መግቢያ የዛሬው የመወያያ ሃሳብ ኢትዮጵያን እንደገና ለማነጽ ኣዲስ የማህበራዊ ፖለቲካ መዋቅር በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ መዋቅር ኢትዮጵያን ወደ ኣዲስ ኪዳን የሚጋብዝ ነው። ኢትዮጵያ የገጠማት የከፋ ችግር በኣብዛኛው ከታችኛው የማህበራዊ ፖለቲካ (socio politics) መዋቅር ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዚህ ላይ ኣማራጭ ሃሳብ ማምጣት በተለይ ይህ የኣሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ይመስላል። ያለፉትን ችግሮች ኣስር ጊዜ እያወጣን ብናወርዳቸው ድካም ብቻ ይሆንብናልና። በተለምዶ ያ ትውልድ እያልን የምንጠራው ቀዳሚው ትውልድ ኣንድ የሆነ ሼል ሰብሮ የወጣ ነበር። ያ ትውልድ ለዘመናት የነበረውን ዘውዳዊ ኣገዛዝ ደፍሮ የጠየቀ፣ የፍትህና የእኩልነትን ጥያቄዎች ኣንግቦ ግንባሩን ለጥይት የሰጠ በመሆኑ ታሪክ ሁልጊዜም ያ ትውልድ....እያለ ሲያስታውሰው እንዲሁ ይኖራል። ያ ትውልድ የሆነ … [Read more...] about ኢትዮጵያን እንደገና ማነጽ
ትግላችን ከእንግዲህ ወዴት? እንዴት?
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about ትግላችን ከእንግዲህ ወዴት? እንዴት?
”ዛሬም ታለቅሳለች!”
''ዛሬም ታለቅሳለች!'' ትላ’ትናም - ዛሬም ቁማም - ተቀምጣም በውኗም - በህልሟም፤ እምባ እያዘነበች ደም እያፈሰሰች፤ ሁሉንም እያየች ዛሬም ታለቅሳለች።……. ‘’ረስታ - ተረስታ በራሷ ላይ ዘግታ፤ ከጥዋት እስከማታ እንቅልፏን ተኝታ’’። ተብሎ ተወርቶባት ለብዙ ዘመናት ታሪክ ተጽፎባት፤……. እሷ ግን፣ እሷ ናት ዓለም የሚያያት፤ እምባ እያዘነበች እህህ…… ትላለች ትንሰቀሰቃለች፤ ሁሉንም እያየች ዛሬም ታለቅሳለች።……… ተማፅኖ ተማሎ ተገዝቶ ምሎ ገ’ሎና አስገድሎ ፤ ‘’ለ’ርሀብ - ‘ርዛትሽ ለልመና - ፅናትሽ ለፍትህ - እጦትሽ ለሰላም - ለፍቅርሽ፤ መድሀኒት አውቃለሁ እኔ እሻልሻለሁ’’፤ ብሎ የሚገባው እምባዋን ሊጠርገው መፍሰሱን ሊያቆመው፤...... ጭራሽ አብሶባት ሀዘን ደራርቦባት፤ ማቁን አስለብሶ አመድ … [Read more...] about ”ዛሬም ታለቅሳለች!”
ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?
በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት "ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል። ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር … [Read more...] about ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?
ከእሁድ እስከ እሁድ
“መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ተተረጎመ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው ቤተክርስትያኗ፤ መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሄደ ባለው የጥቅምት ምልዐተ ጉባዔው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና አጀንዳዎቹ አንዱ ስብከተ ወንጌልን ማዳረስ እንደሆነ የገለፁት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ የመጽሐፉ ሕትመት እንዲቀላጠፍ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡ “መጫፈ ቂዳሴ” በሚል ርዕስ የተተረጎመው የኦሮምኛ መጽሐፉ፤ በቅርቡ ዝግጅቱን የተቀላቀሉትን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ፈስ አጣርቶ የሚያስቀር ውስጥሱሪ በአሜሪካ እጅግ ተፈላጊ ሆኗል
በእንግሊዝ የተፈበረከው ፈስ የሚያጣራ ውስጥሱሪ በአሜሪካውያን ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነቱ እየመጣ መምጣቱ ተሰምቷል፡፡ የአምራች ኩባንያ አፈቀላጤ የሆኑት ሲናገሩ “ከአጠቃላይ ሽያጫችን ውስጥ በአሜሪካውያን የሚገዛው እጅግ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘ ነው” ብለዋል፡፡ ታዋቂው የውስጥሱሪ አምራች ሽሬዲስ በቅርቡ ፈስ አጣርቶ በማስቀረት እንዳይሸት የሚያደርግ ውስጥሱሪ ለወንዶችና ለሴቶች ለገበያ ማቅረቡ ከተሰማ በኋላ ሽያጩ በ400% አድጓል፡፡ ኩባንያው እንደሚለው በውስጥሱሪው የውስጠኛ ክፍል ከካርቦን የተሰራ ዞርፍሌክስ የሚባል ጨርቅ የተሰፋ ሲሆን ይህም አማካይ የሽታ መጠን ያላቸውን የፈስ ዓይነቶችን 200 ጊዜ ያህል እንዳይሸቱ የማድረግ ችሎታ እንዳለው አፈቀላጤዋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ሲቀጥሉም “ይህ የውስጥሱሪ ለሁሉም የሚያስፈልግ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ይፈሳል” በማለት … [Read more...] about ፈስ አጣርቶ የሚያስቀር ውስጥሱሪ በአሜሪካ እጅግ ተፈላጊ ሆኗል
“በአንድ ቀን ትምህርት ፎቶ አንሺ ሆኜ ቁጭ አልኩ” የ69 ዓመቷ አረጋዊ ወ/ሮ ባዩሽ
ካዛንቺስ አካባቢ በልመና የሚተዳደሩ አንድ አይነሥውር ሽማግሌ አሉ፡፡ የሚለምኑት ከካዛንቺስ ስድስት ኪሎና ፒያሳ ለመሄድ ታክሲ ከሚጠብቁ ተሳፋሪዎች ነው፡፡ አንድ ቀን በእለቱ የለመኑትን ገንዘብ ታክሲ እየጠበቅሁ ባለሁበት ቁጠርልኝ አሉኝ፡፡ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት አርባ ብር ለምነዋል፡፡ በሌላ ቀን ተመልሼ ጠየቅኋቸው። በልመና ከሚያገኙት ገንዘብ ልጃቸውን ኮሌጅ አስተምረዋል፡፡ ልጃቸው ሥራ ከያዘ ከዓመታት በኋላም ግን ልመና አላቆሙም፡፡ አሁንም እዚያው ካዛንቺስ እየለመኑ ነው፡፡ “ለምን ልመና አያቆሙም?” አልኳቸው፡፡ “ምን ላድርግ ቁጭ ልበል እንዴ?” በማለት እኔኑ መልሰው ጠየቁኝ፡፡ እዚያው ካዛንቺስ የሚለምኑ ሌላ አረጋዊ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለባቸው፡፡ በምፅዋት የሚያገኙትን ሳንቲም ይዳብሱና አምስት ሳንቲም ከሆነ መልሰው ይወረውሩታል፡፡ በአንፃሩ የእይታም የአቅምም ችግር … [Read more...] about “በአንድ ቀን ትምህርት ፎቶ አንሺ ሆኜ ቁጭ አልኩ” የ69 ዓመቷ አረጋዊ ወ/ሮ ባዩሽ
ምሁር (intellectual)
ከሰው ወይ ከአምላክ ፤ ተምሮ የረቀቀ ቀለም ብዙ የጠጣ ፤ ከባሕር እየጠለቀ ተለይቶ የወጣ ፤ በርቶለት የራቀ አንጥሮ አብጠርጥሮ ፤ መርምሮ የላቀ በአዎንታዊ እሴቶች ፤ ጌጦ ያሸበረቀ ደግነትን ከሸር ፤ ልማትን ከጥፋት ፤ ለይቶ የጠበቀ የሚያሰነካክለውን ፤ የት እንዴት እንደሆን ፤ ነቅቶ የጠነቀቀ ነበር ምሁር ማለት ፤ መሻል መብለጣቸውን ፤ አጣጥሞ ያወቀ አዬ ድንቄም አያ ii ፤ ምሁሩ ሊቅ ዐዋቂ የሀገር አደራ ጠባቂ በአረጋዊያን ተመራቂ በታናናሾቹ ተደናቂ ትውልድን አናጭ አምጣቂ አብእናን ቀራጭ አላቂ በዕውቀት በጥበብ አርቃቂ ለችግር መፍትሔን አፍላቂ የሥልጣኔን ብርሃን ፈንጣቂ ለሀገር ለወገን መከታ ለትውልድ ተስፋ አለኝታ መመኪያ ደጀን ስጦታ አይደለም ? ትርጉሙ ሲፈታ ? አዪ … እ !! ድንቄም ዐዋቂ የመጠቀ የእንስቷን ተስፋ የደመቀ በወላጅ … [Read more...] about ምሁር (intellectual)
ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ
ስብሃት ነጋ የኢህአዴግ አባትና ፈጣሪ የሆነው ህወሃት የመጨረሻው ታሪኩ ጠቦ እንደሚቋጭ ይፋ አደረጉ። ችግር የህወሃት ልዩ በረከትና ስጦታ እንደሆነ በማመልከት ህወሃት ውስጥ ልዩነትና መፈርከስ አደጋ ተከስቶ እንደማያውቅ ሸመጠጡ። አቶ ስብሃት ጠቦ የሚጠናቀቀውን የህወሃት ስውር አጀንዳ የገለጹት ከጋዜጠኛ ደረጃ ደስታ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነበር። በኢህአዴግ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና የኩዴታ አደጋ ሊያስከትል የሚችል አደጋ እንደተረጋገጠ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ስብሃት "አዲስ አበባ መንግስት ገልብጠው የክልሎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ማን እሺ ይላል" በማለት ነበር የመለሱት። አንዴ በመከላከያ ውስጥ የመከፋፈልና የመበታተን አደጋ ሊያጋጥም የሚችልበት አግባብ እንደሌለ፣ ጠያቂው እንዳለው የመፈንቅለ መንግስት አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የህወሃት ስጋት … [Read more...] about ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ
የጎሳ ፌዴራሊዝም
ክፍል አንድ የወያኔ ትግሬዎችና ስለ አማራ ህዝብ ያላቸው ግንዛቤና የቆየ ጥላቻ ምን ይመስላል? የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎችም ሆኑ ተከታዮቻቸው የትጥቅ ትግላቸውን ሲጀምሩ ለትግራይ ህዝብ ችግርና ኋላ ቀርነት ተጠያቂዎቹ ከዳግማዊ ዐጼ ምንሊክ ጀምሮ እስከ ደርግ መውደቅ ድረስ በስልጣን ላይ የነበሩት ወያኔ አማራ ብሎ የሚጠራቸው መንግስታት እንደ ነበሩ በፖለቲካ ፕሮግራም ደረጃ ቀርጸው የትግራይን ህዝብ እንዳስተማሩ ቀድሞ የወያኔ ድርጅት አባል የነበረውና ዛሬ በስደት በሚኖርበት አስውስትራሊያ ሆኖ የወያኔን እኩይ ዓላማ በቆራጥነትና በሃቅ እያጋለጠ ያለው አቶ ገብረ መድህን ዓርዓያ በቅርቡ “እነማን ነበሩ” በሚል ርእስ በመረጃ አስደግፎ አሳውቆናአል። የወያኔ ድርጅት የአማራው ህዝብ በእነዚህ የአማራ መንግስታት ብሎ በሚጠራቸው ከዐጼ ምንሊክ እስከ ደርግ መውደቅ ድረስ በነበሩት መንግስታት … [Read more...] about የጎሳ ፌዴራሊዝም