• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከዝምታው በስተጀርባ

September 5, 2015 09:15 am by Editor Leave a Comment

አንዳንድ ወገኖች የወያኔ አገዛዝ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ያለበት ደረጃ መድረሱ እያበገናቸው፣ በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ጥፋት እያስቆጫቸው የሕዝቡን ዝምታ በፍርሀት ሲገልጹት ይሰማል፡፡ አንዳንዶች እንደውም ገፋ አድርገው በቅርብ ግዜ የታየውን የአረብ አብዮት እየናሱና ተኒዚያና ግብጽን እየጠቀሱ ኢትጵያዊ በምን ያንሳል በማለት በምሬት ይናገራሉ ይጽፋሉ፡፡

የአረብ አብዮት አይነት ሰላማዊ የሕዝብ ተቃውሞና አምቢተኝነት ወያኔ አጥብቆ የሚፈራው፣ ተቀዋሚው ቢሆን የሚሻው፣ የኢትዮጵ ሕዝብ ሊያደርገው የማይችለው ነው፡፡ ሁሉም የየራሳቸው ምክንያት አላቸው፡፡ ወያኔ በሕዝብ አለመወደዱን ማወቁ፣ ለሥልጣኑ መስጋቱና ፍርሀቱ ሲሆን ፤ተቀዋሚው ለውጥ መሻቱ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መናፈቁ ነው፡፡ ሕዝቡ የማያደርገው ደግሞ ከጥንት እስከ ዛሬ የኖረበት ወግ ልማዱ ስላልሆነ፣ ትናንት ንጉሶች በቅርቡ ደግሞ አብዮተኞች ሥልጣን ሲነጣጠቁ ያየው በጠብ-መንጃ እንጂ በሰልፍ ስላልሆነ፣ በውርስ የተቀበለውም ሆነ በልማድ ያዳበረው ባለመሆኑ ነው፡፡

እናም አደባባይ አለመውጣቱ ሆ ብሎ ለአመጽ አለመነሳቱ ፈጽሞ ፍርሀት አይደለም፡፡ የዝምታውን ምንነትና እንዴትነት መረዳት፣ ከዝምታው በስተጀርባ ያለውን ድምጽ መስማት አለመቻል እንጂ ከሕዝቡ ዝምታ በስተጀርባ ታላቅ የሆነ ድምጽ አለ፡፡ ይህን የተረዱት እምየ ምንይልክ ናቸው፡፡ መንግሥታቸው የግብር ጭማሪ አድርጎ ባለሙሎቻቸውን ህዝቡ ምን አለ በማለት ይጠይቃሉ፣ደስተኛ አይደለም እያጉረመረመ ነው ይሉዋቸዋል፣ ቆይት ብሎ ደግሞ ሌላ የግብር ጭማሪ ይደረግና ህዝቡ ምን አለ ብለው ይጠይቃሉ እያማረረ እያጉረመረመ ነው ይሉዋቸዋል፤ ለሶስተኛ ግዜ ጭማሪ ተደርጎ ህዝቡ ምን አለ በማለት ሲጠይቁ አሁንስ ለምዶታል ምንም አላለ ሲሉዋቸው ይህኔ ነው መፍራት ማለታቸው እየተነገረ ከእኛ ደርሷል፡፡ አዎ ምንይልክ ከህዝብ ዝምታ ጀርባ ያለን ታላቅ ድምጽ ለማዳመጥ የቻሉ መሪ ስለነበሩ ነው ህዝቡ   እምየ ያላቸው፡፡

ከምርጫ 97 በኋላ ድምጻቸውም ብዕራቸውም የጠፋው ፕ/ር መድህኔ ታደሰ በ1996 ዓም መጨረሻ አካባቢ ከጦቢያ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የኢትዮጵውያንን ዝምታ ምንነትና አንዴትነት አንዲህ በማለት ነበር የገለጹት፡፡ “የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁ በአጉራ ዘለልነት በአመጽና ቁጣ ገንፍሎ ወደ አደባባይ የሚወጣ አይደለም በታሪኩ ካየነው ማለት ነው፡፡ የውጪ ወራሪን ለመመከት ይሰለፋል አንድ ጉዳይ ነው፡፡ በውስጥ ፖለቲካ ተሳትፎ ግን ከታሪኩና ከንቃተ ህሊና ጋር ብዙ ነገር ስለሚወስነው ይህን ያህል አይደለም፡፡ አንድ ኪሎ ግራም ስኳር ስለጨመረ ነው የሱዳን ሕዝብ መንግሥት የሚገለብጠው፡፡ የኛ ግን የተለየ ነው፡፡” ያሉት ፕ/ር መድህኔ የህዝቡ ዝምታ ወያኔ አንደሚለው አገዛዙ ተስማምቶት፣ ኑሮም ተመቸትቶ አንዳልሆነ ሌላው ወገን እንደሚለውም በፍርሀት ቆፈን ተይዞ አለመሆኑን ሲገልጹ “አንድ መታወቅ ያለበት ነገር አለ፡፡ ይሄ ሕዝብ የሚያስተዳድረውን መንግሥት በመቃወም፣ በመጋፈጥ ላይታወቅ ይችላል፡፡ ተስፋ ከቆረጠ ግን አልምጥ ነው፡፡ ስለዚህ ሕዝቡ አንድ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ መመለሻ የለውም፡፡ ለተቃውሞ ተሰልፎ ባታየውም ባለመሰለፉ ጭምር ብዙ መንግሥታት ወደ መጡበት ሄደዋል፡፡ ሕዝቡ ዝም ይላል ግን ዝምታው መታሰብ ያለበት ይመስለኛል”፡፡

በምርጫ 2002 ወያኔ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ ባለ ማግስት ፕ/ር መስፍን ወልማሪያም ሥልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቁት መጽኃፍ የኢትዮጵያውያንን ውሳኔ እንዲህ ነበር የገለጹት፡፡ “የኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላለፈው መልእክት ሁለቱንም ገዥውንም ሆነ ተቀናቃኙን አንገት የሚያስደፋና የሚያሳፍር ነው፡፡ ተሰብስቦ ሳይመካከር ሳይወያይና ሳይከራከር ተግባብቶና ተስማምቶ አንድ አይነት መልእክት ማስተላለፉ በአንድ በኩል የሰለጠነ ሕዝብ መሆኑን የሚገልጽበት ሰላማዊ የሰላማዊ ትግሉ መንገድ ነው፤ በአንድ በኩል ደግሞ አማራጭ አንዳልቀረበለት ማሳየቱ ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱንም አንደ አማራጭ የቀረቡለትን አንደማይፈልጋቸው በሚያውቀው የሰምና ወርቅ ዘዴው አረጋገጠላቸው፤ ያሸነፈም አለሰሸነፈ የተሸነፈም አልተሸነፈ፣ ያሸነፈም አፈረ የተሸነፈም አፈረ፣ሁለቱም የሀፍረት ማቃቸውን ለብሰው ድሉ የኔ ነው የኔ ነው እያሉ ሲጓተቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኩታውን አፍንጫው ላይ ጣል አድርጎ ይታዘባል፣ ቂል ያደረጉትን ፖለቲከኞች ነን ባዮች ቂልነት፣ አላዋቂ ያደረጉትን አላዋቂነት አንደ ዕቃ የቆጠሩትን ሰዎች እቃነት እያሰበ ጥርሱን ሳያሳይ ይስቃል፣አይ ሥልጣን! ስንት ጉድ አሳየን! እያለ ይታዘባል፡፡” (ገጽ 124)

ለነጻነት የሚደረገው ትግል አደረጃጀቱና ስልቱ የቱም ይሁን የቱ ይህን የህዝብ ሥነ ልቦና የተገነዘበና ተስማሚ መንገድ የተከተለ ከሆነ ብቻ ነው ለውጤት የሚበቃው፡፡

ወያኔ በየግዜው ከንፈርነስ ስብሰባ ግገማ እያለ የህዝብን ልብ ለማወቅ ሥነ ልቦናውን ለመረዳት ጥሯል፡፡ በተለይ በምርጫ 97 ማግስት ሕዝቡን እየሰበሰበ (በተለይ አዲስ አበባ) ምን በደልናችሁ በማለት ለመለማመጥም ለመጠጋጋትም ሞክሯል፡፡ ነገር ግን በሁለት ምክንያት ውጤታማ አልሆነም፡፡ አንድ ህዝቡ ወያኔን አምኖ የልቡን መሻት ባለመናገሩ፤ ሁለት ወያኔ የደደቢት ህልሙን እንጂ የህዝብን ፍላጎት የማዳመጥና መሻቱን እውን የማድረግ ተፈጥሮ የሌለው በመሆኑ፡፡

“እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን” የሚለውን ብሂል እየተናገረ ዝምታን የሚመርጠው ህዝብ ፕ/ር መድህኔ እንደገለጹት በዝምታው መሸኘትን ያውቅበታል፡፡ እያሞገሰ መጣልን፣ አለእናንተ እያለ ማ አለና እያለ የደገፈ መስሎ ሲጥልም አይተናል፡፡ይህን ስነ ልቦናውን የሚያውቅለት ግን እስካሁን አላገኘም፡፡ የመጣው ሁሉ እሱ በሚሻው ሳይሆን እነርሱ በሚሉት ሊገዙት ይዳዳቸዋል፡፡ የግዞት ዘመናቸው ይጠርም ይብዛ አንጂ ኋላ ግን በቅሌት ያወርዳቸዋል፤ ከህዝብ ፍላጎት በታቃራኒ የሚነጉዱ አገዛዛቸውን ማስተካከል ቀርቶ አወራረዳቸውን ማሳመር አይችሉም፡፡ ወያኔ በ1997 ምርጫ ሥልጣን ማስረከብ ቢችል ኖሮ በጫካም ሆነ በቤተ መንግሥት ቆይታው የፈጸመው እኩይ ድርጊት ሁሉ በተሰረየለት ነበር፡፡

የህዝቡ ሥነ ልቦና በሀገር ደረጃም አንድ ሊሆን እንደማይችል ማወቅም ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ቦታ በዞንም ደረጃ የተለያየ የሚሆንበት አለ፡፡ ይህን ማወቅ ተስማሚ ስልት ለመንደፍ ጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ ረገድ አንድ ተጨባጭ ማስረጃ ላቅርብና ልሰናበት፡፡

በምርጫ 97 የምሥራቅ ጎጃም አርሶ አደር ግንቦት ሰባትን(የድምጽ መስጫውን እለት)ምን ያስጠብቀናል፣ እኛ የወያኔ አገዛዝ በቃ ብለናል፤አሁኑን እንገላገል ወዘተ በማለት ምሬቱን ለውጥ መሻቱን በአደባባይ ካድሬው ባለሥልጣኑ ሁሉ ባለበት ይናገር ነበር፡፡ በአንጻሩ የምዕራብ ጎጃም ሰው በየግልም ሆነ በስብሰባ ለካድሬውና ለባለሥልጣናቱ አሁን ከእናነተ ሌላ ምን የሚመረጥ አለ ብላችሁ ነው የምትደክሙ፣ በማለት ሲያረጋጋቸውና እነርሱን እንደሚመርጥ ሲያረጋግጥላቸው ሰነበተ፡፡ በመጨረሻ ግን ከምስራቅ ጎጃም ከማርቆስ ከተማ ብቻ የቅንጅት ዕጩ ሲያሸንፍ በሙሉ ወያኔ ወሰደው፤ ምእራብ ጎጃም ደግሞ አንድ ወ/ሮ ሽታየ (የዕድሜ ልክ ምክትል አፈ ጉባኤ) ስታሸንፍ ሌላውን በመሉ የቅንጅት ዕጩዎች አሸነፉ፡፡ ይህ እንዴት ለምንና በምን ምክንያት ሊሆን አንደቻለ ጠለቅ ብሎ ማጤን የህዝቡን ሥነ ልቦና በማወቅ ትግሉን በድል ለማጠናቀቅም ሆነ ከድል በኋላ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለመመስረትና የህዝብን መሻት እውን የሚያደርግ አስተዳደር ለመመስረት ወሳኝ ይመስለኛል፡፡

አዎ ሊያዳምጠው ለቻለ ከህዝቡ ዝምታ በስተጀርባ ፍርሀት ሳይሆን ታላቅ መልእክት ያለው ድምጽ አለ፡፡

ይገረም አለሙ

abutam2006@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule