ሰኞ ሐምሌ 27፣ 20017 (ኦገስት 3፣ 2015) በሞስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ላይ የህወሓት/ኢህአዴግን ፍላጎት በማስፈጸም የሚታወቀው ፍርድ ቤት ከሰባት ዓመት እስከ 22 ዓመት የሚደርስ እስራት እንደበየነባቸው ይፋ ሆኗል።
የሞስሊሙ ኅብረተሰብን የተቃውሞ ድምጽ መሠረት በማድረግ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ በማፈላለግ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩት እነአቡበከር አህመድ የታሰሩት ከሁለት ዓመት በፊት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ እምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት አመራሩን ለመቆጣጠርና እሱ የሚፈልገውን የእምነት ፈርጅ ኢትዮጵያውያን ሞሰሊሞች በግዴታ እንዲቀበሉ ያውጠነጠነውን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር እምቢ ማለታቸውን ተከትሎ እንደነበር ይታወሳል።
(ሙሉውን የሸንጎ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply