን ከድህነት ወለል በታች የሚገኝ መሆኑ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት፡በስርዓታችን ውስጥ ያለው ትልቁ የልማት አቅም በክልሎች የሚገኝ እንደሆነና ክልሎችን የሚያስተዳድሩ ብሄራዊ ድርጅቶች የየክልላቸውን የልማት አቅም አሟጠው የሚጠቀሙበትን ሁኔታ መፍጠር እንዳለባቸው ሥራ አስፈፃሚው በአጽንኦት አስምሮበታል፡፡
(፬) በፌደራልም በክልልም ያለው ሲቪል ሰርቪስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የአገልጋይነት መንፈስ የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲረባረብ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
(፭) ወጣቶቻችን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በሚገባ ለመመለስና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በልማት ሊኖራቸው የሚገባውን ተሣትፎ በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተከታታይ ሥራዎች እንዲሰሩ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
(፮) ምሁራንና የሲቪክ ማህበረሰቦች ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ተገቢ ሚናቸውን የሚጫወቱበት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ወስኗል፡፡
(፯) የህዝብን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በአስተማማኝ ደረጃ ለማስከበር ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ተጨማሪ ርምጃዎች እንዲወሰዱም አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
(፰) በክልልም ሆነ በፌዴራል ደረጃ ከፖለቲካዊ፣ ከሕጋዊ አሠራርና ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በራቀ መልኩ የሁከትና የግርግር መልእክት በህዝብ ሚዲያ የሚሰበክበትን እድል ለመዝጋት የሚያስችሉ የተቀናጁ እርምጃዎችን እንደሚወስድ በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል፡፡
“መጪው ዕሩብ ዘመን በኢህአዴግ አመራር ብቻ ብሩህ ነው!” የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
በለው! says
ከአማርኛው ይልቅ ቻይንኛው ትንታኔ ተሻለ ልበል?
ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ ማላገጫ!
——————————————–
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች:(ብሔር ብሔረሰቦችን አይመለከትም ማለት ይሆን?)
__ ሀገሪቱ ላይ በተፈጠረው ምስቅልቅል የሕዝብ መፈናቀል፡ ንብረት መውደምና የሰው ሕይወት መጥፋት፡ ሙሉ ሃላፊነትና ጥልቅ ኢህአዴጋዊ/ወያናይት ፀፀት ይሰማናል” ይልና… የመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ አካላት በአስቸጋሪ ሁኔታ ሰላማችንን ለማስከበር ለከፈሉት መስዋእትነት ምሥጋናወን ይገልጻል።
ያጠፋነውን ሥህተት ለማረም ማጥፋት ይቀጥላል…..
* ማንኛውም መርህ አልባ ቡድናዊ ትስስር – አደገኛ ጉዳይ ነው—ሊወገዱ እንደሚገባ ወስኗል
* መንገድ የመዝጋት፣ የዜጎችን በነፃ የመንቀሳቀስ መብት የማወክ — እንዲቆሙ ይደረጋል
*የግልና የመንግሥት የሚዲያ ተቋማት አካሄዳቸውን የሚያስተካክሉበት ሁኔታ ለመፍጠር —ወስኗል!
(አላየንም አልሰማንም በሉ!)
Lemma says
Min yemilut qeld new yenante degmo?