ኢህአዴግ በሥልጣን በቆየባቸው 25 ያህል ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ መቶ ዝሆኖች ውስጥ ከዘጠና በላይ የሚሆኑት ሞተዋል፣ ወደ ጎረቤት አገር ተሰድደዋል፣ የደረሱበት አይታወቅም፣ . . . ሲሉ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ዛሬ (አርብ) ዘግበዋል፡፡
የዝሆኖችን ግድያ ለማስቆም በሚል የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡
ኢህአዴግ ከቻይና ጋር ከተፋቀረበት ጊዜ ጀምሮ የዝሆን ቀንድ ንግድ እየተጧጧፈ እንደሄደ የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በዚህም “ጮማ” ንግድ ውስጥ ቢጂንግን፣ ሲንጋፖርን፣ ታይላንድን፣ … መመላለሻቸው ያደረጉ ቱባ ባለሥልጣናትና ደላሎቻቸው ይጠረጠራሉ፡፡ የቡድሃ ሃይማኖት እጅግ በተስፋፋባቸው በሩቅ ምስራቅ አገራት የዝሆን ጥርስ እጅግ ተፈላጊ ሲሆን ዋንኞቹ አስተላላፊዎች ደግሞ የዘመኑ የቻይና ቱጃሮች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዝሆን ጥርስ ለሩዝ መብያ ስንጥር (chopsticks)፣ ለተለያዩ ዓይነት ጌጣጌጥ፣ ለቤት ውስጥ ዕቃ፣ ወዘተ ተፈላጊነት አለው፡፡
ቻይና በዝሆን ጥርስ ገቢ ንግድ ላይ የአንድ ዓመት ማዕቀብ ጥያለው ብትልም በአፍሪካ ያሰማራቻቸው ባለሃብቶቿ ከየአገሩ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ንግዱን እንደተቆጣጠሩት የእንስሳት መብት ተከራካሪዎች ይናገራሉ፤ ወደ አፍሪካ በሚያስገቡት ኮንቴይነር የአፍሪካን ሃብት ጭነው እንደሚልኩ በስፋት የሚነገር ነው፡፡ ይህም የቻይና አካሄድ በዚሁ ከቀጠለ በአፍሪካ የዝሆን ዝርያ የማይኖርበት ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ይገመታል፡፡
በአንዳንድ ኤክስፐርቶች ግምት ሁኔታው ካልተሻሻለ እኤአ በ2025 አፍሪካ ዝሆን አልባ ትሆናለች ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ደግሞ መሻሻል ካልተደረገበት የኢትዮጵያ ዝሆኖች እስከዚያ ስለ መዝለቃቸው ግምት መስጠት አይቻልም፡፡ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየባቸው 25ዓመታት ውስጥ 90በመቶው ዝሆኖች ካለቁ የቀሩት 10 በመቶው አሉ የተባለው “ምርጫው” እስኪያልፍ ነው በማለት አንዳንዶች ተሳልቀዋል፡፡ (የመግቢያው ፎቶ AFP: Zacharias Abubeker)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
በለው ! says
>> በቀድሞ ግዜ ሻእቢያ ህወአት ኦነግና ኦብነግ አሸባሪዎች በነበሩ ግዜ ዙሪያውን ጦርነት ሲከፍቱ የኬንያ፣ የሱዳን፣ ዩጋንዳና ታንዛኒያ አሳዳሪዎች የጦር መሳሪያ ለአሸባሪዎቻችን እየረዱ በኢሊኮብተር ድምፅ የዱር አራዊቶቻችንን እያስበረገጉና አቀጣጫ እያስቀየሩ ዛሬ በቱሪስት መስዕብነታቸው የሚታወቁት የዛሬው ልማታዊ መንግስት የድሮ የጥፋት ቡድን ሙሉ በሙሉ ተሳታፊነት የተመሳጠሩበት የሀገር ሀብት ብዝበዛ ነበር ። ዛሬም በኮንቴነር ክብሪት ያመጡልሃል ጭረህ እናዳታቃጥለው ጥሬ ሀብትህን በኮንቴነር ያሸሻሉ አሁንም ቻይና ኑሪ!!አንደኛ ቻይና፣ ሁለተኛ ቻይና ሶስተኛ ቻይና ያለው ተጠቅላይ ሚ/ር ማን ነበር?
*** የብአዴኑ ደመቀ መኮንን ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ስድስት ቶን(፮ቶን) የሚመዝን ጌጣጌጥ እንዲቃጠል እሣቱን በለኮሱበት ጊዜ ኢህአዴግ በአገዛዝ በቆየበት 25 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ቁጥር ከ90በመቶ በላይ ለምን ሊቀንስ እንደቻለ የተናገሩት ነገር የለም፡፡… “ዝሆኖችም ተወይኖባቸዋል”!!…
” ግን ደመቀና ዝሆኖች ሲሞቱ የት ነበሩ? ሕዝብና የዝሆን ቀንድ ለማቃጠል ብቅ ማለታቸው በም/ጠ/ሚ ማዕረግ የእሳት አደጋ አቃጣይ ባለሙሉ ባለሥልጣን መሆናቸው ነው?ይህን ወደ ገንዘብ ለውጦ ለድሃ ማብላት ቀሪውን መከላከል ነው ጥሩ ወይንስ በሙቀት ላይ ሙቀት መፍጠር ወሬ!?
** በእርግጥ ቻይና ለአንድ ኣመት ብቻ የዝሆን ጥርስ ንግድ ገቢ ላይ ማዕቀብ በመጣሏ ማስቀመጫ ስለሌለ ከሚባነን ሕዝብ እያየ ጨዋነታችንን እናሳይ ተብሎ ይሆን!? እነንህ ሰዎች ገድለው ቀብረው ፈርሸው ማስተዛዘን የተካኑ አደሉምን!? መራጭ ይወድቃል ከምራጭ አሉ…ወይ የምርጫ ዋዜማ ጨዋ መምሰል!ሠላም ለሁሉም በቸር ይግጠመን>>>>>>