• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለዘብተኞችን ማጥቃት፤ አክራሪዎችን ማብዛት

October 3, 2016 07:54 am by Editor Leave a Comment

የሃሳብ ልዩነት፤ ያለ ነገር ብቻ ሳይሆን፤ አስፈላጊም ነው። የተለያዩ ሃሳቦች መከሰት፤ አማራጮችን በመድረክ ላይ በማቅረብ፤ ልዩነቶችን እንድንመረምርና፤ በብዙኀኑ ዓይን የተሻለ የተባለውን እንድንመርጥ ዕድል ይፈጥርልናል። በነዚህ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስቶ ርስ በርስ መወነጃጀሉ፤ አንድም እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይነት ብሎም ራስን የማግዘፍ ጥንውት ነው። ሌላም ትግሉ መልክ ይዞ ወደፊት እንዳይሄድ እንቅፋት ለመሆን የተጠነሰሰ ሴራ ነው።

አክራሪዎች መኖራቸውንና የትግላችን አንዱ ገፅታ መሆኑን መቀበል አለብን። ይህ በቀኝ ይሁን በግራ፣ በፊት ይሁን በኋላ፣ ፈለግነውም ጠላነውም፤ ያለ ሀቅ ነው። ይህ የትግል አቅጣጫችን ሊቀይር ቀርቶ፤ ትኩረታችን ሊስብ አይገባውም። የሀገራችን የፖለቲካ እውነታ፤ ያደግንበትም ሆነ አሁን ያለው ተጨባጭ ሀቅ፤ መፈናፈኛ በማሣጣቱ፤ አክራሪዎች መፈጠራቸው፤ ሁኔታው የወለደው ክስተት ነው። እናም አክራሪ የምንላቸውን ለማጥቃት ወይንም ለማጥፋት ዓይኖቻችንን ከዋናው ግባችን መንቀል፤ ለራሳችን ጥቃት በሩን ለጠላት በርግደን መክፈታችን ነው። ትኩረታችን መሆን ያለበት ሰፊው ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት የሚሆንበትን በመፈለግና ያን በመቀበል ላይ ነው። ብዙኀኑ የተቀበሉት ለስኬት እንዲበቃ፤ ጥረታችንን በሙሉ በዚያ ላይ ማረባረብ አለብን። በግራና በቀኝ ተፋሰሶች እያበጀን፤ ጉልበታችንን እኛው ራሳችን አናዳክም።

“አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው!” ብለው ቀደምቶቻችን ሲያስተምሩን፤ አሾክሿኪው የጠላት አንድ አካል መሆኑን፤ እነሱም ሆኑ ራሱ አሾክሿኪው ስለሚያምኑበትና ስለሚቀበሉት ነው። በተጨማሪም፤ እጅ ከፍንጅ መረጃው ስለተያዘ ነው። እኛ የያዝነው ግን፤ “እኔ የምለውን ያልተቀበለ፤ ‘ወያኔ’ ነው!” የሚል ጠባብ፣ ራስ ተኮር፣ እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ ባይነትና ከሀገር በላይ ግለሰብን ወይንም የራስ ድርጅትን የሚያስቀምጥ አባዜ ነው።

ባሁኗ ሰዓት፤ በፖለቲካ ትግሉ መስክ፤ ባንድ በኩል የሀገር አንድነትን ፈላጊዎች፤ “ሀገር አቀፍ ትግል እንጂ ሌላ ምን ሲባል!” የሚል ምሽግ ሠርተናል። በሌላ በኩል ደግሞ በሀገር ውስጥ ባለው የፖለቲካ እውነታ በመመርኮዝ፤ “የለም፤ የአማራ ወጣቶችና የኦሮሞ ወጣቶች የትግሉን የበላይነት ጨብጠውታል። እናም ያን ሀቅ ተቀብለን፤ እኒህ ክፍሎች የሚቀራረቡበትንና የሚተባበሩበትን በመፈለግ፤ የወደፊቷን ኢትዮጵያ እንመሠርታታለን!” ባዮች አንድ ምሽግ ሠርተናል። ለኒህ ሁለቱ የትግል መስመሮች ጠላታችንም ግባችንም አንድ ነው። መንገዳችን ግን የተለያየ ነው። በርግጥ የትኛው የተሻለ ይሆናል የሚለውን፤ ሁለቱ ክፍሎች ቀርበን ለመነጋገር፤ አሁን ትልቅ ችግር ላይ ነን። የዜሮ ድምር ፖለቲከኞች፤ “ሌላው መታሰብ እንኳን የሌለበት ነው!” የሚል አቋም ያራምዳሉ። እንዲያውም ሁለቱም ክፍሎች በየጎራችን ጎድበን፤ አንዳችን ሌላችንን፤ ከወራሪው ፀረ-ኢትዮጵያ የትግሬዎች ቡድን የበለጠ ጠላት አድርገን በመፈረጅ፤ ለመጠፋፋት ተነስተናል።

እንግዲህ ሀቁ እንዲህ ነው። አስታራቂ ሽማግሌ ከየትም አይመጣም። እውነት የሕዝቡን ድል ፈላጊዎች ከሆን፤ ከባህላዊ ዘፈናችን አንድ ስንኝ ልዋስና፤ አስታራቂም የለን፤ እኛው እንታረቅ። የርስ በርሳችን መወነጃጀልና ጉልበታችን ለዚሁ ማጥፋት ማንን እንደሚረዳ፤ እኔ ለናንተ አልነግርም። አስቸጋሪ የሆነው ደግሞ፤ ይህ የታጋዮች በሁለት ጎራ መመሸግ፤ እየተከሰተ ያለው በቀጥታ ሳይሆን፤ በተዘዋዋሪና ትግሉን በቀጥታ በሚጎዳ መልክ ነው። መድረካችን በሳል የትግል ነጥቦችን በርጋታ የምንነጋገርበት ሕዝባዊ ስብስብ ሳይሆን፤ ፓልቶክና ፌስቡክ፣ ቲውተርና የየግል የሬዲዮ ስርጭት መሰምሮች ሆኗል።በመጀመሪያ ደረጃ፤ የፖለቲካ ልዩነት መግለጫና መነታረኪያ ባህላችን፤ ስድብ ማሽጎድጎድ ሆኗል። ብዙ በመሳደብ፤ የአቸናፊነት ሽልማት ለመቀበል መስገብገብ ይታያል። “ወያኔ!” ብሎ አንዱ ሌላውን አስቀድሞ ስለወነጀለ፤ ወንጃዩ የሕዝብ ወገን፤ ታርጋው የተለጠፈበት ደግሞ የጠላት ወገን የሆነ ይመስለዋል። አጉል ቅዠት ነው። ስድብ ስለ ቆሸሸውን የሰዳቢ አፍ ይናገራል እንጂ፤ የተሰዳቢውን ማንነት አይገልጽም። ይህ መጥፎ ባህል ነው። ይቅርብን።

አንዱ የመነጋገርያ ነጥብ የአማራውን መደራጀት የሚመለከት ነው። አማራው መደራጀት አለበት ብለው ያመኑና በዚሁ እምነታቸው የገፉ አሉ። ባለፉት ሃይ አምስት ዓመታትና አሁንም በአማራው ላይ እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጽዳት ወንጀል በመንተራስና፤ የትግሬዎችን ቡድን የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ መረጃ በመያዝ፤ አማራው በሕልውና እንዲኖር፤ ተደራጅቶ መታገል አለበት! የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አማራው መደራጀት የለበትም በማለት፤ “ትግሉ መካሄድ ያለበት በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!” የሚለውን ሃሳብ ሙጥኝ ብለው የተጣበቁ አሉ። በጄ! ይህን በተለያየ መልኩ ማየት ይቻላል። ነገር ግን፤ አንዱ ወገን የሌላውን ወገን ከመስማት ይልቅ፤ በራስ ጭንቅላት የፈጠሩትን ደጋፊ ወይንም ነቃፊ ነጥብ በማብጠልጠል፤ ከራስ ጋር ሙግት የተያዘበት ሀቅ ነግሷል። የሌላውን ነጥብ ማዳመጡ ቦታ አልተሠጠውም። አማራው ያለበት የዘር ማጽዳት አውነታ ለመቀየር፤ ማንኛውንም በማድረግ ሕልውናውን መጠበቅ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋል። ይህን እረዳለሁ ብሎ የተነሳን ደግሞ፤ ማንም ቢሆን ማን ሊያቆመው፣ ሊከለክለው ወይንም ሊቃወመው አይገባም። መቃወም ማለት በአማራው ላይ መዝመት ማለት ነው። ለዚህ ክፍል፤ ኢትዮጵያን ከማስብ በፊት፤ አማራው መዳን አለበት። ይህ አከራካሪ የመሆኑን አጥር ዘሏል። ስለዚህ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መሄዱ አስፈላጊ አይደለም። ይልቁንስ ለመረዳት መጣሩ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እንዴት ትድናለች የሚለው ጥያቄ ያንገበገባቸው ሰዎች፤ ታጋዮችንና በሀገሪቱ ያለውን ሀቅ፤ የምርምራቸው መነሻ ማድረግ ይገባቸዋል።

ሁለተኛው መነጋገሪያ ነጥብ፤ ኢሳትን የተመለከተ ነው። ኢሳት የራሱ ግብ ያለው የግል ተቋም ነው። ባለቤት አለው። ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት አይደለም። ውሎ አድሮ ለንግድ የተዘጋጀ ተቋም ነው። ስለዚህ ባለቤቱ የሚያዝበት እንጂ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያዝበት ተቋም አይደለም። ይህን ማለት፤ ኢሳት መጥፎ ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን፤ ማንም ተነስቶ ይሄን ካላደረገ ወይንም ያንን ከላደረገ የሚልበት አለመሆኑን ለማስጨበጥ ነው። ማንም ግለሰብ ይህን የግል ተቋም፤ በግሉ ሊረዳ ይችላል። ማንም ግለስብ ደግሞ፤ በግሉ ይሄን የግል ተቋም ላይረዳ ይችላል። ነገር ግን ማንም ግለሰብ፤ ከባለቤቱ በስተቀር፤ ሊያዝበት አይችልም። ይህ መታወቅ አለበት። እናም ይሄን ይዘን፤ የግሉን ተቋም ለምን ይሄን አላደረገም ብሎ መወንጀል፤ ተገቢ አይደለም። ይህ በታጋዮች መካከል ለመጣላት ምክንያት ሊሆን አይገባውም። የኢትዮጵያዊያን ንብረት ቢሆን ኖሮ፤ ለምን እንዲህ ወይንም ለምን እንዲያ አላደረገም ብለን መናገር መብታችን ይሆን ነበር። አሁን ግን መብታችን አይደለም። ከወደድን እንደግፈው፤ ካልወደድንም ደግሞ እንተወው። በቃ።

ሶስተኛው መነጋገሪያ ነጥብ ደግሞ ትግሬዎችን የተመለከተ ነው። ባሁኑ ሰዓት፤ በሀገራችን ላለው የግፍና የስቃይ ውርጅብኝ፤ ተጠያቂው ወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ይህ ወራሪ ቡድን፤ በምንም መንገድ ይሁን በምንም፤ ትግሬዎችን ወክያለሁ ብሎ፤ በኢትዮጵያዊያን ላይ ግራና ቀኝ ጥፋት፤ በተለይም ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየፈጸመ ነው። ይህን የሚፈጽመው፤ በአብዛኛው ትግሬዎችን በመሣሪያነት ይዞ ነው። በርግጥ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሆኑ አንዳንድ ሆድ አደሮች፤ በግለሰብ ደረጃ፤ በባንዳነት እየረዱት ናቸው። እኒህ ሆድ አደሮች ይሄንን በሚያደርጉበት ሰዓት፤ ሕልውናቸውን ሸጠው፤ የዚሁ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካልና አምሳል ሆነው ነው። እናም እነሱ ትግሬዎችም ባይሆኑ፤ የዚህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን አካል ናቸው። ስለዚህ ይህን ቡድን በምንም መልኩ ብናየው የትግሬዎች ቡድን ነው። አማራውን ለማጥፋት የተነሳው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ስብስብ ነው። ኦሮሞዎችን እየገደለ ያለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። አኝዋኮቹን የጨፈጨፈው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። ኦጋዴኖቹን የበደለው ይህ የወራሪው የትግሬዎች ቡድን ነው። እና ገና ለገና ትግሬዎች ይበደሉ ይሆናል በማለት፤ በውጪ ሀገር ያሉ “ታጋይ ነን!” ባይ ትግሬዎች፤ ጥብቅና ከትግሬው ቡድን ጋር አብረው ተሰልፈዋል። አልሸሹም ዞር አሉ ነው። ጠላት የማብዛትና የማሳነስ ስልት አይደለም። አሁንም፤ ዛሬ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየተፈጸመበት ላለው አማራና ዛሬ ለሚያልቀው የኦሮሞ ወጣት ከመቆም ይልቅ፤ ገና ለገና በትግሬዎች ንብረት ላይ ጉዳት ይደርስ ይሆናል ብሎ የሚጮኽ፤ በምንም መለኪያ ቢታይ፤ የወራሪው የትግሬዎች አጥፊ ቡድን አካል እንጂ፤ የሕዝብ ወገን አይደለም። ጠላቱንና የትግል መስመሩን ለይቶ ያልተነሳ ታጋይ፤ የያዘውን ትግል አያውቀውም፤ ድሉም ምን እንደሆነ ስለማያወቅ፤ ለድል አይበቃም።

የያዝነው የምኞትና የፍላጎት ትግል አይደለም። በቦታው ያለውን ሀቅ ተቀብሎ፤ ያን ለማስተካከል የሚደረግ ትግል ነው። ወራሪው የትግሬዎች ፀረ-ኢትዮጵያዊያን ቡድን የሚታረቅ፤ የሚሻሻል፤ የሚታረም አይደለም። መሠረታዊ እምነቱ ኢትዮጵያዊነት አይደለምና! ከዚህ ቡድን ጋር እርቅ ለማድረግ የሚፈልጉና “ብዙ ሰው እንዳያልቅ!” እያሉ የሚያላዝኑ ሰዎች፤ ጎራቸው ከዚሁ ወራሪ ቡድን ጋር ይቀራረባል። ይህ ወራሪ ቡድን፤ ከትግራይ ውጪ ለሚያልቀው ወገን ደንታ የለውም። እየገፋበትም ነው። ይህን ቡድን በምንም መልኩ ለማዳን መሞከር፤ የዚሁ ቡድን ደጋፊነት ነው። አጥሩ ግልጽ ነው። ይልቅስ በታጋዩ ወገን ያለውን እናስተካክል። ለወራሪው ቡድን አሳቢዎች ብዙ አሉ። እኛ ለሱ መጨነቁን እንተወው። በአንድነት መታገሉን እስከወደድን ድረስ፤ ወደ አንድነት የሚወስደውን መንገድ እንከተል። በታጋዩ ጎራ ያለን ሁሉ፤ ወደ አንድ ለመምጣት ያለው በር አንድ ነው። ተቀራርቦ መነጋገር። እንዴት ወይንም መቼ ወይንም የት የሚለው፤ በሁለተኛ ደረጃ የሚከተል ነው። መጀመሪያ የአንድነቱን አስፈላጊነት መቀበል ነው። ይሄን ደግሞ ያልለፈለፈለት የለም። ታዲያ ቀጥሎ መገናኘት ነው። ለዚህ ጠሪው ብዙ አድማጩ ዜሮ ለሆነበት ትንግርት፤ እግሬን አስቀድሜ አነሳለሁ። እናም ውይይቱ ትናንት መሆን ቢኖርበትም፤ ትግሉ እየተካሄደም፤ ዛሬ ይቀጥል።

አንዱዓለም ተፈራ  – የእስከመቼ አዘጋጅ
ሰኞ፤ መስከረም ፳ ፫ ቀን ፳ ፻ ፱ ዓመተ ምህረት


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule