በዚያው ሰሞን ነው የወያኔ ባለሥልጣናት ሲያሾፉብን “ይሄንን ሁሉ ሰይጣናዊ ድርጊት የሚፈጽሙት በዓላማ እነሱ መሆናቸው ተረስቶ” ከመሀከላቸው አንዱ ምን አለ “የሕወሀት መሪዎች በዚህ ወቅት በብሔሮች መካከል ያለው የጥላቻ መንፈስና የወደፊት የሀገሪቱ ሁኔታ እጅግ አሳስቧቸዋል በጣምም እየተጨነቁበት ያሉበት ጉዳይ ነው የብሔራዊ እርቅ ጉዳይ አስፈላጊነቱ የግድ እንደሆነ ያስባሉ እንዴትና ከማን ጋራ እንደሚጨርሱት ተቸግረው ነው እንጅ….” ብሎ ቀለደብን፡፡ ከእኛም ወገን ደግሞ ጅሎቹ የዋሀኑ ተላሎቹ እውነት መስሏቸው በየፊናቸው አንዳንድ ነገሮችን እስከማለት ደረሱ፡፡ ወያኔ ግን ወያኔ ነውና ንጹሕ መስለው አሳሰበን ካሉ በኋላም እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም በዓላማ ይሄንን ሰይጣናዊ የዘርና የሃይማኖት ግጭት ፍጅት ለመፍጠር ሴራውንና ድርጉቱን እየፈጸመ ይገኛል ተፈጥሯዊ ባሕርይው ነውና እስካለ ጊዜ … [Read more...] about “አርማጌዶን” የፍጻሜያችን ፍጻሜ!
Opinions
የኔ ሃሳብ
የጅዳው ት/ቤታችን እንደ አረቡ አብዮት ከድጡ ወደ ማጡ!
የጅዳ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት በተወሳሰበ የአሰራር፣ አመራር ሂደት ውስጥ በማለፍም ቢሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ከጀመረ ሁለት ወር ደፍኗል። በሁለት ወራት ልጆቻችን ተምረው ተመለሱ ብሎ ለጠየቀ ምላሹ ቆሽት ያሳርራል። በእስካሁኑ የትምህርት ቅበላ ባለው ከስድስት ያላነሰ ክፍለ ጊዜ የሚማሩት ከሁለትና ሶስት ክፍለ ጊዜ ሲሆን አልፎ አልፎ አራት ክፍለ ጊዜ ብቻ ተምረው ይመለሳሉ። ይህን እውነታ ልጆቹን እንደማዋያ ጥሎ ዘወር የሚለው ባይተዋር ወላጅ ከልጆቹ ይሰማዋል። የልጆቹን ደብተር አገላብጦ የሚመለከት የእኔ ቢጤ ብስጩ አባት ደግሞ ከልጆቹ ከመስማት አልፎ በማስረጃ ደብተሩን ሲያገላብጥ የሚታዘበው እውነታ ነው። በአንዳንድ ክፍሎች ዘመናዊውን ትምህርት ትምህርት የሚያሰኙት የእንግሊዝኛና የሒሳብን ጨምሮ ከፍ ሲል የኬሚስትሪ፣ የፊዚክስ፣ የባዮሎጂና የኮምፒውተር ትምህርቶች … [Read more...] about የጅዳው ት/ቤታችን እንደ አረቡ አብዮት ከድጡ ወደ ማጡ!
The honorable Ato Gebru Asrat and his politics
The honorable Ato Gebru Asrat has written a very fat book that is five hundred pages long. I am assuming that the purpose of the book was to present himself as a person of vision and to show us his leadership ability and a map of the road to the future. Unfortunately, he has a handicap that cannot be glossed over since for many years he has operated as member of that infamous organization TPLF (ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) that is still creating havoc in the life of our people and our country. It is a … [Read more...] about The honorable Ato Gebru Asrat and his politics
ሥነ-ኪን ወይስ ኪነ-ጥበብ?
ብዙውን ጊዜ ሥነ-ኪን ወይም የጥበብ ሥራ፣ ነገረ-ጥበብ ማለት እንፈልግና ኪነ-ጥበብ የሚለውን ቃልና ሥነ-ጥበብ የሚለውን ቃል እያጣረስን ስንጠቀም እንስተዋላለን፡፡ ኪነ-ጥበብ ወይም ኪነ-ጥበባት የሚለው ቃል ራሱ ግራ የተጋባ ቃል ነው፡፡ ልንጠቀምበት ፈልገን በምንጠቀምበት ቦታ ሁሉ ሰዋስዉ የተሳሳተ (Grammatically wrong) በሆነ መንገድ ነው፡፡ ቃሉ የግዕዝ ቃል ቢሆንም እነኝህን ሁለት ቃላት ማጣመር ግን የሰዋስው ስሕተትን ይፈጥራል፡፡ ምክንያቱም ኪን የሚለው ቃል ትርጉም ራሱ ጥበብ ማለት ነውና፡፡ ስለዚህም ኪነ-ጥበባት ስንል ጥበበ ጥበባት ማለታችን ነው ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት የጥበቦች ጥበብ ወይም ከጥበቦች ሁሉ የበላይ ጥበብ የሚል ትርጉምን ይሰጣል እንጅ አጠቃላይ የጥበብ ሥራ ዘርፍ ማለት አይደለም፡፡ ንጉሠ ነገሥታት ማለት የነገሥታት ንጉሥ ማለት እንደ ሆነ ሁሉ ማለት … [Read more...] about ሥነ-ኪን ወይስ ኪነ-ጥበብ?
የእርቅና መግባባት ዳሰሳ ጥናት ውጤት
የሚከተለው ውጤት ድህረ ገፆች ላይ ከወጡት ፅሁፎቼ ሊንክ በማድረግ በዚህ ድህረ ገፅ ላይ የተሰበሰበ የዳሰሳ ጥናት ነው። ጥናቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ቢሆንም ለመንደርደሪያ ጥናትና አሳብ ሊረዳ ይችል ይሆናል ብዬ አስባለው። ይህ ማለት ስለ እርቅና መግባባት ውስብስብ ጥያቄ እልባት ለማግኘት አይደለም። ያ በእኔ አይሞከርም ከአቅሜ በላይ ነውና። ዓላማዬ ስለ እርቅ ቅድመ ሁኔታዎች መንደርደሪያ አሳብ ለመሰብሰብ በማሰብ ነው። እነሆ ድምፅ የሰጡትን ሰዎች አሳቦች አጠርና ጠቅለል አድርጌ ከዚህ በታች በጥሬው አቅርቤያለው። የራሴን ትንታኔ ትቸዋለሁ። ያንን ለአንባቢው እተዋለሁ። በዚህ ዳሰሳ ጥናት ላይ የተሳተፉትን ከልብ አመሰግናለው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ። ፍቅርም ይስጠን። Q1: Which generation are you? የትኛው ትውልድ ነዎት? 77.5% I am 30 years old or … [Read more...] about የእርቅና መግባባት ዳሰሳ ጥናት ውጤት
ለወገን ችግር ደራሹ ወገን ነው!
ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል የቱን ያህል የከበደ እንደሆነ የሚያውቀው የግፉ እና የመከራው ተሸካሚ የሆነው ዐማራው መሆኑኑን ማንም አይስተውም። ያም ሆኖ ግን፣ ሰብአዊነት የሚሰማው ማናቸውም ሰው፣ በሰዎች ላይ የሚፈጸምን ግፍ እና በደል በራሱ ላይ እንደተፈጸመ በመቁጠር፣ ድርጊቱን ለማስቆም የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል። ለተራቡት የርሃብ ማስታገሻ ያጎርሳል፤ ለታረዙት የእርቃን መሸፈኛ ከፈን ይለግሣል፤ ለተጠሙት የውኃ ጠብታ ያስጎነጫል፤ አልፎ ተርፎም ግፍ ፈጻሚዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል። በዓለም ዙሪያ በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በወገኖቹ ላይ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የሚፈጽመውን ግፍ ለዓለም ኅብረተሰብ ከማጋለጥ በተጨማሪ ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ ላጡ ወገኖቹ የሚችለውን ያህል እጁን ከመዘርጋት … [Read more...] about ለወገን ችግር ደራሹ ወገን ነው!
በግልጽ እንነጋገር
በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ የፖለቲካ ሁኔታ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም አንድ ስምምነት ላይ ነን። በአንድነት ያልተገኘንበት፤ ምን ይደረግ? በሚለው መፍትሔ መሥጠቱ ላይ ነው። መፍትሔ ደግሞ ከመቅረቡ በፊት፤ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አልፎ፤ በግንዛቤያችን ደረጃ ያለንበትን መመርመሩ ግዴታ ይሆናል። እንግዲህ የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ ይኼው የግንዛቤያችን ጉዳይ ነው። በትግሉ ዙሪያ፤ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ ግለሰቦች ሞልተናል። እያንዳንዳችን የምንፈልገውን እናውቃለን። የሚያስማማን ደግሞ እያንዳንዳችን ከምንፈልገው መካከል ያለው የጋራ ፍላጎታችን ነው። ይህ የየግል ፍላጎታችን በሀገር ደረጃ ሲቀመጥና የጋራ የሆኑት ከመካከሉ ተጎልጉለው ሲወጡ፤ ሀገራዊ መታገያ ዕሴቶቻችን ነጥረው ብቅ ይላሉ። በዚህ ጽሑፍ፤ የሀገራችን፣ የትግላችን፣ የምሁራን ሚናና … [Read more...] about በግልጽ እንነጋገር
Obang addresses Civil Society Policy Forum at the IMF and World Bank meeting
Address by Obang Metho, Executive Director of the SMNE, to the Civil Society Policy Forum at 2014 Annual Meetings of the International Monetary Fund (IMF) and the World Bank Group (WBG), Washington, DC Thank you for inviting me to share in this panel discussion on “The Role of World Bank Indicators in Agricultural Development.” Today’s discussion is very relevant in that the World Bank is investing billions of dollars into agribusiness. Various new tools have been designed to measure and … [Read more...] about Obang addresses Civil Society Policy Forum at the IMF and World Bank meeting
“መጪው ምርጫ ይቅርብን”
ጥላ መጽሔት 11ኛ ዕትም “መጪው ምርጫ ይቅርብን” በሚል ርዕስ እና ከዚህ በታች ያሉትን ጦማሮችና ሌሎችን አካትታ ወጥታለች፡፡ ከቢን ላደን ግድያ በስተጀርባ ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች በስደትም አንደኛ? የወያኔ ፍትሃዊ ምርጫ! መሬት ቆርሶ ... የአገር ስሜት ሳይኖረው ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ የመጽሔቷን የሽፋን ገጽ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about “መጪው ምርጫ ይቅርብን”
ዘዳግም!
የደመራ ዋና ዓላማ፤ “ሲቃወምና ሲጻረር የነበረውን የዕዳ ጽህፈት ክርስቶስ ከነ ሕግጋቱ በመደምሰስ በመሰቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው” (ቆላ ፪፡፲፬)። ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው፤ የተደበቀውን እውነት ለመግለጥ፤ በሰው ላይ ተጭኖ የነበረውን ዕዳ ለመደምሰስ፤ ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነቱን ነገሮች ለማስወገድ ነው። [በሰፊው መረዳት ከፈለጉ ይህን ሰንሰለት ይጫኑ። ደመራ] ሙሴ አራቱን የኦሪት መጻሕፍት ከጻፈ በኋላ፤ በአራቱም መጻሕት የገለጻቸውን ጠቅለል አድርጎ በድጋሚ ያቀረበበት አምስተኛው መጽሐፍ ዘዳግም ይባላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነውን ለማስወገድ የገለጸባቸውን ኃይለ ቃላት ለማስጨበት “አማን አማን እብለክሙ” እያለ በመደጋጋም ተናግሯል። በጸሎተ ቅዳሴያችንም “ተንስኡ ለጸሎት” የሚለውን እንደጋግማለን። ቃጭልም … [Read more...] about ዘዳግም!










