• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አይ አበሻ! አበሻና ቀጥታ መስመር

July 8, 2014 09:07 am by Editor 4 Comments

አበሻና ቀጥታ መስመር አይተዋወቁም፤ ቀጥታ መስመር መጀመሪያ አለው፣ መጨረሻም አለው፤ አበሻ እንዲህ ተጀምሮ የሚያልቅ ነገር አይወድም፤ እልቅ ሲል ጭር ይልበታል፤ አበሻ የባህርዩ የሆነውና የሚስማማው ክብ መስመር ነው፣ ክብ መስመር መጀመሪያ የለው፣ ማለቂያ የለው፣ ሲዞሩ መዋል ነው፤ አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፤ ቤቱ ክብ ነው፣ እንጀራው ክብ ነው፣ ዳቦው ክብ ነው፣ ድስቱ ክብ ነው፣ ጋኑም ክብ ነው፤ ክብ ያልሆነ ነገር አበሻ ምን አለው?

አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፣ አዙሪት ነው፣ ታሪኩም አዙሪት ነው፣ ሄደ የተባለው ሁሉ ተመልሶ ይመጣል። አበሻ ማለት አዙሪት ነው፣ አዙሪት ማለትም አበሻ ነው። የእንግሊዝ ወይም የሩስያ ወታደሮችን ሰልፍ ስታዩ ቀጥታ መስመር ምን እንደሆነ ተገነዘባላችሁ። የአበሻ ወታደሮችስ? ተለያይቶ የተገጣጠመ ክብ መስመር?

አበሻ በመስመር መሄድም ሆነ መቆም አይሆንለትም። አበሻ ቀጥታ መስመር ሲያጋጥመው የሚታየው ተለምጦ ነው፣ ክብ ሆኖ ነው፣ መጀመሪያ የሌለው፤ መጨረሻም የሌለው በፈለገበት በኩል ሊገባበትና በፈለገበት በኩል ሊወጣበት የሚያስችለው ክብ ሲሆን ነው፤ ሰዎች ተራ ይዘው በመስመር እንዲጠብቁ በሚደረግበት ግዜ አበሻ ጭንቀቱ ነው፤ እንዴት ብሎ ጀርባውን ለማያውቀው ሰጥቶ ከፊቱ ደግሞ አንድ የማያውቀው ሰው ተደንቅሮ በሰላም መቆም ይችላል? አንዱ ደፋር ከኋላው መጥቶ ቀድሞት ቢሄድ ግድ የለውም፤ ለነገሩ ራሱም ቢሆን ፈርቶ ነው እንጂ ያደርገው ነበር! የድሮዎቹን ሰዎች ጭንቀታቸውን ለመቀነስ አንተ ቅደም አንተ ቅደም እየተባባሉ የተራውን ቀጥታ መስመር ይቆለምሙት ነበር፤ የዛሬው የሰለጠነው ትውልድ አንተ ቅደም ብሎ ነገር አያውቅም፣ ሁሉም በየፊናው ለመቅደም ሲሞክር መተራመስ ነው፤ መተራመስ ቀጥታ መስመርን ድራሹን ማጥፋት ነው።

አበሻ ለቀጥታ መስመር ያለውን ኃይለኛ ጥላቻ ለመረዳት አምስት ደቂቃ ያህል በአዲስ አበባ መንገዶች ዳር በተለይ መስቀልያ በሆኑት ላይ ቆም ብሎ ማየት ነው። የትራፊክ ፅሕፈት ቤት በፈረንጅ አገር ሲደረግ አይቶ በየመንገዶቹ ላይ ሁሉ ነጭ መስመር ይለቀልቃል፣ ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል እንደሚባለው ሆኖ ነው እንጂ መኪና የሚነዳው አበሻ መቼ ስራ አጥቶ ነው ያንን ቀጥታ መስመር የሚያየው? እያንዳንዱ ነጂ በፊናው በራሱ በውስጡ ያለውን ክቡን እየተከተለ በኩራት የትርምስ ትርኢት ያሳያል፤ ተመልካቾቹ የትራፊክ ፖሊሶች ናቸው። የትራፊክ ፖሊሶቹ አራትም አምስትም እየሆኑ የትርምሱን ቲያትር በመደነቅ ይመለከታሉ፣ በመንገዶቹ ላይ ቀጥታ መስመሮች የተሰመሩት ለመኪናዎቹ እንደአጥር ሆነው ቀጥታ እንዲሄዱ ለማድረግ ነበር፣ አበሻ ምኑ ቂል ነው? መኪናውን በመስመሩ ላይ አንፈራጥጦ እየነዳ ይሸፍነውና መስመሩን ከነኖራው ጋር ከህልውና ውጭ ያደርገዋል። መስመሩ ሲጠፋ ለትርምሱ ይበጃል፤ ለሁለት መኪናዎች የተቀየሰውን መንገድ አንዱ ብቻውን ይዞት ወሬውን እያወራ ይንፈላሰሳል።

ትርምስ ፈጣሪዎች ባለመኪናዎች ብቻ አይደሉም፣ እግረኞችም ናቸው፣ ለእግረኞቹ ማቋረጫ ተብሎ የተሰራ መንገድ አለ፣ እግረኞች ሁሉ በዚያ ለእግረኞች በተሰመረው መንገድ ገብተው ለማቋረጥ ይፈራሉ፤ መፍራታቸው አያስደንቅም። መስመሮቹ ለእግረኞቹም ሆነ ለመኪና ነጂዎቹ አይታዩም፤ የሚያስደንቀው ግን እግረኞቹ በባቡር መንገዱ መሃል ገብተው በሙሉl ልብ ሲያተራምሱ ነው!  የሚተራመሱት የትራፊክ ፖሊሶችም ቢሆኑ መስመሮቹን አያዩም፤ እግረኞቹንም አያዩም፤ መኪናዎቹን አያዩም፣ ለወጉ ለብሰው የሚተራመሰውን እያዩ እነሱም ይተራመሳሉ!

አበሻ በሩጫ በዓለም የታወቀ ሆኖአል፤ ግን በመቶ ሜትር የሩጫ ውድድር ስስጥ አበሻ የለበትም፣ የመቶ ሜትር ውድድር ውስጥ ትርምስ የለም፣ መስመር ይዞ መሮጥ ያስፈልጋል፣ ታዲያ አበሻ በሩጫ የተደነቀ ጎበዝ ቢሆንም በመስመር ውስጥ ገብተህ ሩጥ ሲሉት ግራ ይገባዋል፤ አበሻ ንጉስ እንደኀይሌ ንግሥት እንደ ጥሩነሽ የሚሆነው በርቀት ሩጫ ትርምስ ውስጥ ብቻ ነው፤ በመኪናም የርቀት ውድድር ቢኖር አበሻን ማን ይቀድመው ነበር! ለሽቅድድም የወጣውን መኪና ሁሉ በትርምስ እያጣበቀ ቀጥ ያደርገው ነበር፤ ለመሆኑ ባቡሩ ተሰርቶ ሲያልቅ አበሻ ምን ይበጀዋል? ችግር ነው ጌትነት!

የአበሻ የመስመርና የወረፋ ጥላቻ ከምን የመነጨ ይመስላችኋል ከጌታና ሎሌ ስርዓት አይመስላችሁም?  ከጨዋነት ነው የሚሉም አይጠፉም ይሆናል፣ በመተሳሰብ አንተ ቅደም አንተ ቅደም እየተባባለ ግዜን ሲያቃጥል ኖረና አሁን ደግሞ በትርምስ ጊዜን ያቆመዋል!

ደጉ ዘመን አንተ ቅደም የሚባልበት ዛሬ ከቻለ ገፍትሮ መቅደም፣ጨዋው ሲገፈትሩት አንገቱን ደፍቶ ዝም ማለት፣ በደርግ ዘመን ቤንዚን በሰልፍ በሚቀዳበት ግዜ መኪናዬ ውስጥ ሆኜ ተራዬን እጠብቃለሁ። አንዱ ጮሌ መስመሩን ስቶ መጣና ከእኔ መኪና ፊት ለመግባት ቆልመም አድርጎ አቆመ፤ መኪናዬን አስነሳሁና ገጨሁበት። ከመኪናው ወርዶ የተገጨውን ሲመለከት «እኔ ወፍ የምጠብቅ ይመስልሃል?» አልሁት፤ እሱም አግድም እያየኝ «እኔ ምን አውቃለሁ» ሲል መለሰልኝ።

ሰኔ 2006

(ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. bombu says

    July 8, 2014 09:28 pm at 9:28 pm

    አበሻ የሚሉት መጠሪያችን ሆኖ
    ዘመናት ዘለቁ ባብዛኛው ስው ታምኖ
    ከትውልድ ትውልድ እንዲያው ሲንከባለል
    ምሣሌውም ይኀው ያንብቡት ከጎልጉል

    የቃሉን ኣመጣጥ ያጣራው በቅጡ
    ከኛ ኣይጠፋምና እንየው እስቲ አምጡ

    ከኛ ያልመነጨ ካፋችን ያልወጣ
    መጠሪያችን ሆኖ ፊታችን ሲመጣ
    ዝም ብሎ ማየት መስማት በለበጣ
    ሥንፍና ነውና ከአይምሮአችን ይውጣ

    የኛ የራሳችን የታሪክ መጠሪያ
    ኢትዮጵያዊነታችን አንዳልሆነ መኩሪያ
    አበሻ መባሌን አልሻውም ከቶ
    ጃኖውን አውልቆ ማጥለቁን ቡቱቶ

    እስቲ እናንተም በሉ ይሔ ሥም ይወገድ
    ከአረብ የተስጠን ሳንፈልግ በግድ

    ምናልባት በዘዴ ኢትዮጵያዊነትን
    ላለመንካት ክብር የጋር ስሜትን
    ለትችት ለሽሙጥ ወይም ለመራቀቅ
    አበሻ በማለት በቃል ለመደበቅ
    ከሆነ ፈሊጡ ባብዛኛው ቀመሩ
    ምን ማድረግ ይሻላል ልመለስ ከበሩ»

    Reply
  2. Abe says

    July 9, 2014 05:30 am at 5:30 am

    I often read the write ups and articles of Professor Mesfin related to Ethiopia and Ethiopians. While I appreciate his unreserved contributions, but I strongly oppose some of his judgements on the characters and day today life of the Ethiopian people. He focuses on the result than the cause. For example,his conclusion in this article is that Ethiopians- all”The Habeshas” are orderless, normless, have no discipline and prefer to live in anarchic situations. He accuses the new generation by contrasting it to the old for allegedly making it’s life rotating in ungovernable vicious circle.

    But what he lacks to understand or don’t want to recognize is the norms and traditions of every (the new) generation are mainly derived or inherited from the past. Did he examined as to what good norms and ways of life his generation has transfered to the now existing generation in the past 50 years? what was his and his generation fellow citizens have done yesterday and before yesterday (let alone even at this very juncture) for the betterment of today. I can say very mimimal or nothing at all. It’s like ending up wishing and trying to harvest a good farm production without primarily plowing, preparing, sowing and weeding the farm field. Better he focuses on how to transform the generation and push others to work towards this goal by taking responsibilty himself than trying to play the blame game.

    Reply
  3. aradaw says

    July 9, 2014 07:43 pm at 7:43 pm

    Dear Professor has lived through three dictators doing the same thing, complaining and acting as moral traffic police. I remember his class I attended back in the early 1970 that he was complaining and arguing and angry because one student has his hat on his head in the class room. At the time instructors has the power and the student did not stand for what he was doing is not immoral. We all loughed.

    Reply
  4. Tazabiw says

    July 14, 2014 09:17 pm at 9:17 pm

    I do not blame the professor for getting angry at Ethiopian political
    developments. Its good intentions and policies are always hijacked
    and manipulated by misinformed officials or misguided civil servants
    so as to satisfy their immediate ones or themselves due to a legacy
    and inheritance of backward Ethiopian politics using it as background
    or premise OR due to lack of administrative knowledge and lack of
    trained civil service or lack of enforcement of the laws all the time.
    You can see that how the 1974 Ethiopian revolution fall into the wrong
    hands and how it ultimately become a bone of contention for few elites
    who call themselves party of the people while not even close to it to use
    it to get to power and authority. EG. dergue, Meison, eprp, seded. And how
    it all ended up to Ethiopia and the people with further worst more damage
    than what already existed.
    The list of concrete examples or cases can go on and on from 1890 till today.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule