• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የመሸገው “ወገን ለወገን” ቡድን አፍራሽ ተግባሩ ቀጥሎበታል

October 30, 2015 12:13 am by Editor Leave a Comment

በጅዳ ቆንስላ ጸ/ቤት የመሸገው “ወገን ለወገን” የተሰኘው ቡድን ጽ/ቤቱ ለሕዝብ መሥራት ከሚገባው ጉዳይ በመውጣት በግለሰቦች ማንነት እና ሃይማኖት ላይ ጽንፈኛ አቋም እየያዘ መምጣቱ ታወቀ፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት “በመልካም አስተዳደር ሽፋን” ዙሪያ ይካሄዳል ተብሎ የተጠራው አሁን ካለው የከረረ ሁኔታ አኳያ ግጭት ያስነሳል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡

በተለያዩ ሁኔታዎች ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት “በመልካም አስተዳደር” ዙሪያ ሰሞኑን በተደረገው ግምገማ ጥቂት የደቡብ ተወካይ ነን የሚሉ ግለሰቦች አማራውን በብሄር እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በሃይማኖት በመከፋፈል የከፈቱት የስም ማጥፋት ዘመቻ ጅዳ እና አካባቢዋን ስጋት ውስጥ ከቷል። በተለይ እራሱን “ወገን ለወገን” እያለ የሚጠራው በአቶ ሰመሩ እና ወ/ሮ ሙሉካ የሱፍ የሚመራው የቆንስላ ቡድን የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ በቆንስላው ተገልጋይ ላይ ሲፈፀም ለነበረው በደል እና መጉላላት በቀጥታ የአማራውን ብሄር ተወላጆች ተጠያቂ በማድረግ የጀመሩትን የስም ማጥፋት ዘመቻ በማጠናከር በአካባቢያችን የሚገኙ ታዋቂ የብሄሩ አባላትና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያላቸውን ጥላቻ በመግለጽ ግምገማውን ለሌላ አጀንዳ ማስፈፀሚያ መጠቀማቸውን የቆንስላው ምንጮች ይገልጻሉ።

ይህ ቆንስላ የመሸገው ቡድን በተገልጋዩ ችግሮች ዙሪያ ከመስራት ይልቅ ማህበረሰቡን መቋጫ ወደሌለው የእርስ በእስር ቅራኔና ግጭት ለመዝፈቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይናገራሉ። ቆንስላ ውስጥ የአንድ ብሄር አባል እና እምነት ተከታዮች ነጥሎ ለመምታት እየተደረገ ያለው ጥረት በአሁኑ ሰዓት ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ ላልተወሰን ጊዜ መራዘም እንደሚገባው የሚናገሩ እነዚህ ውስጥ አዋቂዎች በመልካም አስተዳደር ሽፋን በተጠራው ስብሰባ ላይ ሊደርስ ለሚችለው ግጭት የቆንስላው ሹማምንቶች ሃላፊነቱን መውሰድ እንደሚገባቸው ያሳስባሉ። ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ግለሰቦች የሚመራው ቡድን በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያቀነባበረውን ሴራ ከጀመረ አመታትን ቢያስቆጥርም፤ ሰሞኑንን ቆንስላ ውስጥ ቁልፍ ሃላፊነት ቦታ ላይ በተቀመጡ አንዳንድ ሹማምንቶች አይዟችሁ ባይነት በአዲስ መልክ ቡድኑ የጀመረው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እየደረሰ መምጣቱ ለማወቅ ተችሏል።

jedaቡድኑ እስከ ሪያድ በዘለቀው ፀረ ብሄርና ሃይማኖት ቅስቀሳው የ2008 አዲስ አመት ተከትሎ የአማራ ብሄር ተወላጆች ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ሊያከብር የነበረውን አውደ ዓመት አሳግዷል። የአማራን ብሄር ተወላጆችን ከመጠጥ እና ከሴስኝነት ጋር በማያያዝ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ያጠናከረው ይህ ቆንስላ የመሸገው ቡድን እየፈፀመ ባለው አስነዋሪ ተግባር በአካባቢው ማህበረሰብ የሁለቱም እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።

በቪዛ ነጋዴዎችና ደላሎች የሚደገፈው በአቶ ሰመሩ እና ወ/ሮ ሙሉካ የሱፍ የሚመራው ይህ ቡድን ቆንስላ ውስጥ በህዝባችን ላይ ለተፈፀመው በደል የቆንስላው ሹማንቶችን በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ሲገባው “በመልካም አስተዳደር” ሽፋን በጅዳ የአማራ ብሄር ተወላጅ እና የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነው የኢሚግሬሽን ኃላፊ ሹም በመወንጀል ቡድኑ ድብቅ አጀንዳውን ለማስፈፀም በመራወጥ ላይ ይገኛል።

ይህ በዚህ እንዳለ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን በጅዳ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ እና በኮንትራት ሰራተኞች ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እና በደል በመዘገብ የሚታወቀውን ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ጨምሮ በጅዳ እና አካባቢው የሚኖሩ የብሄሩ ተወላጅ የሃገር ሽማግሌዎችና ተዋቂ ሰዎች በዘር ሃረጋቸውና በሃይማኖታቸው ብቻ የዘመቻው ስለባ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ለጥቅምት 5፣ 2015 ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ አግባብ አይደለም የሚሉ ነዋሪዎች ጥሪው በጅዳ እና አካባቢ የተፈጠረውን ውጥረት የሚያባብስ ከመሆኑም በላይ ጥቂቶች የብዙሃኑን ፍቅር ለማግኘት “የቀይ ሽብር ወንጀለኞች የማጋለጥ ድራማ” የሚለይ ባለመሆኑ ከስብሰባው በፊት በኃይማኖት እና በብሄር ጥላቻ የተዘፈቀው ቡድን ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እና ከቆንስላው መታገድ እንዳለበት ይስማሙበታል። (ዘገባውን ከምስል ጋር ለጎልጉል የላኩት Ethiopian Hagere Jed Bewadi ናቸው፡፡)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule