‘ደመራ’ ደመረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ነው:: ትርጉሙ ጭመራ ማለት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው:: ጥሪት (ካፒታል) እንዳይጎድል እንዳይቀነስ ይልቁንም እየበዛና እያደገ እንዲቀጥል ጠብቆ መያዝ የሚያስችል ደመራ ነው:: ስሙ እንደሚያመለክተው ማስታወሻነቱ ለተጠራቀመ፥ ለተሰበሰበና ለተጨመረ ነገር ነው:: በዓሉ አካቶ የያዛቸዉ ሥርዓቱ የሚከናወንባቸው ቁሳቁሶች፥ የደመራው እንጨቶች፥ ችቦዎች፥ አሽክቶችና፥ ሌሎችም በበዓሉ ዙሪያ የሚታዩት፥ የሕዝቡን ስሜት አንድ ላይ ሰብስቦ ስለያዘ ደመራ ተባለ:: የደመራ ተቃራኒው ‘ቅነሳና ከፈላ’ ነው:: በአገራችን በተፈጠረው ታሪካዊ ክስተት ምክንያት፥ በነገረ መለኮት ከኛ ጋራ አንድ ከሆኑት አኀት አብያተ ክርስቲያናት በማይካፈሉት ሁኔታ በተለየና በደመቀ ሥርዓት በመላ ኢትዮጵያ ይከበራል:: ካህኑ የመጀመሪያዋን የደመራ መብራት “ደምረነ ምስለ እለ … [Read more...] about ደመራ
Opinions
የኔ ሃሳብ
ደመራ
ኢህአዴግ የሰራው ቤት! ግድግዳው ሰንበሌጥ!
እንደመግቢያ ፌደራሊዝም የመንግስት ኣወቃቀር ሰፊ የቆዳ ስፋትና ብዙ ህዝብ ላላቸው ኣገሮች፣ በዛ ያሉ የተለያየ ቋንቋና ባህል ያላቸው ቡድኖች ላላቸው ሃገሮች፣ ተመራጭ ኣስተዳደራዊ መዋቅር እንደሆነ እጅግ ብዙ ሰው በዓለም ላይ ይስማማል። ፌደራሊዝም የተመረጠበት ዋናው ምክንያት ስልጣን እና ፍትህ ከህዝቡ እንዳይርቅ ነው። እንዳይርቅ ስንል ከመልክዓ ምድርም ከወረፋም ኣንጻር ነው። ትላልቅ የሆኑ ኣገሮች ስልጣንን ቢያማክሉ ዜጎች ለኣንዳንድ ጉዳዮች ስልጣን ወደተጠራቀመበት ለመሄድ ስለሚርቃቸው ብዙ ከሆኑ ደግሞ ሰልፉ ስለሚበዛ ወረፋው መጉላላትን ስለሚፈጥር ነው። ዜጎች ስልጣን ወርዶ ከፍተኛ የሆኑ ጉዳዮቻቸውን ሳይቀር በክልሎቻቸው እንዲታይላቸው መደረጉ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ፍትህንና ኣገልግሎትን ለማደል በጣም ይረዳል። ስልጣን ተማክሎ የመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ባለስልጣናት እንደ ቧንቧ … [Read more...] about ኢህአዴግ የሰራው ቤት! ግድግዳው ሰንበሌጥ!
The ESFNA’s Executives Untrustworthy “Ticket Sales and Pass Gate Procedures”
To increase the ESFNA executives’ accountability for collected money and to protect the best interests of the federation, the paying public should insist receiving a ticket stub upon entering the ESFNA’s stadium, concert, etc. The purpose of this procedure is to prevent the ESFNA’s executives pocketing the federation’s money without any accountability. To clarify, during the 2014 tournament, the federation’s gate supervisors (ticket takers) retained the whole ticket collected from the … [Read more...] about The ESFNA’s Executives Untrustworthy “Ticket Sales and Pass Gate Procedures”
ሁለት ላሞች/የስርዓተ ማህበሮች ትርጓሜ
የየዘመኑን ስርዓተ ማህበር ምንነት ቅልጥጥ አድርጎ ለማሳየትና የማያሻማ ፍቺ ለመስጠት የየሀገሩ የቱርጁማን ጠበብት ያልቧጠጡት የሃሳብ ኮረኮንችና ያልዳሰሱት ሸካራ ብሂል የለም፡፡ በየዘመኑ ለተከሰቱ የማህበረሰብ አስተሳሰቦች ከተለያዩ ምሁራን የተለያየ ፍቺና ትርጓሜ ተሰጥቷል፡፡ ምሁራኑ በዘመናችን ከደረሱበት መተርጉም አንዱ በሁለት ላሞች ተምሳሌትነት የቀረበው ነው፡፡ የነጠረውን ፍጹማዊ መተርጉም እስኪያገኙ ድረስ የፈረንጅ ሊቃውንት ይህንን በሁለት ላሞች ላይ የተመሰረተ ተምሳሌታዊ መተርጉም ሰጥተዋልና ከግልዎ ግምገማ ጋር በማያያዝ ይህችን አጭር ሐተታ ያነጻጽሩት ዘንድ እነሆ ብለናል፡፡ 1. ሶሻሊዝም እርስዎ ሁለት ላሞች ይኖርዎታል እንበል፡፡ በሶሻሊዝም ስርዓተ-ህይወት እስካሉ ድረስ አንዲቷን ላም ለራስዎ መድበው ሌላይቱን ለጎረቤትዎ መዳረግ ግዴታዎ ነው፡፡ 2. … [Read more...] about ሁለት ላሞች/የስርዓተ ማህበሮች ትርጓሜ
የአይሲል (ISIL) እንቅስቃሴ ምንነትና አንደምታው (ከአንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ዕይታ)
የአይሲል (Islamic State of Iraq and the Levant - ISIL) እንቅስቃሴ ከሰማይ ዱብ ያለ አዲስ ክስተት አይደለም። አይሲል ( አንዳንዶቹ ISIS ይሉታል - Islamic State of Iraq and Syria ) በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው የፖለቲካ ውጥንቅጥ ሀቅ ውጤት ነው። ለአነሳሱ፣ ለዕድገቱና ለሂደቱ ብዙ ነባሪ ምክንያቶች አሉት። በርግጥ የአይሲልን እንቅስቃሴ ከሀይማኖትና ከዘይት ሀብት ለይቶ ማየት አይቻልም። በፍልጥዔማውያንና በእስራዔላውያን መካከል ያለው ማብቂያ የለሽ ያልተቋረጠ ጦርነት አንዱ ምክንያቱ ነው። በኋላ ቀር የአረብ ነገሥታትና በሥራቸው የሚሰቃየው ሕዝብ የኑሮና የሀብት ሥምሪት መራራቅ ሌላው ምክንያቱ ነው። በእስልምና አጥባቂዎችና ለዘብተኛ ተከታዮች መካከል ያለው የግንዛቤ ልዩነት ሌላው ምክንያቱ ነው። አሜሪካኖች የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ … [Read more...] about የአይሲል (ISIL) እንቅስቃሴ ምንነትና አንደምታው (ከአንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ዕይታ)
ቶክ ሾው (ትዕይንተ-ወግ) ከያኔያንና ጥበብ በሀገራችን
ይሄንን ጽሑፍ ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝ “ጆሲ ኢን ዘ ሀውስ” የተሰኘው በዮሴፍ ገብሬ እየተዘጋጀ ኢ.ቢ.ኤስ በሚባል የኬብል ቴሌቪዥን (የመስመር ምርዓየ-ኩነት) የሚቀርበው የጥዕይንተ ወግ ዝግጅት ነው፡፡ ወደዚህ ትዕንተ ወግ ጉዳይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ፡፡ በብዙኃን መገናኛዎች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች ውስጥ የትዕይንተ ወጎችን (Talk shows) ያህል የመወያያ፣ የመገናኛ፣ የመቀራረቢያ፣ የመደማመጫ፣ የመተዋወቂያ እንዲሁም አሳታፊ ዐቢይ መድረክ የለም፡፡ እነዚህ መድረኮች ጠቀሜታቸውና ሚናቸው ጎልቶ የመታየት ዕድል የሚያገኙት ግን ካለው ምቹ የአሥተዳደር ሥርዓት የተነሣ በምእራቡ ዓለም ሀገራት ነው፡፡ መቸም ከመወያየት የማይገኝ ጥቅም የማይፈታ ችግር የለምና እነዚህ ዝግጅቶች በእነዚህ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያበረከቱ የማይተካ ሚናቸውንም እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ ከጠቀሜታቸው ጥቂቶቹን … [Read more...] about ቶክ ሾው (ትዕይንተ-ወግ) ከያኔያንና ጥበብ በሀገራችን
ቅኔና አዘማሪ
መግቢያ ለአዘማሪ ሙያ ተስማሚ የግብር መግለጫ መሆን ያለበት የቱ ነው? አዘማሪ ወይስ አርቲስት? በሚል በአቶ ዓለም ነጻነት ሬድዮ የቀረበው ውይይት ለዚህች ጦማር መነሻ ሆኖኛል። ከቀደሙ አባቶች እንደሰማሁት አዘማሪ ብቻውን የቆመ አይደለም። ከብዙ ነገሮች ጋራ ከቅኔያችን፣ ከዜማችንና ከስሜታችን ጋራ የተያያዘ ነው። አዘማሪ የሚለውን ቃል ከነዚህ ነጥሎ ለማቅረብ መሞከር ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ። ስለዚህ አዘማሪ ወደሚለው ቃል ዘው ብለን ከመግባታችን በፊት የአዘማሪን ተልእኮ መዳሰስ ሊኖርብን ነው። አዘማሪ የሚለው ቃል የግብሩ (የተልእኮው) መግለጫ ነው። ተልእኮውም ራሱ አዘማሪ ተቀኝቶም ሆነ ገጥሞ ወይም ሌላ የተቀኘውን በዝማሬው ቅላጼ ከጉሮሮውና ከመሳሪያ ጋራ አስማምቶ፣ ቀምሞና አስወድዶ አስውቦ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ህዝቡንም ከባህሉ ከታሪኩ … [Read more...] about ቅኔና አዘማሪ
“ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ”
መግቢያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። መባል ስላለበት ነው። ያለፈውማ ዓመት አንደኛውን ጥቁር ዓመት ተብሏል። ሲያንሰው ነው። ወያኔ ከመቼው በበለጠ ጥቃቷን በኢትዮጵያ ልጆች ላይ በሁሉም አቅጣጫ ያጧጧፈችበት ዓመት ነበር። ነጻውን መገናኛ ብዙሀን ከጨዋታ ውጪ አድርጋለች። ብዙ ጋዜጠኞች በማሠሯ ወህኔ ቤቱ ጠቧል መሰለኝ፣ አሁን አሁን የያዘችው ዜዴ፣ በቁጥጥሯ ሥር ከሌሉ፣የፋሺን ጋዜጠኞችም ሳይቀሩ ማዘዣ ሳይደርሳቸው፣ በሬዲዮዋና በጋዜጦቿ “ከስሼአቸዋለሁ!” በማለት፣ ነጭ ሽብር እየነዛችባቸው በርግገው ከአገር እንዲጠፉ ማሳደዷን በሰፊው ተያይዛቸዋለች። በዓመቱ መጨረሻ ወር ብቻ 21 ጋዜጠኞች ተደናብረው አገር ጥለው እግሬ አውጪኝ ብለዋል። ሲሸሹም እያየች አታስቆማቸውም። ብቻ ሲወጡላት፣ “እስየው ተሰደዱልኝ!” ብላ “ደቁሴ ንሬ፣ ተባራብሬ!”ዋን ትደልቃልች! ወንድማችን እስክንድር ነጋ፣ … [Read more...] about “ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ”
The Ethiopian Diaspora and consciousness
The Bay Area that currently is home away from home for thousands of Ethiopians is nothing like any other place that I have known. I was born in a small village on the southern part of Ethiopia and have resided in Addis Abeba, Oregon and Seattle Washington before moving here. The Bay Area is unique. I thank the Gods and celebrate my luck whenever I have a chance. The place where I originated from is not known for such movement of people from one location to another. As much as I remember the … [Read more...] about The Ethiopian Diaspora and consciousness
ጄኔራል ታደሰ ብሩና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ
ይህንን ፎቶግራፍ ሰሞኑን በኢንተርኔት ላይ ሲንሸራሸር ነው ያገኘሁት፡፡ ፎቶውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው በ1967 በመጋቢት ወር አጋማሽ የታተመ አንድ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅጂ ነው፡፡ ያ ጋዜጣ በደርግ ዘመን በድብቅ በከተማችን ይዘዋወር እንደነበረ ትዝ ይለኛል፡፡ በደርግ ውድቀት ማግስት ደግሞ የገለምሶ ከተማ ቀደምት ፎቶ ቤት የሆነው “ፎቶ አብደላ” የጋዜጣውን ኮፒና ይህንን ፎቶግራፍ ለየብቻቸው በማባዛት በሰፊው ሲያሰራጭ ቆይቷል (ፎቶ ቤቱ አንዱን ምስል በሶስት ብር ነው የሚሸጠው)፡፡ ***** በፎቶግራፉ ላይ የሚታዩት የሜጫና ቱለማ ማህበር አንጋፋ አባላት የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ብሩ እና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ ናቸው፡፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሁለቱን ሰዎች ፎቶግራፍ ያተመው “ታደሰ ብሩና ግብረ አበሮቹ ተያዙ” የሚል ርዕስ ከሰጠው የዜና ዘገባ ጋር ይመስለኛል (ሙሉ ርዕሱን … [Read more...] about ጄኔራል ታደሰ ብሩና ኮሎኔል ሀይሉ ረጋሳ










