ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ታላቅ የሥልጣን መቀመጫ ሲረከቡ “ለተደረገልን ምደባ አመሰግናለሁ” ማለታቸውን ተከትሎ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ሹመት “ምደባ” የሚል ስያሜ አግኝቷል። ትላንት ለተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ የሽግሽግ ምደባ አቶ ጁነዲን ሳዶ ከምደባ ተዘለው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ይፋ ሆኗል። የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወንበራቸውን ለአቶ ሙክታር ከድር እንዲያስረክቡ ተደርጓል። ኦህዴዱ አቶ ሙክታር የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ታክሎላቸው አቶ ጁነዲን ሲመሩት የነበረውን የሲቪል ሰርቪስ ተቋም እንዲመሩ ሲደረግ አቶ ሃይለማርያም ስለአዲሱ ተሿሚ አቶ ሙክታር ቁርጠኛነትና ብቃት ሲያብራሩ ስለ አቶ ጁነዲን ከሃላፊነት መነሳት ግን ያሉት ነገር የለም። ለዚህም ይመስላል የመድረክ አባል ብቸኛው ተቃዋሚ አቶ ግርማ ሰይፉ “ህዝብ … [Read more...] about የጁነዲን መጨረሻ አልታወቀም
Archives for December 2012
ህወሃት አረጋግቶ አገገመ
ኢህአዴግ “አረጋግቶ አገገመ” ከተባለው አዲሱ “ምደባ” መካከል የንግድ ሚኒስትር ተብለው በተሰየሙት ላይ ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጠንካራ መከራከሪያ በማቅረብ ተቃወሙ። አቶ ግርማ የሚሾሙ ብቻ ሳይሆን የሚነሱ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም ለህዝብ መቅረብ እንዳለበት አሳሰቡ። አቶ ሃይለማርያም ተቃውሞውን “መክረንና ገምግመን ያደረግነው ነው” ሲሉ ተከላከሉ። አቶ ግርማ ብሩ (አሁን አምባሳደር) ሲመሩት የነበረውን ሚኒስቴር መ/ቤት “ስያሜና ምልክት መለየት የማይችል” በማለት አንቋሸሹት። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በመሩበት ሶስት ወራት ካቢኒያቸውን በደንብ መገምገማቸውን በግምት በመግለጽ ተቃውሞ ያቀረቡት አቶ ግርማ ሰይፉ በምደባው በተወሰነ ደረጃ እንደሚስማሙ ተናግረዋል። የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔን ምደባ የተቃወሙት በማስረጃ … [Read more...] about ህወሃት አረጋግቶ አገገመ