ዛሬ ታህሳስ 3ቀን የሚከበረው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ 100ኛ የዕረፍት ዓመት “እምዬ ምኒልክ ምን ዓይነት ውርስ ትተውልን ሄዱ?” ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጦርነት ለመግባት ሳይፈልጉ “በግድ” ወደሄዱበት የጣሊያን ጦርነት መለስ ብለን የሆነውን እንድናስብ ወደድን፡፡ ክተት፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት ለሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፤ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬ ከብት ማለቁንና የሰዉን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር … [Read more...] about እምዬ ምኒልክ፡ የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
‘‘ፍርድ ሲዘገይ ሀገር እንደታሰረ መቆጠር አለበት’’ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ጠበቃ)
አቶ ተማም አባ ቡልጉ ከአዲስ ጉዳይ መጽሄት ቁጥር 128 ህዳር/2006 ዕትም ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ አዲስ ጉዳይ፡ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደ ታህሳስ 3 ሲዛዋወር እንደ ጉዳዩ ዓቃቤነትዎ እንዲያውቁት ተደርገው ነበር? ተማም፡ በፍጹም ለእኔ የተነገረኝ ነገር አልነበረም፡፡ ከእኔ ጋር አብሮ የሚሰራ ጠበቃ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዶ ‘ጉዳዩ እንዴት ነው?’ ሲለኝ አይ እዚያው ነው ብዬ ሳረጋግጥለት ‘አረ ፍርድ ቤቱ ባዶ ነው’ የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ አንዳንድ ጠበቆች ጋር ስደውልም እከሌ የተባለ ጠበቃ እኮ ፍርድ ቤት በነበረበት ወቅት ከጽ/ቤት ተነግሮት ነበር አሉኝ፡፡ በዚህ ዓይነት መልኩ ነው ቀጠሮው መራዘሙን የሰማሁት፡፡ አዲስ ጉዳይ፡ በይፋ የተነገራችሁ ነገር የለም ማለት ነው? ተማም፡ ለእኛ በይፋ ምንም የተገለፀልን ነገር የለም፡፡ በፍርድ ቤት በይፋ … [Read more...] about ‘‘ፍርድ ሲዘገይ ሀገር እንደታሰረ መቆጠር አለበት’’ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ጠበቃ)
“የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ጋር መያያዟን እጠራጠራለሁ” ፕሬዚዳንት መንግሥቱ
የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈት በማስመልከት አውስትራሊያ ከሚገኘው ኤቢኤስ ሬዲዮ የአማርኛ አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ መንግሥቱ ለሬዲዮው በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ በእሳቸው በትረ ሥልጣን ወቅት ማንዴላ የአገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ከመጎናፀፈቸውም ባሻገር፣ የአንድ መቶ ሺሕ ዶላር ገንዘብ ተበርክቶለቸዋል፡፡ ይህና ቀሪው ንግግራቸው እንዲህ ቀርቧል፡፡ ‹‹ማንዴላና የተወሰኑ ተከታዮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ በስውር መጥተው፣ ወታደራዊ ሥልጠና አግኝተውና እግረ መንገዳቸውን ሞሮኮን ጐብኝተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸውን ተገንዝቤያለሁ፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ አሜሪካኖች በአማካሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ፡፡ እስራኤሎችም ነበሩ፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ግንኙነት የነበራቸው በመሆኑ የማንዴላን ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘትና ወታደራዊ ሥልጠና በመከታተል እግር በእግር እየተከታተሉ መረጃ … [Read more...] about “የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ጋር መያያዟን እጠራጠራለሁ” ፕሬዚዳንት መንግሥቱ
የጋምቤላ ክልል በህንድና በሳዑዲ ኩባንያዎች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ
የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ሦስት የውጭ አገር ኩባንያዎች ከፍተኛ ችግር ታይቶባቸዋል፣ የፕሮጀክት አፈጻጸማቸውም ደካማ ነው በሚል የፌዴራል መንግሥት ዕርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ፡፡ የክልሉ መንግሥት በቅርቡ ለግብርና ሚኒስቴር፣ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ የህንድ ኩባንያዎች የሆኑትን ካሩቱሪንና ቬርደንታ ሃርቨስት፣ እንዲሁም የሼክ መሐመድ አል አሙዲ ኩባንያ የሆነው ሳዑዲ ስታር የእርምትና የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል፡፡ በጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጋትሉዋክ ቱት ኮት ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ የክልሉ መንግሥት በነዋሪዎች አስተያየት ላይ ተመርኩዞ የራሱን ግምገማ አካሂዷል፡፡ ክልሉ ባካሄደው ግምገማ በተለይ እነዚህ ሦስት የውጭ አገር ኩባንያዎች ከፍተኛ ችግር እንደታየባቸውና የፕሮጀክት አፈጻጸማቸውም ደካማ መሆኑን … [Read more...] about የጋምቤላ ክልል በህንድና በሳዑዲ ኩባንያዎች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ
“ድምጽ አልባው አስዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ!”
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሁለት የጸጥታ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በስሩ እንደሚገኙ የሚነገረለት ይህ የመዝናኛ ማዕከል ከተቆርቆረ ሁለት አስርት አመታትን ቢያስቆጥርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ሰንካል ምክንያቶች ከትርፋማነት ይልቅ ኪሳራ፤ ከእድገት ይልቅ ወደቀትን እያቀነቀነ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ እማኞች በሰራተኞቹ ላይ እይተፈጸመ ያለው በደል ከመቸውም ጊዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ካፍቴሪያ ማዕከል ዛሬ ላለበት አሳፍሪ ደረጃ ምክንያት መሆኑ የሚነገረው በተለያዩ ወቅቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጀርባ ታዝለው ያለችሎታቸው አመራር የሚሆኑ ግለሰቦች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች ጋር በቀረበት ተነጋገረው የካፍቴሪያውን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ከማህበሩ … [Read more...] about “ድምጽ አልባው አስዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ!”
የነፃነት አባት
ታ ሪኩ ገናና፤ ስራው የለው አቻ ላ ሰበበት ጉዳይ፤ የሌለው ፍራቻ ቁ ጣን ቂም በቀልን፤ ያጠፋ ጥላቻ ማ ንዴላ ታላቁ፤ የነፃነት ጮራ ን ጥረ መብረቅ ሆኖ፤ አፍሪካን ያስጠራ ዴ ሞክራሲ እንዲያብብ፤ ተስፋውን ሰንቆ ላ ሰበው አላማ፤ ቆሞ ነበር ታጥቆ የ ህይወት ዘመኑ፤ ቢሆንም መራራ ነ ፃነት አላብሷል፤ ስሙን የሚያስጠራ ፃ ድቅ የሆነ ሰው፤ እያለ በሕይወት ነ ውና ተግባሩ፤ መልካም ነገር መስራት ት ዕዛዙን ፈጽሟል፤ በእድሜው ዘመናት ዓ ለም መቆያ ናት፤ ተቀባይ እንግዳ ባ ህሪዋ መራር፤ ወሳጅ በሞት እዳ ት ልቅ ትንሽ ሳትል፤ ድንገት የምትከዳ ና ልን አይባልም፤ ማንዴላም ተመለስ ቸ ሩ ፈጣሪያችን፤ የታላቁን ሰው ነፍስ ው ለታ ይክፈላት፤ ወደሱ ስትደርስ … [Read more...] about የነፃነት አባት
ማንዴላን በተመለከት ለግማሽ ዓመታት የተደበቅ ምስጢር
ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል። በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ መንግስት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች። ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት የግድያ ሙከራ ሴራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል። ሻምበል ጉታ ዲንቃ በንጉሡ ዘመን የፖሊስ መኮንን ነበሩ። ማንዴላን በከፍተኛ ሚስጥር እንዲጠብቁ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ … [Read more...] about ማንዴላን በተመለከት ለግማሽ ዓመታት የተደበቅ ምስጢር
በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”!
የብሔር ጥያቄ በኢትዮጵያ ምላሽ እንዳገኘ የሚያስተጋባው ኢህአዴግ “የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” በዓልን ማክበር ከጀመረ ስምንት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንፃሩ “ተመልሷል” የተባለው ጥያቄ እንደተቀበረ ፈንጂ በየጊዜው በየቦታው እየፈነዳ በህይወት፣ በንብረትና በኢትዮጵያዊነት ላይ አደጋ ማድረሱን ዳዊት ሰለሞን ሁነቶችን በመጥቀስ ይሞግታል፡፡ ከአስርት አመታት በፊት የኢትዮጵያ ተማሪዎች በለውጥ አብዮት ናፍቆት እየተናጡ ነው፡፡ እዚህም እዚያም በተፈጠሩ ቡድኖች የማርክሲስት-ሌኒንስት ፍልስፍናን የሚሰብኩ የርዕዮተ ዓለም ጽሁፎች ይነበባሉ፡፡ ተማሪው ይከራከራል፣ የሌኒኒዝም ፍልስፍና ቀለም ቀለም መሽተት ለጀመረው የ1960ዎቹ ትውልድ ልብ የቀረበ ሆኗል፡፡ ፍልስፍናውን በአገራቸው የፖለቲካ ግለት ለመተርጐም የቋመጡት ወጣቶች በሁለት ጠርዝ ተሰልፈው በኢትዮጵያ ያለው “የመደብ ወይስ የብሔር … [Read more...] about በብሔር ፖለቲካ ሥር “የተቀበረው ፈንጂ”!
ሰማያዊ ፓርቲ በአሜሪካ
ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት …
ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡ ‹‹ይህ ህገ-መንግስቱን የመነዳ ተግባር ነው!!!›› ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ ለመፈረጅ ወይም ለመከሰስ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ ‹‹ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው?›› በማለት ሲተች … [Read more...] about ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት …