• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዶ/ር ዓቢይን “መጨረሻ ለማየት ቢያንስ ስድስት ወራት እንጠብቅ”

April 22, 2018 11:40 am by Editor 4 Comments

ዶር. ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ በኢትዮጵያ መድረክ ላይ መታየት ሲጀምሩ ኢትዮጵያ የተአምር አገር መሆንዋን አስታወስሁና እግዚአብሔር ፊቱን ወደኢትዮጵያ መመለሱን ተረዳሁ፤ ከዚያም በላይ ያለፈው ጠቅላይ ሚኒስትር እናቱን በመውቀስና በመመጻደቅ ጀመረ፤ አዲሱ ደግሞ እናቱን በማወደስ መጀመሩ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ያለውን እምነት በአደባባይ ደጋግሞ በመግለጹ አከበርሁት፤ አከብረዋለሁ።

ከዚህ በፊት ሦስት ጊዜ በፌስቡክ የጻፍሁትን ልድገመው፤

አንድ፤ በ1965 በወሎ ችጋር ዘመን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች እርዳታ ለማድረግ በምንሯሯጥበት ጊዜ አንዳንድ የኢሕአፓ አባሎች ለተራቡት እርዳታ መሰብሰብ አብዮቱ እንዳይመጣ ማድረግ ነው እያሉ ይቃወሙን ነበር፤ ነፍሱን ይማረውና አብርሃም ደሞዝና እኔ ተቆጥተንና አስፈራርተን አደብ እንዲገዙ አድርገናቸው ነበር፤ ዛሬ ደግሞ በዓቢይ ሹመት መደሰቴን በመግለጼ የሚሳደቡ አሉ፤ ስለዓቢይ የጻፍሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆኑ በፊት ነበር፤ አሁን ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆን ያደረገውን ንግግር አዳምጫለሁ፤ ስለዚህም ቀድሜ በተናገርሁት እጸናለሁ፤ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ አረመኔ አይደለም።

ሁለት፤ በአሁኑ ጊዜ በዶር. ዓቢይ ላይ ብዙ ቅሬታዎች ይሰማሉ፤ ለእኔ እንደሚታየኝ ሁለት መነሻዎች ያሉ ይመስለኛል፤

አንዱ መነሻ ዓቢይ የተመረጠበት ሁኔታ ከወያኔ (ኢሕአዴግ) መመሪያ የወጣና ወደአልተሸበበ ነጻነት የሚያመራ መስሎ መታየቱ በወያኔ መንደር ሽብር እንደሚያስነሣ ሳይታለም የተፈታ ነው፤

ሁለተኛው የተለመደው የኢትዮጵያውያን የፖሊቲካ ባሕርይ ነው፤ የተፈለገው ለውጥ እስኪመጣ ድረስ ከመጠለያ ስር አሾልከው እያዩ ከደመናው በላይ ወጥተው የጠራ ሰማይ ለማየት የሚሞክሩ ናቸው፤ የደመናው ግርግርና ሽብር አይመለከተንም የሚሉ ይመስላሉ፤

ዓቢይ አንድ ሰው ነው፤ ዓቢይ ከነቡድኑ ትንሽና ደካማ ነው፤ ይህንን እውነት መገንዘብ ከተመልካችነት ወደቆራጥ ተሳታፊነት መሸጋገርን ይጠይቃል፤ የሚያስፈራውና የዳር አጨብጫቢነትን የሚጋብዘው ይህ ነው፤ የዳር አጨብጫቢነት ውስጥ ያሉት ሁሉ ወደተግባር ተሳታፊነት ቢሸጋገሩ የዓቢይ ዓላማ የማይሳካበት ምክንያት የለም፤ ካልሆነም ለድጋፍ የተገኘው ኃይል የታወጀውን ለመጠበቅም ይረዳል።

ሦስት፤ ዶር. ሰማኸኝ፣ ያለህ ስጋትና ጥርጣሬ ይገባኛል፤ ነገር ግን ያለነው 27 ዓመታት ሙሉ ውል በሌለው በዘፈቀደ የተገመደ የመሀይሞች የፖሊቲካ ውስብስብ ውስጥ ነው፤ አንድ በልልኝ፤ ዓቢይ የኦህዴድ ሙሉም ባይሆን ሰፊ ድጋፍ አለው፤ የኦህዴድን ቅርጽም ልብ ብለህ ግንዛቤህ ውስጥ አስገባው፤ ሁለት በልልኝ፤ ከዚህ በተረፈ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች (በስም የማላነሣቸው አውቄ ነው፤) ሊኖር የሚችለውን ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ዓቢይ 27 ዓመት ሙሉ በወያኔ የተፈተለውን የመንደር ፖሊቲካ መጋረጃዎች ሁሉ ቀዳዶ ሰው መሆንን ከኢትዮጵያዊነት ጋር ማዛመዱን ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፤ ይህ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ በኃይል ስቧል፤ ሦስት በልልኝ፤ የዓቢይን ልምዱንና ትምህርቱን ስናይ ለየዋህነት ቦታ ያለ አይመስለኝም፤ ከጎኑ ለማና ጓደኞቹም አሉ፤ አራት በልልኝ፤ አሜሪካም ደግፎታል፤ አምስት በልልኝ!

*****************

ዶር. ዓቢይ በተለያዩ ስፍራዎች ያደረጋቸውን ንግግሮች በጥሞና አዳምጫለሁ፤ በተለይም ከሀብታሞች ጋር፤ አንድም ቦታ ሀሳቡ ሲደናገር ወይም ሲዛነፍ አልሰማሁም፤ በዚህም የእውቀቱን ስፋት፣ የአእምሮውን ምጥቀት፣ የኅሊናውን ጽዳት፣ የወኔውን ብርታት፣ የዓላማውን ጥራት፣ የዘዴውን ሥልጡንነት በጣም እጅጉን አደንቃለሁ።

ለእኔ ኢትዮጵያ የሰውም ሆነ የአእምሮ ችግር ኖሯት አያውቅም የሚለውን እምነቴን አረጋግጦልኛል፤ የአገዛዝ ጫማ የኢትዮጵያውያንን ራስ ጨፍልቆ ረግጦ አመከነው እንጂ አለን፤ ደርግ ከአገዛዝ አወጣችኋለን ብሎ አሥራ ሰባት ዓመት ረግጦ ገዛን፤ ወያኔ ከደርግ አገዛዝ አወጣችኋለን ብሎ ይኸው እየረገጠ ሲገዛን ሠላሳ ዓመታት ሊሞላው ነው፤ አሁን ዶር. ዓቢይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳ ወደአዲስ አቅጣጫ ሊመሩን የተዘጋጁ ይመስላሉ።

ዶር. ዓቢይና አቶ ለማ በየትኛው መንገድ እንደሚመሩን ገና በትክክል ባናውቅም መድረሻቸው አሁን ካለንበት የተለየ እንደሚሆን ግልጽ አድርገዋል፤ ይህ አስተያየታቸው ተቃራኒ የሰላም ጥያቄዎችን አስነሥቷል፤ ሰላም ምን ማለት ነው? በቀላል ምሳሌ ለማስረዳት፤ … የዓየር አለመኖርና አደገኛነቱ የሚታወቀው ዓየር ሲታጣ ነው፤ ዓየር ሳይኖር ሞት፣ ሰላም ሳይኖር ሞት ነው፤ ጸረ ሰላም የሚሆነው ሬሳን ማንቃት ነው? ወይስ ሞትን ማወጅ? ሬሳን ማንቃቱን አብዮተኛነት የሚሉት አሉ፤ ሞትን ማወጅን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሉት አሉ፤ በሁለቱም በኩል ለሰላም የሚደረገው ጩኸት ሰላምን የሚነሳ ነው፤ የሰላም ጠንቅ ሆነው ሰላምን መሻት የአገዛዝ ማዘናጊያ ዘዴ ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳለ ነው፤ ሆኖም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹም-ሽር አድርጓል፤ በዚህ ሹም፣ሽር የወያኔ ቀኝ እጅ የሚታይ አይመስልም፤ ሆኖም ሹም-ሽሩ የዓቢይ የመጀመሪያ ደረጃ እርምጃ መሆኑ ነው፤ ለእኔ ቅር ያለኝ የሴቶች ቁጥር ማነስ ነው፤ በመጀመሪያው የወያኔ ስብሰባ ላይ ወያኔ አንድም ሴት አልነበረውም፤ ይህንን ጉዳይ ለመለስ ዜናዊ አንሥቼበት ነበር፤ በግዮን ሆቴል አንዲት (እንደነገረችኝ) የአሥራ አራት ዓመት ልጅ ቁመትዋን የሚያህል ጠመንጃ ተሸክማ አየሁ፤ አነጋገርኋት፤ ብዙ እንደእስዋ ያሉ ሴቶች ልጆች ነበሩ፤ በሐምሌው ጉባኤ ላይ አልተወከሉም ነበር፤ መለስ ዜናዊ ስሕተት መሆኑን አምኖ እንደሚታረም ነግሮኝ ነበር፤ በዚህ በኩል የዓቢይም ሹመት ከመለስ ዜናዊ እምብዛም አልተሻለም።

አሁን በዓቢይ ላይ ከየአቅጣጫው የሚወርደው የነቀፌታ ናዳ “የአብዮታዊነት ውጥረት” ከስድሳዎቹ እየተወራረሰ የመጣ የኩርፊያ ውጤት ይመስላል፤ የአጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ሲወድቅ ስንት ወራት እንደፈጀ የማያስታውሱ ወይም የማያውቁ ሰዎች ዛሬ በሃያ አራት ሰዓት ለውጥ ማየት ይፈልጋሉ፤ ያውም እንደወያኔ ያለውን መዥገር ለማላቀቅ! በየካቲት 1966 ጸሐፌ ትእዛዝ አከሊሉ ስንብት አቀረቡ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ጀኔራል ዓቢይ ታጩ፤ ልጅ እንዳልካቸው ተሾመ፤ አልቆየም፤ በልጅ እንዳልካቸው ተተካ፤ ከዚያ በኋላ ጀኔራል ተፈሪ በንቴ፣ ጀኔራል አማን ሚካኤል አንዶም ወንበሩ ላይ ለአጫጭር ጊዜዎች ወጥተው ወረዱና ኮሎኔል መንግሥቱ እስቲኮበልል ድረስ ተቀመጠበት።

ዓቢይ ገና መጀመሩ ነው፤ ራሱ እንደተናገረው “የመጀመሪያ” ሥራውን እየሠራ ነው፤ ገና አንድ እግሩን ብድግ በማድረግ ላይ ነው፤ መሮጥ ቀርቶ መራመድ አልጀመረም፤ ሊጠልፉት ያደፈጡ ብዙዎች ሳይሆኑ አይቀሩም፤ በያለበት እየዞረ ንግግር የሚያደርገውም ከአደገኛ ጥልፊያ ለመዳን ወገኖችን በመፈለግ ይመስለኛል፤ እኔ እንደምገምተው በዶር. ዓቢይ ላይ የከረረ ነቀፌታ የሚሰነዝሩት የቅርብ ደጋፊዎች ሊሆኑ የሚችሉት ይመስሉኛል፤ እንደተገነዘብሁት እስካሁን ዶር. ዓቢይ የነካው ቁስል በአጠቃላይ የወያኔን ሥልጣን፣ በተለይ ደግሞ የአማራን የወልቃይት አካል ነው፤ (በነገራችን ላይ የወልቃይት-ጠገዴ ጉዳይ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በቱርክና በግሪኮች መሀከል በቱርክ የተሠራው ሸርና እስከዛሬ ሙሉ በሙሉ ያልተፈታው ችግር ግልባጭ ነው፤) ከጎሠኛ አመለካከት ከተወጣ ሁለቱም ሕመሞች የሚከስሙ ናቸው።

የዜግነት ጉዳይ ያልገባቸው ፖሊቲከኞች ዛሬም ያሉ ይመስላል፤ የአንድ አገር ሕዝብን በዘር፣ በጎሣ፣ በሃይማኖት፣ በሥራ፣ ወይም በሌላ ማናቸውም ነገር ሳይሆን በሕግ ብቻ እንደዜጋ አንድ ሆነው የሚቆሙ ናቸው፤ ዜግነት አንድን ሰው የአንድ አገር ሕጋዊ ባለቤት ያደርገዋል፤ አንድን ሰው ከሌሎች የዚያው አገር ዜጎች ጋር የአገር ሉዓላዊነትን እንዲጋራ ያደርገዋል፤ የአንድ አገርን ሕዝብ በሙሉ በአንድ የተደለደለ መድረክ ላይ ሊቆሙ ይገባል ብንል በዜግነት ነው፤ በሕግ ተሳስረዋልና በአንድ ዜግነት በቆሙ ሰዎች መሀከል የሕግ ልዩነት የለም።

ገና ከአሁኑ በዓቢይ የቀናት አገዛዝ ጥሩ የለውጥ አዝማሚያዎች ይታያሉ፤ ዋናው በዜና ማሰራጫዎች ላይ የሚታየው ነው፤ በዚያው መጠን ሕዝቡም በነጻነት ሀሳቡን የመግለጽ ልምምድ የሚያደርግ ይመስላል፤ በዜና ማሰራጫዎቹ በኩልም የማታለሉ ዘዴ እየቀጠለ ይመስላል፤ በአንድ በኩል የነጻነት በር ሲከፍቱ በሌላ በኩል በር ይዘጋሉ፤ ለምሳሌ የሕዝብን ድምጽ ለማሰማት በሚል ሰበብ ከመንገድ የሚመርጧቸው ሰዎች እነሱ የሚፈልጉትን መልስ የሚሰጡትን ብቻ ይመሰላል።

መጨረሻውን ለማየት ቢያንስ ስድስት ወራት እንጠብቅ።

(ይህንን ጽሁፍ ፕ/ር መስፍን ጠቅላይ ሚኒስትሩና የኢትዮጵያ ፖሊቲካ በሚል ርዕስ ያወጡት ሲሆን ርዕሱን የቀየረው ጎልጉል ነው – መግቢያ ፎቶ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በጎንደር ከተማ ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት ሲያደርጉ)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ሚያዝያ 2010

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: abiy, Ethiopia, Full Width Top, lemma, Middle Column, prime minister

Reader Interactions

Comments

  1. Ezira says

    April 23, 2018 08:54 pm at 8:54 pm

    አዬ ፕሮፌሰር!
    6 ወር እንቆይ አሉ..? ነገሩ እንዲያ ቢሆንማ የኢትዮጵያ ህዝቦች የማንንም ምክር ሳይጠብቁ ዶ/ር አብይ በሹመተ በዓላቸው ጊዜ በ 30 ደቂቃ ውስጥ 39 ጊዜ ኢትዮጵያን በመጥራታቸው ብቻ ” መሲሁ” መጣ ብሎ Unconditional ህዝብ እጁን ዘርግቶ ተቀብሏቸው ነበር። ህዝባችን ቂመኛ አይደለም። ይሄንን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በ 2005 ምርጫ ወቅትም አይተዉታል የህዝባችንን ትእግስት። የህዝባችን ትእግስት መቼም ወደር የለወም። ለህዝባችን ምስጋና ይግባው። ነገር ግን እጅ አመድ አፋሽ ነው እደተባለው ሁሉ ፡ የዶ/ር አብይ አመል እርሶ እንደሚሉት 6 ወርንም የሚያስጠብቅ ሆኖ አልተገኘም ። “አመል ያወጣል ከመሃል ” እንደተባለው 1 ወርም ሳይሞላቸው ፡ ድመት መንኩሳ ….ዓመሏን አትረሳ ሆኗል ነገር ዓለሙ። እኔ እስከ ዛሬ ድረስ እርስዎ በሚያቀርቡት ሃሳብ ላይ ( ኢትዮጵያን የሚጎዳ ሆኖ እያለም) አንድም ቀን እንኳ በእርስዎ ላይ አስተያያት ሰንዝሬ አላውቅም። ይሄንንም ማድረጌ ለእርስዎ ባለኝ ትልቅ ክብር የተነሳ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የዚህ አገዛዝ ሲኦልነት የሚጠብሰን በተለይ እኛ ወጣቶቹን ነን። አንድ ወቅት እኮ እርስዎም 3 ትዉልድን የሚያሰቃይ ብለውት ነበር ዳኛ ብርቱካን መዲቅሳን ባሰረ ጊዜ ። አገዛዙ ምን የተለወጠ ነገር አመጣ ከዚያ በኋላ – ባሰበት እን። እኛ ቁስላችንን እና ህመማችንንም እናውቀዋለን። ከዚህ ቀደምም ከአንዴ 2 ሶስት ጊዜ”እንያቸው” መሰል አስተያየት ስጥተው ይሄ አስተያዬትዎ በተግባር ተፈትኖና ታይቶ አገራችንንና ህዝባችንን አያስከፈለና ህልውናዋንም እየተፈታተነ 27 ዓመት ጊዜ ሰጠተንተሜልከተነዋል፡ አስቃይቶናል።። ታዲያ ዛሬም ይሄንኑ የሲኦል ኖሮ ነው እንዴ ጊዜ እንስጠው የሚሉን ፕሮፌሰር…? ወጣቶቹ አናሳዝነዎትም ? እሬቻ ላይ እኮ የረገፈው ወጣትና ና የፈሠሠው ደም የእኛ የወጣቶች እንጅ የፋሳካ በሬ ደም አይደለም። ለዚህ ሲኦል አገዛዝ “ጊዜ እንስጠው” ማለት ኢትዮጵያን እንደጀመሩት አፈራርሰው ይጨረሷትና አገር አልባ ያድርጉን እንደማለት አድርርጌ ቆጥሬዋላሁ – የአስተያየተዎን ይዘት ።

    ፕሮፌሰር መስፍን ከይቅርታ ጋር!
    እርስዎ አሁን እድሜው ወደ 90ው ዓመት እየተጠጉ ነው። የርስዎን ዘመን ኖረው አሁን ደግሞ የእኛን ዘመን ነው የሚኖሩት። ከእኛ ዘመን እድሜ ተበድረውም እስከአሁን በህይወት መኖርዎም ፈጣሪ የተመሠገነ ይሁን። ይሄንን ላደረገልዎ ፈጣሪና ተመሠገን ብለው ወደ አመላክ መጠጋትም እኮ መታደል ነው እና ጊዜውም አሁን ነው። የእኛ ዘመን ደግሞ የተሻለ ይሆን ዘንድ የምናደርገዉን ትግል እና ተሰፋችን በእኛው እጅ ላይ ይገኛል። እስከምንችለው እየታገልን ነውና ይሄንን ትግላችን እና ተስፋችንን ባታጨልሙብን ደግሞ የተባበራችሁን ያህል እንቆጥረዋለንን እና እባካችሁ ወጣቶችንም አዳምጡን፤ አክብሩንም። እኔ የትግሬው ወያኔ ሲገባ የ 5 ዓመት ልጅ ነበርኩ። ዛሬ 34 ዓመቴ ነው። ( 2 ዓመት ሳላልኖርኩበት) ቀንሸው ነው። እርስዎ ግን በኢትዮጵያ STANDARD አንድ ኢትዮጵያዊ በህይወት የሚኖርበት የእድሜ ዘመን ተሻገረው በህይወት በመኖርዎ ፈጣሪን ማመሠገን ሲገባ ከእድሜው በላይ (የእኛን ዘመን ሁሉ ኖሮዎ) አሁን ደግሞ እኛ በትግሬው ወያኔ አገዛዝ በገዛ አገራችን እንደ ባዕድ በምንታይበትና እንደ 2ኛና 3 ዜጋ በተቆጠርንበት ሁኔታ ከዚህ አገዛዝ የወጡትን ግለሰብ ዶ/ር አብይን ” ጊዜ እንስጣቸው” ብለው ምክር መሣይ ለእኛ ሲሰጡ በእዉነቱ አሳዝኖኛል። የወጣቱ መከራና ቁሰል እርስዎን የቆነጠጠዎ አልመሠለኝም። ድግሞ እኮ ይሄ ዘመን የኛ ዘመን ነው። በዘመናችን የሚያጋጥመንን ማንኛውም challenge Discover አድርገን ወደ መፈትሄው የምንሄድበትን መንገድም ለመተለም መንገዳችንን ተስፋችንን ሁሉ ባታጨልሙብንስ? የእናንተን ዘመን ኖራችሁበታል። ዶ/ር አብይ ለቃላቸው ተገዥ ሆነው ለመቆየት የጠየቃቸው ጊዜ 1 ሳምንት ብቻ ነበር። ከ1 ሳምንት በኋላ ግን የደበረ ሠይጣን ገብረ ሚካዔል የደደቢት መተት፤ እጁን እና ልሳኑን ቆልፎ ያዘው። እርስዎ ይሄንን ለመረዳት እና ለመገንዘብ 6 ወር የሚያስፈልገዎ ከሆነ ለእርስዎ ፈቅደንለዎታል፡ መብትዎም ነው። ግን ለእኛ ለሚዳሰስን እና ለሚታይ እዉነታ “በጊዜ እንሥጣቸው” ሽፋን ባርነትን ተከናንቦ እንደ ደደቢቶች የድንቁርና እብሪት “ወርቅ”ነን ለማለት መዳዳት “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” ነው ነገሩ። ዶ/ር አብይ ደግሞ አሁን በየክልሉ እየዞሩ ህዝብ ሲያነጋግሩ ህዝብ ከ1 ቀን በላይ ያልዘለለው ንግግርዎና ተግባሮዎ አልተገጣጠመም እያለ ሲሞግታቸው ፤ ህዝዝብ የሚጠይቃቸው ጥያቄ እና እሳቸው የሚመልሱት መልስ አራምባ እና ቀቦ ሆኖ መልስ መስጠት እስኪቸግራቸው ደረስ ውሃ እያስጠጣቼው ነው።
    ፕሮፌሠር መስፍን !
    ይሄ የእርስዎ የ6 ወር (የጊዜ እንስጣቸው) አባባል እንኳን ለዶ/ር አብይ ያኔም ከጉጪማው መለስ ዜናዊም ጋር ተገናኝተው በEtV ላይ እንዲሁ ለእነዚህ ሰዎች “ጊዜ እንስጣቸው እና እንያቸው “፡.. ብለዉም ነበር ። ያ ውይይት አሁንም በyou tube ላይ ይገኛል። ጊዜ እንስጣቸው ያሉት ጉዳይ ት ጊዜ ተስጥቷቸው ፤ ታይተው 27 ዓመት እኮ ሞላቸው። ያ ጊዜ እንስጣቸው አባባል ግን 27 ዓመት ድረስ ቆይተውም “እንያቸው” ያሏቸው እነ ለገሠ ዜናዊ ለኢትዮጵያ የደገሱትን ከወራሪው ጣሊያን በላይ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን “ቂም” አስዩን። ይሄ አይበቃም ነው የሚሉን…? ኢትዮጵያን አፈራረሰው አልጨረሱምና 6 ወር እስቲ እንያቸው ይመስላል የአሁኑ አባባልዎ። ጌታ ይቅር ይበለዎ አባቴ። እግዚኢአብሄር ኢትዮጵያንን እና ህዝቧን ይጠብቅ ! ይማር።

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    April 24, 2018 09:37 pm at 9:37 pm

    ቂቂቂ!! እርስ በርስ ተመሰጋገኑ ወይም ተሸረዳደዱ!! እዝራና መስፍኔ ኣንድ ናችሁ። ያንድ ሳንቲም ሁለት ገፅ። ኣንበሳና ጎፈር ከነዘውዱ።

    Reply
  3. Ezira says

    April 25, 2018 11:40 pm at 11:40 pm

    ሙሉጌታ ሐጎስ !
    ምነው ምነው አፍክን ብትዘጋ የሐጎስ ልጅ -ያንተ ቦታ እኮ Aiga forum ወይም Tigray online ነው። ምን ትሰራላህ እዚህ ?
    ሰዎችን ብንል አንኮሎችን አሉ። እንዳልከው እኛማ 1 ነን ፡ ያንተ ጥልቅ ማለት ነው እንጅ ያለቦታህ ። ሂደ ወደዚያ ወደ አብዮታዊ ዴሞክራሲህ ነፈዝ። እኩል ደራ ደራ ከአልማዞቹ ጋራ አሉ አባ ገብረ ሃና

    Reply
  4. Andargie Mulugeta says

    April 26, 2018 07:12 pm at 7:12 pm

    ለነገሩ ፕሮፌሰርን አከብራቸዋለሁ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ January 26, 2021 11:16 am
  • የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አክቲቪስቶችን በሕግ ተጠያቂ አደርጋለሁ አለ January 26, 2021 10:32 am
  • የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል January 26, 2021 07:17 am
  • በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ January 25, 2021 03:07 pm
  • “…ሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ አይደለም የሚሉ አካላት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው” – ዶ/ር ሙሉ ነጋ January 25, 2021 01:02 pm
  • የሶማሌና ኦሮሚያ መሥተዳድሮች ወሰንን በተመለከተ የሰላምና የጋራ ልማት ስምምነት አደረጉ January 25, 2021 12:50 pm
  • 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው January 25, 2021 09:34 am
  • በመቀሌ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩ ታወቀ January 25, 2021 02:47 am
  • ዊንጉ አፍሪካ (wingu.africa) በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው January 24, 2021 01:23 pm
  • ኢትዮጵያ ድሮኖችን ማምረት ልትጀምር ነው January 24, 2021 02:40 am
  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule