ከተወሰ ግዜ ወዲህ አበበ ተክለ ሃይማኖት እና ጻድቃን ስለ ባህር በር እና አካባቢያዊ ስጋቶች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች ብሎም ደህንነት ላይ ስለሚጋርጡት አደጋ አብዝተው ከመጻፍ አልፈው በቃለ ምልልስ ተጠቅመው ሃሳባቸውን እንድንሰማ እያደረጉን ነው። የሚጽፉትም በአማርኛ ቋንቋ መሆኑ ሌላው አዲስ ነገር ነው። ከመለስ ኩባንያው መንጋ ተሰንጥቀው እስከወጡበት ግዜ ድረስ ምንም አይነት ችግር ሲገጥማቸው ጽሁፍ የሚጽፉትም ይሁን ጉዳዩ ተደራሽ እንዲሆን የሚፈልጉት በትግርኛ ለትግራይ ህዝብ ብቻ ነበር።
ይኽ የሚያሳየው ዛሬም ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ አወራርደው ያልጨረሱት ነገር መኖሩን ዘግይቶም ቢሆን እንደገባቸው እንጅ ሌላ ጤናማ የሆነ አንድምታ ማዘሉን አይደለም። ጽሁፎቻቸው ቢሆኑ ግን ቃላት ከመደረት በቀር ቅንጣት ታክል ጭብጥ የሌለው፤ የአራተኛ ክፍል የህብረተሰብ ሳይንስ (የጂኦግራፊ) ትምህርት ብቻ ማወቅና መረዳት የሚበቃውን ሃቅ ለመረዳት የህወሃት ጀነራሎች የ42 ዓመት የትምህርት የስራና የትግል ልምድ እንደጠየቃቸው ግልጥ ሆኖ የውጣበት ሁኔታ ነው ያለው። እኒህ ገና በወጣት እድሜያቸው ትምህርት ጠልተውና አሮጌ ጠመንጃ ይዘው ጫካ የገቡ፣ መሰረታዊ ግንዛቤ ሊጨብጡበት የሚችሉበትን እድሜ በደደቢት ዋሻዎች አባክነው አዲስ አበባ ሲደርሱ አለም ምን ያህል ጥሎዋቸው እንደነጎደ ያልገባቸውና ዛሬም ድረስ በቁም እንቅልፋቸው በተለየ እውነታ (የራሳቸው ሪያሊቲ) ውስጥ የሚኖሩ ገንገበቶች ናቸው። እንደ ኢዲያሚን ዳዳ ለራሳቸው “የጀነራልነት” ሹመት ስለሰጡ ብቻ ከሚሊሻነታቸው የወጡ የሚመስላቸው፣ ከጥቁር ገበያ ዲግሪ ገዝተው ከስማቸው አጠገብ ስለለጠፉ ብቻ ምሁርነት የሚሰማቸው በድኖች አብዛኛውን ግዜያቸውን ያጠፉት በትምህርትና በንባብ ሳይሆን ከነሱ ባነሱ መናጆዎች ሲዘንብላቸው በኖረ ከንቱ ውዳሴ ካስከተለው ውድቀት ውስጥ ተቆፍሮ በሚወጣ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ነው። እብሪታቸው ከትምህርትና ከትምህርት ቤት በላይ እንደሆኑ አድርጎ ስላሳሰባቸው የመምህርና የተማረ ሰው ንቀትና ጥላቻቸው ለከፋ ድንቁርና ጋርዷቸው አገርና ወገንን ለማይሽር ጠባሳና ችግር ትውልድን ደግሞ ለማይወጣው ፈተና ዳርገውታል። መሃይምነትና ድንቁርና የዚያው የደንቆሮው ሰው ችግር ሆኖ የሚቀረው ሰውየው በማህበራዊና በመንግስታዊ ስልጣን ውስጥ የሃላፊነት ቦታን እስካልተቆናጠጠ ድረስ ብቻ ነው። ምግባረ ሃይማኖትን ከሰብዓዊነት ያላዋሃደ፣ ከፊደል ጋር የተጣላ ሰውና ጠመንጃ የተገናኙ ቀን የጥፋት ሁሉ ጥግ ማለት እርሱ ነው ይባላል። ጻድቃንና የአበበ ተክለሃይማኖትም፤ ከነድንቁርናቸውና የስንፍና ሸለፈታቸው የድርጅትን ብሎም የመንግስትን ስልጣን በመቆጣጠር፤ አገርና ህዝብን ብሎም ትውልድን ለኪሳራ የዳረገ ተግባር ፈፅመዋል።
ዋርዲያዎቹ ጠባብና ዘረኛ አላማቸውን ከግብ ለማድረስ በተጓዙበት አቋራጭ የስንፍናና የጥፋት ጉዞ የአገርን አንድነትና ህልውናን አደጋ ላይ የጣሉ አሳፋሪ ውሳኔዎች እንዲጸድቁ እነጻድቃን ተግተዋል። የተሰጣቸውን ስልጣን እነሱም ሆኑ የፈለቁበት ቡድን ለቆሙለት ዘረኛ ፖለቲካዊ ዓላማ መሳካት ለሚያስፈልገው የወታደራዊ ሃይል ድጋፍና ጥበቃ አውለዋል። ሃገርን ከጥቃት ለመከላከል በማለት የተመደበውን የመንግስት ሃብትና ንብረት እንዳሻቸው በማዘዝ ጠባብና ዘረኛ ፍላጎታቸውን አሳክተዋል። በዚያው ልክ የሃገሪቱ የመከላከል አቅም በአመለካከትም ሆነ በትጥቅ እየጫጨና እየመነመነ ሄዶ የሃገሪቱ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት አደጋ ሲወድቅ ህወሃትና እነጻድቃን የዚህ ኩነት (ሁነት) አቀናባባሪዎችና መሪ ተዋናይ ነበሩ፤ ዛሬም ናቸው። አማርኛ አወቅን ብለው “የተቀቀለ ባቄላ ዘር አይሆንም” በሚል ዘበት የአገሪቱን መከላከያ፣ አየርና ባህር ሃይል ሲያፈርሱ ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ትንሽ የገባቸው የባድመ ወረራ ላይ ማጣፊያው ሲያጥራቸው ነበር።
ያን ግዜ የተቀቀለ ባቄላ ዘር የሚሆንበት ቀመር “ገብቷቸው” በሶ የቋጠሩበትን ባንዲራ አነሱት፤ የተከለከሉ የነፍጠኛ እንጉርጉሮዎች ባደባባይ ተለቀቁ፤ የታሰሩ የደርግ ወታደራዊ መኮንኖችና አየር ሃይሎች ከእስር ተፈትተው ከውርደት እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበ። “አየር ሃይል ምንድን ነው፤ እኛ አዲስ አበባ የገባነው አየር ሃይል ኖሮን አይደለም” በሚል ድንቁርና በየጫካው የተጣሉ ስንት አንጡራ ሃብት የፈሰሰባቸውና ድንበራቸውን ሲያስከብሩ የነበሩ የ አገሪቱ ሞገስ የሆኑ የጦር አውሮፕላኖች የበላቸው ዝገት እየተወለወለ ለግዳጅ ሲሰማሩ አየር ሃይል አዛዥ ተብሎ የተሰየመው አበበ ተክለሃይማኖት ነበረ። እርሱ ቢሆን ያችን ክፉ የወጣት ጀነራል ተጫኔ የተባሉ ስመ ጥር የደርግ ዘመን የአየር ሃይል ባለሙያን ከፊት አቁሞ ነበር። የጀነራልነት ማእረግ ተደክሞበት ሲገኝና በዘር መስፈርት ተለክቶ መታደል ሲጀምር ምን ማለት እንደሆነ በዋርዲያው አበበ ተክለሃይማኖትንና በጀነራል ተጫኔ መካከል ያለውን ከውቂያኖስ የሰፋ ልዩነት ማየት ነው።
ህወሃት የኢትዮጵያን የደህንነት፣ የመከላከያና የጸጥታ ተቋማትን በፍጹም የበላይነት በመቆጣጠር የገነባውን ፖለቲካዊ የበላይነት ለማስጠበቅና ለማጽናት፤ የዘረኛው ቡድን ተከታዮችና አባላት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረታቸውን የማጠናከር ስትራቴጂ ነድፎ ደፋ ቀና ማለት ከጀመረ ሁለት አስርት አመታት አልፈዋል። ይህን በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ኪሳራና ውድቀት ዘረኛው ቡድን ፖለቲካዊ የበላይነቱን ያረጋገጠበትን ሁኔታ አጽንቶ ለማቆየት፤ ህወሃት ማባሪያ ወደሌለው ህገ፡ወጥነትና ስግብግብነት ወደ ተጠናወተው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎችን በቀደምትነት የመቆጣጠር የዘረፋ ሂደት ውስጥ ገብቶ እንዲዳክር አስገድዶታል።ይህ ሂደት ትናንት የማይተካ ዋጋ የከፈልኩባቸው መሰረታዊ አላማዎቼ ናቸው ያላቸውን ፖለቲካዊ ጉዳዮች እስከመካድ ያደረሱት ናቸው። አሁን ህወሃት ወደ ስልጣን ሲመጣ የተራመዳባቸውን መንገዶችና መደላድሎች እየተወ ቀደም ሲል የውድቀትና የጥፋት ያላቸውን መስመሮች በልሂቃኑ አማካይነት እያስተጋባ ይገኛል፤ቆይቶ ደግሞ በተሃድሶና በመሳሰሉት ሰበቦች የድርጅት የመታገያ መርሆዎች ሆነው እንዲቀርቡ ማድረጉ የማይቀር ጉዳይ ነው። ሊጠቀሱ ከሚገባቸው አንኳር የፖለቲካ ጉዳዮች መካከል ህወሃትና ሊህቃኖቹ የማያዳግም መልስ ተሰጥቶባቸዋል ከሚባልላቸውና ዛሬ ላይ የህወሃት ልሂቃን አይናቸውን በአጥበው መልሰው ሊያነሷቸው እየዳዳቸው ካሉ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የባህር በር ጉዳይ አንዱ ሆኗል።
የባህር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ጉዳይ ወይም አጀንዳ አይደለም፤ የሽህዎች አመታት እድሜ ባለጸጋና ጎምቱ ሊባል የሚችል ፖለቲካዊ አጀንዳ ነው፤ ከዚህ አኳያ ሲታይ የህወሃትና የጠባቡ ፖለቲካቸው ሊህቃኖች የባህር በርና የባህር ጂኦፖለቲክስ ትንታኔ እንጭጭ አቱማታ ልንለው እንችላለን። ምክንያቱም ህወሃት ትናንት በድንቁርናና በምቀኝነት መንፈስ በመመራት ያረከሰውን ታላቅና ክቡር አገራዊ ጉዳይ፤ዛሬ እንደ ነጋበት አሮጌ ጅብ በማብቂያው ሊያውም ከሩብ ምዕት ዓመት በኋላ እያነሳሳ ስሜታችንን ሊኮሮኩር መፈለጉ ጉዳዩን ለጠባብ ቡድናዊ አላማ ሊጠቀምበት እንደፈለገ ከማሳበቅ በቀር እንደ አዲስ የሚያስጨብጠን ቁምነገርነ የለም። ህወሃት የትግራይ ሪፐሊክን ለመመስረትና ለማጽናት ኢትዮጵያን በማንኛውም መልኩ ማዳከም ስትራቴጂካዊ ግቡ በማድረግ የተነሳ ቡድን ነበር።
በመሆኑም ኢትዮጵያን ያዳክማሉ ከተባሉ የውጭ የሃገሪቱ ጠላቶች ጋር ለማበር ምንም የሚያቆመው ፖለቲካዊ ምክንያት አልነበረውም። የዚህ ዋና ምክንያቱ ደግሞ የነጻይቱ ትግራይ ሪፑሊክ ጥንካሬ የሚጸናው በምትበታተነው ኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ነው የሚል የበታችነት ስሜት በሽታ የወለደው የህወሃት ልሂቃን የተሳሳተ ትንታኔ የነበረና አሁንም በህገ፡መንግስቱ አንቀጽ 39 ተካቶ እየተሰራበት የሚገኝ መሆኑ ነው። ነባሩና ተጨባጩ ሃቅ ይሄ ሆኖ ሳለ፤ህወሃትና ልሂቃኑ የትናንት አስተሳሰባቸውንና አመለካከታቸውን የተዉት በማስመሰል፤ ዛሬ ላይ ሆነው “ታግለንለታል፣ ሞትንለታል” ያሉለትን የኤርትራ ወይም የባህርን በር አጀንዳ ከጀርባው ለመውጋት ምን አነሳሳቸው፧ እርም ይሁንብን ብለው የተፉትንስ የአገር ዳር ድንበርና የአንድነት ፖለቲካ ጥያቄን መልሰው ለማላመጥ የከጀሉጽ ለምን ይሆን፧ ብለን በመፈተሽ ህወሃት በባህር በር ጉዳይ አሳቦ ዛሬም ያለትወጠውን ጠባብ ዓላማውን ለማጠናከር ምን ዓይነት ተንኮል ያዘለ ፖለቲካዊ አኬያሄድ ለማራመድ እንደፈለገ የቅርብና የሩቅ ጊዜ አስረጂዎችን በመፈተሽ መረዳት ያስፈልጋልል። በተጨማሪም ህወሃት ጨቋኝ አገዛዙ በዘላቂነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን የመፍጠር ዓላማው እየገጠመው ካለው ችግር አንጻር አሁን እነዚህ አጀንዳዎች ምን ትርጉም እንዳላቸው መመርመር ገዢው ሃይል በፖለቲካዊ፣ ወታደራዊና ዲሎማሲው መስክ በቀጣይ ምን ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ለመገመት ያስችላል። በተረፈ ወያኔ እያረመደ ያለው ዘረኛ የኢኮኖሚ ግንባታ አቅጫ ከአለም አቀፍ የገበያ ውዽር አንጻር ወድብ አልባዋ ትግራይን ማዕከል ያደረገው ስታራተጂ ምን ዓይነት ፈተና ሊገጥመው ይችላል የሚለውን የቢዝነስና የትራንዚት ባለሞያዎች በጉዳዩ ላይ ጥናት ቢያድርጉበት ስለወደፊቱ አካባቢያዊና አገራዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ከወዲሁ በቂ ግንዛቤ ለመያዝ አስፈላጊነቱ የላቀ ነው።
ከሁሉ በማስቀደም ህወሃት ወያኔ ጉዳዩን በማስተጋባትና በማናፈስ ተግባር እንዲያገለግሉት በዋናነት የመረጣቸውን ግለሰቦች ማንነት ማየቱ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ጠቃሚነት ያለው ይመስለኛል።ለዚህ የማናፈስ ተግባር በዋናነት የተመረጡት ግለሰቦች ማንነትን እንደሚከተለው በማየት ህወሃት ላሰበው የባህር በር አርዕስተ ጉዳይ ያላቸውን ዝምድናና ተቃርኖ እንዳስሳለን። በርግጥ አስቀድሜን እንደጠቆምኩት ባለጉዳዮቹ ህወሃት የባድሜን ጦርነት ተከትሎ በገጠመው የመሰንጠቅ አደጋ ወቅት ሰልፋቸውን፤ ከተንበርካኪው አባይ ጸሃዬና ሃሰን ሺፋ ጎን በማድረጋቸው ከኤታማዦር ሹምነትና ከአየር ሃይል አዛዥነት ስልጣን በአሸናፊው ቡድን ቁንጮ መለስ ዜናዊ ብቸኛ ውሳኔ የተባረሩት ጻድቃንና አበበ ተክለ ሃይማኖት ናቸው።
እነዚህ ሁለት ተሸናፊ “ጀነራሎች” ለረጅም ግዜ ከፖለቲካው አለም ራሳቸውን በማግለል በግላዊ የሂወት ሩጫ ተጠምደው የነበሩ ቢሆኑም፤ የአለቃቸው መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ አይናቸውን በጨው በማጠብ ከያደፈጡበት ስርቻ በመውጣት አለን ለማለት እየሞከሩ ይገኛል። በእርግጥ የፖለቲካ መሰረቱ የተናጋበትና ከአጀንዳ አጀንዳ እየተወናጨፈና የሚይዝ የሚጨብጠውን ያጣው ህወሃት ሰሞኑን መነነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱትን ኮርኳሪ የፖለቲካ አጀንዳዎችን እያነሳሱ እንዲያስተጋቡ አልጋበዛቸውም ብሎ አለመገመት ግን፤ ዘበት ነው። ያም ሆኖ ግን አስገራሚው ነገር ግን እንዲያራግቡት የተመረጠላቸው ጉዳይ አነጋጋሪነት ሳይሆን በተለይ እነዚህ ግለሰብ(የተባረሩ) ጀነራሎች እያነሱ በሚሞግቱት ጉዳይ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ስልጣን፣ወታደራዊ ማዕረግና ሃላፊነት ተሰጥቷቸው የነበረና፤ አገሪቱ ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ እንዲሆናቸው ከሶስት መቶሺ ወታደር በላይ አሰልጥናና አስጣጥቃ ያሰለፈችላቸውና፤ ነገር ግን ብቃት፣ ችሎታና ወኔ ስለጎደላቸው በመቶሺ የሚቆጠሩትን የሃገሪቱን የቁርጥ ቀን ጀግኖች ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ በመሆን ለሽንፈት የዳረጉ መሆናቸው ነው።
ኋላም የስርዓቱ ቁንጮ የነበረው መለስ የጦርነቱን ሂደትና የመጨረሻ ውጤት በመገመት የዘረኛው ወያኔ ስርዓት እስከ ወዲያኛው ባፍጢሙ ከመደፋቱ በፊት የአልጀርሱን የሰላም(የሽንፈት) ስምምነት ለመፈረም ተገደደ።የዚያን ግዜ ለሽንፈቱ ተጠያቂው ስርዓቱን በበላይነት ይመራ የነበረው መለስ ዜናዊ ቢሆንም ወቅቱ ፈጥሮት የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ ግን፤ እነ ጻድቃንንና አበበ ተክለ ሃይማኖትን ያላንዳች ጣልቃ ገብነት የጦርነት እቅድ እንዲያወጡ፣ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁ፣ ገንዘብ እንዲያንቀሳቅሱ፣ ሰራዊት እንዲመለምሉ፣ እንዲያሰለጥኑ፣ የቀድሞ ሰራዊትን ከጎናቸው እንዲያሰልፉ፣ የውጭ ሃገር የጦር ጠበብትን እንዲቀጥሩና ጦርነቱን ባቀዱት መንገድ እንዲገፉበት ሙሉ ስልጣን የተሰጣቸው ስለነበር፤ በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ለደረሰው እልቂትና ጥፋት ተጠያቂዎች ናቸው። እስራኤሎች ከአረቦች ጋር ባደረጉት ፍልሚያ በወታደራዊ ዓለም ዘወትር የሚዘከር ደማቅ ድሎችን ያስመዘገቡ ቢሆንም በያንዳንዱ ውግያ ለገጠማቸው ሳንካ ግን ወታደራዊ መኮንኖቻቸውን እንደየ ሃላፊነታቸውና ጥፋታቸው ተጠያቂ ከማድረግ አላቅማሙም።
የኛዎቹ ጉዶች አንዳች ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ እርባና ባላላስገኘ ጦርነት ሰራዊትና ንብረት ካስፈጁ በኋላ ሽንፈታቸውን ኤርትራዊ ደም ኖሮዋቸው በወታደራዊና ሲቪል የመንግስት ስልጣናን ላይ በነበሩ የትግል ጓዶቻቸው እንዲላከክ ጥረት አድርገው ነበር። ይህ ደግሞ ሌላ ዙር የሽኩቻና የመጠላለፍ ግብ ግብ በር እንዲከፈት አድርጎ፤ቅይጦቹ ህወሃቶች በነበራቸው የኢንቴክቷል ብቃት ብልጫ ምክንያት ሃያላኑን ሃገራትና የስለላ ድርጅቶቻቸውን ከጎናቸው ለማሰለፍ በመቻላቸው ነባሮቹን (ተጋሩ ወይም ትግራይ በቀል ህወሃቶችን) በቀላሉ ከገዢው ፓርቲ የአመራር ሰንሰለት ተለቃቅመው እንዲወጡ አድርገዋቸዋል። ተጋሩ በክልሶቹ ላይ የቃጡት ዱላ በክልሶቹ ጠንካራ የመከላከል እርምጃ ስለከሸፈባቸው በገዛ ሜዳቸው ላይ በድጋሚ ነጥብ በመጣል ሳይወዱ በግድ የሽንፈትን ጽዋ በመጎንጨት ከፖለቲካው መድረክ ደብዛቸውን አጠፉ። በእንደነ ገብሩ ያሉት የራሳቸው የፖለቲካ ድርጅት በማቋቋም ትንሽ ቢሆን በተቋሞው ጎራ በመሰለፍ የመለስን ቡድን በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እየሰሩ ይገኛሉ። ሁሉ አይቅርብን ባዮቹ ደናቁርት ባለቀ ሰአት ዲግሪ ፍለጋ በስተርጅና ተፍተፍ ማለቱን ሲያያዙት (የተቀቀለ ባቄላ ዘር አይሆንም የሚለው) ብሂል የሚሰራው ለነሱ ቢጤ እንደሆነ በውጤቱ እያየነው ነው። ሲጀመር የምሁር ትምህርት መማርና ምሁር መሆን የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ምን ያህል ተምረሃልና ከተማርከው ምን ያህሉ ገብቶሃል የሚለው ነገር ማንም ሊያልፈው የማይችለው ቁልፍ ጥያቄ ነው። በዛ ላይ ዲግሪው የግዢ ሲሆን ደግሞ ችግሩ ጥልቀት ከድጡ ወደማጡ ነው። እያንዳንዱን የትምህርት መስክ ባጠቃሉ ቁጥር “ለካስ እስከዛሬ የምንነዳው በተሳሳተና በሃሰተኛ፤ የታሪክ፣ የህግና የፖለቲካ ፍልስፍና ላይ ነው” በማለት በየህትመትና የብዙሃን መገናኛው እንዲሁም በጽሁፎቻቸው ላይ ያቀርቡ ነበር። ለዚህ ጉዳይ ዋነኛ ተጠቃሽ የሚሆኑት ደግሞ ስዬ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ ጻድቃንና አበበ ተክለሃይማኖት አማርኛ ማንበብና መጻፍ ስለቻሉ ብቻ ማሰብ የቻሉ መስሎዋቸው የተማረ ሰው ማእረግ ከስማቸው ፊት ለጥፈው ነገረ ኢትዮጵያን መተንተን ጀምረናል ማለትታቸው ድንቁርና የማፈሪያ ጽንሳቸውን ከውስጥ እንዳጨነገፈባቸው አንዱ አስረጅ ምክንያት ነው።
ትናንት በአገር ውስጥ የነበሩ ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅቶች የባህር በርን በተመለከተ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን አስፈርመው ለተባበሩት መንግስታት ሲያስገቡ (በፊርማ የሚመጣ ከሆነ እኔም እፈርምላችኋል በሚል ምጸት በድርጊቱ የተሳለቀው መለስ ዜናዊ ነበረ። ይልቁንም ባህር በር ማለት ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ባሻገር ብሄራዊ ኩራትና ሞገስ፣ ድንበርና ቁልፍ የሉ አላዊነት) የጀርባ አጥንት መሆኑ ቀርቶ ሸቀጥ መሆኑን አፉን ከፍቶ የተናገረው አፈ ሊቁ መለስ ዜናው ነበር። ያን ግዜ እጃቸው እስኪመለጥ ያጨበጨቡትና አፋቸው እስኪቀደድ የሳቁት የያኔዎቹ እቡይ ደቀመዛሙርቶች ዛሬ ላይ ስለ ባህርበር ጥቅም አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ የአለቃቸው አጽም ተመልሶ አይወጋንም ማለታቸው ይሆን። ትናንት ጨዋ የመለስ ተማሪ በነበሩበት ሰዓት እስከወዲያኛው ያሳጡንን ብሄራዊ ጥቅማችንና ምንግዜም ቢሆን በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዲገኝ ያደረጉትን ብሄራዊ ደህንነታችንን፤ ዳግም ወደ ባሰና ወደለየለት አዘቅት ውስጥ እንዳይጨምሩን ያስፈራል። የሆኖ ሆኖ ግን ገና ለገና በብዝኋኑ የመደመጥ እድል አለን በሚል ስሌት ኮርኳሪውን የባህር በር አርስተ ጉዳይ የህወሃት አቅጣጫ የማሳት ስትራቴጂ መንገድ አድርጎ ለመጠቀም መከጀል ትላንት እንደ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ተሰርቷል ከሚባለው ከቀደመው ጥፋት ይበልጥ ከባድ ስተት ይሆናል።
በዚህ የባህር በር ጉዳይ በመለስ አስተምሮት እንዲደነዝዙ ከተደረጉ ከህወሃት ነባርና ከፍተኛው ካድሬ ይልቅ ተራ ተርታው የህብረተሰብ ክፍል በነጻው አይምሮ በመጠቀም የተሻለ ግንዝቤ ጨብጦ እንደነበረው በተለያየ የታሪክ አጋጣሚዎች አስመስክሯል። ከዚህ አንጻር ጻድቃንም ሆነ ጆቤ ዛሬ በየማህበራዊ ሚድያው ላይ እራሳቸውን የአርስተ ጉዳዩ ሊቅ አስመስለው ለማቅረብ የሚያደርጉት ጥረትና በተቃራኒው ደግሞ በህይወት ጎዳናቸው የተጓዙበት የጥፋት መንገድ ሲታይ፤ ወደ አደባባይ ለመውጣት የሚያስችል ሞራል ባልነበራቸው ነበር።እነዚህ በክፉ ቀን ጣራ ላይ የተሰቀሉ እቡዮች ገና ለገና ህዝብ ያውቀናል በሚል እብሪት ትናንት በወገን ላይ ያደረሱት በደል ቁስል ገና ሳይሸር ከነጅናማቸው የአገር ተቆርቋሪ አርበኛ መስለው ለመታየት ከመጣር አልፈው፤ ለብሄራዊ ጥቅማችንና ደህንነታችን ዋነኛ ጠንቅ ለሆነው የህወሃት ዘረኛ አገዛዝ የማወናበጃ ተንኮል መሳሪያ ሆነው መቅረባቸው፤ነገሩን “የማይገባው ጭንቅላት በስሎ ለማይበስል ማገዶዬን አስጨረሰኝ እንዳለችው” ሴት ሲያደርገው ይታያል።
የሰሞኑን የጻድቃን ዲስኩር የሰማ አንድ የቀድሞው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አባል የነበረ ኢትዮጵያዊ መኮንን እንዲህ ሲል ጽፎልኝ ነበር።
“አበበ ተክለኃይማኖትና ጻድቃን እስከ መጦርያ ዘመናቸው ድረስ ሊረዱ ያልቻሉትን፤ ነገር ግን ግፋ ቢል የስድስተኛ ክፍል የጂኦግራፊና የታሪክ እውቀት የማይፈጀውን ጉዳይ ዛሬ ጀምበር ስታዘቀዝቅባቸው፤ በወጣትነትና በጎልማሳነት ዘመን አክ እንትፍ ያሉትን የባህር በር ጉዳይ፤ያደፈውን የዘረኝነት፣ የተላላኪነትና የባንዳነት ታሪካቸውን ይሽርላቸው ዘንድ በመመኘት፤ ክቡር የሆነውን የሃገር አንድነትና የባህር በር ጉዳይ አመሻሽተው ያነሳሱት ገብተዋል። ይብላኝላቸው ለባንዳዎችና ለአድርባዮች እንጂ፤ የኢትዮጵያ ሃቀኛ ልጆች ለባህር በር ብቻ በማለት ሳይሆን፤ ለመላው አገር አንድነትና ድንበር መከበር ከማንም ቀድመው በጊዜውና በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን ታሪካዊ ተጋድሎ በማድረግ ሃላፊነታቸውን ተወተዋል። ይህ ተጋድሎ አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ታሪካዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በማለት የከፈሉት ዋጋ እንጂ፤ እንደ ጻድቃን ገብረ ትንሳይ ወግ ለመጠረቅና የማስትሬት ዲግሪን ቀሚስ ጥለት ማርዘሚያ እንዲሆናቸው አልነበረም። ስለግዛት አንድነትና ስለባህር በር ጥቅም ግንዛቤ ለመፍጠር አርጅተው እስኪያፈጁ ድረስ ትምህርት ቤት ውስጥ መወዘፍን የሚጠይቅ ከሆነ ይህ መማር ሳይሆን መደንዘዝ ነው።
የሃገርን ጥቅምና ደህንነት እከወዲያኛው ትውልድ ድረስ እንዳይፈታ አድርገው ካጠፉ በኋላ ስለ አንድነትና ባህር በር መጠረቅ እንዲሁ አዋቂና አርበኛ መስሎ በመታየት ከሚገኝ ያፍታ የሞራል ሞቅታ ውጪ ሌላ ፋይዳ የለውም። አገር በመገንባት ሂደት ትውልድ የሚያልፈው እልህ አስጨራሹ ጠመዝማዛና ውጣውረድ የበዛበት ጎዳና፤ አገርን ለማፈራረስ እንደሚንደረደሩበት የቁልቁለት መንገድ ቀላል አይደለም፤ ስምና ከፍተኛ ወታደራዊ የጀነራልነት ማዕረግ እንዲያው በመላ የሚያጎናጽፍ አልባሌ ጉዳይም አይደለም። የልፋትና ድካም ውጤት የሆነ ስምና መልካም መዓዛውን ጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ እንዳይኖረው አድሮ መቀመቅ ጅብ ከሄደ ውሻ በአዋቂነት ጎራ ሳይሆን በደንቆሮነት ተርታ የሚያስፈርጅ ጉዳይ ነው። ባለ ብሩህ አይምሮዎቹ የቀደሙ አባቶቻችን ስለሃገር አንድነትና ስለ ዳር ድንበር አውቀው ለአላማው ሰልፍ ሲወጡ እንኳንስ ዲግሪ ሊኖር ቀርቶ ጆቤና ጻድቃን ዲግሪ ሰቶናል ያሉት ተቋም እንኳን ገና አልተወጠነም ነበር።
የኋለኛው ትውልድም ቢሆን በባንዲራ ራሱን እየጠቀለለ ስለ ሃገር ፍቅርና ስለ ባህር በር በቦታውና በጊዜው በመገኘት ዋጋ ሲከፍል እነጆቤና ጻድቃን ወርተራቸውን እንደመወጣት፤እንደነጋበት ጅብ ድንገት ደርሰው የባህር በር ጠያቂና ተሟጋች የመሆን ወግ ካባ ለመልበስ እንደዛሬው ከመዳዳታቸው በፊት “ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ባህርም ሸቀጥ ” የሚሉትን ብሂል ያጋፍሩ ነበር። ዛሬም ቢሆን እነሱ እንደሚያስቡት የባህር በር እጦት ጉዳት የኤፈርት ሸቀጦችን መግቢያና መውጫ የማጣት ጉዳይ ብቻ አይደለም። እነጆቤና ጻድቃን ማወቅ ያለባቸው አንድ ሃገር የባህር ሳይኖራት ቀርቶ ምድረ-ዝግ (ላንድ ሎችከድ) ስትሆን፤ንግዷ ብቻ ሳይሆን የባለባህር በር አገሮችና የሌሎች ሶስተኛ ሃገሮች ፖለቲካዊ፣ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ሰለባ ትሆናለች። በተለይ ደግሞ በዙሪያዋ ያሉ አገሮች ታሪካዊ ጠላቶችና ባእዳን ሲሆኑ የዛች አገር ብሄራዊ ደህነትና ጥቅም ፈጽሞ አደጋ ላይ ይወድቃል። በተለይ በወታደራዊ መነጽር አንጻር ሲታይ አንድ ሰራዊት ለመከላከልም ሆነ ለማጥቃት ከሚያስፈልጉት ሶስት የውጊያ አውዶች (ባህር፣ ምድርና አየር) መካከል አንዱ ወሳኝ የሆነውን ባህርንና የባህር በርን ዝግ ምድር(ላንድሎክድ) አገሮች ስለማይኖራቸው የባህር በር ካለው የጎረቤት አገርም ሆነ የሩቅ ጋር በሚኖራቸው ወታደራዊ ፍጥጫና ግጭት ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ሉዓላዊነትና ብሄራዊ አንድነት ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ለአጠቃላይ መበታተን ይዳርጋል። እነ ጆቤና መሰል የህወሃት ዘረኛ ድውዮች “ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ባህርም ሸቀጥ” በሚለው ለዛ ቢስ ፖለቲካቸው ያተረፉልንም ሆነ ለወደፊቱ ያሰናዱልን ነገር ቢኖር እንዲህ ያለውን አገራዊ ፍርጃ ነው”.. ሲል ይደመድማል። አዎ፤ የህልውናችን፣ የብሄራዊ ጥቅማችንና የብሄራዊ ደህንነታችን ምንጩና ስጋቱ ያለውዛሬ ከባህር በር ይልቅ በጉያችን መሃል ያለው የወያኔ አልጠግባይ ስርዓት መሆኑን የማያውቁት ከዚህ ዘረኛ ስርአት በሚደረግላቸው ፈሰስ የሰማያት ደጅ የተከፈተላቸው ባለግዜዎች ብቻ ናቸው።
በጥቅሉ እስከ አቶ መለስ ሞት ድረስ ጆቤና ጻድቃን ከፖለቲካው መድረክ መጥፋት ብቻ ሳይሆን፤ ለህልውናቸውና ለምቾታቸው ሲሉ ለጠሏቸውና ቢቻላቸውም ቢያጠፏቸው ለተመኟቸው፤ በእነሱ አባባል አፍቃሪ፡ሻቢያ ለሆኑት የትናንት ግብረአበሮቻቸው የዛሬ አለቆቻቸው መንበርከክ ግድ ሆኖባቸው ሞራላቸውን በሆዳቸው የለወጡ ከንቱዎች ነበሩ።
መስቀሉ አየለ (meskeluayele@gmail.com)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Tadesse says
Manenetachewn ketemaru ye dero tagayoch semtenal,sedeb simolabet gen yastelal.
በለው! says
>» አ/ዘመን ጋዜጣ ፡- ግንቦት ፳ ኤርትራንም ወደብም አሳጥቶናል የሚሉ ወገኖች አሉና ለእነዚህ ወገኖች ምላሽዎ ምንድን ነው?
ዶክተር አርከበ፡- ስለ ወደብ የሚያነሳ ነገር ግን ስለ ሕዝብ የማያነሳና የማያስብ ግለሰብ ወይም ቡድን ብቻ ነው ስለ መሬት የሚያነሳው። አገር ማለት ሕዝብ ነው። ስለሆነም ስለ ሕዝቦች በምናስብበት ጊዜ የኤርትራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ነው መወሰድ ያለበት።ዴሞክራሲ ማለት ለሕዝብ መቆም ማለት ነው። ማነው የመጀመሪያ አገር ኤርትራን እንደ አገር የተቀበለው? የኢትዮጵያ መንግሥት ነበር። ያ ሆኖ ሰላም ማረጋገጥ ተችሏል። ስለዚህ ያንን ያደረግነው ከሰላም፣ ከዴሞክራሲ፣ ከሕዝቦች መብት ማረጋገጥ አንፃር ነውና ይሔ መሆኑ ተገቢ ነው።
***“እኛ ወደብ መች ቸገረን”
ስለዚህ ልማትና ዕድገትን የሚያመጣው ወደብና የባህር ዳርቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ያለ ማየት አስተሳሰብ ምንጭ ነው። እኛ ወደብ መች ቸገረን፡፡ በጂቡቲና በበርበራ መጠቀም እንችላለን። የኤርትራም ሁኔታ መቀየሩ አይቀርም፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ለዘለዓለም ይኖራል ብለን አንገምትም!።በእኔ ግምት በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል ባይ ነኝ። የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን። የኬንያን ወደብ መጠቀም እንችላለን። ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ መስመር ለመገንባት ታቅዷል። የሱዳንንም እንጠቀማለን። ቢቻል ወደብ ቢኖረን ጥሩ ነበር ግን የሁሉም መቋጫና መፍትሔ እርሱ ነው ማለት አይደለም። የሚያመጣው መሠረታዊ ለውጥም የለም በእኔ እምነት።
*** በውጭ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ክርክር በሚዲያ ሳይ ነበር። ከተቃዋሚዎች አንዱ “እንዴት ብለን ነው የኢትዮጵያን ውሃ ለጅቡቲ የምንሰጠው?” የሚል ሃሳብ ነው ያነሳው። እነዚህ ሰዎች በእኔ ግምት ምን ዓይነት አስተሳሰብ እንዳላቸው አይገባኝም። ውሃ ልከን ገቢ ብናገኝ ምንድን ነው ችግሩ? የኤሌክትሪክ ኃይል ልከን ገቢ እንደምናገኘው ሁሉ ውሃም ልከን ገቢ ብናመጣ ጉዳት የለውም ጥቅም እንጂ፡፡ ውሃ መላክ ነዳጅ ከመላክስ ምን ልዩነት አለው? ምንም ልዩነት የለውም። እና የዚህ ሰው አስተሳሰብ ልማታዊ አስተሳሰብ ነው? ጅቡቲ ያለው ሕዝብ ውሃ እየፈለገ ውሃ የጠማውን ሰው ውሃ መከልከል ተገቢ ነው? በባህላችንስ ይሔ አለ? ስለዚህ የሚነሱ ነጥቦች በጣም አሳፋሪ ናቸው። እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ዙሪያ የእይታቸው አድማስ መለወጥ አለበት።” ታጋይ አርከበ እንቁባይ
**************************!
***** “አበበ ተክለኃይማኖትና ጻድቃን እስከ መጦርያ ዘመናቸው ድረስ ሊረዱ ያልቻሉትን፤ ነገር ግን ግፋ ቢል የስድስተኛ ክፍል የጂኦግራፊና የታሪክ እውቀት የማይፈጀውን ጉዳይ ዛሬ ጀምበር ስታዘቀዝቅባቸው፤ በወጣትነትና በጎልማሳነት ዘመን አክ እንትፍ ያሉትን የባህር በር ጉዳይ፤ያደፈውን የዘረኝነት፣ የተላላኪነትና የባንዳነት ታሪካቸውን ይሽርላቸው ዘንድ በመመኘት፤ ክቡር የሆነውን የሃገር አንድነትና የባህር በር ጉዳይ አመሻሽተው ያነሳሱት ገብተዋል።ይብላኝላቸው ለባንዳዎችና ለአድርባዮች እንጂ፤ የኢትዮጵያ ሃቀኛ ልጆች ለባህር በር ብቻ በማለት ሳይሆን፤ ለመላው አገር አንድነትና ድንበር መከበር ከማንም ቀድመው በጊዜውና በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን ታሪካዊ ተጋድሎ በማድረግ ሃላፊነታቸውን ተወተዋል። ይህ ተጋድሎ አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ታሪካዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በማለት የከፈሉት ዋጋ እንጂ፤እንደ ጻድቃን ገብረ ትንሳይ ወግ ለመጠረቅና የማስትሬት ዲግሪን ቀሚስ ጥለት ማርዘሚያ እንዲሆናቸው አልነበረም። ስለግዛት አንድነትና ስለባህር በር ጥቅም ግንዛቤ ለመፍጠር አርጅተው እስኪያፈጁ ድረስ ትምህርት ቤት ውስጥ መወዘፍን የሚጠይቅ ከሆነ ይህ መማር ሳይሆን መደንዘዝ ነው።”ትናንት በአገር ውስጥ የነበሩ ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅቶች የባህር በርን በተመለከተ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን አስፈርመው ለተባበሩት መንግስታት ሲያስገቡ (በፊርማ የሚመጣ ከሆነ እኔም እፈርምላችኋል በሚል ምጸት በድርጊቱ የተሳለቀው መለስ ዜናዊ ነበረ። ይልቁንም ባህር በር ማለት ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ባሻገር ብሄራዊ ኩራትና ሞገስ፣ ድንበርና ቁልፍ የሉዓላዊነት) የጀርባ አጥንት መሆኑ ቀርቶ ሸቀጥ መሆኑን አፉን ከፍቶ የተናገረው አፈ ሊቁ መለስ ዜናው ነበር። ያን ግዜ እጃቸው እስኪመለጥ ያጨበጨቡትና አፋቸው እስኪቀደድ የሳቁት የያኔዎቹ እቡይ ደቀመዛሙርቶች ዛሬ ላይ ስለ ባህርበር ጥቅም አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ የአለቃቸው አጽም ተመልሶ አይወጋንም ማለታቸው ይሆን። ትናንት ጨዋ የመለስ ተማሪ በነበሩበት ሰዓት እስከወዲያኛው ያሳጡንን ብሄራዊ ጥቅማችንና ምንግዜም ቢሆን በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዲገኝ ያደረጉትን ብሄራዊ ደህንነታችንን፤ ዳግም ወደ ባሰና ወደለየለት አዘቅት ውስጥ እንዳይጨምሩን ያስፈራል። የሆኖ ሆኖ ግን ገና ለገና በብዝኋኑ የመደመጥ እድል አለን በሚል ስሌት ኮርኳሪውን የባህር በር አርስተ ጉዳይ የህወሃት አቅጣጫ የማሳት ስትራቴጂ መንገድ አድርጎ ለመጠቀም መከጀል ትላንት እንደ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ተሰርቷል ከሚባለው ከቀደመው ጥፋት ይበልጥ ከባድ ስተት ይሆናል። አዎን! የህልውናችን፣ የብሄራዊ ጥቅማችንና የብሄራዊ ደህንነታችን ምንጩና ስጋቱ ያለውዛሬ ከባህር በር ይልቅ በጉያችን መሃል ያለው የወያኔ አልጠግባይ ስርዓት መሆኑን የማያውቁት ከዚህ ዘረኛ ስርዓት በሚደረግላቸው ፈሰስ የሰማያት ደጅ የተከፈተላቸው ባለግዜዎች ብቻ ናቸው። “በመፈቃቀድና በመፈቃቀር” የተደፈረ ሀገርና ሕዝብ!
******************************************!
የኢፈርት ዳይሬክተር ኣዜብ መስፍን ማጭበርበር ከትግራይ ህዘብ አይሠወርም! (ከአስገደ ገብረስላሴ ወ/ሚካኤል)
_____”ብዙ ሀገር በቀል የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ስምንት የስራ ፍቃድ ያላቸው ኮንትራክተሮች እያሉ ። በደረጃ ፭ እና ፮ ገብቶ በመሥራት ሀገር በቀል ኮንትራክተሮች እንዳያድጉ ወይ እንዲሞቱ አድርጓል ። ከሱ ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ኩባንያዎች ስራ የሚሰጣቸው ሱር ኮንስትራክሽን በቃኝ ካለ በኋላ ነው ስራ የሚሰጣቸው ። የተቀሩት ፳፰ ግዙፍ ኩባንያዎችም በሙሉ በሌሎች ሀገር በቀል ኩባንያዎች ሊሰሩ እየቻሉ ስለህዝብ ተጠቃሚነት ደንታ የሌለው የህወሓት አመራር ግን አዜብ መስፍን እንዳለችው ለባለሀብቶችን የሚያሰለጥንና የሚደግፍ ሳይሆን የህወሓት ተላላኪ ያልሆኑ ባለሃብቶች ሆን ብሎ እንዲነቀሉ ነው እየተንቀሳቀሰ የቆየው አሁንም እየተገበረው ያለው ። የመለስ ረኣይ እኮ ” በሀገራችን ያሉ የንግድ እና የእንድስትሪ የእንጅነሪንግ ኩባንያዎች ከ፲ ዓመት በኃላ ፻ በ ፻ በኢህኣደግ አባል ፓርቲዎችና በመከላከያ ሚኒስቴር ፣ ሥር እንደሚሆን በግልጽ አስምሮበት አልፏል!። ታድያ አዜብ መስፍን የምታደናግረው እንዴት ብሎ ተቀባይነት ያገኛል? ። እነዚህ ፍጡራን በበረሃ ዓለም የደረሰበት ሥልጣኔ እንዳናውቅ አፍነውን የኖሩ አልበቃም ብሏቸው አሁንም ለዚህ አዲስ ትውልድ አጭበርብረው ሊያልፉ ነው የሚፈልጉት? ፍጹም አይሆንም!። አይቻልም!።
የሁለቱ ዋርዲያዎች፤ ጆቤና ጻድቃን ገብረተንሳይ በባህር በር አጀንዳ…. ለኢንዱስተሪ መር ግባችን ለባሕር በር ሙቱልን ወይስ ጓዶቻቸውን ከመሞገት ይህን የፈርደበትን ብሔር፫ብሄረሰቦችና፪ ሕዝቦች፩ ማወናበድ፡ ማደናበር፡ማስበርገግ…. አልተግባብቶም አለ!? ዘይገርም..