
ወንድ ልጅ ሲወለድ አባት ለተወለደው ልጁ ጠብ – መንጃ (ጠመንጃ) ለመግዛት ደፋ ቀና ከሚባልበት አካባቢ ነው ተወልጄ ያደኩት፡፡ ይህ የሚደረገው ደግሞ በቂ ሃብት ስላለ ሳይሆን “ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ እንዝርት አቅርቡለት ይፍተል እንደ እናቱ” የሚለው የንቀት አባባል በልጁ ላይ ሲያድግ እንዳይደርስበት ከወዲሁ ለማዘጋጀት ነው፡፡ እንዲያውም ልጅ በልጅ ተሸንፎና ተመትቶ እያለቀሰ ወደ ወላጆቹ ለእርዳታ ሲቀርብ አልቃሻ ልጅ አልወድም/የለኝም ተብሎ በጥፊ ወይም በአለንጋ ይደገማል፡፡ በለው! ትሸነፍና ወዮለህ! እንዳታሳፍረኝ! የሴት ልጅ! (ከወንድ ብቻ የተወለደ ያለ ይመስል)፣ ሊጥ አትሁን!፣ አስለቅስ እንጂ አታልቅስ!፤ አትበለጥ! ኩራት እራቱ! ከአረባባ ግልድም ሙልጭ ያለ ቂ . . . ይሻላል! ከማን አንሼ!. . . ወዘተ እየተባልንና እያልን ነው እኛ ኢትዮጵያውያን በአብዛኛው ያደግነው፡፡ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ተመካክርን ለአገር/ለሕዝብ ጥቅም የሚሆን በጎ ሥራ በሁሉም መስክ መሥራትና ከእኛ የተሻለውን ወንድማችንን ሳይቀር መሪ አድርገን መቀበል ያቃተን፡፡ “ማን ከማን ያንሳል” በሚል ትቢትና ንቀት ምክንያት መሆኑ ነው፡፡ የፈለገውን ያህል ይራቀቅና ይጠበብ እንጂ አበሻ በአበሻ እውቀት አይተማመንም፡፡ እስከ አሁን ድረስ መድሃኒት ያልተገኘለት በሺታችን ይህ የራሳችንን ሰው ችሎታ አምነን በመቀበል መጠቀም አለመቻላችን ነው፡፡ ተግባራዊ ሲደረግ አይታይም እንጂ በተለይ ክርስቲያን “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ” (ፊልጵ 2፡3-4) የሚል ዘላለማዊ የትዕዛዝ ቃል ተሰጥቶት ነበር፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
አቤት አቤት እንዴት አይነት አጭበርባሪና ግብዝ ፍጥሮች በየቦታው አሉ? ጎበዝ! ምን አይነት እርካሽና አታላይ ፍጡሮች ነው ሃገሬ እየፈላባት ያለው? ወንድም የምትለው እውነት ቢሆን ኖሮ፣ ፎቶህን ጭምር ይፋ ማድረጉ ይቅር፡፤ ቢያንስ ትክክልኛ ስምህንና የኢሜይል አድራሻሕን በይፋ መግለጽ በቻልክ ነበር። አልገባሕም እንጂ! ቢገባህ ኖሮ የበለጠ ያጋለጥከው ይሄ አንተ የምትሰብክለትን በእምነት ስም የሚጠራ ድርጅትንና ምን ያሕል አጭበርባሪ፣ አስመሳይና የየዋሆች ሰዎች ጥርቅም እንደሆነ ነው።
Dagnamyelew,
Welcome for your comment even if it has nothing to teach. As to me, it is better to think over and over before you comment whom you don’t know. If you want to know me, please email me so that we can discus about anything you want. Otherwise, such kind of comment won’t be useful for all of us.
Wish you good heart for all Ethiopians and others.
God bless you abundantly!!!!!!!!!!!!!!!!!
Selam