‘ደመራ’ ደመረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ነው:: ትርጉሙ ጭመራ ማለት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው:: ጥሪት (ካፒታል) እንዳይጎድል እንዳይቀነስ ይልቁንም እየበዛና እያደገ እንዲቀጥል ጠብቆ መያዝ የሚያስችል ደመራ ነው:: ስሙ እንደሚያመለክተው ማስታወሻነቱ ለተጠራቀመ፥ ለተሰበሰበና ለተጨመረ ነገር ነው:: በዓሉ አካቶ የያዛቸዉ ሥርዓቱ የሚከናወንባቸው ቁሳቁሶች፥ የደመራው እንጨቶች፥ ችቦዎች፥ አሽክቶችና፥ ሌሎችም በበዓሉ ዙሪያ የሚታዩት፥ የሕዝቡን ስሜት አንድ ላይ ሰብስቦ ስለያዘ ደመራ ተባለ:: የደመራ ተቃራኒው ‘ቅነሳና ከፈላ’ ነው::
በአገራችን በተፈጠረው ታሪካዊ ክስተት ምክንያት፥ በነገረ መለኮት ከኛ ጋራ አንድ ከሆኑት አኀት አብያተ ክርስቲያናት በማይካፈሉት ሁኔታ በተለየና በደመቀ ሥርዓት በመላ ኢትዮጵያ ይከበራል:: ካህኑ የመጀመሪያዋን የደመራ መብራት “ደምረነ ምስለ እለ ይድኅኑ” በሚለው በሊጦኑ ቃለ ቡራኬ ባርኮ፥ ከደመራው እንጨት ጋራ እንዲደምራት ሕዝቡን በአስተዳደር ለሚመራው ሰው ያቀብለውና የደመራውን እንጨት ይለኩሰዋል:: ከዚያ በኋላ በተዋረድ ያገር ሽማግሌ ሁሉ ችቦውን እያቀጣጠለ በደመራው ላይ ይጨምረዋል:: በዚህ ሥርዓት የሚከበረውን የደመራ በዓል በሃይማኖታችን፥ በታሪካችንና በባህላችን አንጸር በመጠኑ እገልጻለሁ:: ዛሬ ባለንበት ዘመን ይህችን እሳት ባርኮ ሰጭው መንፈሳዊው ካህን ማነው? እሳቷን ከካህኑ ተቀብሎ በደመራው ላይ የሚለኩሳትስ ብቃት ያለው የአገር መሪ ማነው? ከዚያስ በተዋረድ እየለኮሰ ደመራውን የሚያቃጥል ሽማግሌ ማነው? በማለት ከሊቃውንት አበው የተማርኩትንና የሰማሁትን
• በሃይማኖታችን፥
• በታሪካችንና በባሕላችን
አንጻር በመዳሰስ ይሕችን ጦማር እደመድማለሁ:: በመጀመሪያ በሃይማኖታችን አንጻር እነሆ! (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply