• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለትብብር እንቆቅልሽ መላ

November 4, 2016 11:25 pm by Editor Leave a Comment

በዚህ ፅሁፍ ስለ አማራጭ ሃይሎች ትብብር አስፈላጊነት የታወቀ ነገር ስለሆነ መናገር አልፈልግም። ማተኮር የምፈልገው እንዴት ትብብሩ እንደሚመጣ መላ ፍለጋ ላይ ነው። ይህም ሲባል ነገሮች ተድበስብሰው አንድ ላይ ተጨፍልቀው ማየት ሳይሆን፥ በየደረጀው ከመነሻው እስከ መድረሻው ጥርት ባለ መልኩ ለማስቀመጥ ነው። ከውጭ ለሚያይ የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች ተባብለው በሁለት ትልቅ ጎራ ተከፋፍለው በጥርጣሬ መተያየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። ባብዛኛው ግን ልባቸው የሚፈልገው ለሁሉም አንድ ነው። ያም ሆኖ አንዳንድ ተስፋ ሰጭ ፍንጭ ከመታየቱ በቀር በሁለቱ ጎራ ዙሪያ ፈቀቅ ያለ ነገር እየተደረገ አይደለም። ስለዚህ አድበስብሰን ለመግባባት እስካሁን የሞከርነው ጠብ ስላላለ አዲስ መንገድ እንከተል። እስቲ ይህንን መንገድ በሶስት ደረጃ ከፍለን እንየው።

1ኛ/ ቅድመ መግባባት ለመሰባሰብ ነው

2ኛ/ መግባባት ለውይይት ነው

3ኛ/ ድህረ መግባባት ለአንድ ድምፅ ነው

1ኛ/ ቅድመ መግባባት ለመሰባሰብ

ስለ ውይይት ከማውራታችን በፊት ከየጎራችን ወጥተን በአንድ ቤት ውስጥ መሰባሰብ ይኖርብናል። ስለዚህ ቅድመ መግባባት ከተለያየ ጎራችን አውጥቶን ወደ አንድ መካከለኛ ቤት እንድንሰበሰብ አቅም ይሰጠናል። ይህም ማለት ቅድመ መግባባት ዓላማው ሁሉንም አግባብቶ አንድ ላይ እንድንቀመጥ እንድንችል መፈቃቀድ እንዲኖረን የሚያደርግ ነው። ለያይተውን በየጎራችን ተዘልለን እንድንቀመጥ ከሚያደርጉን ነገሮች ይልቅ የምንስማማባቸው ነገሮች ይበልጣሉ። አፋችን የተለያየ ነገር ቢያወራም ልባችን የሚፈልገው ነገር ግን ይመሳሰላል። ይህ ቅድመ መግባባት እንዲኖር ልብ ለልብ መናበብ እንደ መጀመሪያ ስሌት መምረጥን ይጠይቃል። ከምናወራው ወሬ ይልቅ፥ ስሩ ጋ ሄደን አንዳችን የሌላውን ልብ ማዳመጥ ይኖርብናል። ልብ ለልብ ስንናበብ፥ ይህ ቅድመ መግባባት እውን ይሆንልናል። ለአብዛኛው ህዝብ ልብ ለልብ በመናበብ ቅድመ መግባባት ይፈጥራል ብዬ የማስበውን ከዚህ በታች እዘረዝራለሁ።

ሀ/ መሬት ላይ ያለው ሕዝብ አንድ ነው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔረሰብ ሳይለይ የተጨቆነና በድህነት ለዘመናት የኖረ ነው። በፍቅር ተጋብቶና ተዋልዶ ደጉንም ክፉውንም አብሮ የሚያሳልፍ ነው። በሕዝብ ደረጃ ጥልና መከፋፋት የለም። ለዳር ድንበሩ ብሔረሰብ ሳይለይ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ኢትዮጵያን እዚህ አድርሷታል። ኢትዮጵያ የተያያዘችው ተፈጥሯዊ (organic) በሆነው የፍቅር ሰንሰለትና አብሮነት ነው። ዛሬም ደምህ ደሜ ነው እያለ ፍቅሩን እየገለጠ የሚገኝ ወንድማማች ነው። ይህ የቅድመ መግባባት መሰረትና መነሻ ነው። ልሂቃንን የሕዝቡ ነፀብራቅ እንዲሆኑ ግድ የሚል እውነት ይህ ነው።

ለ/ ልባችን ውስጥ ያለው ራዕይ አንድ ነው

አዲሲቷ ኢትዮጵያ ብለን ስናስብ የሚመጣልን ለሁሉ የምታጓጓውን ኢትዮጵያ ነው። ያም ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሰፍኖባት፥ ሁሉም በእኩልነት፥ በነፃነት የሚኖርባት ሀገር የምትሆነው ናት። ሁላችንም ከሰፈነው መልካም አስተዳደር የተነሳ የሀገር ባለቤትነት ተሰምቶን ብሶታችንን ሳይሆን ኩራታችንን የምናውጅባት ሀገር የምትሆነው ናት። እኩልነትን መሰረት ባደረገው አንድነታችን ምክንያት ብልፅግና በፍትህ እንዲመጣልን ግድ የምትለን ሀገር የምትሆነው ናት። ይህ የቅድመ መግባባት ዓላማና ግብ ነው። በዚህ ራዕይ ቅድመ መግባባት ሁሉንም አግባብቶ ሁሉንም ያገባኛል ባይ መካከለኛ በሆነው የኢትዮጵያ ቤት አዳራሽ ውስጥ እንዲገኝ የግድ የለዋል።

ሐ/ ድል የሚገኝበት የህብረት አካሄድ አንድ ነው።

ተነጣጥለን እየተፎካከርን ብንገፋፋ ሁላችንም ባዶ እጅ መቅረታችን የታወቀ ነው። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንዲሉ መደጋገፍና መተባበራችን ሃይላችን እንደሆነ ለሁሉም ግልፅ ነው። መከፋፈል ለመጥፋት ሲዳርገን፥ መያያዝ ደግሞ ለድል እንደሚያዘጋጀን እሙን ነው። ይህ ደግሞ የቅድመ መግባባት ስልት ነው። በዚህ ስልት አግባብቶ ሁሉንም ለድል እንዲሰለፉ ይችሉ ዘንድ አንድ ቦታ ለውይይት እንዲገናኙ አፅንዎት ይሰጣል።

በነዚህ ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት የጋሪዮሽ ነጥቦች ላይ መተማመንና መስማማት ካለ ቅድመ መግባባት አለ ማለት ነው። ቅድመ መግባባት ካለ ደግሞ በየጎራችን ተወስነን በስማ በለው ከመጯጯህ ይልቅ፥ ከየጎራችን ወጥተን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን ፊት ለፊት እየተያየን ለመወያየት ተዘጋጅተናል ማለት ነው። ስለዚህ ከቅድመ መግባባት በዋላ የሚመጣው ሁለተኛው ደረጃ ላይ የሚገኘው መግባባትን ደግሞ ቀጥለን እንይ።

2ኛ/ መግባባት ለውይይት

በዚህ ክፍል ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነን ማለት ነው። አብረን ለመኖር ተስማማን እንጂ እንዴት እንኑር የሚለውን ለመፍታት ውስብስብና አስቸጋሪ ነገር ነው። ለኢትዮጵያ ያለን የመፍትኤ አመለካከት ልዩ ልዩ ነው። ግን በዚህ ልዩነት ላይ ፈርጀ ብዙ የሆነውን መፍትኤ ለመፈለግና ለመግባባት የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች የሚባለው ጎራ ውስጥ መሰወር ትርጉም የለውም (በቅድመ መግባባት ያንን ፈተነዋልና)። ምክንያቱም በአስተሳሰብ ላይ ውይይት ሲደርግ ከኢትዮጵያይ አንድነት ሃይል ጎራ ነኝ የሚለው ሁሉ አንድ ዓይነት አመለካከት አይኖረውም። ከብሔር ተኮር ሃይሎች ጎራ ነኝ የሚለውም እንደዚሁ የተለያየ ዓይነት አስተሳሰብ ነው ያለው። በዚህ ስፍራ የብሔር ተኮር ሃይሎችና የኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች የሚለው መለያ አርማ፥ እየሆነ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከመግለፅ ይልቅ እውን ሊሆን የማይችለውን ቅራኔ በባዶ ሜዳ ያጋግላልና በቅድመ መግባባት መጀመሪያ ዕልባት ያግኝ የተባለው ለዚህ ነው። ይህ ሲባል በየብሔረሰቦች አይደራጁ ወይም በየብሔረሰብም አይወያዩ ማለት አይደለም። ግን የማታ ማታ የሚያያይዘን በጠረጵያ ዙሪያ ቁጭ ብለን እንድንወያይ የሚያደርገን በአንድ ቤት ውስጥ ለውይይት መቀመጥ ስንችል ነው። ቅድመ መግባባት ወደ አንድ ቤት ከሰበሰበን ዘንዳ ሰከን ብለን መወያየት እንችላለን ማለት ነው። በመፍትኤው ላይ ለመግባባት ቀጠሮ ሳንሰጠውና ለነገ ሳናሳድር ተወያይተን ዛሬ መንግስት በስራ ላይ ከሚተገብረው መፍትኤ ጋር በትይዩ አማራጭ የምንላቸውን አንድ፥ ሁለት፥ ሶስት ••• ብለን እንወስንና በነዚሁ ዙሪያ እንደ እምነታችን እንሰብሰብ።

3ኛ/ ድህረ መግባባት ለአንድ ድምፅ

በመግባባት በተለያዩ አማራጭ መፍትኤዎች ዙሪያ ከተሰባሰብን የሚቀጥለው ድህረ መግባባት ነው። በድህረ መግባባት አማራጭ ሃይሎች ሁሉ የመፍትኤ ሀሳብ ልዩነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመቀናጀት አንድ የጋራ የሆነ ድምፅ ይኖራቸዋል። ያም ድምፅ ለምሳሌ ዲሞክራሲና የመብት መከበር ጉዳይ ሊሆን ይችላል። በቅድመ መግባባትና በመግባባት ያሉትን ሁለት የቤት ስራዎች ሳንሰራ አማራጭ ሃይሎች አንድ ሁኑ ብሎ መጮህ የትም አላደረሰንም። ግን ጥርት አድርገን በየደረጃው ያሉትን ጥያቄዎች እየመለስን ብንሄድ የትብብር ስኬት የእኛ ነው።

ማጠቃለያ

ኢትዮጵያ ለማንም የመለያያ መለያ አርማ አትሆንም። ምክንያቱም የሁሉም ናትና። ስለዚህ እርስ በርስ ከመካሰስ፥ ከሁሉ በፊት ደረጃ በደረጃ ቅድመ መግባባቱ ተደርጎ፥ በልባችን የተግባባንባቸው ነጥቦች አቀራርበውን ሲያበቁ ያኔ እናስተውልና ድልድይ ሰርተን በአንድ ላይ ቁጭ ብለን ለመነጋገር እንሰብሰብ። እየተፈራራን ሩቅና ሩቅ ሆነን ከምንፈራረድ፥ በቀና መንፈስ ተቀራርበን ፈቀቅ የሚል ነገር እንወያይና በተወሰኑ የተለያዩ አማራጭ የመፍትኤ አሳቦች ላይ መግባባት ላይ እንድረስ። በመጨረሻም በድህረ መግባባት ተቀናጅተን በአንድ ድምፅ እንቁም። በዚህ መንገድ ብንቆርጥና ብንሄድ ለዓመታት እውን ያልሆነው ትብብር በወራት ውስጥ ብቅ ብቅ ማለት ይችላል ብዬ ተስፋ አደርጋለው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ኢሜል፦ ethioFamily@outlook.com 


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

 

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm
  • “ሙሽራው እስኪመጣ የምትቆይ ቤተክርስቲያን እናድርጋት” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ February 15, 2023 03:13 pm
  • በመዝገበ ቃላት የችጋር መጠሪያ የነበረችው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንዴ ወደ ውጭ ላከች February 13, 2023 03:28 am
  • ውዝግቡን በሐዋሪያት መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል February 10, 2023 09:06 am
  • የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው ቄሮ” መሪ ዘመድኩን በቀለ! February 10, 2023 12:48 am
  • በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር February 9, 2023 01:25 pm
  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule