• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ድህረ ምርጫ አሜሪካ

November 13, 2012 12:49 am by Editor Leave a Comment

“ሊሆን የማይችል ነገር ነው”

ባለፈው ማክሰኞ የተከናወነው የአሜሪካ የፕሬዚዳንት ምርጫ ተጠናቅቆ ባራክ ኦባማ ማሸነፋቸው ግልጽ በሆነበት ጊዜ የሚት ሮምኒ የምርጫ ዘመቻ ኃላፊዎች በተወሰኑ ግዛቶች የድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ መፈለጋቸው ተገለጸ፡፡

የመጨረሻው ራት (የኦቾሎኒ ቂቤና ማር)

በተለይ በኦሃዮ፣ ፍሎሪዳና ቨርጂኒያ ግዛቶች የተደረገውን የድምጽ ቆጠራ ለማስደገም አራት አውሮፕላኖች የሪፓብሊካን ፓርቲ ሰዎች ለመላክ በወሰኑበት ጊዜ ሚት ሮምኒ “ሊሆን የማይችል ነገር ነው” በማለት ጉዳዩ እንዲቆም ከልክለዋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በተሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ መሠረት ኦባማ ሦስቱንም ግዛቶች በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸው ይፋ ሆኗል፡፡

በሌላ በኩል ሮምኒ ምርጫውን ያሸንፋሉ በሚል እሳቤ ተዘጋጅቶ የነበረ የእጩ ፕሬዚዳንት ድረገጽ ለተወሰኑ ጊዜያት ተለቅቆ እንደነበር ሮል ኮል የተሰኘ የፖለቲካ ድረገጽ አስታውቆዋል፡፡ ይኸው ሮምኒን እጩ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ የሚያሳይ ፎቶና ፊርማቸውን በማድረግ የተዘጋጀው ድረገጽ ፕሬዚዳንቱ አሜሪካውያንን ወደሥራ ለመመለስ ጥረት እንደሚያደርጉ የሚገልጽ ጥቅስና ለጃኑዋሪ በዓለሲመታቸውና ከዚያም ጋር ተያይዞ ስለሚከተለው ሽግግር እየሠሩ እንደሆነ የሚያሳይ በፎቶ የተደገፈ መረጃ ያሳያል፡፡ ሆኖም ከጥቂት ጊዜያት ቆይታ በኋላ ድረገጹ የተነሳ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡

           

በምርጫ የተሸነፉት ሚት ሮምኒ ወደፊት ጊዜያቸውን በምን እንደሚያሳልፉ ባይታወቅም እርሳቸው በምርጫ ዘመቻ ወቅት ይህ የመጨረሻቸው የፖለቲካ ዘመቻ እንደሚሆን ገልጸው ነበር፡፡ ወዳጅና አማካሪዎቻቸው እንደሚሉት ከሆነ ወደፊት መጽሐፍ እንደሚጽፉ የገለጹ ሲሆን በሞርሞን ቤ/ክ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱና ለዘመናት ያካበቱትን ልምድ በመከተል ወደ ፋይናንስና ኢንቨስትመንት ሥራቸው እንደሚመለሱ ይገምታል፡፡

 2016?

በተጠናቀቀው ምርጫ ከፍተኛ ሽንፈት የገጠመው የሪፓብሊካን ፓርቲ ከአራት ዓመት በኋላ ፓርቲውን ወክሎ ለምርጫ በሚቀርበው እጩ ላይ አጀንዳ ይዟል፡፡ ምርጫው በተጠናቀቀ ማግስት በተሰራጨው ዜና በቀደምትነት ከሚጠቀሱት መካከል “የሪፓብሊካኑ ኦባማ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው የፍሎሪዳው ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ፣ ቤተሰባቸው ከሕንድ የሆኑት የሉዊዚያናው ገዢ ቦቢ ጂንዳል፣ የሚት ሮምኒ ምክትል ፖል ራያን፣ የኒው ጀርዚው ገዢ ክሪስ ክሪስቲ፣ የጆርጅ ደብሊው ቡሽ ወንድም ጄብ ቡሽ፣ ስፓንኛ አቀላጥፈው የሚናገሩትና እናታቸው የሚክሲኮ ተወላጅ የሆኑት የጄብ ቡሽ ልጅ ጆርጅ ፒ. ቡሽ፣ … ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በተለይ በአሁኑ ምርጫ እጅግ ዝቅተኛ የሂስፓኒክ ድምጽ ሚት ሮምኒ ማግኘታቸው ከተሰማ ወዲህ የበርካታዎች ዓይን ከኩባ ቤተሰብ የሚወለዱት ሴናተር ሩቢዮ ላይ ሆኗል፡፡ የ41ዓመቱና የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑት ሩቢዮ በምርጫ ወቅት ከፍተኛ ክርክር ከምታስነሳውና ወሳኝ ድምጽ ሰጪ ግዛት ከሆነችው ፍሎሪዳ መሆናቸው ሌላው ተጠቃሽ ጉዳይ ነው፡፡

“ፓርቲው መጀመሪያ ራሱን እንደገና ማዋቀርና ከደረሰበት ሽንፈት ማገገም አለበት፤ የሪፓብሊካን ኦባማ ፍለጋ መሄድ የሚያዋጣ ሳይሆን አቋራጭ የመፈለግ የተሳሳተ መንገድ ነው” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ቢኖሩም እጩ ተወዳዳሪ ካሁን የመፈለጉ ጉዳይ በቀዳሚነት የተያዘ አጀንዳ እንደሆነ የፓርቲው ስትራቴጂስቶች እየጠቆሙ ይገኛሉ፡፡

የኦባማ ካቢኔ ሽግሽግ

ባራክ ኦባማ ድጋሚ መመረጣቸውን ተከትሎ ካቢኔያቸውን እንደገና እንደሚያዋቅሩ ፖለቲኮ ድረገጽ ዘግቧል፡፡ በዚህም መሠረት ከቀዳሚ ለቃቂዎች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሒላሪ ክሊንተን አንዷ ናቸው፡፡ በ2016 ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት ክሊንተንን ለመተካት ከተሰለፉት መካከል የአቶ መለስ የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ሱዛን ራይስ እንዲሁም የሴኔቱ የውጭ ጉዳይ ሰብሳቢ ሴናተር ጆን ኬሪ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የኮርፖሬሽኖች ወዳጅ ናቸው ተብለው ብዙ የሚነገርባቸው የገንዘብ ሚኒስትሩ ቲሞቲ ጋይትነር ከሒላሪ ክሊንተንም በፊት ይለቅቃሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ከሚተኳቸው መካከል ከፍተኛውን ሥፍራ ይዘው የሚገኙት በአሁኑ ወቅት የቤተመንግሥቱ እልፍኝ አስከልካይ የሆኑት ጃክ ሊው ናቸው፡፡ ጃክ የካቢኔውን ቦታ ከያዙ የእርሳቸውን ቦታ ደግሞ የቤተመንግሥቱን አስተዳደር ከሕዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት ጋር በማገናኘት ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ የሚባሉት የቀድሞው የሴኔት አብላጫ መሪ የነበሩት ቶም ዳሸል ይተኳቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የመከላከያው ሚኒስትር ሊዮን ፔኔታ ጊዜው ትንሽ ቢዘገይም የመልቀቃቸው ጉዳይ በስፋት የሚነገር ቢሆንም ተተኪያቸው ማን እንደሚሆን የሚሰጡት መላምቶች ሰፋ ያሉ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን እስከ ቅርብ ጊዜ የመከላከያ ፖሊሲ ረዳት ጸሐፊ የነበሩት ሚሼል ፍሎርኒይ ግምባር ቀደሟ ናቸው፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከሚቀርቡላቸው እጩ መካከል ፍሎርኒይን ከመረጡ የመጀመሪያዋን ሴት የአሜሪካንን የመከላከያ ሠራዊት እንዲያዝዙ በማድረግ ታሪክ ሰሪ መሪ ይሆናሉ፡፡

“የቀበሮ ባህታዊ”

የዊኪሊከስ (ሹልክዓምድ) መሥራች የሆኑት ጁሊያን አሳንዥ የባራክ ኦባማ እንደገና መመረጥ ምንም የሚያስፈነጥዝ አይደለም በማለት በጥገኝነት ተጠልለው ከሚገኙበት በለንደን የኤኳዶር ኤምባሲ ገለጹ፡፡ የ41 ዓመቱን አውስትራሊያዊ በገፍ ያወጡትን በተለይ የአሜሪካንን ምስጢር በመቃወም የኦባማ አስተዳደር የአደን ዘመቻ ያካሄደባቸው አሳንዥ ስለ ፕሬዚዳንቱ ሲናገሩ “ኦባማ መልካም ሰው ሊመስሉ ይችላሉ፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ችግሩም ይኸው ነው” ብለዋል፡፡

ለሪፓብሊካን ፓርቲም ቢሆን የሰላ ትችት የሰጡት ጁሊያን አሳንዥ “ፓርቲው ባለፉት አራት ዓመታት መንግሥት በሚያካሂደው መስፋፋት ላይ ተገቢ ማዕቀብ ማድረግ አልቻለም” ብለዋል፡፡ “የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ (የቀበሮ ባህታዊ) ከመሆን ይልቅ በቀበሮ ልብስ የሚደበቅ በግ መሆን” የተሻለ ነው በማለት የኦባማን ዳግም መመረጥ የተቹት አሳንዥ “በዊኪሊክስ (ሹልክዓምድ) ላይ የደረሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሙሉ የተካሄደው በኦባማ አስተዳደር ነው” በማለት ፕሬዚዳንቱ የለውጥ አራማጅ ተብለው ሊታመኑ እንደማይችሉ አስታውቀዋል፡፡ በስዊድን አስገድዶ መድፈር ክስ የተመሠረተባቸው አሳንዥ ክሱ በሙሉ የሃሰት መሆኑን የሚናገሩ ሲሆን ወደ ስዊድን እንዲሄዱ ይህ ክስ የተመሠረተባቸው ባጋለጡት ከፍተኛ ምስጢር ምክንያት ወደ አሜሪካ ተላልፈው በመሰጠት እዚያ የሞት ፍርድ እንዲፈረድባቸው ለማድረግ ነው ይላሉ፡፡ የጤናቸው ሁኔታ ያሳሰባት ኤኳዶር ከእንግሊዝ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር መጠየቋም ታውቋል፡፡

መንታዎቹ ኦባማና ሮምኒ

ይኸው ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀው የአሜሪካ ምርጫ በተካሄደበት ቀን መንትያ ልጆች የተገላገለችው ወጣት ልጆቿን ኦባማና ሮምኒ በማለት የሰየመቻቸው መሆኑን የኬንያው ስታንዳርድ ሚዲያ ዘግቧል፡፡ በፕሬዚዳንት ኦባማ አባት የትውልድ ቦታ አካባቢ በሚገኝ ሆስፒታል ልጆቹን የወለደችው የ20 ዓመቷ ሚሊሴንት ኦዉኦር ቀኑን ለማስታወስ ስትል ልጆቿን ባራክ ኦባማና ሚት ሮምኒ በማለት እንደሰየመችቻው ተናግራለች፡፡

በግራ ኦባማ በቀኝ ሮምኒ ከእናታቸው ጋር

በሌላ በኩል ደግሞ የብሉምበርግ ቢዝነስ ኒውስ ሚት ሮምኒ በምርጫውም ቢሸነፉም ያገኙት ታላቅ ድል እንዳለ ማስረጃ በመጥቀስ ዘግቧል፡፡ በኮምፒውተር በታገዘ ቴክኖሎጂ ከ4ዓመታት በኋላ ሁለቱም መራጮች ምን ሊመስሉ ይችላሉ የሚለውን ከዚህ በታች በስዕሉ እንደተመለከተው ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ በዚህም መሠረት ሚት ሮምኒ ፕሬዚዳንት ባይሆኑም የቀረባቸው ነገር ቢኖር የፊት መጨማደድና የሽበት መጨመር ስለሆነ ብዙም ሊያዝኑ አይገባም በማለት ዘግቧል፡፡

ዘገባውን ለማጠናቀር በየጽሁፉ ከጠቀስናቸው ምንጮች በተጨማሪ ሌሎችንም የሚዲያ ውጤቶች መጠቀማችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ከዜናዎቹ ማነስ አኳያ በየጸሁፉ ለመግለጽ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: cabinet, election, obama, Right Column - Primary Sidebar, romney

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule