በኢትዮጵያም ሆነ በጥቁር አፍሪካ ኦሊምፒክ ታሪክ ሁለት ወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ደራርቱ ቱሉ ባለፈው ሳምንት ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀበለች፡፡
ከኦሊምፒክ በተጨማሪ በዓለም ሻምፒዮንም ሆነ በተለያዩ አህጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ቁንጮ በመሆን ታላቅነቷን ማስመስከሯ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ ለመጀመርያ ጊዜ በባርሲሎና ኦሊምፒክ (1984 ዓ.ም.) በ10,000 ሜትር ተወዳድራ የወርቅ ሜዳልያውን ያገኘችው የቅርብ ተፎካካሪዋንና የዓለም አቀፍ ውድድሮች ልምድ የነበራትን ደቡብ አፍሪካዊቷን ኤሌና ሜየርን በረዥም ርቀት ጥላት በማሸነፍ ነበር፡፡ ፎቶግራፉ ደራርቱ የክብር ዶክትሬቷን ከተቀበለች በኋላ ከዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ሐኔኮም (በግራ) እና ከዩኒቨርሲቲው ሬክተር ፕሮፌሰር ብሪያን አ ኮኔል ጋር ሆና ያሳያል፡፡ ሁለተኛው ፎቶ በባርሴሎና ኦሊምፒክ 10000 ሜትር ሩጫ ተከታትለው የገቡት ደራርቱ ቱሉና ኤሌና ሜየር ከድላቸው በኋላ ለተመልካቹ ደስታቸውን ሲገልጹ ያሳያል፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)
Asefa says
Thank you CU for honoring our beloved Derartu! Calm, confident, and strong Derartu is a roll model to what a great citizen should be in addition to what is obviously known for.