• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአባይ ግድብ ዲፕሎማሲ አጀንዳ!

June 21, 2013 07:17 am by Editor Leave a Comment

በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ አባይ ግድብ አወዛጋቢ የሆኑ ጉዳዮች ተፈጻሚነት የሚያገኙት አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ትግል በማድረግ አለም አቀፍ ደጋፊ ማብዛት ሲቻል ነው። የዲፕሎማሲ ትግል ደግሞ ሰላማዊ ትግል ትግል በመሆኑ ብስለት እንጂ ክፉ ቃል አይሻም። ቀረርቶ ደጋፊን አስበርግጎ እንደሚያርቅ እና ለባላንጣ የማጥቂያ ቀዳዳ እንደሚከፍት ግልጽ ነው። የሆነው ሆኖ ይኽን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ የህውሃት ውጭ ጉዳይ ቴዎድሮስ እና አቻው የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰኔ 11 ግድም ዲፕሎማሲያዊ ውይይት አደረጉ ከተባለ በኋላ ቴዎድሮስ “አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” ማለቱን ካነበብኩ በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር ውይይት መክፈት ያስፈልጋል የሚል እምነት ስላደረብኝ ነው።

“አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” የሚለው የቴዎድሮስ አባባል “ግብጽ እና ኢትዮጵያ ላይፋቱ ተጋብተዋል” ከሚለው የአምባገነን መሰል አባባል ብዙም የራቀ አይደለም። ሁለቱም ህውሃታዊ አነጋገሮች ናቸው። ስሜት በመቀስቀስ ኢትዮጵያውያንን ለማስከተል እና ስልጣን ለማጠናከር። የቀድሞው የህውሃት ውጭ ጉዳይ ስዩም መስፍን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ምን ሲል እንደነበር፣ በመጨረሻ ግን ጦርነቱ እና የባድመ ጉዳይ እንዴት እንዳከተመ እናስታውሳለን። ቴዎድሮስም ከስዩም መስፍን የተለየ አደለም። ትናንት ኤርትራን አስገነጠሉ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም አብረው ነበሩ። ዛሬም አብረው ናቸው። የሆነው ሆኖ የዲፕሎማሲ ትግል ‘አብረን እንዋኛለን ወይንም እንሰምጣለን” ከሚለው  አባባል ባሻገር እጅግ ሰፋ ያለ ነው። የዲፕሎማሲ ትግል ህግ፣ ፍትህ፣ ታሪክ፣ ሳይንስ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ሰበዓዊ እና ግብረገባዊ አድማሶች ያሉት የትንታኔ፣ የክርክር፣ የማግባባት፣ የማሳመን ትግል ነው። በተጨማሪ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ከልብ መደረግም አለበት።

ከ1938 እስከ 1945 ዓ.ም.  በነበረው በዚያ በጨለማ ዘመን እንኳን እነ ሎሬንዞ እና አክሊሉ ኃብተ ወልድ ከአለም አቀፍ ህግ አማካሪያቸው ከስፔንሰር ጋር ሆነው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመቀላቀል ባደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ትግል የእነ ካናዳን፣ ህንድን፣ ኖርዌይን፣ ግሪክን እና ሌሎች በርካታ አገሮችን ድጋፍ ሊያገኙ የቻሉት ዲፕሎማሲያዊ ትግላቸው በሳል በመሆኑ ነበር። ከልባቸው ያደረጉትም ትግል ስለነበር ነው። በቅድሚያ በምርምር እና በጥናት የተመሰረተ በሳል የዲፕሎማሲ ትግል አጀንዳዎች በመቅረጻቸው ነበር። ዛሬ ጊዜውም እንደያኔ ጨለማ አይደለም። የኃያላን መንግስታት አስተሳሰብ ከቅኝ ገዥነት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተለወጧል። ዛሬ አፍሪካውያን በተባበሩት መንግስታት ከ50 በላይ መቀመጫ አላቸው። ያኔ እነ ሎሬንዞ እና አክሊሉ ኃብተ ወልድ በተባበሩት መንግስታት መድረክ ለኢትዮጵያ ከልባቸው ሲታገሉ መቀመጫ የነበራቸው እና የድጋፍ ድምጽ የሚሰጡዋቸው ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ብቻ ነበሩ። ለፍትህ የሚደረግ የዲፕሎማሲ ትግል ከዚያ ከጨለማ ዘመን ይልቅ ዛሬ የማሸነፍ እድሉ ከፍተኛ ነው። ሆኖም ግን በሳል የዲፕሎማሲ ትግል አጀንዳዎች መቀመር እና ከልብ መታገል ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያ የምታካሂደው የዲፕሎማሲ ትግል ከግብጽ ሳይንትስቶች፣ መሃንዲሶች፣ የህግ አዋቂዎች እና የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር ውይይት መክፈት ቢችል እና በአለም አቀፍ መድረክ ደግሞ የአፍሪካ ህብረትን፣ የተባበሩት መንግስታትን፣ የአሜሪካን፣ የአውሮፓን፣ የአለም ባንክን፣ የአይ.ኤም.ኤፍን ድጋፍ ማግኘት ቢችል ግንባታው ቀላል ይሆናል። ስለዚህ የዲፕሎማሲ ትግሉ ጥናት ላይ የተመሰረቱ አጀንዳዎች ሊኖሩት ይገባል።  የቀድሞ አባቶቻችንን ድሎች እየጠቀሱ እኛም እንደግመዋለን አይነት አኪያሄድ አይጠቅምም። የሚከተሉት የዲፕሎማሲ አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ አባይ ግድብ ግንባታ ዲፕሎማሲ ትግል ሊያገለግሉ ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ፥

አጀንዳ አንድ (1)፥ ግድቡ በሸለቋማ ቦታ ላይ በመገንባቱ በትነት የሚባክነውን ውሃ ዝቅተኛ ያደርጋል።

አጀንዳ ሁለት (2) በግድቡ የሚሰበሰበው ውሃ ቁልቁል ሲለቀቅ መዘውሮችን (Turbines) በመምታት ያመቀውን ኃይል (Energy) ወደ መዘውሮቹ ካስተላለፈ (እንዲሽከረከሩ በማድረግ) በኋላ የሚስፈነጠረው ውሃ ወደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሱዳን ስለሚፈስ ወደ ግብጽ የሚሄደው የአባይ ውሃ አይቀንስም።

አጀንዳ ሶስት (3)፥ ግድቡን ለመሙላት የሚያስፈልገው ውሃ በግብጽ ላይ ስጋት መፍጠር የለበትም። በበጋም ሆነ በክረምት ወደ ግብጽ የሚፈሰው የአባይ ውሃ ግብጽን አልፎ ሜድትራኒያን ባህር ስለሚገባ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን እና የግብጽ ሳይንትስቶች እና መሃንዲሶች ከአለም እክስፐርቶች ጋር ሆነው ምን ያህል ውሃ ግድቡ ውስጥ እንዲቀር ማድረግ እንደሚቻል ማስላት ይችላሉ። ግድቡን ለመሙላት ከበጋ ይልቅ በክረምት ከፍ ያለ የውሃ ማስቀረት እንደሚቻል ግልጽ ነው።

አጀንዳ አራት (4)፥ ከአባይ ወንዝ ውሃ በተጨማሪ ከሱዳን የኤሌክትሪክ መስመሮች ጋር በመተሳሰር ግብጽ የምታገኘው ተጨማሪ ጠቀሜታ እንዳለም የግብጽ እና የአለም ህዝብ እንዲያውቅ ዲፕሎማሲያዊ ቅስቀሳ መደረግ አለበት። ለምሳሌ ግብጽ እና ጆርዳን የኤሊክትሪክ መስመራቸውን አስተሳስረዋል። የኤሌክትሪክ መስመሮቻቸውን ለማስተሳሰር በየብስ ከግብጽ ወደ ጆርዳን በመማዎች ማጓጓዝ ስላልቻሉ ከፍተኛ ወጪ አውጥተው መስመሩን በቀይ ባህር ወለል ስር ቀብረው የሁለቱን አገሮች የኤሌክትሪክ መስመሮች አስተሳስረው የኤሊክትሪክ ኃይል ይነጋገዳሉ። በቅርቡ ደግሞ ግብጽ ከሳውዲ ጋር ለማስተሳሰር ስምምነት ጨርሳለች። ግብጽ ለጆርዳን ከምተሸጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ የተወሰነው የኤሊክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ የሚፈሰው አባይ አስዋን ግድብ ላይ ከሚፈጥረው 2 ሺ አንድ መቶ ሜጋ ዋት መሆኑን አንባቢ ልብ ይበል።

አጀንዳ አምስት (5) ፥ የ 09 JUNE 2013 ሪፖርተር ጋዜጣ ከቀድሞ ዲፕሎማት አምባሳደር ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገችው  ቆይታ የውሃ አጠቃቀምን አለም አቀፍ ህግ አስመልክታ ላቀረበችላቸው ጥያቄ አምባሳደሩ መልስ “በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ በ101 የድምፅ ድጋፍ፣ በሦስት ተቃውሞና በ27 ድምፀ ተአቅቦ ያለፈው የውኃ ኮንቬንሽን የኢትዮጵያን አቋም የሚደግፍ ነው፡፡” ይህን ሁሉ የግብጽ ህዝብ እንዲያውቅ ይደረግ።

አጀንዳ ስድስት (6)፥ ግብጽ ከመቶ አመቶች በኋላ የህዝቤ ብዛት 3 መቶ ሚሊዮን ወይንም ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል ከሚል የተደበቀ ስሌት አባይ ይለቀቅልኝ ማለት እንደማትችል ግልጽ መሆን አለበት።

አጀንዳ ሰባት (7)፥ የቅኝ አገዛዝ ዘመንን ውል ኢትዮጵያ እንደማትቀበል በጠዋት ግልጽ መደረግ አለበት። የአባይ ውሃ ባለቤትነት እና የመጠቀም መብታችንን ለድርድር እንደማናቃረብ ህግን፣ ታሪክን፣ ፖለቲካን፣ ኢኮኖሚን እና ግብረገብነትን መሰረት ያደረጉ ትንታኔዎች ማቅረብ።

አጀንዳ ስምንት (8)፥ ግብጽ የሚገባው ነጭ አባይ 85% ያህሉን ውሃ የሚያገኘው ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን ከሚፈሱት ጥቁር አባይ (70%)፣ ተከዜ (5%) እና ባሮ (10%) ወንዞች ነው። እነዚህ ሶስት አውራ ወንዞች የሚፈጠሩት በኢትዮጵያ ከተለያዩ ቦታዎች ከሚነሱ በርካታ ገባር ወንዞች ነው። ግብጽ በጸበኛነት የምትቀጥል ከሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ከየአካባቢው የሚነሱትን ትናንሽ ገባር ወንዞች አቅጣጫ ይቀይራል። ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚፈሰው ውሃ መጠን እጅግ ዝቅ ይላል። ግብጽ በወታደራዊ ኃይል የባሮ ወንዝ ከሚገኝበት ደቡብ ምዕራብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ምዕራብ ድረስ ሁልጊዜ መዋጋት አትችልም። ይኽን ሃቅ ግብጾች፣ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ የአለም ባንክ፣ አይ.ኤም.ኤፍ. ሁሉ እንዲገነዘቡት እና የግብጽ ጸበኛነት የማያዋጣ መሆኑ ወለል ብሎ እንዲታያቸው ማድረግ።

አጀንዳ ዘጠኝ (9)፥ ግብጽ ጦርነት ከመረጠችም ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ የሚደርስባት ኪሳራ ብዙ ነው። ጦርነት ለማኪያሄድ የምታወጣው እና በጦርነት ጀማሪነት እንዲሁም ለደረሰችው ጉዳት የተባበሩት መንግስታት ይቀጣታል።

አጀንዳ አስር (10)፥ ኢትዮጵያ እራስዋን የመከላከል መብቷ የተከበረ መሆኑንም የዲፕሎማሲው ትግል ጨምሮ ይገልጻ።

እነኚህ አስር (10) አጀንዳዎች ቢተነተኑ ትልቅ ሰነድ እንደሚወጣቸው ግልጽ ነው። እነዚኽን አሳቦች ካለቀረርቶ ለግብጻውያንም ሆነ ለአለም ህዝብ ወዝ እና ቁርጣኛነት በግልጽ በሚታይበት አነጋገር በማቅረብ ቢያንስ የግብጽን የተወሰነውን የዴሞክራሲ ኃይል ድጋፍ ማግኘት እና አለም አቀፍ ደጋፊዎችን ብዛት ማሳደግ እንደሚቻልም ግልጽ ነው።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ዲፕሎማሲያዊ ትግላቸውን እንዴት ማኪያሄድ ይችላሉ? በብዙ መንገዶች ማኪያሄድ ይችላሉ። በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የሚዘጋጁ የበሰሉ የምርምር ጽሑፎችን እና የዲፕሎማሲ ትግሉን ሂደት ደረጃዎች እየተከታተሉ እነ አንድነት ፓርቲ፣ ሰማያዊዎች እና ሌሎች የዴሞክራሲ ኃይሎች የሚያወጧቸውን መግለጫዎች በየድረገጹ በማቅረብ። ድረገጾቹ ለግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች፣ ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ ዲፕሎማቶች እና የቀድሞው የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ለነበረው ለነ መሐመድ አልባራዳይ አይነቱ የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች ተደራሽነት ቢኖራቸው ጥሩ ነው። የቀድሞው የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበረውን መሐመድ አልባራዳይ እና ሌሎች ግብጻውያንን በመጋበዝ ህዝብ ለህዝብ የሚሉ ጉባኤዎች በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አዘጋጅቶ መነጋገርም ይቻላል። ተደጋጋሚ ቢሆን ጥሩ ነው። በአለም ውስጥ የተሰራጩት ኢምባሲዎች ይኽን አይነቱን ዲፕሎማሲያዊ ቅስቀሳ ቀደም ብለው ማድረግ ነበረባቸው። ችግሩ ህውሃት (ቴዎድሮስ አድሃኖም እና ገብረ ክርስቶስ ) ያላዘዛዋቸውን አያደርጉም።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች በአባይ እና በአገራቸው ጉዳይ የዲፕሎማሲ ትግሉ ባለቤት መሆን አለባቸው። አንድ ነገር በግልጽ መታወቅ አለበት። የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ኃይሎች በራሳቸው አነሳሽነት መራመድ ካልጀመሩ ህውሃት የዲፕሎማሲ ትግል አጋር እንዲሆኑም ሆነ ወደፊት በሚደረጉ ምርጫዎች በነፃ ተፎካክረው ስልጣን እንዲጋሩት ወይንም አሸንፈውት አገር እንዲያስተዳድሩ ፍጹም አይፈልግም። የዴሞክራሲ ኃይሎች ከዳር ቆሞ ተመልካችነትን ከመረጡ የኢትዮጵያ ህዝብም በአባይ ጉዳይ ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ያለኝ ጠበቃ እና ጠባቂ ህውሃት ብቻ ነው የሚል አደገኛ እምነት ሊፈጠር ይችላል። የህውሃትም ፍላጎት የኢትዮጵያ ህዝብ በህውሃት ላይ እንዲያመልክ ማድረግ ነው። ስለዚኽ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች የአባይም ሆነ የኢትዮጵያ ባለቤትነታቸውን እና ሌሎች የሚጠበቁባቸውን ህዝብ የመምራት ግዴታዎች ለመወጣት ህውሃት የዘጋባቸውን በር እስኪከፍትላቸው መጠበቅ የለባቸውም። የመግለጫ ጋጋታም ህውሃት የዘጋውን በር አይከፍትልህም። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሰራዊት ህውሃት የዘጋውን በር እራስህ ከፍተህ በአገርህ ጉዳይ በአቻነት መሳተፍ መጀመር አለብህ! በህዝብህም ዘንድ ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ መታወቅን እና ክብርን የሚያስገኝልህ ብሎም ፕሮግራምህን ተፈጻሚ ማድረግ የምትችለው እንደነዚህ አይነት ስራዎች ስትሰራ ብቻ ነው!

(girmamoges1@gmail.com)

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የኒዳል ሀሰን በርሸና የሞት ፍርድ ሲፈጸምበት በቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ October 9, 2026 12:33 pm
  • ሴቶችን በመሾም ኢትዮጵያ በእርግጥ ተወዳዳሪ የሌላት ነች?  October 8, 2026 11:20 pm
  • Ethiopian Defense Forces Capture Advanced TPLF Military Drones and Documents Linked to Sudan October 7, 2026 12:40 pm
  • በሱዳን በኩል ለትህነግ የተላኩ የM6 ድሮኖችና ወታደራዊ መሣሪያዎች በመከላከያ እጅ መግባታቸው ተገለጸ October 7, 2026 11:20 am
  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
Copyright © 2026 · Goolgule