“ሊሆን የማይችል ነገር ነው” ባለፈው ማክሰኞ የተከናወነው የአሜሪካ የፕሬዚዳንት ምርጫ ተጠናቅቆ ባራክ ኦባማ ማሸነፋቸው ግልጽ በሆነበት ጊዜ የሚት ሮምኒ የምርጫ ዘመቻ ኃላፊዎች በተወሰኑ ግዛቶች የድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ መፈለጋቸው ተገለጸ፡፡ በተለይ በኦሃዮ፣ ፍሎሪዳና ቨርጂኒያ ግዛቶች የተደረገውን የድምጽ ቆጠራ ለማስደገም አራት አውሮፕላኖች የሪፓብሊካን ፓርቲ ሰዎች ለመላክ በወሰኑበት ጊዜ ሚት ሮምኒ “ሊሆን የማይችል ነገር ነው” በማለት ጉዳዩ እንዲቆም ከልክለዋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መሠረት ኦባማ ሦስቱንም ግዛቶች በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸው ይፋ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል ሮምኒ ምርጫውን ያሸንፋሉ በሚል እሳቤ ተዘጋጅቶ የነበረ የእጩ ፕሬዚዳንት ድረገጽ ለተወሰኑ ጊዜያት ተለቅቆ እንደነበር ሮል ኮል የተሰኘ የፖለቲካ ድረገጽ አስታውቆዋል፡፡ ይኸው … [Read more...] about ድህረ ምርጫ አሜሪካ