• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አዲስ ዓመት?

January 15, 2014 06:56 am by Editor 1 Comment

ከሁለት ሳምንታት በፊት የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንደገባ እናስታውሳለን፡፡ ይሄን ተከትሎ የአንዳንድ ድርጅቶች ሲገርመን ባልተለመደ መልኩ ጭራሽ ከሀገርና ከሕዝብ እሴትና ጥቅም አንጻር ከፍተኛ ኃላፊነት ያለበትና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅበት የብዙኃን መገናኛውም (ሚዲያው) ይህንን የባዕዳኑን አዲስ ዓመት እድምተኞቻቸውም ማለትም አድማጭ ተመልካቾቻቸውም በዓሉን በማክበሩ እንዲቀላቀሏቸው በሚጋብዝ መልኩ በድምቀት አከበሩ፡፡ ይህ ስሕተት ጎልቶ ከታየበት የብዙኃን መገናኛዎች አንዱ ኢ.ቢ.ኤስ. በሚል አሕጽሮተ ቃል የሚጠራው የኬብል ቴሌቪዥን ነበር፡፡ በዚህ ቴሌቪዥን (ምርዓዬ-ኩነት) ከሚተላለፉ ዝግጅቶችና ይህን ስሕተት ከፈጸሙት ምስናዶች (ፕሮግራሞች) አንዱ “መቅዲ ሾው” (መቅዲ ትዕይንተ-ወግ) የተሰኘው ምስናድ ነበር፡፡ ጉዳዩ ትንሽ የሚያበሳጭ ስለነበር ለአዘጋጇ በፌስ ቡክ (በመጽሐፈ-ገጽ) አድራሻዋ ከዚህ በታች ያለውን ማስታወሻ በመጻፍ ስሕተቷን እንድትገነዘበው ወደፊትም እንዳትደግመው ለማሳሰብ ሞከርኩ፡፡

በቅድሚያ ግን ስለእኛና ስለምእራባዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ባጭሩ ላውራላቹህ፡፡ ቀደም ሲል ምእራባዊያን ይጠቀሙበት የነበረው የዘመን አቆጣጠር የጁሊያን አቆጣጠር ነበር፡፡ የዘመን መቁጠሪያው በሮም ንጉሥ  ጁሊየስ ቄሳር ስም የተሠየመ ነበር፡፡ ጁሊዬስ ቄሳር ከዛሬ 2052 ዓመታት በፊት ላይ የጀመረ ነበር፡፡ ይህ የዘመን አቆጣጠር እንደኛ ሁሉ አንድ ዓመት 365 ቀናት ከ1/4 ኛ እንዳሉት ያምን ነበር፡፡

የጁሊያኑን የዘመን አቆጣጠር የቀመረው በንጉሡ በጁሊየስ ቄሳር ትእዛዝ መሠረት ከግብፅ አሌክሳንድሪያ የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት አንዱ የነበረው ሶሲጂነስ ነው ፡፡ ይሄንን አቆጣጠር ሲጠቀሙ ቆይተው ጎርጎርዮስ የተባለ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባት በ365 ዓ.ም. ከ1641 ዓመታት በፊት ቀደም ሲል ይጠቀሙበት የነበረውን በአንድ ዓመት ያሉትን ቀናት ትክክል አይደለም በማለትና 11 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመቀነስ ዘመኑን እንደገና ከልሶ ቀመረና አዲስ የዘመን አቆጣጠር በመፍጠር የበፊቱን በመቀየሩ በሱ ስም የሚጠራ የጎርጎርዮሳዊያን (የግሪጎሪያን) የሚባል የዘመን አቆጣጠር ሊኖራቸው ቻለ፡፡  አንድም ይሄው ጎርጎርዮስ የተባለ ሰው የነበረውን የቀየረበት ምክንያት እስካሁን ክርስቶስ ተወልዷል ብለን የምናስበው ዘመን ትክክል አይደለም እስካሁን ከምናስበው ዘመን 8 ዓመታት  ዘግይተን ነውና እየቆጠርን ያለነው መስተካከል አለበት ብሎ ከነበረው ላይ 8 ዓመታትን ጨመረበት፡፡ በዚህም ምክንያት ከእኛና እንደቀድሞው ቢሆን ደግሞ ባጠቃላይ ከምሥራቅ አብያተክርስቲያናት (oriental churches) ጋራ ሊለይ ቻለ፡፡ አሁን አሁን ግን ራሷ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይህ ድርጊት ስሕተት እንደነበርና ወደትክክለኛው መመለስ እንደሚገባ እየተናገሩና ይገኛሉ፡፡

በቅርቡም ጀርመናዊው የሮማ ካቶሊክ ፓፓ የነበሩትና በፈቃዳቸው መንበራቸውን የለቀቁት ፓፓ ቤኔዲክቶስ ትክክለኛው የዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር እንደሆነ የሚመሰክር መጽሐፍ መጻፋቸው ይታወቃል፡፡ እነኝህን ሁለት የተለያዩ የሚመስሉ የጁሊያንና የጎርጎርዮስ የዘመናት አቆጣጠር የመጀመሪያውን ማለትም ለሁለተኛው መሠረት የሆነውን የጁሊያኑን የዘመን አቆጣጠር የቀመረው በንጉሡ በጁሊየስ ቄሳር ትእዛዝ መሠረት ከግብፅ አሌክሳንድሪያ የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት አንዱ የነበረው ሶሲጂነስ እንደነበር አንስተናል፡፡ ለግብፃዊያኑ ደግሞ መሠረት የሆነው እኛ ኢትዮጵያዊያኑ ነን፡፡ ይሄንንም የራሳቸው የግብፃዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ሊቅ የነበረው አቡሻኽር በስሙ በተሰየመው መጽሐፉ ላይ ጠቅሶታል፡፡

የእኛ የዘመን አቆጣጠር ደግሞ ልክ እንደሃይማኖታችን ሁሉ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገን ስናወራ ኢትዮጵያ ከቀደሙት የቀደመ አምልኮ እግዚአብሔር እንዳላት እንጅ ከመቸ ጀምሮ እግዚአብሔርን ማምለክ እንደጀመረች በውል አይታወቅም፡፡ ከቀደሙት የቀደመ አምልኮ እግዚአብሔር ሊኖረን የቻለበት ምክንያት ከአዳም ጀምሮ ሳይቋረጥ በትውፊት ሲወራረስ የመጣው አምልኮ እግዚአብሔር ሳይቋረጥ በእኛ ስለነበረ ነው፡፡ በዚህም ብቸኞች ነን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የዘመን አቆጣጠራችንም አሁንም የሰው ልጆች ሁሉ አባት ከነበረውና ከእግዚአብሔር ጋራ ተቃጥሮ ከነበረው አዳም ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ  ያልተበረዘ ያልተከለሰ ፍጹም ትክክለኛ የዘመን አቆጣጠር ነው፡፡ ይሄንን ያህል ታሪክ ቅርስ ኩራት የሆነን ሀብት ነው ዛሬ ያልገባቸው ወገኖቻችን ጭራሽ ምእራባዊያኑ በዋናው የሃይማኖታቸው መሪ በኩል ትክክለኛው የኢትዮጵያው ነው እያሉ ወደእኛ ለመመለስ በሚግደረደሩበት ወቅት የኞቹ ልጆች ሊያጠፉብን እየተባበሩብን የሚገኙት፡፡ አያሳዝንም???

ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ ለባለ ትዕይንተ-ወግ አዘጋጇ መቅደስ የሰጠኋት አስተያየት የሚከተለውን ይመስል ነበር:-

ሰላም መቅደስ እንደምን አለሽ ሥራ እንዴት ይዞሻል ባክሽ? ልጠይቅሽ የምፈልገው አንድ ጉዳይ አለ ልብ ብለሽ በጥሞና አንብቢው ፡፡ ኢትዮጵያዊነትሽን ትወጅዋለሽ? ትኮሪበታለሽስ? መልስሽ አዎ የሚሆን ከሆነ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ይገባሻል? ምን ለማለት ፈልጌ መሰለሽ ኢትዮጵያን ሀገራችንን መውደድ ማለት እሴቷን፣ መለያዋን፣ ታሪኳን፣ ሥልጣኔዋን ወዘተ. መጠበቅ፣ መንከባከብ፣ ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ፣ በዚህ መሠረት ላይም እንደዜጋ የሚጠበቅብሽን የበኩልሽን ማበርከት ማለት እንደሆነ ልነግርሽ እወዳለሁ፡፡ ከዚህ ውጭ ሀገርን መውደድ ሊገለጥ አይችልምና፡፡ እኛ (የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት) እስከአሁን የበጀት መዝጊያና መክፈቻችን ማለትም ዘመንን የምንቆጥረው በራሳችን የዘመን ቀመር እንደሆነ ታውቂያለሽ ብየ እገምታለሁ፡፡

ሰሞኑን የኢ.ቢ.ኤስ. የወግ ትዕይንትሽን (talk show) ዝግጅቶችሽን ስመለከት እየሠራሽው ያለሽው ነገር በጣም አስገርሞኛል፡፡ ምን እያደረግሽ እንደሆነ አንችም እራስሽ የምታውቂው አልመሰለኝም፡፡ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው የዝግጅትሽ ተመልካች ነጮች አይደሉም ወይም ሐበሾች ናቸው ፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ለምን የነጮችን የዘመን አቆጣጠር እንደምትጠቀሚ አይገባኝም? ዝግጅቴ የሚተላለፈው በመላው ዓለም ላሉ ሁሉ ነው ብትይም እንኳን አሁንም ቢሆን ታዳሚዎችሽ ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ እነሱም ቢሆኑ ከየሚኖሩበት ሀገር ዜጋና ሀገር የሚያነካካቸው ጉዳይ ካልሆነ ወይም ከሌለ በቀር በምዕራባዊያን አቆጣጠር ካልተጠቀማቹህ ተብለው መገደድ አይኖርባቸውም አይገባምም፡፡

ማንነትን ከመጠበቅ የዜግነት ግዴታ አንጻርም ይሄንን ማድረግ አይጠበቅባቸውም፡፡ አንች ግን የምትጠቀሚው የዘመን አቆጣጠር የባዕዳኑን እንደሆነ ለማስታወቅም አሮጌው ዓመታቸው ሲቋጭ በጀትሽን ዘጋሽ በዓመቱ የተላለፉ ዝግጅቶችሽን እየቀነጫጨብሽ ባለፈው ዓመት እነኝህ እነኝህ ዝግጅቶች ቀርበው ነበር ብለሽ አቀረብሽ፣ አዲሱ ዓመታቸው ሲገባ ደግሞ ልክ እኛ የራሳችንን አዲስ ዓመት እንቁጣጣሽ በምናከብርበት ድምቀት አክብረሽ የእንኳን አደረሳቹን ሰላምታሽን በተደጋጋሚ በማቅረብ የአስቴር ዐወቀን የአዲስ ዓመት “አበባ አየሁሽ” የሚል ዘፈን አቀረብሽ፡፡ ሲጀመር ይህ ዘፈን ቁርኝቱና መልእክቱ የተፈጥሮ ዑደት ከሚከሰትበት ከእንቁጣጣሽ ወይም ከእኛው አዲስ ዓመት ጋራ ብቻ በመሆኑ የዘፈን ምርጫሽ ስሜት አልሰጠም ወይም አልተጣጣመም፡፡ አንች ያየሽው የአዲስ ዓመት ዘፈን መሆኑን ብቻ እንጅ ዘፈኑ ከያዛቸው ስንኞች አንጻር የሚፈጠረውን የመልእክት መጣረስ አልነበረምና የዘፈን ምርጫሽ ስሕተት ሊያጋጥመው ቻለ፡፡

መቅደስ ፍላጎትሽ ምንድን ነው በትክክል ታውቂዋለሽ? ይሄንን ማድረግ ለምን አስፈለገ? አንችን ወይም ይሄንን ድርጊትሽን ሌላውም ዜጋ አርዓያ ቢያደርገውና የዘመን አቆጣጠሩንም እንዳንች ሁሉ በምዕራባዊያን ቢያደርገው የራሳችን ጠፋ ተረሳ ማለት እንደሆነና ይሄንን ከዜጋ የማይጠበቅ የጥፋትና የጠላት ሥራ እየሠራሽ እንደሆነና እንደኔ አድርጉ እያልሽ ማስታወቂያ እየለቀቅሽ እንደሆነ እንዴት መገንዘብ ተሳነሽ? መሠልጠን ማለት ይሄ ይመስልሻል? በእርግጥ ከምዕራቡ ዓለም ልንወስደው የሚገባ ብዙ ነገር አለ ይሄ ማለት ግን እንዲህ ዓይነቱን ማለትም የማንነትና የሥልጣኔ አሻራዎቻችንን መገለጫዎቻችንን የሚያጠፋ የሚያስቀር ማለት እንዳልሆነ አበክሬ ላስገነዝብሽ እወዳለሁ ፡፡

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እናም አንችን ጨምሮ ብዙኃን መገናኛ ላይ ያላቹህ “ባለሙያዎች” በሙሉ እባካቹህ እዛ ቦታ ላይ ፊጢጥ ከማለታቹህና በውል የማታውቁትን የማትረዱትን እየዘባረቃቹህ ነገር ከማበላሸታቹህ በፊት ይሄንን ሥራ የሚሠራ ሰው ከኢትዮጵያዊነት ወይም ከብሔራዊ ጥቅም አንጻር መጠንቀቅ ያለበትን ጉዳዮች ጠንቅቃቹህ ዕወቁ ሥራውን ለመሥራ ከመነሣታቹህም በፊት አቅማቹህን በቅጡ ገንቡ አማርኛችሁንም አብስሉ ብዙ ብዙ ብዙ ነገር እያበላሻቹህ ነውና ፡፡ እባካቹህ እባካቹህ …

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. ezra says

    January 25, 2014 02:22 am at 2:22 am

    እናመሠግናለን ሠዓሊ ገ/ኪዳን! ግሩም አስተያየት (COMMENT) ነው። እነ መቅደስ የማንነት ቀውስ ያለባቸው ይመስላል። ሲጀመር የፕሮግራማቸው መጠሪያ ”’Mekdi Show” “Jossy In Z house” ወዘተ…የሚል ነው ፤ ይሄ የሚያሳየው የማንነት ቀውሳቸዉን ውስጣዊ ይዘት ነው። በማንነት ቀውስ ውስጥ ከሚዋዥቁ ሰዎች ደግሞ ኢትዮጵያዊ እስቴቶችንና ስነ ምግባሮችን መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደመጠበቅ ይሆናልና እነ መቅዲን የማንነት ቅውሳቸዉን በልብስ “በፋሽን ሾው” ደበቀው ሲዘባነኑ ነው የሚያሳዩን ። ሠዓሊ ኣምሳሉ በድጋሚ ሞቅ ያለ ምስጋናዬን እልግሳለሁ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule