• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በኢትዮጵያ ዝሆኖችም “ተሸብረዋል”

March 20, 2015 11:19 pm by Editor 1 Comment

ኢህአዴግ በሥልጣን በቆየባቸው 25 ያህል ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ መቶ ዝሆኖች ውስጥ ከዘጠና በላይ የሚሆኑት ሞተዋል፣ ወደ ጎረቤት አገር ተሰድደዋል፣ የደረሱበት አይታወቅም፣ . . . ሲሉ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ዛሬ (አርብ) ዘግበዋል፡፡

የዝሆኖችን ግድያ ለማስቆም በሚል የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡

ኢህአዴግ ከቻይና ጋር ከተፋቀረበት ጊዜ ጀምሮ የዝሆን ቀንድ ንግድ እየተጧጧፈ እንደሄደ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በዚህም “ጮማ” ንግድ ውስጥ ቢጂንግን፣ ሲንጋፖርን፣ ታይላንድን፣ … መመላለሻቸው ያደረጉ ቱባ ባለሥልጣናትና ደላሎቻቸው ይጠረጠራሉ፡፡ የቡድሃ ሃይማኖት እጅግ በተስፋፋባቸው በሩቅ ምስራቅ አገራት የዝሆን ጥርስ እጅግ ተፈላጊ ሲሆን ዋንኞቹ አስተላላፊዎች ደግሞ የዘመኑ የቻይና ቱጃሮች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ  የዝሆን ጥርስ ለሩዝ መብያ ስንጥር (chopsticks)፣ ለተለያዩ ዓይነት ጌጣጌጥ፣ ለቤት ውስጥ ዕቃ፣ ወዘተ ተፈላጊነት አለው፡፡

ivory 2ቻይና በዝሆን ጥርስ ገቢ ንግድ ላይ የአንድ ዓመት ማዕቀብ ጥያለው ብትልም በአፍሪካ ያሰማራቻቸው ባለሃብቶቿ ከየአገሩ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ንግዱን እንደተቆጣጠሩት የእንስሳት መብት ተከራካሪዎች ይናገራሉ፤ ወደ አፍሪካ በሚያስገቡት ኮንቴይነር የአፍሪካን ሃብት ጭነው እንደሚልኩ በስፋት የሚነገር ነው፡፡ ይህም የቻይና አካሄድ በዚሁ ከቀጠለ በአፍሪካ የዝሆን ዝርያ የማይኖርበት ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ይገመታል፡፡

በአንዳንድ ኤክስፐርቶች ግምት ሁኔታው ካልተሻሻለ እኤአ በ2025 አፍሪካ ዝሆን አልባ ትሆናለች ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ደግሞ መሻሻል ካልተደረገበት የኢትዮጵያ ዝሆኖች እስከዚያ ስለ መዝለቃቸው ግምት መስጠት አይቻልም፡፡ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየባቸው 25ዓመታት ውስጥ 90በመቶው ዝሆኖች ካለቁ የቀሩት 10 በመቶው አሉ የተባለው “ምርጫው” እስኪያልፍ ነው በማለት አንዳንዶች ተሳልቀዋል፡፡ (የመግቢያው ፎቶ AFP: Zacharias Abubeker)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: Uncategorized Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    March 21, 2015 07:16 pm at 7:16 pm

    >> በቀድሞ ግዜ ሻእቢያ ህወአት ኦነግና ኦብነግ አሸባሪዎች በነበሩ ግዜ ዙሪያውን ጦርነት ሲከፍቱ የኬንያ፣ የሱዳን፣ ዩጋንዳና ታንዛኒያ አሳዳሪዎች የጦር መሳሪያ ለአሸባሪዎቻችን እየረዱ በኢሊኮብተር ድምፅ የዱር አራዊቶቻችንን እያስበረገጉና አቀጣጫ እያስቀየሩ ዛሬ በቱሪስት መስዕብነታቸው የሚታወቁት የዛሬው ልማታዊ መንግስት የድሮ የጥፋት ቡድን ሙሉ በሙሉ ተሳታፊነት የተመሳጠሩበት የሀገር ሀብት ብዝበዛ ነበር ። ዛሬም በኮንቴነር ክብሪት ያመጡልሃል ጭረህ እናዳታቃጥለው ጥሬ ሀብትህን በኮንቴነር ያሸሻሉ አሁንም ቻይና ኑሪ!!አንደኛ ቻይና፣ ሁለተኛ ቻይና ሶስተኛ ቻይና ያለው ተጠቅላይ ሚ/ር ማን ነበር?
    *** የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን(፮ቶን) የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡… “ዝሆኖችም ተወይኖባቸዋል”!!…
    ” ግን ደመቀና ዝሆኖች ሲሞቱ የት ነበሩ? ሕዝብና የዝሆን ቀንድ ለማቃጠል ብቅ ማለታቸው በም/ጠ/ሚ ማዕረግ የእሳት አደጋ አቃጣይ ባለሙሉ ባለሥልጣን መሆናቸው ነው?ይህን ወደ ገንዘብ ለውጦ ለድሃ ማብላት ቀሪውን መከላከል ነው ጥሩ ወይንስ በሙቀት ላይ ሙቀት መፍጠር ወሬ!?
    ** በእርግጥ ቻይና ለአንድ ኣመት ብቻ የዝሆን ጥርስ ንግድ ገቢ ላይ ማዕቀብ በመጣሏ ማስቀመጫ ስለሌለ ከሚባነን ሕዝብ እያየ ጨዋነታችንን እናሳይ ተብሎ ይሆን!? እነንህ ሰዎች ገድለው ቀብረው ፈርሸው ማስተዛዘን የተካኑ አደሉምን!? መራጭ ይወድቃል ከምራጭ አሉ…ወይ የምርጫ ዋዜማ ጨዋ መምሰል!ሠላም ለሁሉም በቸር ይግጠመን>>>>>>

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule