የትግራይ ህዝብ ከማን አገዛዝ ነጻ እንዲወጣ እንደሚፈለግ በውል ባይታወቅም ራሱን “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር” የሚለው ህወሃት በቢሾፍቱ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ የሚዘክር ሃውልት እንዲቆም ሃሳብ መቀረቡ ተሰማ። የኢሬቻን ክብረ በዓል ለማክበር የተሰባሰቡ የኦሮሞና የሌሎች ቦታዎች ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ ትውልድ ሁሉ በማንና እንዴት እንደተፈጸመ እንዲያውቅ፣ እንዲማርና የተከፈለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ እንዲረዳ፣ እንዲሁም ምስክር ሊሆን በሚያስችለው መልኩ ሃውልቱ እንደሚታነጽ ለማወቅ ተችሏል።
ለመብታቸው የተነሱና በሰላማዊ መንገድ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን “በቃህ፣ ልቀቀን” በማለታቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላለፉት አስራ አንድ ወራት ሲገደሉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲገረፉና ሲሰቃዩ መቆይታቸው ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ቢሾፍቱ የኢሬቻን ክብረ በዓል ላይ በተገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግን አእምሮ ያላቸው ሁሉ ሊቀበሉት ያልተቻላቸው የግፍ ሁሉ ግፍ ሆኖ ተመዝግቧል።
በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባሰሙ ወገኖች ላይ የደረሰው ይህ ታሪክ የማይረሳው ጭፍጨፋ ያስቆጣው ድፍን የኢትዮጵያን ህዝብ ነው። ክልል፣ ቦታ፣ ዘር፣ አካባቢና እምነት ሳይለይ ድፍን አገርን እንባ ያራጨው የጅምላ ጭፍጨፋ ያላሳዘነው የህዝብን ጩኸት “አንሰማም” ላሉት ክፍሎችና ድርጅታቸው ብቻ መሆኑ ደግሞ ሃዘኑን የከፋ እንዳደረገው በተለያዩ ዘዴዎች የሚወጡ የህዝብ አስተያየቶች ያረጋግጣሉ።
አንድም ጉዳት ያላደረሱ፣ ለማድረስም ባልሞከሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ የህወሃት አንጋቾች በመርዝና በጥይት ያደረሱት ዘገናኝ ጭፍጨፋ በታሪክ ሁሉ ሲታወስ እንዲኖር በኦሮሞ ተወላጆች ዘንድ መግባባት አለ። ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም ድጋፍ እንደሚሰጡ ማቅማማት የለም። ለጎልጉል ሃሳባቸውን የሰነዘሩ የስዊትዘርላንድ ነዋሪና የብሄሩ አባል “አሁን ቅድሚያ የሚሰጣቸው የነጻነት ስራዎች ቢኖሩም የዚህ ጭፍጨፋ ሰነድና መረጃዎች በጥንቃቄ ይከማቻሉ” ብለዋል። ሃውልቱ ህወሃት ያልተፈጠረ ታሪክ እየሠራ ሕዝብን ለመከፋፈል እንደተጠቀመባቸው ሳይሆን በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ እንደሚሆን ተነግሯል።
ሌላ የሚኖሶታ ነዋሪ የኦሮሞ ተወላጅ “ህወሃትና የኦሮሞ ህዝብ መካከል ለሚኖረው ግንብ የሃውልቱ መሰራት ለትውልድ የሚዘልቅ መልስ ነው” ብለዋል። በማህበራዊ ገጾችም “ተስፋ ቁረጡ፣ ካሁን በኋላ እርቅ ጠይቆ ኦሮሞ ላይ ቁማር መጫወት አይቻልም” በሚል ስሜታቸው የመረረ መሆኑንን የሚገልጹ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።
የጅምላ ጭፍጨፋውን ተከትሎ በሚኖሶታ የኦሮሞ ተወላጆች ባካሄዱት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ “ህዝብ እየጨፈጨፉ ዛፍ ሥር በመቀመጥ ይቅርታ መጠየቅ ያከተመበት አስተሳሰብ ነው” ሲሉ አቶ ጃዋር መሐመድ ተናግረዋል። ተሰብሳቢዎቹም በጭብጨባ ተቀብለውታል። አሁን ትግሉ የደረሰበት ደረጃ ወደፊት የመጓዝ ብቻ እንደሆነም ተጠቁሟል።
የሃውልቱ መገንባት ዋና አስፈላጊነት ግፍን ለማስታወስና ሁልጊዜ አንድን ወገን እየወቀሱ ለመኖር ሳይሆን ተመሳሳይ የመብት ጭቆና በድጋሚ እንዳይደርስ የተከፈለውን መስዋዕትነት በማሰብ እንዳይደገም ለማስተማር ነው ተብሏል። ከንግዲህ ወዲህ የኢሬቻ በዓል የሚከበረው ህወሃት የፈጸመውን ይህንን ጭፍጨፋ ሳይዘከር ስለማይሆን በሃውልቱ ጉዳይ ላይ ተጎጂ ወገኖች በሙሉ እንዲተባበሩ ሃሳብ ተሰጥቷልተነግሯል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Angile says
የህዝብ ጥያቄ ስልጣን በአንድ አንስተኛ ጠባብ እጅ ስለወደቀ እኩል ተካፍለን አገራችን በጋራ እናስተዳድር ነው። የ 100 ሚሊዮን ህዝብ አገር በጥቂቶች መተዳደር ይብቃ። የአደራ መንግስት ሁሉንም ያካተተ ይቋቋም ነው ያለው ህዝቡ። ጥገና ሳይሆን ለውጥ። ሰው መቀያየር ሳይሆን የስርዐት ለውጥ። አባ ድላን አንስቶ ተሾመ ቶጋን መተካት ሳይሆን ምሁራንን የአገር ሽማግሌዎችን ተቃዋሚዎችን ያካተተ የአደራ መንግስት በአስቸኳይ ይቋቋም ነው ጥያቄው መልሱም እሱ ብቻ ነው።
20 ሚሊዮን ብር ብቻ?
ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
አዲስ አበባ ቄራ አካባቢ አንድ ቤት ለሽያጪ ወጥቷል፡፡ እድሜው በ18 እና 20 መካከል የሆነ ልጅ የመጀመሪያ ቤት ገዢ ሆኖ ከቦታው ይገኛል፡፡ ሻጪዎችም ከእድሜን ልጅነት፣ ከሀገሪቱ ሁኔታና ከዋጋው ውድነት አንፃር ለመቀለድ በማሰብ ከቤቱ ዋጋ በእጥፍ ጨምረው 20 ሚሊዮን ብር ነው ይሉታል፡፡ ለመሳቅና ልጁንም በማስደንገጥ ለማባረር አስበው እንደ ቀልድ ያደረጉት የ20 ሚሊዮን ብር ጨዋታ ግን ቁም ነገር ሆነና ቤቱን ልየው፣ ዋጋ ቀንሱ ወይም ሌሎችን በዚህ ወቅት መጠየቅ የሚገባቸውን ሳይጠይቅ ኑ እንፈራረም አለና አስደነገጣቸው፡፡ ለማመን ባለመቻላቸውና እየቀለደባቸው አንደሆነም ገምተው ለመቆጣት እየቃጣቸው እያሉ የ2 ሚሊዮን ብር ቼክ አወጣና የመፈራረሚያ ቅድሚያ ክፍያ አሳያቸው፡፡ እነሱም ያልጠበቁትን ግብይት እንዳደረጉ በመረዳት ካቀዱት ዋጋ በእጥፍ አትርፈው ቤቱን 20 አመት ለማይሞላ ልጅ በ20 ሚሊዮን ብር ሸጡ፡፡
ይህም ብቸኛው ክስተት ሳይሆን በስፋትና በጥልቀት በየዘርፉ በየቀኑ የሚፈፅሙት ወንጀል ነው፡፡
ትልቁ ጥያቄ ግን ይህ ልጅ ማን ነው የሚለው ብቻ ሳይሆን የማን ልጅና ዘመድ ነው የሚለው ነው፡፡ ልጁ ሕውሓት ነው፡፡ ወላጆቹና ዘመዶቹም ያው ሕውሓቶች ሲሆኑ አነማን ናቸው የሚለው ግን መጣራት ቢኖርበትም ሁሉም በዚህ አይነት ወንጀል ተሰማርተው ስለሚገኙ ሁሉም ናቸው ብሎ በሀዘን ማለፍ ሳይሆን በነሱ እየተበደለ ያለ ህዝብ በውስጡ ሰላም አግኝቶ፣ አንድነትን ፈጥሮና በጋራ ተነስቶ ሊያስወግዳቸው ይገባል፡፡ ወንጀላቸው ብዛቱ፣ አይነቱና ይዘቱ በየቀኑ አዲስና ህዝብ ሊቋቋመው የማይችል ሆኗል፡፡