1/ መግቢያ
በድሮ ጊዜ ሰው በሰው ሲበደልና ፍትሕ ሲጓደል ‘ያገር ያለህ’ ወይም ‘የዳኛ ያለህ’ በማለት ይጮህ ነበር፤ ይህ ዓይነቱ የተበዳይ ጮኸትም ለትውልድ መርገም እንዳይሆን ተብሎ በአካባቢው በሚኖሩ እድሜና ልምድ ጠገብ ሺማግሌዎች ገላጋይነት/ዳኝነት የበደለ እንዲክስ የተበደለ ደግሞ እንዲካስ በማድረግ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ይደረግ ነበር፤ እኔም ዛሬ በዲሞክራሲ ስም በምድራችን ውስጥ እየሆነ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ /በተለይ ባለውለታ በሆነችው በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ/ ቀረብ ብየ ስመለከት ይህ እውነተኛ የፍትህ ፈላጊዎች ያገር ያለህ ጩኸት ትዝ ብሎኝ ለኢትዮጵያውን በሙሉ ለውይይትና ለመፍትሄው ፍለጋ ጭምር የሽማግሌ ዳኞች ያለህ በማለት ጮኸቴን ላቀርብ ተገደድኩ።
መቸም ለተወሰኑ ዓመታት ከአገሩ ራቅ ብሎ ለኖረ ኢትዮጵያዊ የአዲስ አባባ ገጽታ ቀየር እንደምትልበት ይታመናል፤ በርካታ ሕንጻዎችና መንገዶች ተሠርተዋል፤ ባቡርም ተጀምሮ ሕዝቡ እየተጠቀመበት መሆኑን በግልጽ ማየት ይቻላል፤ ለራሴ ሕሊና ታማኝ መሆን ስላለብኝ የሚታዩትን መልካም ነገሮች እሰየው በማለት፣ ደስ የማይሉትንና ደካማ የሆኑትን ደግሞ ለእርምት በግልጽነት ብጠቁም ሰውነቱን የሸጠ ካልሆነ በስተቀር ቅር የሚሰኝ እውነተኛ ሰው የሚኖር አይመስለኝም። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Yikir says
Ethiopia kibiruwa befokina be babur ayidelem. Jeginoch andinetiwan,dardinberiwan yaskeberut be AGER FIKIR NEW.ZARE ETHIOPIAN BEMITELU HIZIBUWAN BEGIF BEMIGEDILU meseriwoch zerafiwoch yeteseraw hulu yezegochin dem bemafises new. Lemagni ,yabedewi,berenda adariw,/ye hitsanat lemagnochin ,….be tiwilid lay teremamido yeteseran neger atadanki. SILE RIHAB,WENJEL,YESEW KIBIR HIWOT BEWELAJ GUYA SIR YEMIGEDELIBETIN HAGER fok ,babur batawera yishalal.
eunetu says
ይቅር????
የምትለው ጨርሶ አልገባኝም!
ምክር የምትሰማ ከሆነ አጠገብህ ካሉ ምሁራን ትንሽ እውቀት ማግኘት ብትችል ጥሩ ጸሀፊ ትሆናለህ፤ ድፍረትህ ከእውቀት ጋር ቢሆን ውበት ይኖረዋል።
አይዞህ እውነቱን ሳልነግር ማለፌ አንተን በድፍረትህ ገደል እንድትገባ ማድረግ ነውና። ብልህ ሰው የሚማር ሰው ነው!!!
እውነቱ