በአገራችን፣ ህወሓት በመጀመሪያ በትግራይ ከ40 አመት በፊት በመላ ኢትዮጵያ ደግሞ በበላይነት በሚቆጣጠረው ኢህአዴግ ከ25 አመት በፊት የጀመረው የግድያና የአፈና ስርዓት አሁንም በመቀጠል ላይ ነው፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ተቋማዊ ባደረገው የዘውግ ፖለቲካ ምክንያት ህዝባችን ተከፋፍሎ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ውስጥ በተወሰኑ ክልሎች እንደ ባዕድ የሚታዩበት ሁኔታ ከተከሰተ ቆይቷል።
ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣኑን ፍፁማዊ ለማድረግ ሃይማኖትን በመሳሪያነት ስለሚጠቀም በክርስቲያኖች ውስጥና በሙስሊሞች ውስጥም ወደ ግጭት የሚያመራ ክፍፍል ፈጥሯል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ስርዓቱን ለማቆየት የተገነባው የዘውግና የሃይማኖት ክፍፍል ስርዓቱን ለማስወገድ ወደሚጠቅም መሳሪያነት እየተቀየረ ነው፡፡
በአገራችን ያሉ ዋናዎቹ ችግሮች፡
1. ህወሓት/ኢህአዴግ ገዳይ፣አፈኝና ከፋፋይ መሆኑና ህዝባችን በህይወት የመኖር ዋስትና ማጣቱ፣ ሰብአዊና ዴሞከራሲያዊ መብቶቹ መረገጣቸውና ባገሩ ውስጥ በነፃነት መኖር አለመቻሉ ናቸው።
በኢህአዴግ ውስጥ ህወሓት፡
1.1 ጉልበት በሚጠቀሙ ተቋሞች፡ በሰራዊቱ፣ በደህንነትና በእስር ቤቶች፣
1.2 በአስተሳሰብ ላይ ጫና በሚያደርጉ ተቋሞች፡ በመገናኛ ብዙሃንና በሃይማኖታዊ አመራሮች፣
1.3 በውጭ ጉዳይ
1.4 ከፍተኛ ያገሪቱን ሃብት በመቆጣጠርና በመዝረፍ በዘውግ ላይ የተመሰረተ ቡድናዊ የበላይነት
ይዟል፡፡
እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ ወሳኙ እርምጃ ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን አስወግዶ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ነው፡፡
ይህን ኣላማ ለማሳካት በትግሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከነዚህም ችግሮች ውስጥ በሚከተሉት ላይ ትኩረት ያስፈልጋል፡፡
በአገራችን ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎች፡
1. ህወሓት/ኢህአዴግ በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ሊያካሂድ ይችላል፡፡
አባይ ፀሃየና ስዩም መስፍን በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ እነሱ „የዘር“ የሚሉትና ከሆሎካስትና ከሩዋንዳ እልቂት ጋር የሚያመሳስሉትና የእርስ በርስ ጦርነት አስከትሎ አገሪቷን የሚበታትን አደጋ እንደሚያሰጋ የሚገልፁት ማስፈራሪያ አለ፡፡
ይህ ማስፈራሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ለመግታትና የኢትዮጵያ አንድነትን ለመጠበቅ እርምጃ የሚወስዱ አስመለስለው ተቃውሞ ያነሳባቸውን ህዝብ ለመጨፍጨፍ የሚጠቀሙበት የለመዱት ስልት ነው፡፡ አባይ ፀሃየና ስዩም መስፍን የትግራይን ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መመስረት አላማቸው እንደሆነ በማኒፌስቶ ከገለፁት ጥቂት የህወሓት መስራቾች ውስጥ ስለሆኑ ለኢትዮጵያ አንድነት ተቆርቋሪዎች መስለው የመቅረብ የሞራል ብቃት የላቸውም፡፡ እንደዚሁም ሁለቱ ሰዎች የዘውግ ልዩነት ተቋማዊ እንዲሆን ካደረጉ በሁዋላ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በዘረኝነት መፈረጃቸው ከቅንነት የመነጨ ቅስቀሳ አይደለም፡፡
ስለዚህ ሰራዊቱና የመንግስት ታጣቂው ሃይል የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በወገኑ ላይ የጭፍጨፋ ወንጀል እንዳያስፈፅሙት መቃወም አለበት፡፡
2. ህዝብን የሚያጋጩ ስህተቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ በሚወስዳቸው የጭካኔ እርምጃዎች ምክንያት በህዝብ ውስጥ ስጋት ሰፍኗል፡፡ በዚህ የውጥረት ሁኔታ ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉና በህዝብ ውስጥ ግጭት የሚያስከተሉ እርምጃዎችን የሚወስዱ ግለሰቦችና ቡድኖች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ በህዝብ ውስጥ ግጭት ሲከሰት ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሊጠቀምበት
ይችላል፡፡
ስለዚህ ሁሉም ፍትህ፣ ሰላምና አንድነት የሚፈልጉ ወገኖች ለዘመናት አብሮ በኖረውና ነፃነቱን በጠበቀው ህዝብ ውስጥ ግብታዊ ግጭት እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
የስም ዝርዝር᎓
1. ህይወት ተሰማ
2. ሓረገወይኒ ገ/ኢየሱስ
3. ሕሉፍ በርሀ
4. ሜሮን አብርሃ
5. ሲራክ ኣማረ
6. ስልጣን ኣለነ
7. በላቸው ለማ
8. በየነ ገብራይ
9. ብሩክ እንግዳ
10. ተስፋዬ መሓሪ
11. ተስፋይ ኣፅብሃ
12. ታደሰ በርሀ
13. ታደሰ ገብረእዝጊ
14. ነጋሲ በየነ
15. ናትናኤል ኣስመላሽ
16. አሰር አሉላ
17. አባይ ኪሮስ
18. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
19. ኣብራሃ በላይ
20. ኣብርሃም ኀይለ
21. ኤልያስ በየነ
22. ኪዳነ ኃይሌ
23. ኪዳነማርያም ፀጋይ
24. ካሕሳይ በርሀ
25. ዘልኣለም ንርአ
26. ዮሃንስ በርሀ
27. ዮሴፍ ብርሃነ
28. ዮናስ ሓጎስ
29. ዮናስ መብራህቱ
30. ደስታ ኣየነው
31. ገብረኪዳን ዳዊት
32. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ
33. ጥላሁን አረፈ
34. የማነ ምትኩ
በመጨረሻም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ 16 የምንሆን የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ መግለጫ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ አሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥራችን ከእጥፍ በላይ መብዛቱ ያነሳነው ሃሳብ በብዙ ሰዎች አእምሮ እንዳለና እየተጠናከረ እንደሚሄድ ያመለክታል፡፡
ሌሎችም በዲያስፖራው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የትግራይ ህዝብ ከጥንትም ለወደፊትም እጣ ፈንታው ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መሆኑንና ጥቅሙና ህልውናው የሚጠበቀው በፍትህ፣ በዴሞክራሲ፣ በእኩልነትና በአንድነት ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲሆን ብቻ መሆኑን ተገንዝበው፤ የህወሓት ባለስልጣኖች በስልጣናቸው ላይ ለመቆየት የሚያደርጓቸውን መሰሪ ቅስቀሳዎች በማጋለጥና የሚፈፅሟቸውን ጭፍጨፋዎች በማውገዝ ድምፃቸውን እንዲያስሰሙና ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በዚህ መግለጫ ይዘት ላይ የሚስማሙና አስተያየቶች ያሏቸው ሰዎች ወደሚከተለው ኣድራሻ መፃፍ ይችላሉ፡፡
ethiocivic@gmail.com
8 መስከረም 2009
(ከአንድ ወር በፊት የትግራይ ተወላጆች የመጀመሪያውን መግለጫ አውጥተው ነበር – እዚህ ላይ ይገኛል)
Leave a Reply