• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወያኔና ትግሬ

April 14, 2016 12:13 am by Editor 7 Comments

አዳም በበደለ መድኃኔ ዓለም ካሠ፤ የተጠቀሰውን አባባል የማያውቅ ክርስቲያን ያለ አይመስለኝም፤ ለእስላሞችም ቢሆን አዲስ ነገር አይሆንባቸውም፤ አዳም ትእዛዝ ጥሶ ዕጸ በለስን በላና ተረግሞ ከገነት ወጣ፤ አዳም በደለ የሚባልበት ምክንያት ይህ ነው፤ አዳም በገነት ባካሄደው አብዮት የተነሣ የሰው ልጆች ሁሉ ከገነት እንደወጡ የሚቀሩ ሆነ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አዘነ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያት ወረደና ከድንግል ማርያም ተወለደ፤ እግዚአብሔር ይህንን በማድረጉ ሰዎች ከአዳም የወረሱት የጅምላ ኃጢአት ተሻረ፤ ከዚያ በኋላ ኃጢአት የግል እንጂ የጅምላ መሆኑ ቀረ፤ ይህ የሆነው መድኃኔ ዓለም የሰው ልጅን ከራሱ ጥፋት ለማዳን በመሰቀሉ ነው፤ ሃይማኖት ለመስበክ ሳይሆን የጅምላ አስተሳሰብ ቀና እንዳልሆነ እግዚአብሔር እንዳስተማረን ለማመልከት ነው፤ በዚህም መሠረት ፍትሐ ነገሥት ልጅ በአባቱ ወንጀል አይጠየቅም፤ አባቱም በልጁ ወንጀል አይጠየቅም ይላል፤ በአስተሳሰብና በፍትሕ ጉዳይ የሰው ልጅን የእድገት በር የከፈተው ይህ ነው፤ እያንዳንዱ ሰው የሚመዘነውና የሚፈረድለት ወይም የሚፈረድበት እሱው ራሱ በሠራው ነው፤ ይህ ቁም-ነገር ዛሬ በሠለጠኑ አገሮች ሁሉ ሕግ ሆኖ የሚሠራበት ነው፤ ወደማኅበረሰብ ደረጃ ሲወርድ ቁም-ነገሩ ሰፊውን ሕዝብ አዳርሷል ለማለት ያስቸግራል።

ከላይ እንደመግቢያ ያቀረብሁት አስተያየት ከወያኔ ጎሠኛ አስተዳደር ጋር ተያይዞ የመጣ አንድ የአስተሳሰብ ግድፈትን ቢቻል ለማረም ነው፤ ይህ መሠረታዊ የአስተሳሰብ ግድፈት በአጠቃላይ የሰው ልጅን ሁሉ የሚመለከት ቢሆንም ኋላ-ቀሮችን ይበልጥ ያጠቃል፤ በተለይ ደግሞ በአንዳንድ ልዩነቶች ላይ ጎልቶ ይታያል፤ ለምሳሌ ወንዶች ሁሉ ስለሴቶች ያላቸው የተዛባ አመለካከት ከአካላዊ ልዩነት ተነሥቶ አእምሮንና መንፈስንም ጨምሮ ሴቶችን ከወንዶች በታች ያደርጋል፤ ዛሬ ሴቶች ያልገቡበትና ያልተደነቁበት ሙያ ባይኖርም አንዳንድ ወንዶች አሁንም አሮጌ አስተሳሰብን ይዘው የቀሩ አሉ፤ እንዲሁም ስለጥቁሮች ያረጀ አስተሳሰብ ይዘው የቀሩ ነጮች አሉ፤ ክርስቲያኖችም፣ እስላሞችም እንዲሁ፤ በእውቀት ዓለም አጠቃላይ ወይም የጅምላ አስተሳሰብ የሚፈቀድበት ጊዜ አለ፤ ይህ የሚሆነው ተጨንቀው፣ ተጠብበው፣ ብዙ ፈተናዎችን አልፈው ነው ወደማጠቃለያው የሚደርሱት፤ ሁለት ነጫጭ ውሻዎችን ያየ ሰው፣ ሁለት ነጫጭ ውሾች አየሁ ቢል እንቀበለዋለን፤ ነገር ግን ውሾች ሁሉ ነጫጭ ናቸው ወደሚል ማጠቃለያ ቢደርስ የከረረ ሙግት ይነሣል።

የቀለም ልዩነት ባለበት አገር ሁሉ ቀለም ለአስተሳሰብ ግድፈት መነሻ ይሆናል፤ ነጮች ጥቁሮችን ይንቃሉ፤ የሚንቁት አንድ ደደብ፣ ወይም አስቀያሚ፣ ወይም ባለጌ … ሆኖ ያገኙትንና የሚያውቁትን አንድ ጥቁር ሰው አይደለም፤ እንዲሁ ሾላ በድፍን አይተውት የማያውቁትን ጥቁር ሰው ሁሉ ያለምንም ሚዛን በአንድ ከረጢት ውስጥ ጨምረው ነው፤ እውነትን ለሚፈልግ በአውቀት መለኪያ ከብዙ ነጮች የሚበልጡ ጥቁሮች ይኖራሉና ጥቁሮችን በጅምላ ደደብ ማለት ልክ አይደለም፤ በውበት መለኪያም ቢሆን ያው ነው፤ በሌላ በማናቸውም ነገር ቢሆን የጅምላ ሳይንሳዊ ፈተናዎቹን ያላለፈ የጅምላ አስተሳሰብ ቁም ነገርን ያበላሻል፤ እንዲህ ያለው የአስተሳሰብ ግድፈት የሚያቀራርብና የሚያሳድግ አይደለም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደርግና ወያኔ የእውቀትን ደረጃ ሰባብረው ጉልበትን የደረጃ መለኪያ በማድረጋቸው የአስተሳሰብ ግድፈት እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ነው፤ መነሻው ጥላቻ ነው፤ ወያኔ ጥላቻን በስልቻ ቋጥሮ አመጣና በኢትዮጵያ ላይ ዘራው፤ የማሰብ ችግር ስላለ የተዘራው ጥላቻ ፊቱን አዙሮ ወደራሱ ወደወያኔም እንደሚደርስ አልተገነዘበም ነበር።

አሁን ብዙ ሰዎች የወያኔ የአእምሮ ሕመም ተጋብቶባቸው ትግሬዎችን በሙሉ ወያኔ በማድረግ ያላቸውን ጥላቻ በመረረ ቋንቋ ይገልጻሉ፤ በቅርቡ አንድ ሰው ይህንኑ እኔ በሽታ የምለውን ስሜት በፌስቡክ ላይ ገለጠና የሚከተለውን ሀሳብ ጫረብኝ።azeb and aster

የእኔ አመለካከት እንደሚከተለው ነው፤ ትግሬን የማየው በሁለት ከፍዬ ነው፡– ወያኔ የሆኑ ትግሬዎችና ወያኔ ያልሆኑ ትግሬዎች፣ ወያኔን ደግሞ እንደገና ቢያንስ ለሁለት እከፍለዋለሁ፡– ዘርፎ የከበረ ወያኔና ደሀ ወያኔ፤ ዓይኖቹን ከፍቶ ደሀ ወያኔዎችን ማየት ያልቻለ ሰው ከአለ እኔ ለማሳየት ዝግጁ ነኝ፤ ጥቅም ያቅበዘበዘው ወያኔ ዘራፊው ነው፤ ግን ሲዘርፍ ያልዘረፈውን ወያኔ መሣሪያ አድርጎ ነው፤ ለምሳሌ በማእከላዊና በቃሊቲ ያሉ ጠባቂዎች ወያኔዎች የዘራፊዎቹ መሣሪያዎች ናቸው፤ ከተዘረፈው ሲንጠባጠብ ይለቅሙ ይሆናል እንጂ እነሱ መናጢ ደሀ ናቸው፤ የዘረፉ ወያኔዎች በመቀሌ ሕዝቡ “የሙስና ሰፈር” ብሎ የሰየመውን የሀብታሞች መንደር ሠርተዋል፤ በአዲስ አበባም “መቀሌ” ተብሎ የተሰየመውን የሰማይ-ጠቀስ ፎቆች መንደር ሠርተዋል፤ በሻንጣ የአሜሪካን ብር ወደውጭ ይልካሉ፤ ሌላም ብዙ አለ።

እነዚህ በዘረፋ ሀብታም የሆኑ ወያኔዎች ረዳት መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙባቸው ሌሎች ደሀ ወያኔዎች እንዳሉ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ የተባረሩም ወያኔዎች እንዳሉ አውቃለሁ፤ የተባረሩበትንም ምክንያት አውቃለሁ፤ ወደመቀሌ የሚሄዱበት የአውቶቡስ መሳፈሪያም የሰጠኋቸው ነበሩ፤ ለሚያምኑኝ ሰዎች እነዚህን መረጃዎች የምሰጠው ለመመጻደቅ አይደለም፤ እውነቱን እንዲረዱልኝ ነው፤ እውነትን ለማየት የሚችሉ ሰዎች እንዳይሳሳቱ ለመርዳት ነው፡፡

ስለወያኔ ግፈኛነት፣ ዘራፊነትና ጭካኔ ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ ያላልሁት ያለ አይመስለኝም፤ ነገር ግን እንኳን ትግሬን በጅምላና ወያኔንም በጅምላ ለመኮነንና ለመርገም የአእምሮ ብቃትም ሆነ የኅሊና ጽዳት ያለው ሰው የለም፤ የወያኔን ፍርደ-ገምድልነት የሚጠላ በፍርደ-ገምድልነት በትግሬ ሁሉ ላይ አይፈርድም፤ ጥላቻ ኅሊናን ያቆሽሻል፤ ጥላቻ አእምሮን ያሰናክላል፤ ጥላቻ ወደኋላ እንጂ ወደፊት የማየትን ችሎታ ይጋርዳል፤ ጥላቻ በተለይ በማቆጥቆጥ ላይ ያለውን ወጣት እንደበረሀ ጸሐይ እርር ድብን አድርጎ ያጫጨዋል።

በአጠቃላይ ስለ ወያኔ ገዳይ፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ … መሆን አንካካድም! ልዩነታችን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው፤ ስለወያኔ የምንናገረው ሁሉ ለትግሬዎች ሁሉ ይሆናል የሚለው የተሳሳተ አሰተያየት ላይ ነው፤ እኔ በማእከላዊም ሆነ በቃሊቲ ጎንደሬዎች፣ ጎጃሜዎች፣ ወሎዬዎች፣ አሮሞዎች፣ ወላይታዎች … የወያኔዎች አገልጋዮች ሆነው እስረኞችን ሲያሰቃዩ አይቻለሁ፤ ትግራይም ሄጄ ከሌለው የኢትዮጵያ ክፍል የተዘረፈው ሀብት ሁሉ እንኳን ለትግሬ ሁሉና ለወያኔዎች ሁሉ እንዳልተዳረሰና ገና ከጥቂት አልጠግብ ባዮች ወያኔዎች እንዳልወጣ አይቻለሁ።Bereket-Simon-tplf

በሌላ በኩል ሲታይ ወያኔም የተነሣው “አማራ” የሚባል ጭራቅ በዘበዘን፤ ብቻውን እየወፈረ እኛን አከሳን በማለት በ”አማራ” ላይ ወፍራም ጥላቻውን እያስፋፋ በአፈ-ጮሌዎቹ በመለስ ዜናዊ፣ በረከት ስምዖንና ዓባይ ጸሐይ ስብከት ጀሌዎቹን አሳምኖ ነው፤ ወያኔዎች ገና ሰሜን ሸዋ ሲዘልቁ የሚያዩአቸው ሰዎች፣ የሚያዩአቸው ቤቶች ውሸታሞቹ ጮሌዎች እንደነገሯቸው አለመሆኑን ሲገነዘቡ ጥያቄ ያነሡ እንደነበረ ሰምተናል፤ ዛሬም ሌሎች የመለስ፣ የበረከትና የዓባይ የመንፈስ ደቀ መዝሙሮች ኢላማውን ገልብጠው በትግሬዎች ላይ በጅምላ እያነጣጠሩ ነው፤ አንድን ከአንድ መቶ፣ ዝርዝርን ከጅምላ፣ ፖሊቲካን ከዘር መለየት የሚችል አእምሮ ሳይኖር ከአለንበት ሁኔታ አንወጣም፤ ብንወጣም ከጣልነው ጋር ለመንከባለል ነው፤ ወያኔ ደርግን ጥሎ አልተነሣም፤ እዚያው ከሬሳ ጋር ሲንከባለል ተዳከመ! የተሻልን እንሁን!

ወያኔ ሁሉ ትግሬ ነው፤ ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም፤ የወያኔ ዘረፋ እንኳን ለትግራይ ሕዝብና ለወያኔዎች በሙሉ አልደረሰም፤ በየዕለቱ በጠዋት እየተነሣች ምን እንደሆነ የማላውቀውን ዕቃ አዝላ ወደትምህርት ቤት ከሚሄዱ ልጆችዋ ጋር ከቤትዋ እየወጣች ከሰዓት በኋላ ዕቃውን አዝላ የምትመለስ ወያኔ አውቃለሁ፤ ይቺ ወያኔ (ትግሬ አላልሁም፤) በወያኔ ሥርዓት ተጠቅማለች የሚለኝ ሰው ወደሀኪም ዘንድ መሄድ ያስፈልገዋል።

ሚያዝያ 2008

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. eunetu says

    April 24, 2016 03:57 pm at 3:57 pm

    እረ ምን ይሻለናል?
    ቋት ሙሉ ችግር ታቅፈን እስከ መቼ?
    እንደነዚህ ያሉ የአባቶችንስ ምክር ሰምተን የምንማረው መቼ ይሆን???

    ምንአልባት፡

    ኢትዮጵያዊ መልኩን
    ነብር ዥንጉርጉርነቱን
    ይቀይር ዘንድ አየ

    ጆሮ ያለው በጥንቃቄ ይስማ!!!
    የሰማም እራሱን በዚህ ምክር ይመዝን!!!
    መዝኖ የት ላይ እንደቆመ የተረዳም ያስተካክል!!!
    ያስተካከለም ይህን አባታዊ ምክር ተግባራዊ ያድርግ!!!
    እውነተኛ ጥፋተኞችን አውቆ ልካቸውን መንገር ተገቢ ቢሆንም!
    ሰሊጥን ከኑግ ጋር መውቀጡ ተገቢ አይደለምና!
    ከዋኖቻችን ለመማር የተሰጠንን አእምሮ እንደሚገባ እንጠቀምበት
    በአሉባልታና በጥላቻ አገር ይቅርና የግልን ኑሮ እንኳ መገንባት እንደማይቻል እንረዳ???

    ስለዚህ ሁላችንም፡
    ይነስም ይብዛ ላገር/ለወገን ያለንን ፍቅር፣
    በእውነት ለእውነት እንተግብር?
    ከጅምላ ጥላቻ እንፈወስ በፍቅር፣
    አንድ ብልሹ ሰው ስናይ
    እንደ እሱ አንፈርጀው የሰውየውን ዘር!!!
    እረ እባካችሁ እሱ/ሷ እንዲ ነው አሉ!ይቅር???
    እንዲህ ነው በሚል እውነተኛ መረጃ ይቀየር!!!
    በበሬ ወለደና በባዶ የጥላቻ ፉከራ አይገነባምና አገር!!!
    እኔም በምክርዎ ተስማምቻለሁና ፕ/ር
    ከእርስዎ ጋር ተስማምቼ ለመፍትሔው
    እነሳለሁ፣እሠራለሁ፣ እጮሃለሁ ላገር!!!

    እግዜ/ር በእውነት ለሁላችንም ማስተዋል ይስጠን!!!
    የገባው ብቻ አሜን!!!
    እውነቱ
    eunethiwot@gmail.com

    Reply
  2. eunetu says

    April 24, 2016 03:57 pm at 3:57 pm

    እረ ምን ይሻለናል?
    ቋት ሙሉ ችግር ታቅፈን እስከ መቼ?
    እንደነዚህ ያሉ የአባቶችንስ ምክር ሰምተን የምንማረው መቼ ይሆን???

    ምንአልባት፡

    ኢትዮጵያዊ መልኩን
    ነብር ዥንጉርጉርነቱን
    ይቀይር ዘንድ አየ

    ጆሮ ያለው በጥንቃቄ ይስማ!!!
    የሰማም እራሱን በዚህ ምክር ይመዝን!!!
    መዝኖ የት ላይ እንደቆመ የተረዳም ያስተካክል!!!
    ያስተካከለም ይህን አባታዊ ምክር ተግባራዊ ያድርግ!!!
    እውነተኛ ጥፋተኞችን አውቆ ልካቸውን መንገር ተገቢ ቢሆንም!
    ሰሊጥን ከኑግ ጋር መውቀጡ ተገቢ አይደለምና!
    ከዋኖቻችን ለመማር የተሰጠንን አእምሮ እንደሚገባ እንጠቀምበት
    በአሉባልታና በጥላቻ አገር ይቅርና የግልን ኑሮ እንኳ መገንባት እንደማይቻል እንረዳ???

    ስለዚህ ሁላችንም፡
    ይነስም ይብዛ ላገር/ለወገን ያለንን ፍቅር፣
    በእውነት ለእውነት እንተግብር?
    ከጅምላ ጥላቻ እንፈወስ በፍቅር፣
    አንድ ብልሹ ሰው ስናይ
    እንደ እሱ አንፈርጀው የሰውየውን ዘር!!!
    እረ እባካችሁ እሱ/ሷ እንዲ ነው አሉ!ይቅር???
    እንዲህ ነው በሚል እውነተኛ መረጃ ይቀየር!!!
    በበሬ ወለደና በባዶ የጥላቻ ፉከራ አይገነባምና አገር!!!
    እኔም በምክርዎ ተስማምቻለሁና ፕ/ር
    ከእርስዎ ጋር ተስማምቼ ለመፍትሔው
    እነሳለሁ፣እሠራለሁ፣ እጮሃለሁ ላገር!!!

    እግዜ/ር በእውነት ለሁላችንም ማስተዋል ይስጠን!!!
    የገባው ብቻ አሜን!!!
    እውነቱ
    eunethiwot@gmail.com

    Reply
  3. eunetu says

    April 26, 2016 05:27 pm at 5:27 pm

    Golgule!

    Why the above comment is awaiting for moderation for so long?

    ምንአልባት:

    ሁለተኛው ፓራግራፍ ያለው የመጨረሻው ስንኝ ከሆነ፡

    ይቀይር ዘንድ አይችልም የሚለው የትንቢት ቃል በእኛ ላይ ተግባረዊ ሆኖብን ይሆንን?

    ተብሎ ቢተካ መልካም ነው!!!

    Reply
  4. Getu says

    May 6, 2016 01:31 am at 1:31 am

    “እኔ በማእከላዊም ሆነ በቃሊቲ ጎንደሬዎች፣ ጎጃሜዎች፣ ወሎዬዎች፣ አሮሞዎች፣ ወላይታዎች …” This guy has a serious issue on Amhara. It was OK for him to say Oromo, Tigria, Welaita, but de doesn’t want to call us Amhara.

    “ትግራይም ሄጄ ከሌለው የኢትዮጵያ ክፍል የተዘረፈው ሀብት ሁሉ እንኳን ለትግሬ ሁሉና ለወያኔዎች ሁሉ እንዳልተዳረሰና ገና ከጥቂት አልጠግብ ባዮች ወያኔዎች እንዳልወጣ አይቻለሁ።” Was he expecting to see all Tigrea to be millionaires? What is wrong with him?

    Reply
  5. ሸመልስይማም says

    May 12, 2016 09:38 am at 9:38 am

    ሀሉምአንደህወሀትኢህአዴግዘራፌናሊቦችአየደሉምተረከንሰነይየአትዮጵያየመጀመራመንግስትመሰራቾችአንደነበሩይነገረናልሰለዘህከስንዴመሀልአንክርዳድአይጠፋምናአነዚህንአንክርዳዶችየኢትዮጵያህዝብሊየጠፋቸውይገባል

    Reply
  6. you r weyane says

    May 16, 2016 01:08 am at 1:08 am

    what all this belaboring who paid you to be a defendant for tegray ethnic groups. we all knew all of them are not weyanes, but we want them to march with the rest of ETHIOPIANS.

    Reply
  7. much says

    May 18, 2016 12:11 pm at 12:11 pm

    ሁሉም ትግሪ ወያኔ ነው ማለት ምንድን ነው።? በሂሳብ መስፍረት ከመቶው 55 ፕርሰንቱ ሆኖ ከተገኘ አመዛኙ ሆኖዋል ማለት ነው። እኔ እምለው ግን 99 ፐርሰንቱ የትግራይ ተወላጅ ወያኔ ነው። ሊላው ቀርቶ እነ አረጋዊ በርሄ የሚባሉት ተማርኩ የሚል ወያኔ ችግሩ ከወያኔ ጋር ሳይሆን ስልጣን ላይ ካሉት አፍቃሪ ኤርትራዊያን ጋር ነው። በእውነት ይሁንብኝ ከዚሁ ሰውየ ጀምሮ ማንኛው ትግሪ ወያኔ ዘላለማዊ ገዥ እንዲሆን ፍላጎታቸው ነው። በእርግጥ ብጥቅም ሊናተረኩ ይችላሉ መሰረታዊ ፍላጎታቸው ግን አማራን ከምድረገጽ ማጥፋት የውያኔን ዘላለማዊነት ማጽናት ነው። አትሞኝ ሰውየ።!!!!!!!!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule