የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምፕዩተሬ ላይ “የስለላ ማልዌር ልኮብኝ ሲሰልለኝ ቆይቷል” ሲሉ ኪዳኔ ተብለው የተጠሩ አሜሪካዊ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ወረዳ ፍርድ ቤት ክሥ መሥርተው ጉዳዩ ትናንት ዳኛ ፊት ቀርቧል፡፡
የከሣሽና የተከሣሽ ጠበቆች ረዥም ክርክር አድርገዋል፡፡
የግለሰቦችን የግል ሕይወት ወይም ገመና መዳፈር፣ የስልክ ንግግሮቻቸውን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጥለፍ፣ ኢሜሎቻቸውን ማንበብ ከአግባብ ውጭ፤ እንዲያውም ሕገወጥ የሆነ አድራጎት ነው ተብሎ ይበየንልን ሲሉ የኪዳኔ ጠበቃ ኔት ካርዶዞ ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ጠበቃ አድራጎቱን ፈፅሟል የተባለው የውጭ ሉዓላዊ መንግሥት በመሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት ክሡን የማየት ሥልጣን የለውም ስለዚህም ችሎቱ ውድቅ ሊያደርገው ይገባል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሃኪንግቲም የሚባለው ጣልያን የሚገኝ የስለላ ማልዌር ሠሪ ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን አስታውቋል፡፡ (ርዕሱ በጎልጉል የተቀየረ)
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ በመጫን ያዳምጡ፡፡ (ምንጭ: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)
Leave a Reply