• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ከሞቱት ያልሞትነው!”

April 25, 2015 03:33 am by Editor Leave a Comment

” ….. የለቅሶና የብዙ ዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ ልጆችዋ ስለሞቱባት መጽናናት እምቢ አለች።….” /ማቴዎስ 2፡18/

ኮንፊሽየስ ወደ ጫካ በመሄድ ግዜውን ማሳለፍ ይወድ ነበር ይባላል። ከዕለታት እንድ ቀን እንደተለመደው ወደ አንድ፤ ከአካባቢው ‘ርቆ ወደሚገኝ ጫካ አመራ። ከሰዓታት ጉዞ በኋላ ጥቅጥቅ ባል ጫካ ውስጥ እንደደረሰ ለማርፍ ሲሞክር የገጠመው፤ የተለመደው የወፎች ዝማሬና የአበባወችና የዛፎች ውብ ማዕዛ ሳይሆን እጅግ አሳዛኝ ፣ የለቅሶና የሲቃ ድምጽ ነበር። ኮንፊሽየስ የሰማውን ማመን እያቃተው ወደዚያው አመራ፤ ወደ ድምጹ እየተጠጋ ሲሄድ፤ አንዲት ሴት ሳሩን እየነጨች መሬቱን እየቧጨረች የ ”ኤሎሄ” ዋይታ ታስተጋባለች። ራሱን ለመቆጣጠር እየሞከረ ቀስ እያለ ተጠጋት። ሊያጽናናትም ሞከረ። ግን የምትጽናና ሴት ሁና አላገኛትም። ይሁን እንጂ በዚህ ጫካ ውሰጥ ለምን እንደመጣችና የዋይተዋን ምክንያት እ‘ድትነግረው አግባባት። እሷም ከአንድ ልጇ ጋር ወደዚህ ጫካ ለመኖር እንደመጣችና ልጇ ግን በአውሬዎች እንደተበላባት ቋንቋ ሊገልጸው በማይችል ሀዘን ነገረችው። ‘’ አውሬዎች አንድ ልጀን ብሉት።”

ኮንፊሽየስም በመገረም ”ለምን ከተማ ውስጥ አትኖሩም ነበር? እንዴት ጫክ ወስጥ መኖር ትመርጣላችሁ?” በማለት ጠየቀ። ያገኘው መልስ ግን ” ጌታዬ ከተማ ያሉት አውሬዎች ከዚህ ጫካ ውስጥ ካሉት አውሬዎች ይብሳሉ፤ የከተማዎቹ አውሬዎች ባሌንና ታላቁን ልጅን በልተዋል፤ የቀረኝን አንድ ልጀን ለማትረፍ ነበር ወደዚህ ጫካ የመጣውት፤ ይኽው እሱንም አጣውት።” አለችው። እኛም ከወያኔ አውሬዎች የተርፉትን ወገኖቻችን በጫካ አውሬዎች አስበላናቸው፣ አሰየፍናቸው::

ግን እኛ ”ያልሞትነው” በህይወት ያለነው ምን እያደረግን ነው? አሁንም እንዳለፈ ሁሉ “መግለጫ እናወጣለን!….. ሻማ እናበራለን!……. ሰላማዊ ሰልፍ እንወጣና፣ ድርጊቱን እናወግዛለን!……. ወያኔ ወገኖቻችን ይታደግ እንላለን (ሃያ አራት ዓመት ሙሉ) ……ወያኔ ደግሞ ቆመጡን ያቀምሰናል፤ ጥይቱን ያጠጣናል፤ እስርቤት ያጉረናል፤ በባዕድ ሀገር እየሄድን እንድንታረድ፣ ከሳአውዲ እስከ የመን፣ ከደቡብ እፍሪካ እስከ ሊቢያ፣ ከሳህራ እስከ ካለሀሪ በርሃ ፣ ከኤደን እስከ ሜድትራኒያን ባህር ብሎም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ እስከ አለበት ድረስ ባህር፣ እሳት፣ በርሃና ሰይፍ እንዲበላን ያመቻቸናል።

የገዛ ሀገራችን ለወያኔ አውሬዎች አስረክበናልና፤ መንግስትና ሀገር እስከሌለን ድረስ በየትም ቦታ ብንሄድ የሚጠብቀን በባዕዳን አውሬዎች እጅ መውደቅና መታረድ ነው። ኮንፊሽየስ ጫካ ውስጥ እንዳገኛት እናት።

ከዚህ ላይ ከዚህ በፊት የጦመርኩትን በከፊል በድጋሜ ልጠቀም፤

”ዓለም የም‘ጠፋው፣ ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ምንም ሳያደርጉ ቀጭ ብለው በሚመለከቷቸው ሰዎች ነው።” /አልበርት አነስታየን/

እናም የምድርን የሰቆቃና የሞትን አይነት ሁሉ እያስከፈሉን፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን እያጠፉ ያሉት፣ እስላማዊ መንግስት ነኝ ባይ (አይሲኤል) ፣ ወያኔ፣ ሳአውዲ አረቢያ/ አረቦች፣ ምእራቡ ዓለም፣ ደቡብ አፍሪካ ወይም ሌላ ሳይሆን፣ እኛ እራሳችን ቁጭ ብለን የምንመለከተው ወይም ለታይታ የምንታይው፣ ኢትዮጵያዊያኖች ነን። እኛ ነን….. በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ተቀምጠን፤ ለወገኖቻችን መሆን ያልቻልነው። እኛ ነን….. ለጠባብ መንደርተኞች ሀገራችን አሳልፈን የሰጠን። ትላ’ትናም ይሁን ዛሬ እውነቱ ይኸው ነው። ይኸን እውነታ ተቀብለን፣ በተለይም በዚች ወቅት ለኅልውናችን ስንል የሚጠይቀውን መሰዋእትነት እስከ አልከፈልን ድረስ፣ ስቃይና ሰቆቃ፤ እንደ በግ መታረድ፣ እንደትላ’ቱና እንደዛሬው ሁሉ፣ ነገም ተባብሶ ይደገማል።

ባለፉት ዓመታት ከሀገርቤት ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እንደ ቅጠል የረገፉትንና የምድራችንን ስቃይ የከፈሉትን ለግዜውም ቢሆን ወደ ጎን ትተን፤ እስቲ ለደቂቃ የአይሲኤል ሰይፍ የበላቸውን ወግኖቻችን የመጨረሻ ሰዓት እናስበው? ሀዘን፣ …ለቅሶ፣ …. ምን ይበቃል? ዋይታችንን የሚገልጽ ቋንቋ በዚች ምድር ላይ ይኖር ይሆን? ኅሊናችን ምን ይለናል? ” ከሞቱት ላልሞትነው” ለኛ ለቀሪዎቹ ሸክሙ አይከብድም? ”ሰው ከንቱ ነውና……” እንደ ትላንትናዎቹ ወግኖቻችን ነገም እነዚህን እንረሳቸው ይሆን? በየትም ቦታና በማንኛውም ግዜና ሁኔታ ብንሆን ፣ በህይወት ላለን ዜጎች የማናመልጠው ነገር ፤ እነሱ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀናጅተው፤ የቤት ስራውን ለኛ ጥለውልን ሄደውል።

ሚያዚያ 2007

ኢ-ሜል: philiposmw@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Uncategorized Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule