- ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደገቢ ምንጭ የሚጠቀሙበት ወንድ አዳሪዎችና (male prostitutes) ደላሎች አሉ!
- ግብረሰዶማዊያኑ የራሳቸው መገናኛ ቤቶችና ምሽት ክለቦች አሏቸው “ዜጋ” የሚለው ቃል የመግባቢያ ኮድ ሥማቸው ነው!
- ግብረሰዶማዊያኑ በድብቅ መኖሪያ ቤቶችና በምሽት ክለቦቻቸው “የጋብቻ ሥነሥርዓታቸውን” ይፈጽማሉ!
ዳዊት ተሰማ (የባለ ታሪኩ ስም የተቀየረ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በድህረ ምረቃ መርሐ-ግብር የህብረተሰብ ጥናት ተመራቂ ተማሪ ነው፡፡ ተማሪው ለዲግሪ ማሟያ ጥናት ለማዘጋጀት ለአማካሪው ካቀረበው የጥናት ሀሳብ አንዱ ግብረሰዶማዊነት በአዲስ አበባ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፤ በተለይም ሁኔታውን ከውጪው ዓለም ተጽዕኖ አኳያ በማያያዝ ለማቅረብ ነበር፡፡ የተማሪው የጥናት ሀሳብ በአማካሪው መምህሩ ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ሌላ ርዕስ የጥናት ሀሳብ ለመምረጥ ተገደደ፡፡ ያም ሆኖ ዕጩ ተመራቂ ተማሪው የቀደመውን ጥናቱን ገፋበት፡፡ “ለጥናቱ ምልከታና መረጃ አሰባሰብ በአብዛኛው የምሸት ሠዓታትን ጠብቆ መጠቀም ግድ ይላል” የሚለው ተማሪ ዳዊት፤ ወራትን በተሻገረዉ የጥናት ውጤቱ “አዲስ አበባ ከአዕምሮ በላይ የሆኑ የግብረሰዶማዊያንን ታሪክ በጉያዋ ይዛለች፡፡ ይህንንም ባደረግነው ጥናት አረጋግጠናል” ይላል፡፡ ጥናቱ ሌሎችንም ባለሙያዎችና ተማሪዎች ያካተተ ነው፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የእነ ዳዊት የጥናት ውጤትን መነሻ በማድረግ ያጠናቀረውን ዘገባ ለአንባቢ እንዲመች አድርገን አቅርበናል፡፡
አዲሱ የአለም ስርዓትና የሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐብይ ክሥተት ነው እየተባለ ብዙ የሚባልላት ሉላዊነት (Globalization) ዓለምን በሙሉ በድንበር የለሽ አንድ ምጣኔ ሀብት ሥርዓት ጥላ ሥር ለማድረግና ነፃ የካፒታል፣ የሸቀጥ፣ የሰው ኃይል፣ የአገልግሎት፣ … ዝዉውር እንዲኖር የሚደረግ እንቅስቃሴ ነዉ፡፡ የሃሳቡ አስተሳሰቦች (ፍልስፍናዎች) እና የሚወስዷቸው እርምጃዎች አሳሳቢነታቸው እየጎላ መጥቷል፡፡
ሉላዊነት ዓላማው ዓለምን ለጥቂት ሀብታም ኮርፖሬሽኖች በተለይም ለምዕራቡ ዓለም ግዙፍ ኮርፖሬሽኖች ማመቻቸት ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ሉላዊነትን ዘመቻ ኮርፖሬሽን (Operation Corporate) ይሉታል፡፡ ለዚህ የሉላዊነት ዓላማ መሳካት “እንቅፋቶች” ናቸው ብለው የሚታሰቡትን ማናቸውም ነገሮች በተለያየዩ ዘዴዎች በተቻለው መንገድ ሁሉ የማድከምና የማጥፋት አካሄዱ የበለጠ አሳሳቢ ሆኖ ይታያል፡፡ ሉላዊነት ለዓላማው መሳካት በሦስት ዘርፎች የሚሠራ ሲሆን፣ የሁሉም መዳረሻ ግብ ግን ዓለምን የጥቂት ሀብታም ኮርፖሬሽን የገበያ ማዕከልና የሸቀጥ ማራገፍያ ማድረግ ነው፡፡ እነዚህ ፖሊስዎችም የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የፖለቲካ ፖሊሲ እና የማህበራዊ ፖሊሲ (ኃይማኖት፣ ባህል፣ ወግ፣ ሥርዓት ….) ናቸው፡፡ የአንድን አገር በተለይም ጥንታዊ የሆኑትን የራስ ማንነት፣ ባህል፣ የእምነት እሴቶችና አገር በቀል ፖሊሲዎችን በማዳከምና በማጥፋት ራሱን ለማቆም ብዙ ርቀት የተጓዘው ሉላዊነት፤ በ“ሥልጣኔ” ሥም የሦስተኛውን ዓለም አገራት አገራዊ አዕማዶች በማፍረስ ላይ ይገኛል፡፡
በግብረሰዶማዊነት ስናስብም ሆነ ስናወራ ጉዳዩ ከሉላዊነት መስፋፋት ጋር ተያይዞ እየተጠናከረ መሆኑን ልብ ማለት ያሻል፡፡ በድህነት በደቀቀች አገር እንደመኖራችንና የትምህርት ስርዓቱ ደካማና ግልብ መሆኑ ግልጽነት ከጎደለው (ነፃ ውይይት የሌለው) የልጅ አስተዳደጋችን ጋር ተያይዞ ትውልዱ በ“ሥልጣኔ” ሥም ለመጤ የምዕራቡ ዓለም ባህል አደግዳጊ ሆኗል፡፡ ግብረሰዶማዊነት ይበልጥ እንዲስፋፋ በምዕራቡ አለም አገራት እና በእነርሱ ተፅዕኖ ሥር ባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጠቀም ያለ የበጀት ድጋፍ የሚደረግለት መሆኑ ደግሞ ትውልዱን ተጋላጭ አድርጎታል፡፡
ግብረሰዶማዊነትና ትስስሮሻቸው በአዲስ አበባ
አዲስ አበባ የፖለቲካ ከተማ ብቻ አይደለችም፡፡ የአገሪቱ የኢኮኖሚ የደም ሥር እና የማህበራዊ ዕድገትና ኪሳራ ማሳያ ጭምር ናት፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ አገሪቱ አማራጭ የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም፣ …. ከተሞች የሏትም፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሁሉ ነገር ነች፡፡ ምናልባትም ከተማዋ በጉያዋ ከያዘቻቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች አኳያ “የኢትዮጵያ ችግር ዞሮ መጀመሪያ” ብንላት ገላጭ አረፍተ ነገር ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ከአዲስ አበባ ይነሳሉ፤ የአገሪቱ ችግሮች ሁሉ አዲስ አበባ ላይ ዙረው ያርፋሉ፡፡ ከአገሪቱ ማህበራዊ ዘርፍ ተጠቃሽ ችግሮች አንዱ ግብረሰዶማዊነት ሆኗል፡፡ ከየትኛውም የአለም ጫፍ የሚመጡ ግብረሰዶማዊያን በአገሪቱ ዉስጥ በአንፃራዊ ነፃነት የሚንቀሳቀሱባት ከተማ አዲስ አበባ ነች፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ የግልና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ የግል ት/ቤቶች በተለይም ወንድ ተማሪዎች ብቻ ተለይተው በሚማሩባቸው የካቶሊክ ት/ቤቶች፣ የመዋኛ ገንዳዎች፣ ሲኒማ ቤቶች፣ የቀን ዝግ ጭፈራ ቤቶች (ፓርቲዎች)፣ የተመረጡ የምሽት ክለቦች፣ … በዋናነት ግብረሰዶማዊያኑ አጋሮቻቸውንና ከዚህ ሕይወት ውጪ ያሉ ዜጎችን የሚያጠምዱባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ግብረሰዶማዊያኑ ርስ በርሳቸው “ዜጋ” በሚል የጋራ መግባቢያ የኮድ ስም ይጠራራሉ፡፡ ከግብረሰዶማዊነት ህይወት ውጪ ያሉ ሰዎችን ደግሞ “ቀጥ” (በእንግሊዝኛ straight የሚባለውን) በሚል መጠሪያ ሥም ይጠሯቸዋል፡፡ በአንፃሩ ግብረሰዶማዊ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ግብረ ሰዶማዊያኑን “ቡሽቲ” ሲሉ ይጠሯቸዋል፡፡
ግብረሰዶማዊያኑ እርስ በእርሳቸው “ባሌ” እና “ሚስቴ” በመባባል ይጠራራሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ የአብሮነት ቆይታቸው ከሦስት ወር በላይ አይቆይም፡፡ አንዳንዶች ከአንድ ጊዜ ግንኙነት በላይ ድጋሚ መገናኘት አይፈልጉም፡፡ ድጋሚ የሚገናኙትም በወራት ልዩነት በመሰላቸት ይለያያሉ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በዚህ ሕይወት የሚኖሩ ታዋቂ አርቲስቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራንና ጋዜጠኞች ራሳቸውን ሸሽገው ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ግብረሰዶማዊነት በአገሪቱ ህግ ተቀባይነት እንዲያገኝ አምባሳደሮችንና ዲፕሎማቶችን ከመወትወት ጀምሮ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
በከተማዋ ውስጥ ግብረሰዶማዊነት በአስገራሚ ፍጥነት መስፋፋቱን ቀጥሏል፡፡ የመስፋፋቱ ማሳያ ሆኖ የሚቀርበው ደግሞ ግብረሰዶማዊነትን እንደገቢ ምንጭ የሚጠቀሙበት ወንድ አዳሪዎችና (male prostitutes) እና አገናኝ ደላሎች በተጠና የጋራ መግባቢያ ኮድ ሥራቸውን የሚሰሩ መሆናቸው ነው፡፡ በተለይም በዚህ ህይወት የሚኖሩ በዲፕሎማትነት፣ በዓለም አቀፍ ድርጅት ሰራተኛነት፣ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ተሳታፊነት፣ በጉብኝት፣ በጥናት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመምህርነት፣ ወዘተ ወደኢትዮጵያ የሚመጡ የውጪ አገር ዜጎችን በአስጎብኝዎችና በአገናኝ ደላሎች አማካይነት ወንድ አዳሪዎችን ፈልገው የሚያቀርቡ ደላሎች ጠቀም ያለ ገንዘብ ያገኛሉ፡፡
“ባል” ወይም “ሚስት” መሆን የሚችሉ ሁለት አይነት ወንድ አዳሪዎች አሉ፡፡ አቀራረቡ እንደ ፈላጊው ባህሪ ይወሰናል፡፡ በዚህ ህይወት ውስጥ ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችም የዚህ መሰል የግብረ ሰዶማዊያን ገበያ ትስስር ተሳታፊ ናቸው፡፡ በአብዛኛው የውጪ አገር ዜጎች በሚያርፉበት ትልልቅ ሆቴል በየሆቴሎች ባሉ ወኪሎች በኩል ወንድ አዳሪዎች ይቀርባሉ፡፡ የውጪ አገር ዜጎችን ቋሚ ደንበኛ ማድረግ ባይቻልም በቆይታቸው የሚያስደስቷቸው ወንድ አዳሪዎች ለወሮታቸው ውድ ስጦታዎችንና ጠቀም ያለ የገንዘብ ክፍያ ያገኛሉ፡፡
በዚህ ሕይወት ውስጥ ያሉ ኗሪነታቸውን በከተማዋ ያደረጉ የውጪ አገር ዜጎች በወንድ አዳሪዎች አቅራቢ ደላሎች በኩል እንደምርጫቸው የፈለጉት ወንድ አዳሪ ይቀርብላቸውል፡፡ የደላላውን ክፍያ ሳይጨምር ለአንድ ቀን አዳር እስከ 5,000 ብር ይከፍላሉ፡፡ የእረፍት ቀናቸውን እንደ ሶደሬ፣ ቢሾፍቱ፣ ሐዋሳ፣ . . . ባሉ ሪዞርቶች የሚያሳልፉ ከሆነ ደግሞ ወንድ አዳሪዎቹ እስከ 15,000 ብር ድረስ ተከፋይ ይሆናሉ፡፡ ደላሎቹ ደግሞ ከሁለቱም ወገን የኮሚሽን ክፍያቸውን ይወስዳሉ፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ በግብረሰዶማዊነት ህይወት ውስጥ የሚኖሩ ወጣቶች በቀን ፓርቲዎችን በማዘጋጀት፣ የምሽት ክለቦችን በዝግ በመያዝ፣ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለዚህ ዓላማ ብቻ በመከራየት ያሻቸውን ድርጊት ይፈፅማሉ፡፡ ድርጊቱ “የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት” እስከ መፈፀም ይደርሳል፡፡ ግብረሰዶማዊያኑ በአብዛኛው በምሽት የተሻለ ነፃነት የሚያገኙ ቢሆንም፤ ቀን ላይ ከላይ በተመለከቱ ሁኔታዎች ፍላጎታቸውን ያሟላሉ፡፡ የፌስቡክ፣ የዋትስኧፕ፣ የቫይበርና መሰል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ግሩፕ በመፍጠር የግንኙነት ሠንሰለታቸውን የሚያጠናክሩት ግብረሰዶማዊያኑ በአካል ባይተዋወቁ እንኳ በአለባበስ መናበብ (መተዋወቅ) ይችላሉ፡፡
ፀጉራቸውን በቅባት ማሳመር፣ ጆሯቸውን በመበሳት ጌጣጌጥ ማስገባት፣ ቅንድባቸዉን በስሱ መቀንደብ፣ ከንፈርን ፈዘዝ ያለ ቀይ ቀለም (ቻፒስቲክ) መቀባት፣ ጥብቅ ያለ ቦዲ ቲሸርትና ጠባብ ስኪኒ ሱሪ መልበስ፣ በጣም አጭር ካልሲ ቀለል ካለ ጫማ ጋር መጫማት የወንድ አዳሪዎች የአለባበስ መለያ ባህሪ ነው፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ የማይተዋወቁ ግብረሰዶማዊያን ርስ በርሳቸው ለመተዋወቅ ገላጭ የሆነውን አለባበሳቸውን በመልበስ በትልልቅ ሆቴሎች፣ ካፌዎች፣ መዋኛ ገንዳዎች፣ ሲኒማ ቤቶች ይገኛሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እግራቸውን በማነባበር ይቀመጣሉ፡፡ እጃቸውን በአነባበሩበት እግራቸው ውስጥ በማስገባት ቢጤቸውን በምልክት ይፈልጋሉ፡፡
ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ቦሌ፣ ሳሪስ፣ መካኒሳ፣ ጎተራ፣ ሲ.ኤም.ሲ.፣ ሃያ ሁለት፣ ካዛንቺስ፣ ገረጂ … በተለየ ሁኔታ ግብረሰዶማዊያን የሚገናኙባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ መገናኛ ቤቶቹ ካፌ፣ ሆቴል፣ ሲኒማ ቤት፣ ግሮሰሪ፣ የምሽት ክለቦች፣ የኮንደምኒየም ቤቶች፣ … ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በተለይም ቦሌ ከሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ ያሉ ደብዛዛ የምሽት ቤቶች፣ ኤድና ሞል ሲኒማ፣ አትላስ፣ ፍሬንድሺፕ፣ ፍላሚንጎ፣ ወሎ ሰፈር፣ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀርባ፣ … ያሉ ሰፈሮች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ቦታዎች ናቸው፡፡ አምባሳደር የሚገኘው ፍል ውሃ መታጠቢያ አነስተኛ የሆነ የገቢ አቅም ያላቸው ግብረሰዶማዊያን “የቤተሰብ መታጠቢያ ክፍል” በመያዝ ፍላጐታቸውን የሚፈፅሙበት ተመራጭ ቦታ ሆኗል፡፡ ሃያ ሁለት አካባቢ ያሉ ፔንሲዮኖች ለተመሳሳይ ፆታ ለአጭር ጊዜና ለአዳር ለማከራየት ዓይናቸውን አያሹም፡፡ ጎተራ ኮንደሚኒየም እና ሲ.ኤም.ሲ. አፓርታማ ግብረሰዶማዊያኑ በብዛት ይገኛሉ፡፡
ግብረሰዶማዊነት በኢኮኖሚ አቅም፣ በዕድሜ ገደብ፣ በማህበራዊ መሰረትና መሰል ጉዳዮች የራሱን አጥር የሚሰራ ድርጊት አይደለም፡፡ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ፣ ከዓመታት የእስር ቆይታ በኋላ የወጡ፣ በአነስተኛ የገቢ ምንጭ የተሰማሩ ከታዳጊ እስከ አዛውንት፣ ከድሃ እስከ ቱጃር፣ ከመሐይም እስከ ምሁር ድረስ ያሉ ሰዎች የድርጊቱ ተሳታፊ ናቸው፡፡ አብዛኞዎቹ ግብረሰደማዊያን ተደፍረው ወደዚህ ህይወት የገቡ ቢሆንም አዲስ ነገር የማየት ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በዕድሜ አቻቸው ግፊት ወደዚህ መሰል ህይወት ይገባሉ፡፡ በእርግጥ ተገደው በመደፈር ወደዚህ ሕይወት የገቡት ቁጥር ይበልጣል፡፡ በነገራችን ላይ የወንዶችን ያህል ባይሆንም በሴቶች ላይም ተመሳሳይነት ያለዉ የሌስቢያን (ግብረገሞራውያን) ድርጊቶች ይፈጸማሉ፡፡
ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በተለየ መልኩ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው የዜጎች ፍልሰት ጨምሯል፡፡ በዚህ ፍልሰት ውስጥ ታዳጊ ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች ነፍሳቸውን ለማሰንበት አዲስ አበባ ውስጥ ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ሥራዎችን ሳይመርጡ መስራት ግድ ይላቸዋል፡፡ የትምህርትና የክህሎች እጦት ከመግባቢያ ቋንቋ እጥረት ጋር ተያይዞ ለታዳጊ ወጣቶቹ የአዲስ አበባ ህይወት ከባድ ፈተና ይሆንባቸዋል፡፡ የተለየ ዕውቀት የማይጠይቀውን የሊስትሮ ሥራ፣ ሸቀጣሸቀጦችን መሸከም፣ ከየመኖሪያ ቤቱ ቆሻሻ መሰብሰብ፣ ወዘተ መሰል በሆኑ ሥራዎች ይሰማራሉ፡፡
አብዛኛዎቹ ታዳጊ ወጣቶች የከተማዋን መግቢያ መውጫ ለይተው የማያውቁ በመሆቸው ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ በግብረሰዶማዊያኑ ጥቃት ሲደርስባቸው ይስተዋላል፡፡ ከጥቃቱ በኋላም ጥቃት የደረሰባቸው ታዳጊዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የማያውቁ በመሆኑ የደረሰባቸውን ጥቃትና የውስጥ ስብራት ታቅፈው ይቀራሉ፡፡ አንዳንዶቹን ታዳጊ ወጣቶች በአልባሳትና በገንዘብ በመደለል፣ ማስቲሽ (እንደ አደንዛዥ ዕጽ የሚያገለግል) እንዲስቡ በማድረግ፣ … ጥቃት ይፈፅሙባቸዋል፡፡
እንዲህ ያለውን የተቀነባበረ ወንጀል የሚያመቻቹ ደላሎች በቦሌ፣ ሲ.ኤም.ሲ፣ ሳሪስ ተፈልገው አይጠፉም፡፡ ደላሎቹ ዋነኛ ሥራቸው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች (በአብዛኛው ከደቡብ ኢትዮጵያ) ወደ አዲስ አበባ በቅርብ የመጡ ታዳጊዎችን በማፈላለግ “ሥራ ላስቀጥርህ” በሚል ወደ ጥቃት ፈፃሚው ግብረሰዶማዊ ቤት መውሰድና ማስረከብ ነው፡፡ በዚህ መሰል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ኑሯቸውን የሚገፉ ደላሎችን፣ ገደብ የለሽ ልቅ የወሲብ ፍላጎታቸውን የሚያረኩ ግብረሰዶማዊያንን አዲስ አበባ በጉያዋ ታቅፋ ይዛለች፡፡ ከተማዋ በጊዜ ሂደት በግብረሰዶማዊያን እየተወረረች ትገኛለች፡፡ ዝምታው በበዛ ቁጥር የችግሩ መፍትሔ እየራቀን ሄዷል፡፡
ምን ይሻላል?!
ከዚህ በላይ የቀረበው ዘገባ በመግቢያችን ላይ እንደጠቆምነው ተማሪ ዳዊት ተሰማና ጓደኞቹ አዲስ አበባ ላይ ያጠኑት ጥናት ለአንባቢ እንዲመች ሆኖ የተቀናበረ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 6/29 ግብረሰዶም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ተያያዥነት ባለው መልኩ አንቀጽ 6/32 ደግሞ በዚህ ተግባር ተሰማርቶ የተገኘ ከቀላል እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ያስቀጣል በሚል ተደንግጓል፡፡ ህግና ተግባር ለየቅል በሆኑባት ኢትዮጵያ የግብረሰዶማዊያን ጉዳይ ሆን ተብሎ የተዘነጋ ይመስላል፡፡ ለምዕራቡ ዓለም ለጋሽ አገራት ውትወታና ጫና እጅ የሰጠው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በራሱ ግፊት “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” የግብረሰዶማዊያን ጉዳይ በይቅርታ ከማይታዩ ወንጀል ነክ ጉዳዮች ወጥቶ በይቅርታ ከሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች አንዱ ሆኖ እንዲታይ አስወስኗል፡፡
ይህ ውሳኔ ቀድሞውንም በለዘበ አካሄድ የተያዘውን ግብረሰዶማዊነት ህጋዊ ዕውቅና ለመስጠት እንዳለመ መንደርደሪያ የቆጠሩት ግብረሰዶማዊያን ዛሬ ላይ በድብቅም ቢሆን “የጋብቻ ሥነሥርዓት” እስከመፈፀም የሚደርስ ድርጊት ለማከናወን ተደፋፍረዋል፡፡ ይህ ድርጊት ከገዥው ኃይል ቸልተኝነትና ተንበርካኪነት የመጣ ነው፡፡
ህወሃት በበረሃ ልምምዱ ከወሲብ ጋር በተገናኘ ምን ዓይነት ህይወት አባሎቹ እንዳሳለፉ ራሱን የቻለ ምሥጢር ነው፡፡ አሁን አገርን በግፍ እየገዙ ያሉት 17 ዓመታት በምን ዓይነት ልቅነት የበረሃውን ኑሯቸውን እንደገፉት ትናንሽ ፍንጭ ከመስማት በስተቀር ይህ ነው ተብሎ ከራሳቸውም ሆነ ከቀድሞ አባላቱ የተሰማ የለም፡፡ ሴቶቻቸውን ለሱዳን ባለሥልጣናት ወሲብ ማርኪያነት በስጦታ ያበረክቱ የነበሩት የህወሃት ሹሞች ከሰብዓዊነት ወርደው “ነውር” የሚባለውን ተግባር አልፈጸሙም ወይም አይፈጽሙም ማለት አይቻልም፡፡ አገር ለመገንጠልና ለማስገንጠል እኩይ ዓላማ ተግባራዊነት እብድ መስሎ ለመታየት ሲባል ሠገራ እስከመብላት የደረሱት የህወሃት “ጉምቱ” ኃላፊዎች ግብረሰዶማዊነት በኢትዮጵያ መስፋፋቱ ብዙም የሚያስጨንቃቸው ሊሆን አይችልም፡፡ ለዚህም ይመስላል “እንደ እኛ መስዋዕት ሆነህ፣ ታግለህ ድል አድርግ” እያሉ ሲናገሩ የሚሰሙት፡፡ ምናልባት ከሰዶማዊነት እስከ ሰማዕትነት የከፈሉትን “መስዋዕትነት” በሌላ ቋንቋ መናገራቸው ይሆናል፡፡
የሰውን ልጅ የመዋለድና ዘርን የማስቀጠል ሂደት አደጋ ላይ የሚጥለው ግብረሰዶማዊነት የኃይማኖት፣ የባህል፣ የወግና የሥርዓት የሞራል እሴቶችን ከመጣሱ ባሻገር ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ቀውስ የሚያስከትል እኩይ ድርጊት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባለች የራሷ ታሪክ፣ ባህል፣ ወግና ሥርዓት ያላት አገር የግብረሰዶማዊነት መስፋፋት አገሪቱን እንደ አገር ያቆሟትን አዕማዶች የሚንድ አፍራሽ ተልዕኮ አለው፡፡
የምዕራቡን ዓለም ተፅዕኖ በርን በመዝጋት መቋቋም አይችልም፡፡ ይሁንና የአገሪቱን ታሪክ፣ ባህል፣ ወግና ሥርዓት እንዲሁም የሞራልና የግብረገብ ግንባታ ትውልዱ ላይ መስራት ከተቻለ ግብረሰዶማዊነትንና መሰል እኩይ ድርጊቶችን ከህግ ጉዳይ በመለስ መከላከል ይቻላል፡፡
ትውልድ ከመጥፋቱ በፊት የኃይማኖት ተቋማት ግብረሰዶማዊነትን በጥብቅ አውግዘው ነውረኝነቱን በየቤተእምነቱ ሊያስተምሩ ይገባል፡፡ ወላጆች ከታዳጊ ልጆቻቸው ጋር፣ ወጣቶች ከአቻዎቻቸው ጋር ስለግብረሰዶማዊነት አስከፊ ገጽታ ነፃ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ት/ቤቶች “ፀረ-ኤድስ ክበብ” በሚል ስለ ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ ለተማሪዎች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚሰሩት ሁሉ ስለግብረሰዶማዊነት አስከፊ ገጽታ ለተማሪዎች ማስተማር ግድ ይላል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ጉዳዩን በሥርዓተ ትምህርት ደረጃ ማካተት ትውልዱ እንዳይጠፋ ያደርጋል፡፡ ከአስከፊው የግብረሰዶማዊ ህይወት ለመውጣት የሚጥሩትን ሊያግዝና ሊደግፍ የሚችል አገር በቀል የዕርዳታ ድርጅት ማቋቋምና በየሚዲያው ትምህርት መስጠት፣ በግልጽ መነጋገር የተሻለ መፍትሄ ያመጣል፡፡
እኤአ በ2014 ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ባተደቀችበት ጊዜ ጎልጉል ያስነበበው የዜና ዘገባ ነበር፡፡ “ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”፤ ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች! በሚል ርዕስ በታተመው ዜና ሥር የዑጋንዳን ውሳኔ አስመልክቶ የማኅበራዊ ጉዳይ ባለሙያ የሆኑ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል ይህንን አስተያየት መስጠታቸው ሰፍሮ ነበር፡፡“ኢህአዴግም ከየምዕራቡ ለሚለቃቅመው ዕርዳታ ብሎ የአገርን ባህልና ማኅበራዊ እሴት ከሚያጠፋ ይልቅ (እንደ ዑጋንዳ) ተመሳሳይ ተግባር ሊወስድ ይገባዋል፤ የተቃወመውን ሁሉ “አሸባሪ” በማለት በጸረ አሸባሪ ህግ ስቃዩን ከሚያሳይ የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በማውጣት ይህንን በአገራችን በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ወረርሽኝ መላ ሊለው ይገባል” ብለዋል ነበር፡፡
በእርግጥ በግብረሰዶማዊነት ዙሪያ እነዚህን መሰል ዘመቻዎች ለማካሄድ ኃላፊነት የሚሰማው “መንግስት” ሊኖር ይገባል፡፡ በአንፃሩ ትውልድን አስልሎና አምክኖ አገሪቱን ረግጦ የመግዛት ህልም ያለው ህወሓት/ኢህአዴግ ግብረሰዶማዊነትን በእስር ቤቶች ሳይቀር በማስፋፋት ላይ የተጠመደ በቀለኛ ገዥ ኃይል ነው፡፡ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን እስር ቤት ውስጥ በግብረሰዶማዊያን ተገደው እንዲደፈሩ የሚያደርገውና የቂምና የበቀል ድርጅት የሆነው ህወሓት ለአገዛዙ እስከጠቀመው ድረስ የግብረሰዶማዊነትን መስፋፋት ይፈልገዋል፡፡ ሞራሉ በእንደዚህ ዓይነት ልቅነት የከሸፈ ትውልድ ከአደንዛዥ ዕጽ ሱሰኝነት ጋር ተቀላቅሎ ግፍን የሚቃወምበት ኅሊና አይኖረውም፡፡ በዚህ ዓይነት የላሸቀ ትውልድ እንኳን ግፈኛ ሥርዓትን ለመቃወም ሱሪውን ከፍ አድርጎ ለመልበስ ዓቅም የሌለው መሆኑን ህወሃት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የህወሃቶችና ደጋፊዎቻቸው “ገና ሞቶ ዓመት እንገዛኻለን” ፉከራ እንዲህ ዓይነቱን የራሳቸውን መሠሪነት ከማወቅ የመነጨ ይመስላል፡፡ መፍትሔው እንደ ሰዶማዊነት ያሉትን የችግሩን ውጤቶች ከመታገል ባሻገር የችግሩን ምንጭ ማድረቅ ሲቻል ነው፡፡ (መግቢያ ፎቶ የግብረሰዶማዊነት ደጋፊዎች በኬኒያ AP Photo/Ben Curtis).
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Selam says
Let me tell you something, people like you who try to oppose the government based on fabricated stories aimed at the most vulnerable group the society only make people like us have no option but keep on supporting this regime even though we know it’s not the best.
If you do not understand about homosexuality fine but spreading hate and campaigning for people to stand up and commit violence against these vulnerable people is beyond any ignorance level. Sexuality is a complicated issue but religiously blind people like you can’t understand that.
My point is, using the issue of homosexuality as a weapon to oppose the government can only led to more support to it… because this issue is very personal to many individuals and you have no idea how many these individuals are.
Stand says
When there is no ever production it is not sex it is just a moral weakness. They need help. I will support in helping them not bring to them to destroy the LIFE of MARRIAGE.
zegoch says
Now, this is pure garbage fabricated by one who
1. has too much time on his/her hand,
2. lazy enough not to do the leg work needed to even remotely qualify as investigative journalism,
3. is probably himself a self-hating individual (maybe a closeted gay) who somehow manages to square it that he is doing good by spreading misinformation and hatred
Now, as far as this site goes, now I fully realize that you are nothing but a breeding ground for hatred and you just making your way to the gays.
Please, live and let live, why do you care, and don’t drag to me about the core fabric of the society and so on, because that dear you (giving you the benefit of the doubt that you are a hetro) eroded long before gay became ended up at your cross-hair.
Good luck with such admirable mission.
አዲል አህመድ says
በአዲስ አበባ ሆነ በሌላ ክልል ግብረሰዶማዊያን ማለት ምን እንደሆነ ብዙ ሰው አልተረዳውም :: ስንት አባቶች እና አያቶች ለዘመናት ታፍነው የኖሩ አሁን ከመንግስቱ አገዛዝ መገርሰስ በሁዋላ ለጋ ልጆች ምስራቸውን እንደምናወጣላቸው እንደነበረ ብታዩ እንደ አዲስ ነገር አሁን አይዘገብም ነበር:: አዲስ አበባ ስታድዮም ዙርያ ወይም የስታድዮም ሰልፍ ላይ ይህ ማለት እንደ የትም ሃገር በአገራችን ግብረሰዶማዊያን የሆንን አግብተን ወልደን ተከብረን አንኖርም ማለት አይደለም:: በየስራ ቦታ ወይም በየ ሌላ ቦታው ግብረሰዶማችንን አድርገን ቤት ስንገባ ሚስት ልጅ እናስተዳድራለን:: በነገራችን ላይ ናዝሬት ትምህርት ቤት ፒያሳ ወይም እቴገ መነን አዳሪ ትምህርት ቤት ደግሞ ዋና የሴቶች ግብረሰዶም መናሀርያ ነበር ገና መንግስቱ ሳይገረሰስ ጀሞሮ እስከ አሁን ድረስ ሁሉም ሲያድጉ አግብተውም ቢሆን መላላሳቸው እንዳለ ነው:: ስለዚህ እንደ አዲስ ነገር ታፍኖ የነበር አሁን አላልታፈነ ብቻ ትውልድ ችግር አደጋ አለበት ማለት ስህተት ነው:: እንድያውም ትውልዱ በራሱ አባት ወይም እናት ተለማምዶ ከዛ በሁዋላ አዲስ ነገር አልሆነበትም :: ፍየል ያልነካ የለም አዲስ ነገር ሆኖበት በታፈነው ዘመን :: አሁንም ቢሆን በፍየል የሚለማመደውን ማን ይዘግበው?
Samuel says
What vice will the Tigre occupation army that was installed by Ethiopia’s historical enemies fail to soil the moral foundation of the Ethiopian society?
It is incumbent on TPLF to wage an all-out war on everything Ethiopian. The unfettered prostitution and now transactional homosexual practices are part of its destructive scheme. Only the total annihilation of this evil force can redeem what is left of our country.
abu hameza says
እነኝህን የፈላ ዘይት ውስጥ መጨመር ነው፡፡ እነሱን መግደል ወንጀል አይደለም፡፡
Kalkidan E says
This is very ignorant i support lgbt stop hating on them!!!