• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሁሉም ለሀገሩ ዘብ ይቁም !!

April 18, 2013 12:52 am by Editor Leave a Comment

በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሀገራችን ዉስጥ የተጣለብን ከፋፍለህ ግዛ ዘመቻ ከቀድሞው በተለየ እጅግ ዘግናኝና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ላይ መገኘት የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሞራል ሳይነካ አይቀርም ብዬ እገምታለሁ።  ከዚህም ውስጥ ዋነኛውና የመጀመሪያው ሰሞኑን በአማራዉ ብሔረሰብ ላይ በመድረስ ላይ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ህዝቡን ከአድማስ አድማስ እያነጋገረው መምጣቱ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሬ ምን ሠራሁ በማለት እራሱን እየጠየቀ ? ይህን ዘረኛ የሆነ የወያኔ መንግስት ከስር መሰረቱ ነቅሎ ለመጣል በቁርጠኝነት በመነሳት ሀገራዊ የዜግነት ግዴታውን መወጣት አለበት ፡፡ ለዚህም በዋንኛነት ትኩረት ተሰጥቶት ለነገ ይደር የማይባልበት ጉዳይ ፣ ማናቸውም የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ፥ የድጋፍ ድርጅቶች ፣ አንድ በመሆንና እጅ ለእጅ በመያያዝ ቅድሚያ ለሀገር ሰጥቶ የመጣብንን የወያኔ ሰደድ እሳት ማጥፋት ግድ ይለናል ፡፡

ለዚሁም ለ- April 8 ቀን  በኦስሎ ኖርዌይ የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያና  ኢህአፖ የጠሩት ሀገርህን አድን ዘመቻ ጥሪ እንደ አንድ አብነት ሆኖ የሚጠቀስ  ነው ፡፡  ዘረኛው የወያኔ መንግስት ከጥነሰሱ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ስልጣን ላይ ፊጥ ብሎ እስከቀጠለበት ድረስ ሰንቆ ያመጣውን የሀይማኖትና የዘር ማጥፋት ትልም በተግባር ላይ ማዋል ከጀመረ እነሆ ብዙ አመታትን አስቆጥሯል ፡፡ ይኸውም የመጀመሪያው በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የተጀመረው የሀይማኖት ብጥብጥ በአይበገሬው የሙስሊም ወንድሞቻችን ትግል ዕለት በዕለት እየተፋፋመ ወያኔን እንቅልፍ ቢነሳውም ፣ ህወሃት-ኢሃዴግ ተስፋ ባለመቁረጥ እንደገና ፊቱን ወደ ኦርቶዶክስ ኃይማኖት በማዞር የተለመደውን የስልጣን ማራዘም ዘመቻና ህዝብን ከህዝብ የማፋጀት አባዜን በማፋፋም እነሆ አሁን ደግሞ የአማራውን ህዝብ ከእናት ምድሩና ሀገሩ የማባረርና ዘር የማጽዳት ዘመቻውን በሰፊው ተያይዞታል።

ይህም ከማናለብኝነትና ለህዝቡ ካለው ከፍተኛ ጥላቻና ንቀት የመነጨ በመሆኑና በአንድ ዘር የበላይነት ብቻ የማመን ጠባብነት ጭምር የተጸናወተው በመሆኑ ነው ። ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ በኢትዮጵያ አንድነት የማያምንና ጭራሽ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንደሌለችና ኢትዮጵያ የሚለውንም ስም ያገኘችው በሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት መሆኑን ለማሳመን የሚያደርጉትን ባዶ ጥረት በመረጃ  አንድ ግለሰብ በኢሳት ቲቪ ላይ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አገኔ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ከነ መረጃቸው አስደምጦናል ። ይህም ማለት አማራው ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ መሆኑን አስምረው አረጋግጠውልናል ማለት ነው ። እንደውም ለአማራ ያላቸውን ጥላቻና ዘረኝነት ለመግለጽ ሲሉ ! ሆስፒታል ውስጥ አንድ በሽተኛ ከፈረንጅ ሀኪምና ከአማራ ሀኪም ማን እንዲያክምህ ትፈልጋለህ ተብሎ ምርጫ ሲቀርብለት የመለሰው መልስ አማራ ከሚያክመኝ ፈረንጁ የፈለገውን ቢያደርገኝ ይሻለኛል ብሎ በሽተኛው እስከመመለስ መድረሱን አድምጠናል።

ጎበዝ ! ወያኔዎች እኮ ዛሬ አማራውን ነገ ደግሞ ጉራጌውን ከዛም ኦሮሞውን ከሀገር በማፈናቀል እንደተባለውም ኢትዮጵያ የተባለችውንና ለዘመናት ተከብራና ታፍራ የኖረችውን፤ ጀግኖች አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ያስረከቡንን ሀገር ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሆን ብለው የተነሱ አረሞች ናቸው።  እምነበረድ ይክበዳቸውና ! አሁን በአካለ ህይወት የሌሉት ፣ የቀድሞው ጠ.ሚኒስተር የነበሩት በራዕያቸው ግን አገሪቱን የሚያስተዳድሩት ሰው ባለቤት የሆንችው ወ\ሮ አዜብ መስፍን(ጎላ) ሰሞኑን በኢቲቪ ማቅ (ጥቁር ለብሳ)  እኛን ግን ሳቅ  አላብሳናለች ፣ ስለ ባለቤትዋ የወር ደሞዝ ማለት ነው ለኢህአዲግ መዋጮ ከፍሎ የሚደርሰው 4,000ብር ብቻ ነው ብላናለች ፡፡  አንድም ቀን ልጆቼን ፣ ቤቴን ሳይል ለሀገሩ 24 ሰአት ያገለገለ መሪ ነው ፥ ወደዚህ ሀገር ሲመጣም ጭንቅላቱን ብቻ ነው ይዞ የመጣው ብላናለች ። ሌላው ሰው ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ምን ጨብጦ እነደመጣ ፣ ኧህ ! ካሏት አዜብ መስፈን ብዙ ቀልዶችን ሳትነግረን አትቀርም ፡፡

ወይዘሮዋን አንድ ያልገባት ነገር ቢኖር ፣  መለስ  ጭንቅላቱን አሟጦ የተጠቀመበት ፣ የባንዳ ልጅ እየተባለ ያደገበትን በቀል ፣ህዝቡ ላይ በመበቀል ሙሉ ኃይሉን የተጠቀመ  አረመኔ ፥ ጨካኝና ዘረኛ  መሪ መሆኑን ያለመረዳቷ ጉዳይ ነው ። ከዚህ በፊት የመለስ ራእይ ሳይደለዝና ሳይበረዝ ትግሉ ወደ ፊት ይቀጥላል ያልሽው እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ዛሬ ደሞ በትንሽ ደሞዝ እየተከፈለው ሌት ተቀን እየሰራ ሀገራችንን ትልቅ ደረጃ ላይ እንድትደርስ ያደረገ የመጀመሪያው መሪ መሆኑ ተሰምሮበት (Guinness book of records) ላይ ተመዝግቦ መቀመጥ አለበት አይነት ትእዛዛዊ የማስጠንቀቂያ መልክት በማስተላለፍ “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ” አይነት ጨዋታሽን በጥሩ ተውኔታዊ ገቢር ! የሃዘን ልብስሽን እንደ ጉሬዛ ግንባርሽ ድረስ ተከናንበሽ ትውነሽልናል፡፡

ምናልባት መለስ ዜናዊ ትግራይን አልምቶ ይሆናል አላውቅም በእርግጠኝነት ግን መናገር የምችለው ቀሪዋን ኢትዮጵያን አድምቷል ። ህዝቡንም እርስ በእርሱ ደም እንዲቀባባና ፥ በዘርና በሀይማኖት በመከፋፈል የሀገሪቷንም መሬት ለባእዳን በመሸጥ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግርና መከራ አጋፍጦ ፣ ዜጋ ሁሉ የሚወዳትን ሀገሩን እየጣለ በየአረብ ሀገሩና አውሮፓ ውስጥ እንዲሰደድ ያደረገ ትልቅ የማይረሳ ነቀርሳና ጠባሳ ህዝቡ ላይ  ትቶ የሄደ መሪ ነው ። የእርሱን ራእይ በመከተል እነሆ አሁንም ያሉት መሪ ተብዬ ጃሌዎቹ ከሱ በባሰና አስከፊ በሆነ ሁኔታ ህዝቡን ከተወለደበትና እትብቱን ከቀበረበት ቀዬ በግፍና በጭቆና እያባረሩት ይገኛሉ ። ስለዚህ ጎበዝ ይህን ጉዳይ ዝም ብለን ማየት የማንችለውና ሁላችንም በአንድ ላይ ሆነን እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔንና አንጃዎቹን “በቃ” ማለት የሚጠበቅብን ወቅቱ  ከምንግዜውም በላይ አሁን ነው ።

በመጨረሻም ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር የኢህአፓ ወክንድ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እጅግ የሚያኮራ በመሆኑ ሳይደነቅ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ነው። ለዚሁም ከዚህ በፊት በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ወያኔ ያደረሰውን በደል አብሮ ከጎኑ በመሰለፍ ፣በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ላይም እንዲሁ ችግሩን አብሮ በመጋፈጥና አሁን ደሞ በአማራው ህዝብ ላይ ወያኔ የሚያደርሰውን አሰቃቂ በደል በመቃወም በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። ሌላው ደግሞ ማናቸውም ለሀገራችን ተቆርቋሪዎች ነን የሚሉ ኢትዮጵያዊያኖች ወገኖቻችንን በሙሉ የሚያሳትፍ (keep of fighting ethiopian youth forum KOFEYF) የሚል የፓልቶክ (paltalk room) ከፍቶ ዘውትር በየሳምንቱ እሁድ ከ15፡00 – 3፡00pm ሰአት ጀምሮ አንጋፋ የሆኑ የፖለቲካ ባለሞያዎችንና የሀገር ተቆርቋሪዎችን በመጋበዝ ትልቅ አስተዋጾ በማድረግ ላይ ይገኛል ። እርሶም ይህን እድል በመጠቀም ያለዎትን እውቀት ለማህበረሰቡ በማስተማርና በመማር ለሀገርዎ ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ዉድ ሀገራችንን  ኢትዮጵያን ከገባችበት የድጥ ማጥ ውስጥ እናውጣት የሚል ተማጽኖዬን በማክበር እጠይቃለሁ።

ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያ ሀገራችንን በምህረቱ ይጎብኛት!!!

Dawit Abebe, April 2013. Oslo

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule