የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን(ዮሐ 3፡11)
ዓለም እንደሚያውቀው የጣሊያን ጦር በአድዋ ጦርነት እጅግ በሚያሳፍር ቅጣት ተቀጥቶ ከኢትዮጵያ ምድር መውጣት ለመላ አውሮጳ የሐፍረት ማቅ መከናነብ ምክንያት ሆነው።
በዚህ ታሪካዊ ውርደት የተሸማቀቀው ጣሊያን፤ ዘመናዊ የምድርና የሰማይ ጦሩን ከበፊቱ በላቀ ሁኔታ አደራጅቶ፣ኢትዮጵያን በጎሳ ሸንሽኖ በቋንቋ ለያይቶ እርስ በርሱ የማዋጋት ስልቱን ቀምሮ፣ አማራና ተዋህዶ ቤተክርስትያንን የማጥፋት እቅዱን ዘርግቶ እንደገና በ1928 ዓ.ም. ወረረን።
የመጀመሪያውን የክተት ጥሪ የሰሙ ኢትዮጵያውያን የየራሳቸውን መሳሪያ እየገዙና ሥንቃቸውን እያዘጋጁ ከሸዋ፣ ከወሎ፣ ከምስራቅ፣ ከምዕራብ፣ ከመካከለኛውና ደቡቡ ክፍል ወረራውን ለመመከት በማይጨው በኩል ዘመቱ። በተከዜ በኩል ከጎጃም ከቤገምድርና ስሜን ጣልያን መሰረቱን ወደ ጣለበት ወደ ትግሬ ዘመቱ። በወረራ በተያዙት ቦታዎች የነበሩ ከሀድያን ካህናትም ባንዳወችን በመደገፍ ወረራውን በሸብሸባ እያጀቡ የጣሊያንን መንግስት አጸደቁ፡፡
ዘማቾች አርበኞቻችን እንደ ምንይሽር፣ በልጅግ፣ ጓንዴ፣ ጦርና ጎራዴ በመሳሰሉ ዘመናዊ ባልሆኑ መሳሪያዎች በባንዳዎች እየተመራ በሰማይ መርዝ በምድር ባሩድ እሚረጨውን የጣሊያን ጦር ገጠሙ፡፡ ከእንዲህ ዓይነት የወረራ ተጋድሎ በኋላ ትግሬ የዘመተቱት አርበኞቻችን ወደ መሐል፣ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለስልት ሲያሸገሽጉ የኢትዮጵያ ጦር ተፈታ፤ ንጉሡም ከአገር ወጡ፤ ጣልያንም በባንዳዎች እየተመራ አገሪቱን እያዳረሰ ነው የሚል ወሬ በብቸና ተሰማ፡፡ (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply