በመጀመሪያ ደረጃ “የትግራይ ህዝብ” ስል ከኢትዮጵያ ህዝብ በተዘረፈ ሃብት የቅንጦት ህይወት የሚኖሩትን፣ በስርቆት ሃብት አጉል የሚቀብጡትን የካድሬ ልጆችና ወዳጆች አይመለከትም። “የትግራይ ህዝብ” ስል በህወሓት ድጋፍና ድጎማ የሚኖሩ የድርጅቱን አባላትና ፅንፈኛ ደጋፊዎች አይመለከትም። የእነዚህ ሰዎች ስኬት እና ውድቀት፣ ድህነት እና ሃብት፣… በአጠቃላይ ሁሉ ነገራቸው ከህወሓት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ የድርጅቱ አመራሮች የደገፉትን ይደግፋሉ፣ የተቃወሙትን ይቃወማሉ። የእነሱ ዕለት-ከእለት ኑሮ ከህወሓት መኖርና አለመኖር ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ህወሓት የህልውናቸው መሰረት ነው። በእርግጥ እነዚህ ሰዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች “የህወሓት አፈ-ቀላጤዎች” እንጂ “የትግራይ ህዝብ” ሊሆኑ አይችሉም፤ እነሱ የህወሓት ካድሬዎች እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደሉም! ከዚያ … [Read more...] about የትግራይ ህዝብ ሆይ፦ “ሀገርና ህዝብ ከህወሓት በፊት ነበሩ፣ ከውድቀቱም በኋላ ይኖራሉ!”