• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምርጫው ተአማኒና ሰላማዊ ነበር – የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ

June 23, 2021 12:32 pm by Editor 1 Comment

ኢትዮጵያ ያካሄደችው ምርጫ ተአማኒና ሰላማዊ ነበር ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ተናገሩ።

ታዛቢ ቡድኑ ከምርጫ ቅስቀሳው አንስቶ እስከ ምርጫው እለት ያለውን ሂደት መከታተሉን የጠቀሱት የታዛቢ ቡድኑ መሪ የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በቀር የቅስቀሳ ሂደቱ በፓርቲዎች ዘንድ ፍትሃዊነቱ የተጠበቀ ነበር ብለዋል።

የተመረጡ ጣቢያዎች ላይ ምልከታ አድርገናል ያሉት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ምርጫውን ተዘዋውረን በተመለከትንበት፣ የምርጫ ቦርድን ተቋማዊ ጥንካሬ ተመልክተናል፣ መንግስት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን አስፈላጊ የጸጥታ እርምጃ ተግባራዊ አድርጓል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ያደረገው ጥረትም የሚመሰገን መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ምርጫው ከሞላ ጎደል ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው የተካሄደው ያሉም ሲሆን አንዳንድ ቦታዎች ላይ በተለይም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ከጸጥታ ጋር ተያይዞ ስጋቶች እና በአንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎችን የማዋከብ እና የማንገላታት ችግሮች እንደነበሩ ገልጸዋል።

በምርጫው እለት የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ መንግስት እና የጸጥታ አካላት ስራቸውን በአግባቡ መስራታቸውንም ነው የቁሳቁስ እጥረትና የመራጮች ብዛት በድምጽ አሰጣጡና በቆጠራው ሂደት ላይ ጫናን ፈጥሯል ያሉት ኦባሳንጆ የተናገሩት።

የሲቪክ ማህበረሰብ አካላት በምርጫው የሚያደርጉትን ተሳትፎ መቀጠልና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተቋማትን፣ በተለይም ለምርጫ ቢርድ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናከሮ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የሚያደርገው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

የምርጫ ውጤቱ በሚመለከተው አካል ይፋ እስኪሆን ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትእግስት ሊጠባበቁ ይገባልም ነው ኦባሳንጆ ያሉት።

ቡድኑ በ5 ክልሎች እና 2 ከተሞች ታዛቢ ልኮ ምርጫውን መታዘቡን አስታውቋል፡፡

ድምጽ ሰጪዎች በምርጫው ደስተኛ መሆናቸውንና የፈለጉትን በነጻነት መምረጣታቸውን ነግረውኛል ያለም ሲሆን የመራጮቹ ትዕግስት አስገራሚ ነበርም ብሏል።

ምርጫውን በ4 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች በ190 የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝቶ መታዘቡን የገለጸው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫው የተረጋጋና ሰላማዊ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡

ቡድኑ የትዝብቱን የተጠቃለለ ሪፖርት ከ2 ወራት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ (አዲስ ሚዲያ ኔትወርክና አል-ዐይን)

Filed Under: News, Right Column Tagged With: election 2013, election 2021

Reader Interactions

Comments

  1. Qomchei Ambaw says

    June 26, 2021 04:09 am at 4:09 am

    You say:
    “ቡድኑ በ5 ክልሎች እና 2 ከተሞች ታዛቢ ልኮ ምርጫውን መታዘቡን አስታውቋል፡፡

    . . . . .

    ምርጫውን በ4 ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች በ190 የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝቶ መታዘቡን የገለጸው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫው የተረጋጋና ሰላማዊ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው”
    So is 4 or 5 Kilils? And how about the election report from the groupf of the eu and 13 other countries? That is too uncomfortable? Or it doesn’t fit with your comical and biased reporting gigsaw?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule