የሚድሮክ ኢትዮጵያ የበላይ አመራሮች አባዱላ ገመዳን ለማነጋገር ቀጠሮ አስይዘው የተወሰኑ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀው እንደነበር የጎልጉል ምንጮች አስታወቁ። በኦሮሚያ የሚገኙ የሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ንብረት የተባሉ ድርጅቶች ላይ የተደረጉ የሂሳብ ምርመራዎችና ግብር ታሪፍ የተሰራባቸው ሰነዶች ዝርፊያ ምርመራ ተድበስብሶ እንዲታፈን መደረጉ እስካሁን ምላሽ ያላገኘ ጉዳይ እንደሆነ ተጠቆመ። አባዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት ሚድሮክ የሰየማቸውና በዶ/ር አረጋ የሚመራ ልዑክ ቢሯቸው የተገኘው በወቅቱ የሼክ መሀመድ ድርጅቶች ላይ ክልሉ ግብር እንዲከፍሉ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነበር። የክልሉ ካቢኔ ግብር መክፈል የሚገባቸው ባለሃብቶች በሙሉ ሊከፍሉ የሚገባቸውን ውዝፍ እዳ ገቢ እንዲያደርጉ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ክልሉ ውስጥ … [Read more...] about የሚድሮክ ልዑክ ለአባዱላ ያቀረቡት ጥያቄ
በደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር
አንድ ምራቅ መዋጥ የጀመረ የ28 ዓመት ወጣት የኑሮ አጉራ ቢጠናው ጊዜ ወደ ጠንቋይ ቤተ ይሄዳል፡፡ ለአጋፋሪው ሣንቲም ቢቴ ቦጨቅ ያደርግና ወረፋውን አፋጥኖ በተሎ ይደርሰዋል፡፡ በሁሉም ቦታ መቼም ይቺ ሙስና ተንሰራፍታለችና በዚህ አይግረማችሁ፡፡ ሀገራችን በተለይ በዚህ አንደኛ ሳትሆን የምትቀር አይመስለኝም፡፡ ጠንቋይ፤ ምን ፈልገህ መጣህ? አውሊያው ምን እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ አንተ ብላቴና? አስጠንቋይ፤ የኑሮ ችር ነው ወደዚህ ያመጣኝ፡፡ ሕይወቴ ልፋት ብቻ ሆነ፤ ቀን ከሌት ብለፋ ድካም እንጂ ውጤት የለም፡፡ ጓደኞቼ የትና የት ሲደርሱ እኔ በድህነት እየማቀቅሁ ቀረሁ፡፡… ጠንቋይ፤ አይዞህ፤ ገና ወጣት እኮ ነህ፡፡ ተስፋ አትቁረጥ… አስጠንቋይ፤ እሺ! በርስዎው መጀን አባቴ፡፡ ያለርስዎ ማን አለኝ፡፡ እስካሁንም ወደርስዎ ያልመጣሁት … [Read more...] about በደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር
“የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው”
የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም። ከፍተኛ ስልጣን የያዙትንና አቶ መለስ ለመተካካት ያዘጋጇቸውን አዳዲስ አመራሮች፣ በቅርቡ ደንብና ህግ በመጣስ ሹመት የሰጡዋቸውን ጨምሮ የሰራዊቱን አዛዦችና ደህንነቱን ከጎናቸው ያሳተፉት ክፍሎች የተፈጠረው ልዩነት እልባት ማግኘት ይገባዋል የሚል አቋም መያዛቸውን የሚጠቁሙ ክፍሎች እነማን ተለይተው እንደሚመቱ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንን ይገልጻሉ። “ፓርቲያችን ከእንጥሉ በስብሷል” በማለት ከዛሬ አስራአንድ ዓመት በፊት በአገር ክህደት ሊያስወግዷቸው የተነሱትን ጓዶቻቸውን የረቱት መለስ የተጠቀሙበት ዋንኛ ስልት አባይ ጸሃዬን … [Read more...] about “የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው”
የጎልጉል ቅምሻ
“የድመት ጸጉር የመብላት ሱሰኛ ነኝ” የሱሰኛነት ነገር ሲነሳ ሰሞኑን ከወደ ሚሽጋን ጠቅላይግዛት የተሰማው ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ የ43ዓመቷ ሊሳ በቀን ሦስት ሩብ መጠን ያለው የድመት ጸጉርጥቅል እንደምትበላ ተናግራለች፡፡ “የድመት ጸጉር የመብላት ሱሰኛ ነኝ” በማለት የምትናገረው ይህች ግለሰብ ሱሰኝነቱ የጀመራት የዛሬ 15ዓመት እነደሆነና እስካሁ 3200 ጥቅርል እንደበላች ታስረዳለች፡፡ ጥቅልሉን ከወለል፣ ከሶፋ፣ … እንደምታዘጋጅ ገልጻ በጣም አሪፍ የሆነው ግን በቀጥታ ከድመቷ የምታገኘው እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ማርገዝ --› መጠጣት --› ጽንሱ ማበላሸት --› ዳረጎት ማግኘት ከደቡብ አፍሪካ አስደንጋጭ ነገር ከተሰማ ጥቂት ቀናት ቢያልፉም የዜናው አስደንጋጭነት ግን እስካሁንም እውን ነው፡፡ ከመንግሥት የሚገኝ ጥቂት ዳረጎት ተጠቃሚ ለመሆን እርጉዞች ልጆቻቸውን በሽተኛ ሆነው … [Read more...] about የጎልጉል ቅምሻ
በ “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ”
ከዝግጅት ክፍሉ፤ መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በሚል ርዕስ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ አቶ ዳንኤል ክብረት የራሳቸውን አስተያየት የሰጡ ሲሆን ይህንንም አስተያየት ተከትሎ ፕ/ር መስፍን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሁለቱንም አስተያየቶች እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡፡ መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በዳንኤል ክብረት ከጥቂት ቀናት በፊት ታዋቂው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› በሚል ርእስ አንድ አነጋጋሪ፣ አከራካሪና አመራማሪ መጽሐፍ አውጥተዋል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ሃሳባቸውን በአደባባይ፣ ሕዝብ በሚረዳው መንገድና ቋንቋ ከሚገልጡ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ልሂቃን አንዱ ናቸው፡፡ በሦስት የመንግሥት ሥርዓት ፕሮፌሰር መስፍን ሃሳባቸውን ሲገልጡ፣ ሲጽፉ፣ ሲከራከሩና፣ መልካም የመሰላቸውን ሁሉ ለሕዝብ ሲያቀርቡና ሲሞግቱ የኖሩ የአደባባይ … [Read more...] about በ “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ”
ለ “የጣመ ውይይት” ምላሽ
"እኛ የመጨረሻዎቹ" የሚል አንድ ጽሁፍ በድረ ገጾች የሚሽከረከር አይቼ፣ እውን እንዴት ቀን ቀንን ዓመት ዓመትን እየተካው ዓለም ምንኛ በተጨባጭ በግብርም፣ በሃሳብ በመንፈስም እንደተሽከረከረች እንደገና ልብ ብዬ ነበር። እኔም የትላንት ሰው ስለሆንኩ። ነገር ግን እዚህ የውይይት መድረክ ውስጥ ሰገባ፣ የሃገሬ ልጆች አሁንም የዛሬ ሰላሳ ዓመት የፖለቲካ ቡድኖች የተከራከሩበትን፣ የተናቆሩበትን፣ ከዚያም ብዙ መዘዝና መዓት ሃገራችን የገባችበትን የፖለቲካ ልዩነቶችና ነጥቦች (ለምሳሌ የትጥቅ ትግል ዛሬ ያስፈልጋል፣ አያስፈልግም፣ ወይንም ግንባር፣ አንድነት፣ ወዘተ) አንስተው ዛሬም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሲከራከሩበት ስሰማና ሳነብ፣ ጉድ ነው፣ ዛሬም እዛው የዛሬ ሰላሳ ዓመት ከገባንበት ጭቃ፣ ይቅርታ ይደረግልኝና፣ አልወጣንም ማለት ተገደድሁ። ስለሆነም ዝርዝር ውስጥ ገብቼ እንዲህ ቢሆን እንዲህ … [Read more...] about ለ “የጣመ ውይይት” ምላሽ
እግርኳሳችን የራሷን ሙሴ ትፈልጋለች
ስሜት ጎርፍ ነው፤ ያውም ደራሽ ጎርፍ፤ ብሄራዊ ቡድናችንን ስንደግፍም ሆነ ስናወድስ እንዲሁም ስንወቅስ በዚሁ ደራሽ ጎርፍ መወሰዳችን ይታያል። ይሄ ችግር ግን እንደ ሃገርም ችግራችን እየሆነ የመጣ ነገር ነው በስሜት መደገፍ በስሜት መቃወም፤ ዛሬ ያወደሱትን ነገ መርግም ሁሉንም ነገር በዘላቂ ጥቅም፤ በዘላቂ ስራ እና በዕውቀት መመዘን እያቃተን ነው። ከዚያም ዐልፎ ስሜታችን ጫፍ ላይ በሚደርስበት ጊዜ ሰከን ብሎ የሚያስብ ሰው ሲያጋጥመን እንደጭራቅ እንመለከተዋለን። ከእኛ በሓሳብ የተለየ አስተያየት የሰጠ እንደሆነማ በቃ ቤተክርስቲያን ውስጥ የገባ ውሻ እናደርገዋለን።… የሰሞኑ የብሄራዊ ቡድናችን ውጤትም የዚህ ጎርፍ ሰለባዎች መሆናችን አንዱ ማሳያ ነው። መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አበባ ከቤኒን ብሄራዊ ቡድን ጋር ሲጫወት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የአሰላለፍ ስህተት … [Read more...] about እግርኳሳችን የራሷን ሙሴ ትፈልጋለች
Ethiopia: call on Congressman Chris Smith to save life of the most revered young political prisoner.
There is a renewed hope in Ethiopia that the much awaited visit of Congressman Chris Smith to the severely tyrannized nation would help alleviate the plight of venerated political prisoner Andualem Arage who is serving a lengthy jail sentence for “terrorism.” (Read more) … [Read more...] about Ethiopia: call on Congressman Chris Smith to save life of the most revered young political prisoner.
ከእሁድ እስከ እሁድ
ሻማ ማብራት ፣ ኤምባሲ መውረር በአብዛኛው የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሻማና ጧፍ ማብራት፣ በሰላማዊ ሰልፍ መጮህ፣ ፒቴሽን መፈራረም፣ በተለያዩ ማህበራዊ አውታሮችና ድሮች መሳደብና የመሳሰሉት ናቸው። ባለፈው ሳምንት የኤርትራ ተወላጆች ሎንዶን የሚገኘውን የኢሳያስ ኤምባሲ ጥሰው በመግባት የፈጸሙት የተቃውሞ ተግባር ከፍተኛ የሚዲያ ትኩረት ስቧል። “ኤምባሲው የእኛ ነው። ከኤምባሲያችን ወደ የትም አንሄድም” ያሉት የኤርትራ ተወላጆች የሚፈሩትን ኢሳያስን ያገኙ ያህል ፎቷቸውን ከግድግዳ በማውረድ መሬት ላይ በመከስከስ ረጋግጠው ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ራሳቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስና ዓለም ተመልክቷል። ይህ ታላቅ የተቃውሞ መልዕክት ለሁሉም ባለስልጣናት መልዕክት ሲሆን በተለይም ስደት ልዩ መለያው ለሆነው የኤርትራ ህዝብ ባንድነት ይነሳሳ ዘንድ የሚቀሰቅስ ተግባር ሆኖ ተገኝቷል። የእኛ አገር ተቃዋሚዎችና … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ለላሊበላስ ማን ይድረስ?
የላሊበላ ውቅር አብያተ ከርስቲያናት የመፍረስ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ መነገር የጀመረው ዛሬ አይደለም። ቢያንስ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት ያካባቢው ነዋሪዎች፣ በወፍ ዘራሽ ወደዚያ ያቀኑ ጋዜጠኞችና ለልቦናቸው የቀረቡ የገዳማቱ አገልጋዮች አስጠንቅቀዋል። ማስጠንቀቂያው ግዙፍና ዕረፍት የሚከለክል ቢሆንም ተግቶ ምላሽ የሰጠ አካል ባለመኖሩ፣ ጉዳዩን በመያዝ የተከራከረና ገዢውን ፓርቲ ያስጨነቀ የህዝብና የቅርስ ጠበቃ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ባለመገኘቱ “ለላሊበላ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች አንድ ናቸው” የሚል አስተያየት እየሰጡ ነው። ዛሬ ጥያቄው አንድ ነው፡- “ለላሊበላ ማን ይድረስለት?” የሚል! የኢትዮጵያዊያን ጉልህ ታሪክ የሆነው ላሊበላ በመፍረስ አደጋ ውስጥ ነው፤ እየተሰነጣጠቀም ይገኛል፤ ውሃ ዘልቆት እየገባው ነው። ላሊበላ አንድ ቀን ወደ አለመኖር ሲቀየር “ሰበር ዜና” ማለትና … [Read more...] about ለላሊበላስ ማን ይድረስ?