… ቋንጣ ዜና አመጣሽ አትበሉኝና፤ ሰሞኑን ከፌስቡክ ጠፍቼ በከረምኩበት ወቅት የአራት አመት ከስድስት ወር ልጅ የደፈረው ዋልጌ በአራት ወር "ሲቀጣ"፣ ምስር ወጥ የሰረቀው ሰው ደግሞ አመት ከአራት ወር እስር ተፈርዶበታል ሲባል ሰምቼ በንዴት ስንተከተክ ከርምኩ፡፡ ከዚያ ደግሞ እነ አብርሃ ደስታ ሲፈቱ በደስታ ተፍነከነኩ፡፡ …ልጅ ሆኜ እናቴ ሰው ቤት ይዛኝ ሄዳ ለየኔ ቢጤ ምግብ ለመስጠት የሚሰስት ሰው ስታይ፤ "አበስኩ ገበርኩ…!ደግሞ ለሞተ…ለበሰለ ምግብ መስቆንቆን ምንድነው!" ትል ነበር፡፡ እነሆ ፍትሃችን፣ "የበሰለ" እና "የሞተ" ምግብ ለሰረቀው ሰውዬ ፣ አመት ከአራት ወር! "ያልበሰለች" እና "ታዳጊ" ልጅ ለደፈረው ሰውዬ፣ አራት ወር ሆኗል፡፡ እነሆ ፍትሃችን፣ እንዲህ እንዲህ የሌሎችን መብት ግጥም አደርጎ የሚጥስን ማበረታቻ በሚመስል የአራት ወር "ቅጣት" … [Read more...] about እነሆ ፍትሃችን
Opinions
የኔ ሃሳብ
ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ…!
* የ4 ዓመት ከ6 ወር ህጻን የደፋረን በ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል? * ወላጆቿ "ወላጅ ይፍረደን፣ ህዝብና ሀገር ይፍረደን!"ይላሉ የኢፌዴሪ ህገ መንግሥት ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በሕገ-መንግሥቱ እኩል መብትና ጥበቃ እንዲሰጣቸው ይደነግጋል። ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም … [Read more...] about ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ…!
ታሪክ የማይረሳው የኮሚቴዎቹ ስቅየት
የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፈንታ አጨልመን እንድናይ ከሚያስገድዱን ሁነቶች ውስጥ ለእስልምና ሃይማኖት የትኞችም አይነት ጥያቄዎች በአገዛዙ በኩል እየተሰጡ ያሉ አሉታዊ ምላሾች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሐምሌ 27/2007 ዓ/ም የተላለፈው “የፍርድ ውሳኔ” ኢሕአዴግ የሚል ገዥ መደብ እስልምናን በምን ያህል መጠን አፍኖ እየገዛ እንዳለ የአደባባይ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል፡፡ በኮሚቴው አባላት ላይ የተላለፈውን “የፍርድ ውሳኔ” ከሃይማኖታዊ መነጸር ባሻገር ጉዳዩን ከፍትህና ከሞራል ልዕልና አኳያ ማየት ተገቢ ነው፡፡ የዚህ አጀንዳ ቀዳሚ ጉዳይ የኮሚቴውን አመሰራረት በማስታወስ የፍርድ ሂደቱን በመጠኑም ቢሆን በመቃኘት የኮሚቴ አባላቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ በተመለከተ ሦስት የሚሆን እድል (Scenarios) በማስቀመጥ ማሳየት ይሆናል፡፡ የንቅናቄው … [Read more...] about ታሪክ የማይረሳው የኮሚቴዎቹ ስቅየት
በሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፀረ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃውሞ ተደረገ
ሰሞኑን ህወሃት/ኢህአዴግ በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውሳኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ አርብ ኦገስት 7 2015 ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል። ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት ይህ ታላቅ ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደ ነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱ የትግሉ አንድነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በአገዛዙ ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተዋል፡፡ ሲቀጥሉም ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥ ትግሉን በበሰለና በሰለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም … [Read more...] about በሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፀረ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃውሞ ተደረገ
በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የተወሰነውን እስራት ሸንጎ ያወግዛል
ሰኞ ሐምሌ 27፣ 20017 (ኦገስት 3፣ 2015) በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የህወሓት/ኢህአዴግን ፍላጎት በማስፈጸም የሚታወቀው ፍርድ ቤት ከሰባት ዓመት እስከ 22 ዓመት የሚደርስ እስራት እንደበየነባቸው ይፋ ሆኗል። የሞስሊሙ ኅብረተሰብን የተቃውሞ ድምጽ መሠረት በማድረግ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ በማፈላለግ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩት እነአቡበከር አህመድ የታሰሩት ከሁለት ዓመት በፊት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ እምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት አመራሩን ለመቆጣጠርና እሱ የሚፈልገውን የእምነት ፈርጅ ኢትዮጵያውያን ሞሰሊሞች በግዴታ እንዲቀበሉ ያውጠነጠነውን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር እምቢ ማለታቸውን ተከትሎ እንደነበር ይታወሳል። (ሙሉውን የሸንጎ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ … [Read more...] about በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የተወሰነውን እስራት ሸንጎ ያወግዛል
የሰላም ትግሉ ያቸንፋል
የሰላማዊ ትግል ተግባራዊነትና ስኬት መለኪያው ምንድን ነው? በዚህ ልጀምር ጽሑፌን። በርግጥ መጀመር ያለበት፤ ሰላማዊ ትግል ምንድን ነው? የት ተተገበረ? እንዴት ተተገበረ? ከትጥቅ አመጹ በምን ተሽሎ ይገኛል? እዚህ ሰላማዊ ትግል፤ እዚያ ግን የትጥቅ ትግል የሚባለው እንዴት ነው? በሚሉት ነበር። ነገር ግን፤ አንባቢዬ በትክክል እንደሚረዱት፤ አሁን የያዝነው፤ በተጨባጩ በሀገራችን ባለው የፖለቲካ ሀቅ፤ ምን ላይ ነው ያለነው? ምን ማድረጉ ለትክክለኛው ሕዝባዊ ድል አመርቂ ውጤት ያስገኝልናል? ከሚለው በመነሳት ነው። እንግዲህ መሠረታዊው መነሻ፤ አሁን ያለንበት የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ነው፤ ማለት ነው። እዚህ ላይ ነው እኔ፤ ሽንጤን ገትሬ፤ “ሰላማዊ ትግሉ ያቸንፋል!” በማለት የቆምኩት። እናም ላስረዳ! ገዥው ወገንተኛ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፣ ከሕዝቡ ተነጥሎ … [Read more...] about የሰላም ትግሉ ያቸንፋል
ሁለቱ ትግሎች
ብርሃኑ ነጋ ዱር ገባ! አንዳርጋቸው ጽጌ መፅሃፍ ጨረሰ! ኦባማ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መመረጣችንን እውቅና ሰጠ! እነዚህ እንግዲህ የሰሞኑ ፖለቲካዎች ናቸው። ያለወትሯቸው በአሜሪካ ድምፅ ላይ ለቃለመጠይቀ የቀረቡት ዶ/ር ቴድሮስ አድኅኖም ያልበላቸውን ሲያኩ ተደምጠዋል። አድማጭ ልብ ሊለው የሚገባ ጉዳይ አለ። ዶፍተሩ ስለ ብርሃኑ ነጋም ሆነ ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ የተናገሩት ሳይጠየቁ ነበር ይኼ እንግዲህ “የማርያምን ... ምን የበላ …” እንደሚባለው ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በዚህ ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይዘገባሉ፡፡ ይህ በጎልጉል … [Read more...] about ሁለቱ ትግሎች
ከሳሽ ሲከሰስ
(ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ቢኖር እኛ ኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንዲህ ብለን እንከስ ነበር!) የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 የተመለከተውን በመተላለፍ የተከፈተ ክስ የቀ/ቁ/001/2006 የወ/መ/ቁ. 01/0001/06 ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ በመላው ዓለም ከሳሽ ….. ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ) ተከሳሾች… 1/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት የሽብር ቡድኑ አጠቃላይ አስፈጻሚ 2/ የህውኃት/ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሽብር ቡድኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 3/ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (በሌሉበት) የሽብር ቡድኑ የቀድሞ አመራር 4/ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ የሽብር ቡድኑ አመራር 5/ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ 6/ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል 7/ … [Read more...] about ከሳሽ ሲከሰስ
አዱሊስ/Adulis
ባለ 21 ገጽ የአዱሊስን ልዩ ዕትም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about አዱሊስ/Adulis
በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ” ላይ የተቃጣው ሴራ ከሸፈ
ሳውዲ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም የትግል አንድነት ላይ የተቃጣው የህወሃት/ኢህአዴግ ሴራ መክሸፉ ተሰማ! ከዕርዳታ አሰባሰብ ጋርም በተያያዘ የተፈጸመው ተግባር ለሕዝብ ይፋ ሆኗል፡፡ የህወሃት/ኢህአዴግ ካድሬዎች መቀመጫቸውን ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ ካደረጉ ወዲህ የህዝበ ሙስሊም እንቅስቃሴ ለማፈን የተለያዩ ስልቶችን ነድፈው ከአካባቢው የመንግስት ሹማምንቶች ጋር ሲንቀሳቀሱ እንደ ነበር ይታወቃል። እነዚህ ምስለኔዎች ለአገዛዙ ባላቸው ታማኝነት ከጅዳ እስከ ሪያድ በዘለቀ የስለላ መረባቸው በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ” በሚያደርገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፉ ሙስሊም ወገኖቻቸውን ስም ዝርዝር ለኢህአዴግ በማቅረብ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ግፊት ሲያደርጉ የነበረ ከነፍሳቸው ይልቅ ለጥቅም ያደሩ መሆናቸውን አያሌ የእምነቱ ተከታዮች ይገልጻሉ፡፡ በተለይ እነዚህ … [Read more...] about በሳውዲ “ድምጻችን ይሰማ” ላይ የተቃጣው ሴራ ከሸፈ









