በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አራተኛ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ዌንዲ ሸርማን ሰኔ 23፤ 2007 ዓም ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ከተሰማ ጥቂት ሳምንታት የተቆጠሩ ቢሆንም ተመልሰው በከፍተኛ ባለሥልጣንነት ሊመጡ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ሸርማን በወቅቱ ከቴድሮስ አድሃኖም ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ያሰሙት ንግግር ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶባቸው ነበር፡፡
ባለሥልጣኗ ፈጽሞ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለኢህአዴግ በካድሬ ደረጃ ሙገሳ ቸረው ነበር፡፡ ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያ ያለውን ህዳሴ ካወደሱ በኋላ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተመረጠ አስተዳደር ሥር እንዳለች ተናግረው ነበር፡፡ በመቀጠልም ይህንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን በኃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱ በሙሉ ሊጠነቀቁ እንደሚገባቸው አሳሰቡ፡፡ ሲቀጥሉም ግንቦት ሰባትን በስም በመጥራት ሌሎችንም የኃይል እርምጃ በመውሰድ ለውጥ ለማምጣት ለሚፈልጉት ኃይላት ሁሉ “አሸባሪዎች” ናችሁ የሚል መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ከዚህ የዌንዲ ሸርማን ንግግር በኋላ በተለይ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡ ካቀረቧቸው ጥያቄዎችም መካከል ባለሥልጣኗ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ ከሥልጣን እንዲነሱ፣ ወዘተ የሚሉት ጥቂቶቹ ነበሩ፡፡
ለሳምንታት የዘለቀው ተቃውሞ ጋብ እንዳለ ባለፈው ሰሞን ዌንዲ ሸርማን አሁ ካሉበት ሥልጣን ሰኔ 23 (ጁን 30) እንደሚለቁ ደብዳቤ አስገብተው መጽደቁን ይፋ አደረጉ፡፡ አለቃቸው ጆን ኬሪና ፕሬዚዳንት ኦባማ የሸርማንን ታላቅነትና የአገልግሎት ዘመን በማወደስ ታላቅ ሙገሳን ቸሯቸው፡፡
ዜናው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተቀናጀ ትግል ውጤት እንደሆነ ተደርጎ ሲወሰድ ተሰምቷል፡፡ በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ላይ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ተጽዕኖ እንዳለ ሆኖ የዌንዲ ሸርማን አሁን ከሥልጣን መልቀቅ ምናልባት ራሳቸውን ለከፍተኛ ሥልጣን ለማዘጋጀት ነው የሚሉም አሉ፡፡
በቢል ክሊንተን የአስተዳደር ዘመን በውጭ ጉዳይ መ/ቤት ሥራቸውን የጀመሩት ሸርማን፤ የሒላሪ ክሊንተን የቅርብ ወዳጅ ናቸው፡፡ ሸርማን አሁን ላሉበት ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ በ2011ዓም ብቁ ያደረጓቸው በወቅቱ የውጭ ጉዳይ መ/ቤቱን የመሩት ሒላሪ ክሊንተን ነበሩ፡፡ ወ/ሮ ክሊንተን በመጪው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሁሉም በብቃት ላይ የሚገኙ ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል፡፡ የማሸነፋቸውም ዕድል ከፍተኛ እንደሆነ በብዙዎች እየተጠቆመ ነው፡፡
ዌንዲ ሸርማን ባሁኑ ወቅት ከሥልጣን የለቀቁበት ተደርጎ የተወሰደው ቀዳሚው ምክንያት የኑክሌር መሣሪያዎችን በተመለከተ ከኢራን ጋር ይካሄድ የነበረው ድርድር ወደ መጨረሻው በመድረሱና ሴኔቱ ረቂቅ ሕጉን በማጽደቁ እንደሆነ በስፋት ተነግሯል፡፡ ሆኖም ግን የርሳቸው ቦታ ለኑክሌር ድርድር ተብሎ ብቻ የተቀመጠ የሥልጣን እርከን እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡
ከክሊንተን ቤተሰብ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው የሚነገረውና በኒውዮርክ ከታዋቂ ይሁዲ ቤተሰብ የሚወለዱት ሸርማን ሒላሪ ክሊንተንን በምርጫ ዘመቻቸው ላይ የውጭ ጉዳይን በተመለከተ በማማከርና በመሥራት ሊያገለግሉ ይችላሉ ከሚለው አስተያየት አኳያ ምናልባት ከሥልጣን መልቀቃቸው ታስቦ የተደረገ ነው የሚሉም አሉ፡፡ ይህ ከሆነ እና ሒላሪ ክሊንተን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን አሸንፈው ነጩ ቤተመንግሥት የገቡ ዕለት ለከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ወይም በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደርነት የሚሾሙት ዌንዲ ሸርማንን ሊሆን ይችላል፡፡
አሁን ከሥልጣን ሲለቁ ወደ መንግሥታዊ የሥልጣን እርከን የማይመለሱ የመሰለው የዌንዲ ሸርማን ጉዳይ ቀን ጠብቆ የተቃዋሚውን ኃይል ይበልጥ ሊጎዳ የሚችል እንደሆነ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የጠቆሙ ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው አሁን ከኢህአዴግ ጋር ካላቸው ይህንን የመሰለ ቁርኝት አኳያ ወደፊት ከፍ ያለ ሥልጣን ይዘው ብቅ ካሉ በተቃዋሚው ኃይል እንቅስቃሴ ላይ የሚያመጡት ተጽዕኖ እጅግ የከፋና የከረረ ሊሆን ይችላል፡፡
“ብሄድም እመለሳለሁ” የሚመስለው የዌንዲ ሸርማን የሥልጣን መልቀቅ ጉዳይ ከአሜሪካ የፖለቲካ አዘዋወር ጋር ወደፊት በሂደት የሚታይ ቢሆንም የተቃዋሚው ኃይል በተለይ በውጭ ያለው አስቀድሞ ሊሰራው የሚገባው የቤት ሥራ እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
melak says
Let she come again. We will wait her under a strong Ethiopia, or if delayed somehow, on the road towards a strong Ethiopia. America is committing another historical blunder in Ethiopia and East Africa. But I don’t think USA is ignorant of the current political, economic, and social situation unfolding in the country very fast today. What matters is only unity among Ethiopians for a shared goal-overthrowing woyane to begin with.
Ethiopia will rise again!!! Green, Yellow, and Red
Terminator says
As in Ethiopian I will not vote for Mrs, Clinton because of the vote she while she was a senator for Ethiopian HR 2003 .not only that it her husband who put the infuriate complex ridden Tygerias in power for 24 years not only that he took 20 million dollars from Al modie in the name of charity.
Jonathan Takele says
Shalom Ethiopians in USA:- I recommand the system like the Jewish and Isralis did, Ethiopians in USA almost 2.5 millions according to some datasn out of this data almos 1 milion they have USA citizenship and have full right to do vote for both parties so the answer on your hand just the next general election do your homework don’t give up your voice both of the parties start the campaign soon.