• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የንባብ ባሕል ለምን እንዴትስ ይፈጠራል?

July 25, 2013 11:19 pm by Editor 1 Comment

ስለ ንባብ ባሕል ስናነሣ በሀገራችን ያለው የንባብ ባሕል በዓለማችን ብቸኛውና የመጠቀ የረቀቀ የመጨረሻው ደረጃም ላይ የደረሰ ነው፡፡ይህም ማለት መጻሕፍትን ጥሬ ንባባቸውን ብቻ ሳይሆን ከነምሥጢራቸው ጥጥት አድርጎ በቃል እስከ ማነብነብ ወይም መያዝ የደረሰ ፡፡ ሀገራችን ስላሏት እሴቶች ምንጭ ወይም አድራሻ ስናስስ ዞረን ዞረን የምንደርሰው አንድ ቦታ ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከላይ የጠቀስኩትን የራሳችን የሆነን የንባብ ባሕል የፈጠረች ቤተክርስቲያን ነች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ ብዙ ዓይነት መጻሕፍት አሉ የሚገርመው ታዲያ ከእነዚህ መጻሕፍት በሊቃውንቱ በቃል ያልተያዘ መጽሐፍ አለመኖሩ ነው እንዲኖርም አይጠበቅም፡፡ ይሄ ዓይነት የተለየ የንባብ ባሕላችን ታዲያ ሀገራችን በተደጋጋሚ በጠላት በተጠቃችና መጻሕፍት በወደሙ፣ በጠፉ፣ በተቃጠሉ ጊዜ እነሱን መልሶ ለመጻፍና ለመተካት እንዲቻል አድርጓል፡፡ አንዳንዴ ግን ኧረ ምን አንዳንዴ በብዛት ማለት ይቻላል ሊቃውንቱም በአደጋው አብረው የመጥፋት ችግር ሲያጋጥማቸው የነበሩን መጻሕፍትም እስከወዲያኛው ጠፍተው የመቅረት ችግር ሊያጋጥም ችሏል፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ያለን የንባብ ባሕል እዚህ ድረስ ማለትም መጻሕፍትን በአንድም በሌላም ምክንያት ቢጠፉ መተካት በሚያስችልበት ደረጃ በመሸምደድ ሳይሆን አመስጥሮ በቃል ጥጥት አድርጎ መያዝ ደረጃ ላይ የደረሰ ነው፡፡የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን መጋቤ ጥበብ መሆኗ ይታወቃል ይሄንን የማያውቅ ዜጋም ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ ከፊደል እስከ የሕክምና ጥበብ ድረስ ያሉንን ዘርፈ ብዙ ብርቅና ድንቅ ሀብቶቻችንን እሴቶቻችንን ያገኘነው ከዚህችው ቤተክርስቲያን ነው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ዘመናዊት ኢትዮጵያ ብዙ ነገሮችን ከቤተክርስቲያን ስትወስድ ለዘመናዊነቱ የኑሮ ዘይቤዋ ሊጠቅሟት ይችሉ የነበሩ ነገር ግን ያልወሰደቻቸው ወይም ልትወስዳቸው ያልቻለቻቸው በርካታ ቁም ነገሮች አሉ፡፡ከነዚህ ጥቅሞች ውስጥ አንዱ ይህ ከላይ ያለሣነው የንባብ ባሕል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የሒስ ባሕል ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሙሉውን ቀርቶ ቅንጣቱን ማለትም በቃል ልቅም አድርጎ መያዙ ቀርቶ የመጻሕፍትን ንባብ ፍላጎት ፍቅርና አንብቦ የመረዳትን ያህል እንኳን የንባብ ባሕሏን ብንወስድ ኖሮ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሌሎቹ በአንባቢነታቸው እንደምናደንቃቸው ሀገራት አንባቢ ሕዝብ ማግኘታችን እርግጥ በሆነ ነበር፡፡ አንድ እጅግ የሚገርመኝና የሚደንቀኝም ነገር አለ ደራሲያንና ሐያሲያን የተባሉ ግለሰቦች በብዙኃን መገናኛ በቀረቡ ቁጥር  ስለ የንባብ ባሕልና የሒስ ባሕል ሲናገሩት የምሰማው፡፡ በእውነት እጅግ ሀፍረት ይሰማኛል አዝናለሁም ፡፡ እንደነሱ ግንዛቤ እኛ ኢትዮጵያውያን የንባብና የሒስ ባሕል የለንም፡፡ እስከዛሬ ከሰማኋቸው ከእነዚህ ግለሰቦች አንዳቸውም እንኳን እንዲያው ተሳስተው እነኝህ እሴቶች እንዳሉን ለመናገር የሞከረ ሰምቸ አላውቅም፡፡ የሚገርመው የሚሰጡትን ሐሳብ ሲሰጡ ኢትዮጵያን ወይም ማንነታችንን ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ሆነው ማውራታቸው ነው፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩት ብንወስድ ኖሮ ይጠቅመን የነበረ ግን ያልወሰድነው የሒስ ባሕል ነው፡፡ እነኝሁ ደራሲንና ሐያሲያን ስለ ዘመናዊው ሥነ ጽሑፋችን እድገትና ችግሮቹ ሲያወሩ፣በእንድ የሥነጽሑፍ ሥራ ላይ ሒስ ስለመስጠትና መቀበል ያለንን ልምድ ሲናገሩ ‹‹እኛ የሒስ ባሕሉ ስለሌለን በቅን ሐሳብ ላይና ሞያው በሚጠይቀው ሥነምግባር ላይ ተመሥርቶ ሞያዊ ሒስ የሚሰጥና የሚቀበል የለም›› በማለት የደመድማሉ፡፡ እንግዲህ እንደነሱ ግንዛቤ እኛ የሒስ ባሕል የለንም፡፡ የሚደንቀው ነገር ግን እንደ ዜማና የዜማ ምልክት(ኖታ) ሁሉ ሒስንም ለዓለም ያስተማርንና ያስተዋወቅን እነኝህ ‹‹ምሁራን›› ባሕሉ የላችሁም የሚሉን እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቅኔ የሚባል የአብነት ትምህርት ዓይነት አለ ይህ የትምህርት ዓይነት ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች አንሥቶ እስከ ፍልስፍና ያሉ ዕውቀቶች የሚፈተቱበት፣የሚበለቱበት፣የጭንቅላት የማሰብና የማስተዋል ችሎታና አቅም የሚፈተንበት የትምህርት ዓይነት ነው፡፡ ይሄንን ትምህርት የሚማር ተማሪ ብቃቱን አስመስክሮ ለመመረቅ እስኪበቃ ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ የሚከውነውና የሚከወንበት ጉዳይ አለ እሱም የቋጠረውን ቅኔ ከመምህሩና ከባልንጀሮቹ ተማሪዎች ፊት ቆሞ መቀኘት መዝረፍ መናገርና ብስለት ጥንካሬውን ማስመስከር በሒስ ማስፈተሸ ማስበርበር ላቅ ባሉትም ላለመነጠቅ ማራቀቅ ይኖርበታል፡፡ በሒደቱም መጀመሪያ ተማሪዎቹ እየተፈራረቁ የቻሉትን ያህል እየተቀባበሉ የቅኔውን ድክመት ጥንካሬ እየጠቀሱ ይተነትናሉ ይዘረዝራሉ ይፈተፍታሉ፡፡ በመጨረሻ ላይ ደግሞ መምህሩ እንደመምህርነታቸው የቅኔውን ድክመት ጥንካሬና የተሰጠውንም ሒስ አብጠርጥረው ይተቻሉ(ያሔሳሉ) ይገመግማሉ፡፡ ያ ተማሪ በዚህ ዓይነት ሒደት በተደጋጋሚ አልፎ ብቃቱን ሲያረጋግጥ ያ ተማሪ ይመረቃል ፡፡ ሒስና የቅኔ ትምህርት የዚህን ያህል የጠበቀ ሀገርኛ ቁርኝት አላቸው፡፡ እንግዲህ ይህ ሒሳዊ የትምህር ባሕል በትንሹ ለ1500 ዓመታት ያህል ሲካሄድ ቆይቷል አሁንም በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ይሄንን የማያውቁ የኛ ደራሲያንና ሐያሲያን ታዲያ የሒስ ዋነኛ ባለሀብቶች መሆናችንን ባለማዎቅ የንባብና የሒስ ባሕል የለንም በማለት በድፍረት ይናገራሉ ፡፡እንዲህ በድፍረት ለመናገር ከመቸኮል  በፊት ግን መለስ ብለው ማንነታችንን ለመፈተሸ ቢሞክሩ ተሳስቶ ከማሳሳት መዳን በቻሉ እላለሁ፡፡ ይሄንን ጥንቃቄ ባለማድረግ ብዙ ሰዎች በብዙ ጉዳዮች ላይ እጅግ የተሳሳቱ ነገሮችን ሲናገሩ እስተውላለሁ፡፡

ሌሎች ብዙ ነገሮችን ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደወሰድን ሁሉ ይሄንን በሳል የሒስ ባሕልም ወስደን ቢሆን ኖሮ ዘመናዊው የሥነጽሑፍ እድገታችን የት በደረሰ ነበር፡፡ እዚህ ላይ ይህ የሒስ ባሕል ለእኛ እንግዳ ካልሆነ ጭራሽም እንደ ባሕል ካለንና ከነበረን እንዴት ጥቅም ላይ ሳናውለው ጭራሽም እንዳለን እነኳን ሳናውቀው ልንቀር ልንረሳው ቻልን የሚል አግባብንት ያለው ጥያቄ ሊነሣ ይችላል ይገባልም፡፡ የዚህ ክፍተት መፈጠር ብቸኛ ምክንያትም ዘመናዊት ኢትዮጵያን የመሰረቱ አውሮፓና አሜሪካ ተምረው የመጡ ምሁራኖቿ ዘመናዊት ኢትዮጵያን የመሠረቱበት መሠረት ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ምዕራባዊ መሆኑ ነው፡፡ በራሷ ወይም በነበራት መሠረት ላይ ሳይሆን እንደአዲስ ሀገር በአዲስ አውሮፓዊ መሠረት ላይ የተመሠረተችው አዲሲቷ ኢትዮጵያ ነባሩን ዕውቀትና የዕውቀት መንገድ ይጥቀም ይጉዳ በቅጡ ሳትመረምረውና ሳታጤነው ኋላ ቀር እንደሆነ በመቁጠር ጣል እርግፍ አድርጋ የሁሉም ነገር መፍትሔና መላ አውሮፓዊ አስተሳሰብ ነው ብላ ማመኗ ከሁለት ያጣ ሊያደርጋት ቻለ ፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ የንባብና የሒስ ባሕሎቻችን ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎቻችንም አብረው ተዳፍነው እንዲቀሩና እንዲረሱም ሊያደርጋቸው ቻለ፡፡ ዛሬ ላይ ያለው ትውልድም እነዚህ ምርጥ ባሕሎቻችን ጭራሽም እንደሌሉን አፉን ሞልቶ እስከመናገር ደረሰና ዓረፈው ፡፡

የሌሎች ሀገሮችን የንባብና የሒስ ባሕሎች ተሞክሮዎችን ስናይ እንደኛ እድሜ ጠገብ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ በንባብ ባሕሏ ተደናቂ የሆነችውን አንድ ሀገር ተሞክሮ ዕንይ፡-

እንግሊዞች በአንባቢነታቸው እጅግ የሚደነቁ ናቸው፡፡ አንባቢነትን የባሕላቸው አካል ለማድረግ የቻሉም ናቸው፡፡ ይሄንን እመርታ ወይም ታላቅ ውጤት ያገኙት ግን ያለማሰለስ በብዙ ጥረትና ድካም እንጂ እንዲሁ የተዋሐዱት ወይም አብሯቸው የተፈጠረ ልማድ ሆኖ አይደለም፡፡ ሕዝባቸውን የዚህ ድንቅ ባሕል ባለቤት ሊያደርጉት የቻሉት ከኢንዱስትሪ(ከምግንባብ) አቢዮት በኋላ ወይም ሩቅ ባልሆነ ጊዜ በዚያው ወቅት ምቹ ፖሊሲ መመሪያ በመቅረጽ ለምሳሌ ወረቀትና መጻሕፍትን ከቀረጥ ነጻ በማድረግ አድካሚ የሆነ ታላቅ ዘመቻ በመክፈት ነበር፡፡ ለዚያ የተቀናጀና የተደራጀ ዘመቻ አንድ ጥሩ ግልጽና ሳቢ መሪ ቃል (slogan) ነበራቸው “እያነበብክ ያግኙህ” ወይም ‹‹እያነበብክ ተገኝ›› በቋንቋቸው ባልሳሳት “Let them find you while you are reading ወይም let you be found when you are reading” የሚል ነበር፡፡

በዘመቻው ወቅት በምድረ እንግሊዝ ይህ መፈክር ያልተሰቀለበት ቦታና  ግድግዳ የማስታወቂያ ሠሌዳ አልነበረም ማለት ይቻላል በየአውቶቢሱ እና ሕዝብ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ በትልልቅ እና ባጌጡ ቃላት “እያነበብክ ተገኝ” የሚለው ጽሑፍ ይጻፍ ነበር፡፡ የብዙኃን መገናኛዎችም በልዩ ትኩረት አመርቂ ጥረት አድርገዋል፡፡ የዚህ ጠንካራ ጥበብ የተሞላበት ጥረት ውጤትም በሚያስደስት ሁኔታ ማንበብ ወይም አንባቢነት ባሕሉ የሆነን ማኅበረሰብ ማግኘት ሆነ፡፡ በመሆኑ ይሄንን ያህል መድከም ያስፈለጋቸው ለምን ነበር ስንል መልሱ ቀላልና ግልጽ ነው፡፡ አንባቢ ሕዝብ ጠንካራና ባስተማማኝ ሁኔታ ያደገች የበለጸገች ሀገርን መፍጠር ስለሚችል፣ አንባቢ ማኅበረሰብ ራሱንና አካባቢውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅና ስለሚረዳ፣ አንባቢ ማኅበረሰብ ተወደውም ሳይወደዱም ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሔ ሰጭና የመፍትሔ አካል ስለሆነ፣ አንባቢ ማኅበረሰብ ፈጣሪና ፈልሳፊ ስለሆነ፣ አንባቢ ማኅበረሰብ የነቃና የበቃ ሥልጡን ስለሆነ፣ አንባቢ ማኅበረሰብን መግባባትና ማስተዳደር ቀላልና ማራኪ አዝናኝም ስለሆነ፣ አንባቢ ማኅበረሰብ በራስ መተማመኑ ጠንካራ ስለሆነ፣ አንባቢ ማኅበረሰብ ኃላፊነት ስለሚሰማው ወዘተ ወዘተ…

እኔ ደግሞ የእኛዋን አህጉር መሪዎች እንዲህ ስል ልጠይቅ፡-

ያደጉ ሀገሮች ለምንድን ነው ወረቀትን ከቀረጥ ነጻ ያደረጉትና የሚያደርጉት? ገንዘብ ስለተረፋቸው ነውን? ለምንስ ነው አንባቢ ሕዝብ እንዲኖራቸው ያለመታከት የደከሙትና የሚደክሙት? ሥራ ፈት ሆነው የሚሠሩትን ሥራ ስላጡ ይሆን? በጉዳዩ በመድከማቸው ያገኙትን ውጤት በማየትና በመረዳት በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት እኛስ ከዚህ ግሩም ተሞክሮ ልንማረው ልንቀስመው የምንችለው ቁምነገር እንዴት ነው ሊኖር የማይችለው? የጥመት ወይስ የእውቀት ማነስ? የጥፋት ዓላማ ወይስ የግንዛቤ አድማስ መጥበብ? የዚህች አህጉር መንግሥታት ከንባብ በሚገኙ ከላይ በዘረዘርናቸው ጥቅሞች የታነፀ የተገነባ ሰብእና ያለው ሕዝብ እንዲኖራቸው አይፈልጉምን? ለምን? ይሄ ለሀገሩና ለሕዝቡ እሠራለሁ አስባለሁ ከሚሉ መሪዎች የሚጠበቅ ነውን?፡፡

የአንድ አፍሪካዊ ሀገር መንግሥት በወረቀት ላይ ቀረጥ ጥሎ የገዛ ሕዝቡን ከንባብ (ከዕውቀት) ጋር አቆራርጦ ወይም አራርቆ ከቀረጡ ገንዘብ ቢያገኝ ለነገሩ እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ ከወረቀት ቀረጥ የሚያገኝ የለም ብቻ እንዲያው አገኘ ብለን እናስብና ምንም ያህል ብር ቢያገኝ ያቺ ሀገርና ያሕዝብ በምንም መመዘኛ ቢታይ ተጠቀሙ ወይም ይጠቀማሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ ሕዝቡ በቀረጥ ምክንያት ከንባብና ከዕውቀት ተራርቆ እንዴት ነው ተጠቀመ ብለን ልናስብ የምንችለው? ምክንያቱም ያች ሀገር በወረቀት ላይ ቀረጥ ጥላ ከምታገኘው መናኛ ጥቅም ይልቅ አንድ ሚሊዮን ጊዜ እጥፍ ወረቀት ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ቢቻል እንዲያውም ቢደጐምና ያሕዝብ አንባቢ ሆኖ ከንባብ የሚገኙ የዕውቀት ፍሬዎችን የሚመጠምጥ እና የሚውጥ ቢሆን ለሀገርና ለራሱ የሚያስገኘው ጥቅም ያለጥርጥር ከላይ እንዳልኩት አእላፋት (ሚሊዮን) ጊዜ እጥፍ ይበልጣልና፡፡ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ወረቀትን ይቀርጣሉ ማለቴ ግን አይደለም፡፡ ወረቀትን አይደለም እንዲያውም አብዛኞቹን የኪነት ሥራዎች እና ውጤቶችን ጭምር ከቀረጥ ነጻ ያደረጉም አሉ፡፡ ጐረቤት ሀገር ኬንያን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አቤት አቤት እንዴት ያስጐመጃል ይሄንን ዕድል የእኛ ሕዝብ ቢያገኘው ኖሮ ካለው የተሟላ አቅምና የጥበብ ሀብት አንፃር ምን ተአምር ሊፈጥር ይችል እንደነበር ስገምት እጅግ እበሳጫለሁ፡፡ እዚህ ላይ አሜሪካውያን የሚጠቅሱትን አባባል ብጠቅስ ደስ ይለኛለ “taxing paper is taxing knowledge” ወረቀትን መቅረጥ እውቀትን መቅረጥ ነው ይላሉ፡፡ እንዴታ ጃል በትክክል እንጂ ላወቀውማ ነበር፡፡

የኢትዮጵያን ታሪክ ለሚጽፉና ለሚመረምሩ ሰዎች መጻሕፍትን ሲመረምሩ በየዘመናቱ ስለነበረው ነገር ሁሉ ሙሉ መረጃ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ እና ፈትኝ ሥራ ሆኖባቸው ያገኙታል፡፡ ለዚህ ችግር ደግሞ ተጠያቂ የሚያደርጉት በወቅቱ የነበሩትን በተለይም የክብረ ነገሥትንና የየነገሥታቱን ዜና መዋዕሎችን ጸሐፍት ነው፡፡ ስለነገሥታቱ ጥፋትና ሌሎች ችግሮችን ሊጽፉልን አልቻሉም በማለት፡፡

ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ ያላቸው የዘመናችን ታሪክ ተመራማሪዎችም ሆኑ ሐያሲያን እንዲሁም ጸሐፍት ያልተረዱትና ልብ ያላሉት ነገር ቢኖር በዘመናችን ያሉ የኋላ ቀር ሀገሮች መንግሥታት ጸሐፍትን ለምን እንደሚጫኑና ነጻነታቸውን እንደሚነፍጉ፣ እንዲጽፉ ከፈቀዱ ለእነርሱ መልካም መስሎ የታያቸውን ማለት ለየአስተዳደሮቻቸው አመቺ የሆነና ተቺ ያልሆኑ ባስ ካለም የሌላቸውን ዲሞክራሲያዊነት (በይነ ሕዝባዊነት) እና ፍትሐዊነት የሚያወድስ መጣጥፍ ብቻ ለምን እንዲጻፍ እንደሚያደርጉ፣ የዘመናችን ታሪክ ጸሐፊ ነን ተመራማሪ ነን፣ ሀያሲ ነን ባዮችም የዘመናችንን እምነተአስተዳደራዊም (ፖለቲካዊም) ሆነ ማህበራዊ ኩነቶችን ያለፍርሀት፣ ያለችግርና መሸማቀቅ እንደወረደ ያለውን ነገር ለመጻፍም ሆነ ለመናገር ለምን እንዳልቻሉ መረዳት መገንዘብ ቢችሉ የክብረ ነገሥትንና የየዜና መዋዕሎችን ጸሐፍት የሚኮንኑበት አንዳችም አፍና ምክንያት እንደሌላቸው በተረዱ ነበር፡፡

እንግዲህ የአፍሪካ ሀገራት መንግሥታት በተለይ አንባገነኖቹ በወረቀት ላይ ከባድ ቀረጥ የሚጥሉበትና ጸሐፍትም የተሰማቸውን የሚያውቁትን እንዳይጽፉ የሚያደርጉበት ምክንያትም የመረጃ ፍሰቱ ቀላልና ፈጣን እንዳይሆን ለባለቤቱ ማለትም ለሕዝቡ ተደራሽ እንዳይሆን በማሰብና ይህንን በማድረጋቸውም ወንጀሎቻቸውና ግፎቻቸው እንዲደበቁ እንዲሰወሩ ያደረጉ ስለሚመስላቸው፣ እንዲደበቅ እንዲሰወር በማድረጋቸውም አገዛዛቸውን ያረዘሙ ስለሚመስላቸው ነው፡፡ እንጂ ወረቀት ከቀረጥ ነጻ ቢሆን የመማር ማስተማር ሂደቱን ማለትም የቀለም ትምህርትን ጨምሮ የመረጃ ፍሰትንም ቀላልና የተሳለጠ እንዲሆን ከማስቻል አንጻር ሕዝብና ሀገር ምን ያህል ሊጠቀሙ እንደሚችሉ መረዳት ተስኗቸው ወይም አተውት አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን ይህንን ማድረግ ለተጠያቂነት ስለሚዳርጋቸው መጠየቅ ስለሚፈሩና ስለማይፈልጉ እንጂ፡፡ አይገርምም? በጥቂቶቹ ጥቅም ምክንያት የስንት አእላፋት (ሚሊዮኖች) ወይም የአንድ ሀገር ሕዝብ እጣ ፈንታ ወይም ሁለ ነገር እንዲጨልም መፈረዱና መደረጉ? እንዳይበራና እንዳይፈካ መከልከሉ? አያሳዝንም?

amsalugkidan@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Social

Reader Interactions

Comments

  1. Berhanu says

    July 31, 2013 08:48 pm at 8:48 pm

    Lots of old books and Manuscripts were smuggled out of Ethiopia to different American and European liabraries and Universities.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule