• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የእርቅና መግባባት ዳሰሳ ጥናት ውጤት

October 16, 2014 06:19 am by Editor 2 Comments

የሚከተለው ውጤት ድህረ ገፆች ላይ ከወጡት ፅሁፎቼ ሊንክ በማድረግ በዚህ ድህረ ገፅ ላይ የተሰበሰበ የዳሰሳ ጥናት ነው። ጥናቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ቢሆንም ለመንደርደሪያ ጥናትና አሳብ ሊረዳ ይችል ይሆናል ብዬ አስባለው። ይህ ማለት ስለ እርቅና መግባባት ውስብስብ ጥያቄ እልባት ለማግኘት አይደለም። ያ በእኔ አይሞከርም ከአቅሜ በላይ ነውና። ዓላማዬ ስለ እርቅ ቅድመ ሁኔታዎች መንደርደሪያ አሳብ ለመሰብሰብ በማሰብ ነው። እነሆ ድምፅ የሰጡትን ሰዎች አሳቦች አጠርና ጠቅለል አድርጌ ከዚህ በታች በጥሬው አቅርቤያለው። የራሴን ትንታኔ ትቸዋለሁ። ያንን ለአንባቢው እተዋለሁ። በዚህ ዳሰሳ ጥናት ላይ የተሳተፉትን ከልብ አመሰግናለው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ። ፍቅርም ይስጠን።

Q1: Which generation are you? የትኛው ትውልድ ነዎት?

77.5% I am 30 years old or above ሰላሳና ከሰላሳ አመት በላይ ነኝ

22.5% I am less than 30 years old ከሰላሳ አመት በታች ነኝ

Q2: Reconciliation is the only way out for Ethiopia? እርቅና መግባባት ብቸኛ መፍትኤ አድርገን መውሰድ ይገባናል?

86% Agree እስማማለሁ

14% Disagree አልስማማም

Please tell us if you have other ideas (ተጨማሪ አዲስ አሳብ ካለዎት ይንገሩን) (ዝርዝሩ ከታች ይቀጥላል)

Q3: Who should reach out for reconciliation first? ለእርቅና መግባባት ቀደምተኛውን በጎ ድርጊት ማን ይጀምር?

48.5% Government መንግስት

21.5% Ethiopian elders የአገር ሽማግሌዎች

21.25% Other Option ሌላ  (ዝርዝሩ ከታች ይቀጥላል)

8.75% Opposition ተቃዋሚ

Q4: Who has a solution for Ethiopia’s complex problems? ለኢትዮጵያ ውስብስብ ችግር ማን መፍትኤ ያመጣል?

69% Both reconciled ሁለቱም በእርቅ

17.75% Other Option ሌላ (ዝርዝሩ ከታች ይቀጥላል)

6.75% Government መንግስት

6.5% Opposition ተቃዋሚ

Q5: Ask God’s blessings on a national level (like USA)  በብሔራዊ ደረጃ የአምላክን በረከት እንጠይቅ (እንደ አሜሪካ)

83% Agree እስማማለሁ

17% Disagree አልስማማም

Total Complete Responses = 400 (ጠቅላላ የተሟላ ድምፅ)

Q2: Reconciliation is the only way out for Ethiopia? Please tell us if you have other ideas (እርቅና መግባባት ብቸኛ መፍትኤ አድርገን መውሰድ ይገባናል? ተጨማሪ አዲስ አሳብ ካለዎት ይንገሩን።

  • መንግስት ስህተቱን አምኖ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ
  • የኃይል ሚዛን እኩል እስኪሆን እርቅ አሁን አያስፈልግም
  • አንድ ላይ እንሁንና ያለፈውን ቂም እንርሳና በሰላም አብሮ በመኖር ኢትዮጵያን እናሳድግ
  • ማንና ማን ይታረቅ? የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይስ ዘርና ጎሳ? የትኛው ይቅደም?
  • ከእርቅ ውጭ ሰው ሰራሽ ከሆነው ውስብስብ ችግር የሚታደገን መፍትሔ የለም
  • የሰላሙ ትግል ባገር ውስጥም ሆነ በኢንተርናሽናል ይጨምርና በመንግስት ላይ ጫና ካላደረገ እርቅ አይሰራም
  • እርቅና መግባባት የተባረከና ለሕዝባችንና ለተወዳጁ አገራችን አንድ እመርታ ነው
  • ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡ ካሉ እንዴት ሊሆን ነው?
  • አመፅን የሚያራምዱ የእርቅ እንቅፋት እንዳይሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?
  • እርቁ ዘላቂ መፍትሔ እንዲኖረው ሰነድና አስፈፃሚ ህግ ሊኖረው አይገባምን?
  • እርቁ ስልጣን ለማግኘት መሆን የለበትም። ይልቁንስ ባረጀው ትውልድ መተማመንን ለመፍጠር ይሁን
  • በመጀመሪያ መከባበር አለብን
  • በቃላት ብቻ ሳይሆን በስራ እንዋደድ
  • ይህ መንግሥት እርቅና ሰላምን እሺ አይልም። እርቅ አይሰራም።
  • በኢትዮጵያ ጦርነትን ማየት አልፈልግም
  • እርቅ ማለት በሃይማኖት መቻቻል መፍጠርን ያጠቃልል።
  • የበደለ አምኖና ስህተቱን ተቀብሎ ይቅርታ መጠየቅ አለበት
  • ኢትዮጵያዊነትን እንደገና በአዲስ መልክ መተርጎም ያስፈልጋል።
  • እርቅ ማለት ያለፈውን ስህተት ማስተካከል ይጠይቃል።
  • ከኢህአዴግ ጋር ብቻ ሳይሆን ካለፉት መንግስታትም ጭምር እርቅ ያስፈልጋል
  • እርቅ ፍትሕን ይጋፋል፥ የበለጠም በዳዩን ይጠቅማል
  • እርቁ በሁለቱም በኩል ያለ ሃይል በፈቃደኝነት ተቀባይነትን ማግኘት አለበት
  • በእውነት ስለ እውነት መነሳሳት ይገባናል
  • መንግስት እልህኛ ከመሆን ቶሎ በጠረጴዛ ዙሪያ እንሰብሰብና አባይም ይገደብ
  • ኢትዮጵያን ከወደድን ህዝቡን እንውደድ፥ ደግሞም የምንጠላውንም ሰው እንውደድ
  • ልዩነታችን ብቻ ሳይሆን ጣልቃ የምናስገባውም ነገር መቅረት አለብን
  • ቅን ልቦና ከሌለ እርቅና መግባባት አይሰራም
  • ለእኛ አገር ከእርቅና መግባባት የሚቀድም ነገር የለም
  • የታሰሩት ሁሉ መጀመሪያ እንዲፈቱ ይሁን (ምህረትም ተደርጎ ቢሆንም)
  • ስልጣን የሕዝብ ብቻ መሆኑንና መንግስትም የሚወክለው ህዝብን ብቻ መሆኑን ሁሉም ይመን
  • ችግራችንን እኛው ራሳችን እንፍታ
  • በእሳት ላይ ጋዝ ሳይሆን ውሃ የሚጨምር ትውልድ ያስፈልገናል
  • ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እየተቻለ በብጥብጥና በጥላቻ ለመፍታት መሞከር ሞኝነት ነው
  • ሞተን ሁሉን ትተን ለምንሄደው መልካምን ስም ትተን እንለፍ
  • እርቅ እንዲሰምር በህብረተሰባችን ውስጥ ያለፈውን ፍትሕ አልባ ሁኔታ እንደገና ዛሬም ለመመለስ አይሞከር
  • እርቅ ብቸኛ ምርጫችን ነው
  • እርቅና መግባባት ከማንና ስለ ምን ጉዳይ ነው?
  • አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የትምህርትና የንቃተ ህሊና ደረጃ ለዚህ መልስ ለመስጠት አልደረሰም
  • ላለመስማማትም እየተስማማን የሁላችንም የሆነችው ኢትዮጵያ ናት
  • በጎ አሳብ ቢሆንም የሚሆን አይመስልም። ግን እፀልያለው እንዲሆን።
  • አማራው ለሁሉ ነገር ኢህአዴግን መውቀስ ትቶ ያለፉት አማራ ገዥዎች ያደረጉትን ይመርምሩ
  • ከድህነት መውጣት ብቸኛው መፍትሔ ነው
  • እርቅና መግባባት ብቸኛውና ድንቁ መንገድ ነው
  • ኢህአዴግ እሺ አይልም። ይህ ከህልም ያለፈ አይደለም
  • ያለፈው ታሪካችን ጥሩም ሆነ ክፉ እንማርበት እንጂ ለመጣላት ምክንያት አይሁንብን
  • ከእርቅ በፊት መረጃ ፕሮፓጋንዳን ይተካ፥ አገሪቱ እውነትን በመክዳት ላይ ነች ያለችው
  • አገዛዙንም ሆነ ታጣቂዎችን ተቀምጠው እንዲደራደሩ የሚያስገድድ ሃይል ያስፈልጋል
  • እርቅ ማለት ምን ማለት ነው? ጥፋተኛን ወደ ፍርድ ማምጣት አይጠቀልልም?
  • እርቅ ላለፉት 150 በላይ አመታት አማራና ትግሬ ያደረገውን ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ይጀምር
  • ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በአዲስ ትውልድ ከሁሉም ለሁሉም አሳታፊ የሆነ ቢሆን ከቂመኝነት ይፀዳል
  • እርቅን በመጀመሪያ ከራስ ጋር ይጀምር። ያኔ ሁሉም ይቀላል።
  • እርቅ የትግሉን መስክ እንዳያዘናጋ እንጠንቀቅ
  • ለነፃነት እንዋጋ
  • ጥላቻን እስወግደን፥ መሃከለኛው መንገድ መፍትሔ ነው
  • አንድነትን ካልፈጠርንና ልዩነታችንን ካላቻቻልን፥ ኢትዮጵያ ለሚቀጥለው ትውልድ አትተላለፍም
  • እርቅ መልካም ነው ግን ምን ይቅር እንደሚባል መጀመሪያ መስማማት አለብን።
  • እርቅ ይሁን ግን ሕግን የተላለፉት ተጠያቂ ይሆኑ ዘንድ ይገባል። ወደ ፍርድ መምጣት አለባቸው።
  • ዝም ብለን ከተቀመጥንና ለችግራችን መፍትሔ ካልፈለግን ኢትዮጵያ ወደ እርስ በርስ ጦርነትና ብጥብጥ ታመራለች
  • እርቅን በፍፁም አንፈልግም።
  • በመጀመሪያ የዘር ጉዳይ ይታይ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው።
  • መንግስት ያደረገው መልካም ነገር ምስጋና ይሰጠው።
  • እርቅ በተቃዋሚዎች መካከል ያስፈልጋል
  • ዲሞክራሲያዊ መዋቅሮች፥ የህግ የበላይነት፥ ነፃና ፍታዊ ምርጫና ነፃ ፕሬስ ሰላም ያመጣል።
  • በእርቅና መግባባት የሚያምኑ ሁሉ የጋራ መድረክ ፈጥረው አሳቡን ያዳብሩ
  • የበላይነት ወይም የበታችነት ስሜት ይቅር
  • የዘር ክፍፍልና ጥላቻን ለመፈወስ የሚያስፈልገው እርቅና መግባባት ነው
  • እርቅ ብቸኛ ምርጫ ሊሆን አይገባም።

Q3: Who should reach out for reconciliation first? (OTHER responses) (ለእርቅና መግባባት ቀደምተኛውን በጎ ድርጊት ማን ይጀምር? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••

  • ይህ መንግስት ከወረደ በኋላ እንደ ደቡብ አፍሪካ ይሁን
  • ዜጎቹን ለማሰባሰብና ለሃገሪቱ ሰላም ለማምጣት ሃይልና ሃላፊነት ያለው መንግስት ነውና መንግስት ይሁን
  • እያንዳንዳንዱ ሰው
  • ሽማግሌም ባይሆን ግን በህዝቡ ተሃማኒ የሆነ ቅንና ገለልተኛ በእውነትም ኢትዮጵያን የሚወድ ሰው ይሁን
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ
  • ተቃዋሚው በአንድነት ተደራጅቶና የተቀናጀ ፕሮፖዛል ለህዝብ ያቅርብና ብሔራዊ ቀን ይጥራ
  • መንግስት ተቃዋሚ አለኝ ካለ የሚቃወሙት ምንድነው? ብሎ መጋበዝ አለበት
  • የተዘረዘሩት ምርጫዎች ሁሉ ያካተተ ይሁን
  • አንድ ሰው (ማን ይሁን ኢትዮጵያዊ ማንዴላ)
  • ሁለቱም ስምምነቱን ገለልተኛ ሶስተኛ  አካል ባለበት ይፈራረሙ
  • እርቅ አያስፈልግም። ዲሞክራሲ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስምምነት ይኑረን ብቻ
  • የኢትዮጵያ አባወራ መንግስት ነውና የመጀመሪያውን የእርቅ በር መንግስት እንደ አባት ይክፈትና ይጀምር
  • መንግስትና ተቃዋሚ በአንድነት ይጀምሩ
  • እርቅና መግባባት የሚጠቅማቸው ሁሉ እኩል ሃላፊነቱን ይውሰዱ
  • መንፈሳዊ መሪዎች፥ ግን ተጠሪነታቸው ለአምላክና ለህዝቡ ብቻ የሆነ
  • ከሁሉም ጎሳዎች በዲሞክራሲ አመራረጥ የተመረጡ ሽማግሌዎች (ሁሉንም ብሔር የሚወክሉ)
  • የመንግስት ቁርጠኝነት ለእርቀ ሰላሙ መሳካት ጉልህ ሚና አለው
  • ማንም ቢጀምር መንግስት በቀና ልብ ካላየው ፍሬያማ አይሆንም
  • መንግስት ተቃዋሚና ሽማግሌዎች አብረው
  • ሁሉም ሃላፊነት አለው፥ ግን መንግስት ይስማማ በአሳቡ የሚያስከፍለውን ዋጋ ከፍሎ
  • የሚቀጥለው ምርጫ ፍታዊ ክሆነ በኋላ
  • ከህፃናት በስተቀር በህይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሲተባብር ብቻ ነው የሚሳካው
  • ከራስ ይጀምራል
  • ከመንግስት ይልቅ እርስ በርሱ የተጣላው ተቃዋሚው ክፍል ነው
  • መንግስት በእርቅ ላይ የሌለውን ጊዜ አያባክን
  • ከውጭ አገር ከምንኮርጅ፥ በራሳችን ባህል እርቅን እናውርድ፥ ሽማግሌዎች ይምሩን
  • ስልጣን ቢሞት የማይለቅ መንግስትና ራዕይ የሌለው ደካማ ተቃዋሚ ስላለን መፍትሔ የለም
  • ምሁራን፥ የሃይማኖት መሪዎች፥ ተፎካካሪና የመንግስት ተወካዮች፥ በፖለቲካ ያልተሳተፉ ሁሉ በጋራ
  • ሽማግሌዎችና አባቶች ይጀምሩ
  • አማራ ያለፉትን ጨካኝ አማራ መሪዎችን መደገፍ ያቁሙ
  • ነፃ የሆነ ከመንግስት፥ ተቃዋሚና ሽማግሌዎች የተውጣጣ ካዉንስል
  • ኢትዮጵያውያን የሆኑ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች፥ ሃይማኖታዊ መሪዎችና ሲቪል ተቋማት
  • መንግስት መጀመሪያ ይቅርታ ይጠይቅ
  • ከታች የሕዝብ ንቅናቄ
  • በመካከል ሆነው መንግስትንና ተቃዋሚን የሚደግፉ
  • ከመንግስት በስተቀር ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሊጀምሩ ይችላሉ
  • የድሮ ፓርቲዎች እርስ በርሳቸው ሰላም ይፍጠሩና ከፖለቲካ ራሳቸውን ያግልሉና አዲሱ ትውልድ ይረከብ
  • ሶስተኛ ነፃ አካል (ከአሜሪካና ከእንግሊዝ ውጭ) በዚህ ላይ ይሳተፉ
  • የተከበሩ ሽማግሌዎች ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የተውጣጡ
  • መጀመሪያ እርቅ በተቃዋሚዎች መካከል ይሁን
  • ሁሉም ሃይማኖቶችና የዘርና ጎሳ ክፍሎች
  • ተቃዋሚዎች ይጀምሩ (ምሁራንና ግለስቦችን ይጨምርና)
  • ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ማንኛውም ተቋምና ድርጅት መጀመር ይችላል

Q4: Who has a solution for Ethiopia’s complex problems? (Other Option) (ለኢትዮጵያ ውስብስብ ችግር ማን መፍትሔ ያመጣል? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••

  • ህብረተሰቡ
  • ሰላም መፍጠርና ነፃ ምርጫ መፍትሔ ያመጣል። መጀመሪያ የአገሪቱ ሰራዊት የህዝብ መሆን አለበት።
  • የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ፥ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አለበት
  • እግዚኦ እንበል
  • የውጭ ረጅ ድርጅቶች በነገሩ ላይ ይሳተፉ
  • ወጣቱና ሴቶችን ያሰባሰበ መግባባት በቤተሰብ ደረጃ ሲጀምር፥ ከዚያም በጎረቤት እያለ ለውጥ ይመጣል
  • ነፃ የህዝብ ተወካዮች፥ መንግስትና ተቃዋሚዎች
  • ሁሉም መንግስት ተቃዋሚና እያንዳንዱ ዜጋ
  • ሁሉም ዜጋ (በፖለቲካ የሚሳተፉ ብቻ አይደሉም)
  • መንግስት ብዙ የተከፋፈለ ተቃዋሚ ይፈልጋል፥ ይህ ችግር ነው።
  • አንድ ወጥ አገር ሳይሆን ልዩነታችንን እንከባከበው
  • ምሁራን በመጀመሪያ እርስ በርስ ለስልጣን ከመጣላት እንደ ጋና ምሁራን ጥሩ ሚና ይጫወቱ
  • ሁሉም ስልጣንን ብቻ ዓላማ አድርጎ መንቀሳቀስ ሲያቆም
  • ሁሉም ያለው በመንግስት እጅ ነው
  • ከመቶ በላይ የሆኑትን ፓርቲዎች ወደ ሁለት በመቀየር (ብሔራዊና ጎሳዊ)
  • በጎ ህሊና ያለው በሙሉ፥ ሁሌም ፈጣሪ ያግዘናል
  • ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ነው መፍትሔው (ታይዋን፣ሲንጋፖር፣ ሆንክ ኮንግን ተመልከቱ)
  • ሴቶች፥ ወጣቶች በማናቸውም ፖለቲካን ዘር ጎሳ ጥቅማጥቅም ያልተለከፉትን ማፈላለግና ማሰባሰብ
  • የጥላቻ ፖለቲካ መፍትሔ አያመጣም ብለው የሚያምኑ ሁሉ
  • ከየጎሳው የተውጣጡና ኢትዮጵያን የሚወክሉ ሁሉ
  • ዋናው መንግስት ሲሆን ባነሰ መልኩ ተቃዋሚ
  • እግዚአብሔር
  • ህዝቡ ነው እንጂ መንግስትና ተቃዋሚ አይደለም
  • መንግስት እሺ አይልምና የገበሬው አብዮት
  • ተቃዋሚና ሕዝቡ
  • በመንግስትና ተቃዋሚ እርቅ ቢፈጠርም የኢትዮጵያን ስር የሰደደ ችግር አይፈታም
  • ሁሉም በእርቅ የሚወልዱት አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ
  • እርቅ ይቻላል ብለው የሚያምኑት ሁሉ
  • የድሮ የግፍ ኢትዮጵያ ለማምጣት የሚታገሉና የአሁኗ የጎሳ ኢትዮጵያን የሚያቀነቅኑ መሃከል ያለው ሽኩቻ ሲፈታ
  • ሃይማኖት አለመንካት
  • ነፃነትና ዲሞክራሲ
  • የተደባለቀ ጎሳ የተወለዱ

——–

ዶ/ር ዘላለምን ለማግኘት በዚህ አድራሻ ይፃፉ፦ Z@myEthiopia.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    October 20, 2014 09:33 am at 9:33 am

    <<የተከበሩ ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር በጥናታቸው ትኩረት ሊሰጡአቸውና እንደገና የህዝብ ድምፅ ሊያሰጡባቸው የሚገባ ሀሳቦች፡(የግል ሀሳቤ)
    *፩*እርቅና መግባባት ብቸኛ መፍትኤ አድርገን መውሰድ ይገባናል? ተጨማሪ አዲስ አሳብ
    ———————————————————————
    *ማንና ማን ይታረቅ? የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይስ ዘርና ጎሳ? የትኛው ይቅደም?
    *ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡ ካሉ እንዴት ሊሆን ነው?
    *እርቁ ዘላቂ መፍትሔ እንዲኖረው ሰነድና አስፈፃሚ ህግ ሊኖረው አይገባምን?
    *እርቅና መግባባት ከማንና ስለ ምን ጉዳይ ነው?
    *ያለፈው ታሪካችን ጥሩም ሆነ ክፉ እንማርበት እንጂ ለመጣላት ምክንያት አይሁንብን!
    *ከእርቅ በፊት መረጃ ፕሮፓጋንዳን ይተካ፥ አገሪቱ እውነትን በመክዳት ላይ ነች ያለችው!
    *እርቅ ማለት ምን ማለት ነው? ጥፋተኛን ወደ ፍርድ ማምጣት አይጠቀልልም?
    *እርቅ ላለፉት 150 በላይ አመታት አማራና ትግሬ ያደረገውን ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ይጀምር
    *አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የትምህርትና የንቃተ ህሊና ደረጃ ለዚህ መልስ ለመስጠት አልደረሰም!?
    *ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በአዲስ ትውልድ ከሁሉም ለሁሉም አሳታፊ የሆነ ቢሆን ከቂመኝነት ይፀዳል!
    *እርቅ መልካም ነው ግን ምን ይቅር እንደሚባል መጀመሪያ መስማማት አለብን።!
    *እርቅ ይሁን ግን ሕግን የተላለፉት ተጠያቂ ይሆኑ ዘንድ ይገባል። ወደ ፍርድ መምጣት አለባቸው።!?
    *በመጀመሪያ የዘር ጉዳይ ይታይ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው።
    *ዲሞክራሲያዊ መዋቅሮች፥ የህግ የበላይነት፥ ነፃና ፍታዊ ምርጫና ነፃ ፕሬስ ሰላም ያመጣል።!?

    <፪<ለእርቅና መግባባት ቀደምተኛውን በጎ ድርጊት ማን ይጀምር? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••
    —————————————————————–
    *ሽማግሌም ባይሆን ግን በህዝቡ ተሃማኒ የሆነ ቅንና ገለልተኛ በእውነትም ኢትዮጵያን የሚወድ ሰው ይሁን!
    *ከሁሉም ጎሳዎች በዲሞክራሲ አመራረጥ የተመረጡ ሽማግሌዎች (ሁሉንም ብሔር የሚወክሉ)
    *ከህፃናት በስተቀር በህይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሲተባበር ብቻ ነው የሚሳካው!
    *ስልጣን ቢሞት የማይለቅ መንግስትና ራዕይ የሌለው ደካማ ተቃዋሚ ስላለን መፍትሔ የለም!
    *ምሁራን፥ የሃይማኖት መሪዎች፥ ተፎካካሪና የመንግስት ተወካዮች፥ በፖለቲካ ያልተሳተፉ ሁሉ በጋራ!
    *በመካከል ሆነው መንግስትንና ተቃዋሚን የሚደግፉ!?
    *ኢትዮጵያውያን የሆኑ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች፥ ሃይማኖታዊ መሪዎችና ሲቪል ተቋማት
    *ሶስተኛ ነፃ አካል (ከአሜሪካና ከእንግሊዝ ውጭ) በዚህ ላይ ይሳተፉ!?

    <፫>ይህን የተቀደሰ ዓላማ ላሰቡ፣ ለመከሩ፣ ለተሳተፉና የአቅማቸውን የዜግነት ድርሻ ድምፅ በመስጠትም፣አዲስ ሐሳብ በማፍለቅም፣ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡ መልካም ፍቃደኝነት፣እኔስ ማነኝ? ከማን ሀገር አንሼ! ዘለዓላም ብጥብጥ፣ ድንቁርና፣ ኋላቀርነት ለምን አስከመቼ ?ቤታችንን አፍርሰን ብለን በቁጭት ከተነሳን የሕዝብና የሀገር ተቆርቋሪነት እስካለ ድረስ የሀሳብ ፍጭት እንዳለ ሆኖ አካላዊ መጎዳዳትን አስወግዶ ማናቸውም መልካም ነገር በእግዝሐብሔር ቸርናትና ቡራኬ ከተጀመረ ይፈፀማል።!ሠላም ለሁላችንም ይሁን በቸር ይግጠመን>>>>

    Reply
  2. በለው ! says

    October 20, 2014 09:41 am at 9:41 am

    >>>>ከይቅርታ ጋር ቁጥር ፫ ተቆርጦ ቀርቶ ነበር!?

    <፫<ለኢትዮጵያ ውስብስብ ችግር ማን መፍትሔ ያመጣል? ሌላ አሳብ የተሰጠ •••
    ——————————————————–
    *ሰላም መፍጠርና ነፃ ምርጫ መፍትሔ ያመጣል። መጀመሪያ የአገሪቱ ሰራዊት የህዝብ መሆን አለበት።
    *አንድ ወጥ አገር ሳይሆን ልዩነታችንን እንከባከበው!?
    *ምሁራን በመጀመሪያ እርስ በርስ ለስልጣን ከመጣላት እንደ ጋና ምሁራን ጥሩ ሚና ይጫወቱ!
    *ከመቶ በላይ የሆኑትን ፓርቲዎች ወደ ሁለት በመቀየር (ብሔራዊና ጎሳዊ)
    *ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ነው መፍትሔው (ታይዋን፣ሲንጋፖር፣ ሆንክ ኮንግን ተመልከቱ)!
    *ሴቶች፥ ወጣቶች በማናቸውም ፖለቲካ፣ ዘር፣ ጎሳ፣ ጥቅማጥቅም ያልተለከፉትን ማፈላለግና ማሰባሰብ!
    *የጥላቻ ፖለቲካ መፍትሔ አያመጣም ብለው የሚያምኑ ሁሉ?
    *የድሮ የግፍ ኢትዮጵያ ለማምጣት የሚታገሉና የአሁኗ የጎሳ ኢትዮጵያን የሚያቀነቅኑ መሃከል ያለው ሽኩቻ ሲፈታ!?
    *ከተደባለቀ ጎሳ የተወለዱ!?
    _________________________________________ከምስጋና ጋር!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule